
10/08/2025
የስልጤ ልማት ማህበር /Siltie Development Association
የአቶት ሆቴል ባለቤትና የስልጤ ልማት ማህበር
ስራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ሃጂ ሙከሚል ከዲር በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው ለአዲስ አበባ የስልጤ የባህልና የቢዝነስ ማዕከል የብሎኬት ድጋፍ አደረጉ ፡፡
ለስልጤ ልማት ማህበር ለተደረገው ድጋፍ የስልማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
የስልጤ ልማት ማህበር የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ሃጂ ሙከሚል ከዲር እንደገለፁት አዲስ አበባ ላይ የስልጤን ህዝብ ሁለንተናዊ የከፍታ ጉዞ ሂደትን ከዳር ለማድረስ የሚያግዘውን የህንፃ ግንባታ ማጠናቀቅ ትርጉሙ ብዙ እንደሆነ ገልፀው ሁሉም በሚችለው የአቅሙን ድጋፍ በማጠናከር ግንባታውን ማጠናቀቅ ይጠበቅብናል ብለዋል ፡፡
አያይዘውም ሃጂ ሙከሚል የህንፃው የግንባታ ሂደት እስከሚጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡
የስልጤ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሸምሴ ኑሪ በበኩላቸው የስልማ የስራ አመራር ቦርድ አባልና የአቶት ሆቴል ባለቤት ሃጂ ሙከሚል በተለያዩ ድንበር ተሻጋሪ ልማትና የበጎ ስራ እንዲሁም ቃልን በተግባር ተፈፃሚ የሚያደርጉ ባለሃብት ናቸው ብሏል ፡፡
አያይዘውም ስራ አስፈፃሚው ከዚህ በፊት ለስልጤ የባህልና የቢዝነስ ማዕከል ግንባታ ሂደት ብሎኬት ለማቅረብ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ በዛሬው ዕለትም ቃል የገቡትን ብሎኬት ማቅረብ መጀመራቸውን አንስተው ቃላቸውን በተግባር ስላረጋገጡልንና ገንዘብና ጊዜያቸውን ሰውተው የስልጤ ልማት ማህበርን ለማጠናከር እያደረጉ ላሉት ድጋፍ በስልጤ ልማት ማህበርና በህዝቡ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