Bright future for Ethiopia

Bright future for Ethiopia Run in to success for peace and wellbeing of Ethiopia in horn and the world

የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል በተባሉ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ*********** ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላ...
25/08/2024

የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል በተባሉ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ
***********

ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ፦
• ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣
• አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣
• ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣
• ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣
• ይዲድያ ነጻነት አበበ እና
• እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገልጿል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል።

በጥላሁን ካሳ

15/02/2021

ክፍል ሁለት

ምኒልክ ሽዋ ከገቡ በኋላ የነበረው ኩናቴ ምን ይመስል ነበር?👇

እንደታሰበው ግን ምኒልክ ወደ ሸዋ ለመግባት አልተመቻቸውም ነበር ነገሩም አልጋ በአልጋ ከመሆን ይልቅ ቀጋ ከቀጋ ሚለው የበለጠ ይገልፀዋል፡፡ የሸዋው ንጉስ የነበሩት በዛብህ
"ምኒልክ ከአጤ ቴዎድሮስ ጋር ውል አለው፡፡ ውሉም እኛን አሳልፎ ለቴዎድሮስ መስጠት ነው፡፡ ...." በማለት አዋጅ አስነግሮ ለጦርነት እንዲዘጋጁ አደረገ፡፡

ቢሆንም ምንሊክ ሸዋ እንደደረሱ ደጃች ወልዴ እና አቶ ሀብተየስ ሳይዋጉ በሩን ለቀው ወደ ደፍራታ ሸሹ፡፡ የምኒልክ ሰራዊትም እየበዛ ሄደ..
የምኒልክን ወደ መሀል መግባት የሰሙት አቶ በዛብህ ከምኒልክ ጋር ጦር ለመግጠም ጋዲሎ ከተባለው ቦታ ተሰለፉ በዚህን ጊዜ አንዲት ሴት

"ማነው ብላችሁ ነው
ጋሻው መወልወሉ
ማነው ብላችሁ ነው
ጦራችሁ መሳሉ
ማነው ብላችሁ ነው
ካራችሁ መሳሉ
የጌታችሁ ልጅ ነው
አረ በስመዐብ በሉ" በማለት ገጠመች

ውጊያው ጋዲሎ ላይ ነሐሴ ፲፮ ቀን ተፋፍሞ
ሳለ ከአቶ በዛብህ ጋር ተሠልፈው የነበሩት
የ ሸዋ መኳንንት “በጌታችን በኃይለ መለኮት
ልጅ ላይ አንተኩስም” ብለው ወደምኒልክ
ዞሩ። አቶ በዛብህም ሸሽተው አፍቀራ ገቡ፤
ድሉም የምኒልክ ሆኖ ምሥራቅ ምስራቁን
ተጉዘው በድል አድራጊነት አባቶቻቸው ከተማ
አንኮበር ገቡ። ንጉሥ ምኒልክም በ አንኮበር
ጥቂት ወራት ከተቀመጡ በኋላ ወደ ደብረ
ብርሃን ወርደው አዲሱን ከተማቸውን ልቼ ን
እያሠሩ ተቀመጡ።
በጦርነቱም ምኒልክ ድል አደረጉ፡፡....ቀጣዩ ስራቸው የሆነውም ግዛታቸውን ማስፋፋት ሆነ፡ ከመጀመሪያው ጀምረው አብዛኛው ስራቸው ነገሮችን በሰላም መጨረስ በሸዋ አከባቢ ለተከፈሉት የኦሮሞ ባላባቶች
"ያሳደጋችሁኝ ልጃችሁ አብረን ያደግን ባልንጀራችሁ ነኝና በአባቴ አልጋ ከተቀመጥሁ በፍቅር ተገዙልኝ" እያሉ መልዕክተኛ ይልኩ ጀመር፡፡
በዚህም መሰረት
አርሲ:-__አንገዛም ብለው በማስቸገሩ ምኒልክ በ1874 ዘምተው ነበር፡፡
ወለጋ:-__ ባላባቱ ኩምሳ በሰላም ገበሩ
ከፋን ወላይታንም ማስገበር ጀመሩ፡፡
ምኒልክ ከነበሯቸው ጠባይ ዋነኛው የዲፕሎማሲ ዘዴ ስለነበረ ከባላባቱ ጋር ተዋግተው ዋናውን ባለባት ሲማርኩ በቦታው መልሰው ሚሾሙት ያንኑ የድሮውን ባላባት ሲሆን ካልሆነው የበላባቱን ልጅ ያለዚያም ህዝቡን እየሰበሰቡ የመረጠው ይሾሙ ነበር፡፡

እድሜ እና ጤና ከቸረን--. ይቀጥላል......

Address

London

Telephone

+251963327128

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bright future for Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bright future for Ethiopia:

Share