Sheger info

Sheger info Sheger info ማህበራዊ እና የመዝናኛ መረጃዎችን የሚቀስሙበት ገጽ

ግራኒት ዣካ ከብሔራዊ ቡድኑ ታገደ ! የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ግራኒት ዣካ የህግ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ተገልጿል። ግራኒት ዣካ አስፈላጊውን ክትባት ሳያደርግ በሀሰት የ...
21/09/2026

ግራኒት ዣካ ከብሔራዊ ቡድኑ ታገደ !

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ግራኒት ዣካ የህግ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

ግራኒት ዣካ አስፈላጊውን ክትባት ሳያደርግ በሀሰት የኮቪድ ሰርተፍኬት ወስዷል በሚል ተጠርጥሯል።

በዚህም ምክንያት ግራኒት ዣካ እና የህክምና ባለሙያው ላይ ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የግራኒት ዣካ ጥፋት እስከ አምስት አመታት ለእስር ሊዳርገው እንደሚችል ተዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ የስዊዘርላንድ እግርኳስ ፌዴሬሽን ግሪንት ዣካን ከስብስቡ ውጪ ማድረጉ ተነግሯል።

ፌዴሬሽኑ ዣካ በቀጣይ ሶስት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ወቅቶች እንደማይሳተፍ የገለፀ ሲሆን ውሳኔው የጋራ ስምምነት መሆኑን አሳውቋል።

ከ 85 በመቶ በላይ የጉበት በሽታ ተጠቂዎች ወደ ጤና ተቋም የሚሄዱት ለከፋ ሕመም ከተጋለጡ በኋላ መሆኑ ተገለጸ!ከ 85 በመቶ በላይ የሚሆኑ የጉበት በሽታ ታካሚዎች ወደ ሕክምና ተቋም የሚሄዱ...
21/09/2026

ከ 85 በመቶ በላይ የጉበት በሽታ ተጠቂዎች ወደ ጤና ተቋም የሚሄዱት ለከፋ ሕመም ከተጋለጡ በኋላ መሆኑ ተገለጸ!

ከ 85 በመቶ በላይ የሚሆኑ የጉበት በሽታ ታካሚዎች ወደ ሕክምና ተቋም የሚሄዱት ሕመሙ ወደ ከባድ ደረጃ (የጉበት ጠባሳ) ከተቀየረ በኋላ መሆኑን የኢትዮጵያ ጋስትሮአንትሮሎጂ ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ጂግሳ ዳበሳ አስታወቁ።

የጉበት ቫይረስ በሽታ ለአስርት ዓመታት ምንም ዓይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። አብዛኛው ሰው በሽታው እንዳለበት የሚያውቀው በድንገት ለሌላ የጤና ጉዳይ፣ ለሥራ ቅጥር ወይም ለተለያዩ ጉዳዮች ምርመራ በሚያደርግበት አጋጣሚ ነው።

የሕብረተሰቡ ስለ በሽታው አስከፊነት ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ በመሆኑ ታካሚዎች ዘግይተው ወደ ሕክምና ይመጣሉ፤ ይህ ደግሞ በጉበት ላይ ሊቀለበስ የማይችል ከባድ ጉዳት (ጠባሳ) ያስከትላል።

ሕመሙ ደረጃው ከፍ ሲል እና መባባስ ሲጀምር ከመጠን ያለፈ ድካም፣ የሆድ አካባቢ እብጠት፣ የዓይን ወደ ቢጫነት መቀየር፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ማቅለሽለሽ እና ትውከት የመሳሰሉ ምልክቶችን ያሳያል።

አብዛኛዎቹ ተጠቂዎች በቅድሚያ ምንም ዓይነት ምልክት ስለማያሳዩ፤ ሕመሙ ከፍ ወዳለ ደረጃ ሳይደርስ እና የጉበት ጠባሳን ለማስቀረት ሕብረተሰቡ በየጊዜው የጤና ምርመራ (Check-up) ማድረግ እንዳለበት ዶክተር ጂግሳ መክረዋል።

ያለ ምንም መነጽር በዓየር ላይ የተንሳፈፈ 3D ምስል የሚያሳየው አዲሱ የቻይና ቴክኖሎጂ!በቻይና የተሰራ እና የመሬትን (Earth) ምስል ያለምንም ልዩ መነጽር በዓየር ላይ ተንሳፍፎ እንዲታይ...
21/09/2026

ያለ ምንም መነጽር በዓየር ላይ የተንሳፈፈ 3D ምስል የሚያሳየው አዲሱ የቻይና ቴክኖሎጂ!

