Afar People's Voice - APV

Afar People's Voice - APV ይህ ፔጅ የአፋርን ህዝብ ታሪክና ባህል፣ ማህበራዊና ፖለቲካን የሚዳስስ እና ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች የሚያቀብል የእርሶ ገፅ ነው።
(6)

 !መስከረም ወር ሲጠናቀቅ;-👉የደሞዝ ጭማሪው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፤👉ክልሎች መረጃ አሟልተው ባለማድረሳቸው መክፈል     አልተቻለም፤👉መረጃ ስላልተሟላ በቀጣይ ወራት ይከፈላል፤👉በቀጣይ ወ...
20/09/2025

!

መስከረም ወር ሲጠናቀቅ;-

👉የደሞዝ ጭማሪው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፤
👉ክልሎች መረጃ አሟልተው ባለማድረሳቸው መክፈል
አልተቻለም፤
👉መረጃ ስላልተሟላ በቀጣይ ወራት ይከፈላል፤
👉በቀጣይ ወራት ከነውዝፉ ተፈፃሚ ይሆናል፤... ወዘተ

የሚሉ ዘገባዎችን የመንግስት ተሿሚዎችን ጨምሮ ሁሉም የመንግስት ተቀጣሪዎች መስከረም ወር 2018 ሲጠናቀቅ መስማት አይፈልጉም።

ስለዚህ የደመወዝ ጭማሪውን መንግስት ማንም ሳይጠብቅ ድንገት ይፋ እንዳደረገው ሁሉ የተናገረው ጊዜ ምንም ሳይሸራርፍ እና ምክንያት ሳይደረድር ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ሁሉም የመንግስት ተቀጣሪዎች በእምነት ይጠባበቃሉ።
Temesgen Tanto

#ማሳሰቢያ;- ጭማሪዉ እኔን አይመለከተኝም።

13/09/2025

Big shout out to my newest top fans! Yonas Yoni, Tedy Tafara, Deved Haylu, Mohmed Arago, Abdu Bedewi, Danko Jeldo Sorsa, ሲፋን ፋኑት ሲፋን

 የአፍዴራ ህዝብ «ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ» ይሉት ተረት በገሀድ ኑሮታል። ኡኡ*ታው ሳይደመጥ፤ ጩኽቱ ሳይሰማ በራሱ እርስት ላይ ባይተዋር ሆኖ የግዞት ህይዎት ይገፋ ዘንድ ተገዷል።...
13/09/2025


የአፍዴራ ህዝብ «ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ» ይሉት ተረት በገሀድ ኑሮታል። ኡኡ*ታው ሳይደመጥ፤ ጩኽቱ ሳይሰማ በራሱ እርስት ላይ ባይተዋር ሆኖ የግዞት ህይዎት ይገፋ
ዘንድ ተገዷል። እጅግ ከፍተኛ በሆነ በርሃ፤ በዚያ ምድረ በዳ ላይ የሀገር አጥር እና ከለላ መሆኑ ተረስቶ የበርሃውን ፀጋ ነጩን ወርቅ እንዳይጠቀም ከልክለውታል። ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ጉልበቱን በዝብዘውታል። አቅሙ እስኪዳከም ፣ ጉልበቱ እስኪዝል፣ ላቡ እስኪደርቅ ፤ ወዙ እስኪጠፋ ፣በመሬቱ ከሚያመርተው ምርት ጉልበተኞችን ያፈረጥም ዘንድ ግድ ሁኖበታል። ስንጥቃት አንድ መፅሐፍ " ነጩ ጅ*ብ ስሄድ ጥቁሩ ጅ*ብ ተተካ" በሚል አርእስት ስር አፍዴራን በዝርዝር ተመልክተዋል.....!!

