11/07/2025
🌹እንኳን አደረሳችሁ ሐምሌ 5 (፭) የፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው።
➦ ሐምሌ 5 ለጻድቁ አባታችን ድንግል ማርያም የብርሃን ዐይን የተከለችለት እለት ነው! ይኸውም ጻድቁ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዝቋላ ምድር ስለእትዮጵያ ሕዝብ ኃጢአት በባህር ቁልቁል ተዘቅዝቀው በመጸለያቸው #እግዚአብሔርም ይህን ጸሎታቸውን በመቀበል የኢትዮጵያን ሕዝብ እምርልሃለሁ ብሎ ስሙን ለጠሩ ዝክሩን ለዘከሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ከሳቸው ጋር ካደረገ በኃላ ወደ ምድረ ከብድ ላከው። አባታችን #ገብረ #መንፈስ #ቅዱስም በምድረ ከብድ እንደ አምድ ተክል ሆኖ ሰባት አመት ቅንድቡን ሳይከድን፤ ራሱን ወደ ምድር ዝቅ ሳያደርግ እጆቹን እንደዘረጋ ወደ ሰማይ እየተመለከተ ሰባት አመት ቆዬ። በዚህ የሰውን ጸሎትና #የእግዚአብሔርን ምሕረት የምቃወም ጠላት ዲያብሎስ በአባታችን የጸሎት ጽናት በመቅናት ጸሎታቸውን ልያቋርጥ በቁራ ተመስሎ ወደ እሳቸው ጋ መጣና "ውኃ ጠምቶኛል ቀድተህ አጠጣኝ" ስላቸው አባታችንም "ጸሎቴን አቋርጬ አንተን ውኃ አላጠጣም ና ከአይኔ ጠጣ" ብሎ አዘዘው። በመጽሐፍ "ሳታቋርጡ ጸልዩ" ተብሎ እንደተጻፈ ( #1ኛ.ተሰሎንቄ.5፥17)። ቁራውም ከአይናቸው ልጠጣ እንደመጣ መስሎ አይናቸውን ወጋው! ጸሎት አቋርጦ በሁለት ዐይን ገሃነም ከምገቡ ጸሎትን ባለማቋረጥ በአንድ ዐይን መንግሥተ ሰማያት መግባትን ሽተዋልና። #ጌታችንም በወንጌሉ "ሁለት ዐይን ኖሮህ ገሃነም ከምትገባ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ብትገባ ይሻላል" ብሎአልና ( #የማርቆስ.ወ.9፥47።) አባታችን #ገብረ #መንፈስ #ቅዱስም በጽናታቸው ሰይጣንን ድል ነሱት። ከፈተና መዳን የምንችለው ፈተና ውስጥም መግባት ከገባንም መውጣት የምንችለው በጸሎት ስንተጋ ነውና #(ሉቃስ.ወ.22፥40)። #ጌታችን #አምላካችን #መድኃኑታችም #ኢየሱስ #ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ ዲያብሎስን ድል እንዳደረገው ( #ማቴ.ወ 4፥1-11)። ጻድቁ ሰው ኢዮብም ከሰይጣን ጋር በመታገል ድል እምደነሳው #(መ.ኢዮብ 1) አባታችንም ዲያብሎስን በጸሎት ጽናት ድል ነስተውታል። ሐምሌ 5/፭ ቀን #እመቤታችን ለአባታችን የብርሃን ዐይን አምጥታ ተከለችለት።
የቅዱሳን መታሰብያቸው ከበረከት ጋር ለዘለዓለም ነውና የቅዱሳን ሀገር፣ የክርስትና መድና፣ ሀገሬ #እግዚአብሔር የሆነች እትዮጵያ #ቅዱሳንን ከማክበር በተጨማሪ #ቅዱሳን የምወለዱባት #ጻድቃን የምጠጉባት ሀገር ናት። ቅድስና ቅዱስ የሆነው #እግዚአብሔርን ቅዱስ እንደሆኔ በቅድስና ቅዱስ የምንሆንበት ሕይወት ነው። "እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" እንዳለን #(ኦ.ዘሌዋ 20፥7)። #ቅድስና የምታልፈውን አለም ንቆ የማታልፈውን ዘላለማዊ ሕይወት መናፈቅ ነው፤ #ቅድስና ራስን #ለእግዚአብሔር ነጥሎ ማውጣት, መለየት ነው። #ቅድስና አለም በሞቷ በምትገዛው ከካራን መውጣት #(ኦ.ዘፍጥረት.12፥1) ወተትና ማር የምታፈልቀው #የእግዚአብሔርን መንግሥት ከናአንን መናፈቅ ነው። የ #ቅዱሳን ሁሉ #አምላክ #ቅዱስ የሆነው #እግዚአብሔር ለእኛ ለኃጢአተኞችም የቅድስናን ሕይወት ያድለን። አሜን
የአባታችን በረከት ረድኤት ይደርብን ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን።አሜን አሜን አሜን 🤲🤲🤲