በቻይና የተሰራ እና የመሬትን (Earth) ምስል ያለምንም ልዩ መነጽር በዓየር ላይ ተንሳፍፎ እንዲታይ የሚያደርግ አዲስ ማሳያ (Display) በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ትኩረትን እየሳበ ይገኛል።

እንዴት ይሰራል?፦ ቴክኖሎጂው በልዩ ፍጥነት በሚሽከረከር ማራገቢያ (Fan) እና በልባሶቹ ላይ በተገጠሙ የ LED መብራቶች አማካኝነት የሚሰራ ነው። ማራገቢያው በፍጥነት ሲሽከረከር መብራቶቹ በተቀናጀ የጊዜ ሰሌዳ ብልጭ ድርግም በማለት፤ የዓይናችንን የእይታ ተከታታይነት (Persistence of Vision) በመጠቀም አንድ ወጥ የሆነ ባለ 3-ልኬት (3D) ምስልን ይፈጥራሉ።

ምንም እንኳን ብዙዎች ቴክኖሎጂውን "ሆሎግራም" (Hologram) ብለው ቢጠሩትም፣ እውነተኛ ሆሎግራም ሳይሆን በሚሽከረከሩ የ LED መብራቶች አማካኝነት የተንሳፈፈ ምስልን የሚፈጥር የዕይታ ማሳያ ነው።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የንግድ ሱቆች እና የንግድ ትርኢቶች (Trade shows) ላይ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ (ተወዳጅነትን ያተረፈውን አዲሱን ቪዲዮ ያዘጋጀው ትክክለኛው ኩባንያ ማንነት ግን እስካሁን አልተረጋገጠም)።

ከቦክስ መድረክ ባሻገር የድሆች አጋር የሆነው ማኒ ፓኪያዎ!በፈረንጆቹ 2015 ከፍሎይድ ሜይዌዘር ጁኒየር ጋር ያደረገው ግጥሚያ በቦክስ ታሪክ እጅግ ከፍተኛ ገቢ ከተገኘባቸው ውድድሮች አንዱ ሲ...
21/09/2026

ከቦክስ መድረክ ባሻገር የድሆች አጋር የሆነው ማኒ ፓኪያዎ!

በፈረንጆቹ 2015 ከፍሎይድ ሜይዌዘር ጁኒየር ጋር ያደረገው ግጥሚያ በቦክስ ታሪክ እጅግ ከፍተኛ ገቢ ከተገኘባቸው ውድድሮች አንዱ ሲሆን፤ ፊሊፒንሳዊው የቦክስ ኮከብ ማኒ ፓኪያዎ (Manny Pacquiao) ከጨዋታው ወደ 120 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ማግኘቱ ይታወሳል።

ቦክሰኛው በትውልድ ቦታው ሳራንጋኒ (Sarangani) ውስጥ “ፓክማን ቪሌጅ” በተሰኘው መንደር፤ ከራሱ ገንዘብ 28.5 ሚሊዮን ፔሶ (ወይም 604 ሺህ ዶላር ገደማ) ወጪ በማድረግ 150 መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለችግረኛ ቤተሰቦች በነፃ አበርክቷል።

ከዚህ ስጦታ አንድ ዓመት ቀደም ብሎም በተመሳሳይ መልኩ ለ 100 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ማስረከቡ ተጠቅሷል።

ማኒ ፓክያው ለሚያሳየው ለዚህ አርአያነት ያለው ሰብዓዊ ተግባር፤ በብዙ ፊሊፒናውያን ዘንድ በቦክስ መድረክም ሆነ ከስፖርቱ ዓለም ውጭ እንደ ትልቅ ጀግና ይቆጠራል።

ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ነገ አዲስ አበባ ይገባል!በኮፐንሀገን በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ ኬንያን ተከትሎ ከዓለም...
21/09/2026

ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ነገ አዲስ አበባ ይገባል!