ደራሲ Allo Yayo

Big shout out to my newest top fans! 💎 Yonas Yoni, Tedy Tafara, Deved Haylu, Mohmed Arago, Abdu Bedewi, Danko Jeldo Sors...
02/09/2025

Big shout out to my newest top fans! 💎 Yonas Yoni, Tedy Tafara, Deved Haylu, Mohmed Arago, Abdu Bedewi, Danko Jeldo Sorsa, ሲፋን ፋኑት ሲፋን

Drop a comment to welcome them to our community, fans

07/08/2025

በኢሳዎች የተ*ጨፈ*ጨፈ ሙሉ ቤተሰብ 😭
ባል ሚስት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በተኙበት ኢሳ በሚል የዳቦ ስም የሚጠራ የሱማሌ ክልል ታጣቂ በቀን 30/11/2017 ሙሉ ቤተሰባችን ተገ*ድሏ*ል 😭

አረ*መኔ*ያዊ የሆነ በአረ*መኔ*ዎች የተፈፀመ ድርጊት ነው!!

የሁለት ዓመት ህፃን የሚ*ገል ሴጣ*ናዊ ድርጊት የፈፀሙ እጆች መቀ*ጣት አለባቸው‼️

07/08/2025

ኢናሊላሒ ወኢና ኤለይሒ ራጅኡን 😭

አፋር አዝናለች፣ ተክዛለች፣ ደም*ታለች፣ አንብታለች፣ አሁን ግን በዛ ከዚህ በላይ አንችልም 💔

 #አሏሁአክበር ከ300,000ሺህ ሰዉ በላይ የተሳተፈበት ያዉም በከባድ ዝናብ የተደረገ አሜ*ሪካ*ንን እና እስ*ራኤ*ልን በመቃወም ስለ*ጋዛ ፍትህን በማለት ዛሬ ጧት በአዉስትራሊያ የተደረገ ታ...
03/08/2025

#አሏሁአክበር ከ300,000ሺህ ሰዉ በላይ የተሳተፈበት ያዉም በከባድ ዝናብ የተደረገ አሜ*ሪካ*ንን እና እስ*ራኤ*ልን በመቃወም ስለ*ጋዛ ፍትህን በማለት ዛሬ ጧት በአዉስትራሊያ የተደረገ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ

የኦ*ሮሞ  ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የሶማሌ ክልልን ''ህገ-መንግስታዊ ያልሆነ'' መልሶ ማዋቀር በፅኑ አወገዘ‼️=====================የኦ*ሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣የሶ...
30/07/2025

የኦ*ሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የሶማሌ ክልልን ''ህገ-መንግስታዊ ያልሆነ'' መልሶ ማዋቀር በፅኑ አወገዘ‼️
=====================

የኦ*ሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በቅርቡ ይፋ ያደረገውን እና ከኦሮ*ሚያ ክልል ሲተዳደሩ የነበሩ ወረዳዎችን ያካተተውን የአስተዳደር መልሶ ማዋቀር እቅድ "ህገ-መንግስታዊ ያልሆነና ሆን ተብሎ የተፈጸመ ቅስቀሳ ነው" ሲል በጽኑ አወገዘ።

ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 22, 2017 ዓ.ም. በወጣው መግለጫ ላይ ፓርቲው፣ ይህ የአንድ ወገን እርምጃ በኦሮ*ሞና በሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ግ*ጭት ለመፍጠር ያለመ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጾ፣ የፌደራልና የኦሮ*ሚያ መንግስታት በጉዳዩ ላይ የያዙትን "አደ*ገኛ ዝምታ" እንዲሰብሩ አጥብቆ ጠይቋል።

መግለጫው አክሎም፣ የአሁኑ መንግስት ከገጠሙት ፈተናዎች የህዝብን ትኩረት ለማዘናጋት በወንድማማች ህዝቦች መካከል ግ*ጭት ለመፍጠር እየሞከረ ነው ሲል ከሷል።

ፓርቲው፣ ችግሩ ሳይባባስ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚከተሉትን አምስት ዋና ዋና ጥያቄዎች አቅርቧል፦

1ኛ. አፋጣኝ ስ*ረዛ፦ የሶማሌ ክልል መንግስት፣ የሞያሌን ጨምሮ የኦ*ሮሞ ግዛቶችን ሁኔታ የሚቀይረውን ይህንን ህገ-መንግስታዊ ያልሆነ እቅድ በአስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲ*ሰርዝ ጠይቋል።

