
05/10/2025
የ3 ልጆች እናት የሆኑትን እናት እናሳክማቸው !!😢
: እኚህ እናት አየለች አበበ ይባላሉ ። የ3 አዳጊ ልጆች እናት ናቸው ። በጡት ካንሰር ተጠቅተው ከአንድ ዓመት በላይ ሕመም ላይ ይገኛሉ።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ያላቸውን ጥሪት አሟጥጠው ተከታታይ የኪሞ ቴራፒ ሕክምና መውሰድ ችለዋል ። በሕመሙ ሳቢያ አንደኛውን ጡታቸውን አጥተዋል።
ያ ሁሉ አልፎም ግን አሁን ደግሞ አስቸኳይ የጨረር ሕክምና ማድረግ እንዳለባቸው፣ አለዚያ ግን አሳሳቢ እንደሚኾን የሕክምና ባለሙያዎች ገልጸውልናል። ለዚህም 70 ሺ ብር ተጠይቋል።
እትዬ አየለች በሽታው ከያዛችው ወዲህ ሥራ አቁመው፣ የነበረቻቸውን ጥሪት ለሕክምና በማዋላቸው አሁን ምንም ፍራንክ እጃቸው ላይ ባለመኖሩ ይህን ገንዘብ መክፈል አልቻሉም።
ያለንን አዋጥተን እኚህን የ3 አዳጊ ልጆች እናት እንታደግ የሚል ሰብዓዊ ጥሪ ቀርቦልናል።
አየለች አበበ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000721306503
አቢሲንያ ባንክ
20798882
*ማስታወሻ መርዳት ባንችል የሚረዳ ይኖራልና መረጃውን ለሌሎች በማጋራት እንተባበር !❤️🙏❤️