በኮፐንሀገን በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ ኬንያን ተከትሎ ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን፤ ዛሬ ሌሊት ከስፍራው በመነሳት በቪየና ትራንዚት አድርጎ ነገ ንጋት 11፡25 አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

ልዑካን ቡድኑ በልቅና አምባው በ 5 ኪሎ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ፣ እንዲሁም በፍሬወይኒ ሀይሉ በአንድ ማይል የብር ሜዳሊያ አስመዝግቧል። በቡድን ደረጃ ደግሞ በሴቶች ግማሽ ማራቶን ነሐስ፣ በወንዶች ግማሽ ማራቶን የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችሏል። በአጠቃላይ 1 ወርቅ፣ 2 ብር እና 1 ነሐስ (በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን) ሰብስቧል።

ጎረቤት ሀገር ኬንያ በግማሽ ማራቶን በግል (ሴቶች) እና በቡድን (ወንድና ሴት) ወርቆችን ጨምሮ፤ በአጠቃላይ 3 ወርቅ፣ 3 ብር እና 1 ነሐስ (በድምሩ 7 ሜዳሊያዎችን) በማግኘት ውድድሩን ከአለም 1ኛ በመሆን አጠናቃለች።

ኤርትራ፣ ስዊድን፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ እያንዳንዳቸው አንድ የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ውድድራቸውን ሲያጠናቅቁ፤ አሜሪካ በአንድ የነሐስ ሜዳሊያ ውድድሩን ፈጽማለች።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመስከረም ወር በዓላት 3 ሚሊዮን ጎብኚዎችን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን አስታወቀ!የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፤ በመስከረም ወር በሚከበሩት የመስቀል ...
21/09/2026

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመስከረም ወር በዓላት 3 ሚሊዮን ጎብኚዎችን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን አስታወቀ!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፤ በመስከረም ወር በሚከበሩት የመስቀል እና የብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት ላይ 3 ሚሊዮን ጎብኚዎችን ለማስተናገድ ማቀዱን ይፋ አድርጓል።

በክልሉ የመስቀልን ጨምሮ የየም (ሄቦ)፣ የሀድያ (ያሆዴ) እና የከንባታ (መሰላ) የዘመን መለወጫ በዓላት በድምቀት የሚከበሩ ሲሆን፤ ከነዚህም ሁነቶች ከ 1.5 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

በዓላቱ ባህላዊ ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የባህል ፌስቲቫል፣ የእደ ጥበብ ውጤቶች ኤግዚቢሽን፣ የባህላዊ ዳኝነትና የሽምግልና ሥርዓት ትውውቅ እንዲሁም በደንብ ያልበለጸጉ ቋንቋዎችን ለማልማት የሚያስችል የቋንቋ ሲምፖዚየም ይካሄዳል።

ወደ ክልሉ ይመጣሉ ተብለው ከሚጠበቁት 3 ሚሊዮን ሰዎች መካከል፤ ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ ተወላጆች፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ይገኙበታል።

የጊፋታ በዓል በሌላ በኩል በዩኔስኮ በማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ከተመዘገበ በኋላ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በድምቀት የተከበረው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል፤ ትላንት ምሽት በ'ጉሊያ' ሥነ-ሥርዓት በሰላም መጠናቀቁን የወላይታ ዞን አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸው አረጋግጠዋል።

(ምንጭ፡ አሐዱ ሬድዮ)

በአዲስ ዌስት ማከፋፈያ ጣቢያ ባጋጠመ ብልሽት በበርካታ የአዲስ አበባ አካባቢዎች መብራት ተቋረጠ!በአዲስ ዌስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት ሳቢያ፣ በ...
21/09/2026

በአዲስ ዌስት ማከፋፈያ ጣቢያ ባጋጠመ ብልሽት በበርካታ የአዲስ አበባ አካባቢዎች መብራት ተቋረጠ!