2ኛ. ህገ-መንግስታዊ ሂደትን ማክበር፦ ማንኛውም የወሰን ማካለል፣ የ1997ቱን ህዝበ ውሳኔ ውጤት ጨምሮ ህጋዊና ሁሉንም ማህበረሰቦች ያሳተፈ መሆን እንዳለበት አሳስቧል።

3ኛ. የህዝቦችን አንድነት ማስቀጠል፦ የሶማሌ ህዝብ፣ በክልሉ አመራር የሚገፋውን ይህንን "ከፋፋይ አጀንዳ" እንዲቃወም ኦፌኮ ተማጽኗል።

4ኛ. ኃላፊነት የሚሰማው አመራር፦ የፌደራል እና የኦሮ*ሚያ መንግስታት ዝምታቸውን ሰብረው፣ የግዛት አንድነትን እንዲያስከብሩና ግጭትን ለመከላከል ወሳኝ እርምጃ እንዲወስዱ አጥብቆ ጠይቋል። "ዝምታ ተባባሪነት ነው" ብሏል መግለጫው።

5ኛ. ሰላማዊ ምላሽ፦ የኦ*ሮሞ ህዝብ መብቱን ለማስከበር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ሰላማዊ፣ በዲሲፕሊን የተመራና ህጋዊ በሆኑ መንገዶች ብቻ እንዲሆን አሳስቧል።

ኦፌኮ በመግለጫው ማጠቃለያ ላይ፣ በውይይት፣ በጋራ መከባበርና በህግ የበላይነት ላይ የተመሰረቱ መፍትሄዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

©️ዘ_ሀበሻ

በትግራይ ክልል ለጦ*ርነት አፈሳ ተጀመረ‼  በትግራይ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣው የፖለቲካ አለመግባባት ስጋት በመፍጠሩና ለጦርነት አፈሳ መጀመሩን ተከትሎ፤ ወጣቶች ክልሉን ለቀው እ...
26/07/2025

በትግራይ ክልል ለጦ*ርነት አፈሳ ተጀመረ‼

በትግራይ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣው የፖለቲካ አለመግባባት ስጋት በመፍጠሩና ለጦርነት አፈሳ መጀመሩን ተከትሎ፤ ወጣቶች ክልሉን ለቀው እየወጡ መሆኑን አስታውቀዋል።

"እኛ ጦር*ነት አንፈልግም" ያሉት ወጣቶቹ፤ "ከየትኛውም በኩል ኢትዮጵያዊነታችንን ለመግፋት የሚደረግ ጫና ተቀባይነት የለም" ብለዋል፡፡ "ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው አለመረጋጋት ስጋት ስላሳደረብን፤ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ቦታ ለቀን እየወጣን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

"በክልሉ እስር፣ ግድ*ያና ማስፈራራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መጥቷል" የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "ችግሩን የሚፈታ ሳይሆን የሚባባስ እየሆነ በመሄዱ ስጋት እየተፈጠረብን ነው። በዚህም ምክንያት ሕይወ*ታችንን ለመታደግ ስደትን እየመረጥን ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

"እኛ በአሁኑ ወቅት ወደ ጦር*ነት የሚያስገባን ጉዳይ የለንም። ከሆነም በንግግር መፍታት ነው የምንፈልገው" ያሉም ሲሆን፤ "ሆኖም ይህንን እንድናደርግ ዕድል የሚሰጠን ባለማግኘታችን በቂ ገንዘብ ያላቸው ጓዳኞቻችን ተመቻችቶላቸው ከሀገር አስቀድመው ወጥተዋል" ብለዋል።

አሐዱም ስለጉዳዩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማናገር ያደረገው ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ አልተሳካም።

ነገር ግን በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ አብዮታዊ ሕዝቦች (ኢህአፓ) ፓርቲ ዋና ሥራ አስኪያጅና የትግራይ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ወኪል ይሳቅ ወልዳይን እና የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃንን አነጋግሯል።