በአዲስ ዌስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት ሳቢያ፣ በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ዋና ዋና አካባቢዎች እና የጥገናው ሁኔታ፦

በአዲስ ከተማና አካባቢው፦ አውቶብስ ተራ፣ እህል በረንዳ፣ መሳለሚያ፣ አዲሱ ሚካኤል፣ አማኑኤል፣ 7ኛ፣ ታይዋን ገበያ ማዕከል እና አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካባቢዎች።

በኮልፌና አካባቢው፦ ኮልፌ 18 ማዞሪያ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያና መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደር እና ፈጥኖ ደራሽ።

በቀራንዮና ቤተል፦ ቀራንዮ መድኃኔዓለም፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ እና መስጊድ አካባቢ።

በጦር ኃይሎችና ዙሪያው፦ ጦር ኃይሎች፣ ሆላንድና ቻይና ኤምባሲ፣ ወይራ ሰፈር፣ ኮንዶሚኒየም፣ አውጉስታ፣ ሞቢል እና የሺ ደበሌ አካባቢዎች።

የጥገናው ሁኔታ፦ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ባለሙያዎች የተፈጠረውን ብልሽት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማስተካከል አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

ተቋሙ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ ደንበኞች በትዕግሥት እንዲጠባበቁ በአክብሮት ጠይቋል።

(ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)

ኬንያ ለፖሊስ አባላቶቿ ከ 28 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ልትገነባ ነው!የኬንያ መንግሥት 137 አበይት ፕሮጀክቶችን በማካተት፣ ከ 28 ሺህ በላይ የፖሊስ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስች...
21/09/2026

ኬንያ ለፖሊስ አባላቶቿ ከ 28 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ልትገነባ ነው!

የኬንያ መንግሥት 137 አበይት ፕሮጀክቶችን በማካተት፣ ከ 28 ሺህ በላይ የፖሊስ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ሰፊ የልማት ዕቅድ መንደፉን አስታወቀ።

አሁን ባለው መረጃ መሠረት፤ ከታቀዱት ቤቶች ውስጥ 870ዎቹ ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅተዋል፣ 12 ሺህ ገደማ የሚሆኑት በግንባታ ላይ ሲሆኑ፣ ከ 1,500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በግዢ እና ጨረታ ሂደት ላይ ይገኛሉ።

ቀሪዎቹ 15 ሺህ የሚጠጉ የመኖሪያ ቤቶች በቀጣዮቹ የልማት ምዕራፎች ውስጥ ተካተው ግንባታቸው የሚከናወን ይሆናል።

ይህ ግዙፍ መርሃ ግብር የፖሊስ አባላትን የመኖሪያ ሁኔታ ለማሻሻል ያለመ ሲሆን፤ በሀገር ደረጃ ከተዘረጋው ሰፊ የመንግሥት የመኖሪያ ቤት ልማት ጋር የተያያዘ መሆኑ ተገልጿል።

የዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት መተግበርና መስፋፋት በኬንያ የመንግሥት ቤት ግንባታ እና አጠቃላይ የሕንፃ ግንባታ ገበያ ላይ ከፍተኛ የቁሳቁስና የፋይናንስ ፍላጎት እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

የቦሮ-ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጋሪ-ዎሮ” በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከበረ!በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከሚኖሩት ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ-ሺናሻ ብ...
21/09/2026

የቦሮ-ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጋሪ-ዎሮ” በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከበረ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከሚኖሩት ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ-ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጋሪ-ዎሮ” በዓል በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ከተማ ተከብሯል።