የኢሕአፓ ዋና የሥራ አስፈፃሚ አባሉና የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ተወካይ የሆኑት አቶ ይሳቅ ወልዳይ በሰጡት ምላሽ፤ ህወሓትና የፌደራሉ መንግሥት ወደ ጦር*ነት በመግባታቸው የትግራይ ወጣት ከኢትዮጵያዊን ወንድም እና እህቶቹ ጋር እንዲዋጋ ሆኗል" ሲሉ አስታውሰዋል።

"እንደ በፊቱ የትግራይ ወጣት ጦር*ነት አይፈልግም" ያሉት የሥራ አስፈፃሚ አባሉ፤ "አሁን የሚፈልገው ስደት ሳይሆን መማር እና መስራት ወደቀደመው ሕይወቱ መመለስ ነው" ብለዋል።

"የትግራይ ወጣቶች በአሁኑ ሰዓት ለስራ አጥነት፣ ለከፋ ችግር፣ ለጦር*ነት እና ለግጭት በመጋለጡ ስደትን እየመረጠ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃነ በሰጡት ምላሽ፤ "በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ወታደራዊ አመራሮችና በፌደራል መንግሥቱ መካከል በተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመግባባት ሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠትም ተግዳሮት ሆኗል" ሲሉ ገልጸዋል።

"ወጣቱ ትውልድ በአሁኑ ወቅት ወደ ሳዑዲ አረቢያና በሌሎች ሀገራት በባህር እየተሰደደ ነው፡፡ ይህን ደግሞ እልባት ሊሰጠው ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።

"አሁን ላይ የክልሉ ሕዝብ የሚፈልገው ጦር*ነት ሳይሆን ሰብዓዊ አቅርቦት ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

ለአሐዱ ቅሬታቸውን የገለጸት የትግራይ ክልል ወጣቶች በበኩላቸው፤ "የሚመለከተው አካል በሀገራችን በሰላማዊ መንገድ ሰርተን የምንቀየርበትን መንገድ እንዲፈጥርልን እንጠይቃለን" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ነው

እንኳን የአዲስአበባ ኮሪደር፣ የኒዮርክ ሲቲም ኮሊደር ጎርፍ ያጠልቀልቀዋል።
24/07/2025

እንኳን የአዲስአበባ ኮሪደር፣ የኒዮርክ ሲቲም ኮሊደር ጎርፍ ያጠልቀልቀዋል።

"ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ ትኩረት ታድርግ"ኢሳያስየኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት ረቡዕ ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም. ከአገራቸው ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢው ጋር ባደረጉት ሁለተኛ ክ...
24/07/2025

"ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ ትኩረት ታድርግ"ኢሳያስ

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት ረቡዕ ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም. ከአገራቸው ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢው ጋር ባደረጉት ሁለተኛ ክፍል ቃለ ምልለሳቸው "ኢትዮጵያ ከምታሰማው የጠብ አጫሪነት ንግግር ተቆጥባ በአንገብጋቢ የውስጥ ችግሮቿ ላይ ታተኩር" ሲሉ ተደምጠዋል።
ጠ/ሚ አብይ ከዚህ በፊት በም/ቤት የተናገሩት ተያይዞ ቀርቧል።
Wasu Mohammed - Mereja

 #አዲስ አበባ  ጊዮን ሆቴል አካባቢበተለይም በጊዮን ሆቴል እና አካባቢው መንገዶች በውኃ የተጥለቀለቁ ሲሆን ይህም በንብረት ላይ ጉዳት አስከትሏል።በማኅበራዊ ሚዲያ በሚዘዋወሩ ምስሎች እና ቪ...
23/07/2025

#አዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል አካባቢ

በተለይም በጊዮን ሆቴል እና አካባቢው መንገዶች በውኃ የተጥለቀለቁ ሲሆን ይህም በንብረት ላይ ጉዳት አስከትሏል።በማኅበራዊ ሚዲያ በሚዘዋወሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ላይ እንደታየው፣ በርካታ መኪኖች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በውኃ ውስጥ ተነክረው ታይተዋል።

Address

London
EC1A

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afar People's Voice - APV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Afar People's Voice - APV:

Share