የበዓሉ አከባበር “ጋሪ ዎሮ” (ወይም “ጋሮ”) በመባል የሚታወቀው ይህ በዓል በብሔረሰቡ አባቶች ምርቃት የሚጀመር ሲሆን፤ ዕድሜና ፆታ ሳይለይ ወንዶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ሕፃናት በአብሮነት የሚሳተፉበት ትልቅ የባህል መገለጫ ነው።

በዓሉ ከድግስ ባሻገር ከፍተኛ ማኅበራዊ ፋይዳ አለው። የተጣላ የቤተሰብ አባል ካለ ተፈልጎ እርቅ የሚፈጸምበት፣ ጥፋተኛው ተበዳዩን ክሶ ይቅርታ የሚባባልበትና ሰላም የሚሰፍንበት መድረክ መሆኑ ተገልጿል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልጎሪ በዓሉ አብሮነትንና ብዝሀነትን ለትውልድ ለማስተላለፍ ያለውን ዓላማ አብራርተዋል። ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኙት ረ/ፕ ከፍያለው አብዲሳ በበኩላቸው፤ ሚኒስቴሩ የብሔር ብሔረሰቦች ባህልና እሴቶች እንዲለሙ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሕዝብ ክብረ በዓላት የሀገሪቱን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አበርክቶ በሚያሳድግ መንገድ እንዲከበሩ በአዋጅ ቁጥር 13334/2016 እና በመመሪያ ቁጥር 1116/2018 መሠረት እየሰራ መሆኑ በዝግጅቱ ላይ ተነስቷል።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ሲያሸንፉ፤ ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ጥሏል!በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች፤ ማንችስተር ሲቲ...
20/09/2026

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ሲያሸንፉ፤ ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ጥሏል!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች፤ ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ማንችስተር ዩናይትድ በአቻ ውጤት ተለያይቷል።

ማንችስተር ሲቲ 5 - 3 ሰንደርላንድ
ማንችስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ 5ኛ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ መሪነቱን አጠናክሯል። ለሲቲ የድል ግቦቹን ሴሜንዮ (2)፣ ሀላንድ፣ ሼርኪ እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ ሲያስቆጥሩ፤ የሰንደርላንድን ሶስት ግቦች ብሮቤይ (ሀትሪክ) ከመረብ አሳርፏል።

ማንችስተር ሲቲ በ 15 ነጥብ 1ኛ፤ ሰንደርላንድ በ 4 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ማንችስተር ሲቲ ቀጣይ ከ ሊቨርፑል

ሊቨርፑል 1 - 0 በርንማውዝ
ሊቨርፑል በአሌክሳንደር አይሳክ ብቸኛ ግብ በማሸነፍ የውድድር ዘመኑን 2ኛ የሊግ ድል አሳክቷል። በጨዋታው አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ የቀድሞ ክለባቸውን ገጥመው ሶስት ነጥብ ይዘው መውጣት ችለዋል።

ሊቨርፑል በ 9 ነጥብ 6ኛ፤ በርንማውዝ በ 3 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ሊቨርፑል በቀጣይ ከ ማንችስተር ሲቲ

ማንችስተር ዩናይትድ 1 - 1 ፉልሀም
ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ነጥብ ለመጣል ተገዷል። የፉልሀምን ግብ ማርቲኔዝ በራሱ መረብ ላይ ሲያስቆጥር፤ ማቲውስ ኩንያ ዩናይትድን አቻ አድርጓል። ማንችስተር ዩናይትድ በመጀመሪያዎቹ 5 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 1 ብቻ ሲሆን፤ ፉልሀም ባደረጋቸው ጨዋታዎች 3ቱን ተሸንፎ በ2ቱ አቻ ወጥቷል።

ማንችስተር ዩናይትድ በ 5 ነጥብ 12ኛ፤ ፉልሀም በ 2 ነጥብ 19ኛ (ወራጅ ቀጠና) ላይ ይገኛሉ።
ቀጣይ ጨዋታ፦ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

Address

Trinity Road
London

Telephone

+251913242401

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sheger info posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sheger info:

Shortcuts

Share