ስለ ቴክኖሎጅ about tech

ስለ ቴክኖሎጅ about tech Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ስለ ቴክኖሎጅ about tech, Digital creator, London.

FBC ውሃ ውስጥ የገባን ሞባይል ስልክ ማከሚያ መንገዶችአንዳንድ ስልኮች ውሃን በቀላሉ እንዳያሰርጉ ተደርገው የተዘጋጁ ቢሆንም፥ ውሃ ወደ ውስጠኛ ክፍላቸው የሚገባባቸው ሁኔታዎችን ግን ሙሉ በ...
04/12/2024

FBC
ውሃ ውስጥ የገባን ሞባይል ስልክ ማከሚያ መንገዶች
አንዳንድ ስልኮች ውሃን በቀላሉ እንዳያሰርጉ ተደርገው የተዘጋጁ ቢሆንም፥ ውሃ ወደ ውስጠኛ ክፍላቸው የሚገባባቸው ሁኔታዎችን ግን ሙሉ በሙሉ የዘጉ አይደሉም።
በየትኛውም አጋጣሚ የሞባይል ስልክዎ ውሃ ውስጥ ቢወድቅብዎ
• ፈጥኖ ከውሃው ውስጥ ማውጣት፦ ስልኩ በውሃ ውስጥ በቆየ ቁጥር የሚደርስበት ጉዳት እየከፋ ይመጣል።
• ስልኩን ፈጥኖ መዝጋት
• ከስልኩ መለየት የሚችሉ ለምሳሌ ባትሪውን እና ሲም ካርዱን ፈጥኖ ማውጣት
በሞባይል ስልኩ ውስጥ እርጥበት ስለሚኖር ይህ ካልተወገደ ስልኩ መስራት አይችልምና፥ እርጥበቱን ለማጥፋት፦
• በደረቅ እና ነፋስ ሊያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ፣
• ከ100 እስከ 110 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት እንዲያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ።
ስልኩ የአፕል ምርት ከሆነ ደግሞ፥ ኩባንያው እስከ 115 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት ሰጥቶ እርጥበቱን ማስወገድ እንደሚቻል ይመክራል።
• የሞባይል ስልኩ እስከሚደርቅ ድረስ ጥቂት ቀናት ማቆየት፣
ስልኩን በሩዝ ማከምም ሌላኛው አማራጭ ነው።
ለዚህም ውሃ ውስጥ የወደቀውን የሞባይል ስልክ በጥሬ ሩዝ ውስጥ በመክተት ማቆየት።
ይህ ደግሞ ሩዝ በተፈጥሮው እርጥበት የመሳብ ባህሪ ስላለው በስልኩ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመምጠጥ እንዲደርቅ ያደርገዋል።
ምንጭ፦ verizonwireless.com

የኮምፒውተሮን ፓስወርድ ረስተው ለመክፈት ተቸግረዋል? ይኸው መፍትሄውኮምፒውተሮን ፎርማት ማድረግ ሳይጠበቅቦ እንዲሁም ምንም አይነት መረጃ ሳይጠፋቦ የረሱትን ፓስወርድ በቀላል ዘዴ እንዴት እን...
16/04/2024

የኮምፒውተሮን ፓስወርድ ረስተው ለመክፈት ተቸግረዋል? ይኸው መፍትሄው
ኮምፒውተሮን ፎርማት ማድረግ ሳይጠበቅቦ እንዲሁም ምንም አይነት መረጃ ሳይጠፋቦ የረሱትን ፓስወርድ በቀላል ዘዴ እንዴት እንደሚስተካከል እንንገሮ

በመጀመሪያ ከሚከተሉት አንዱን OS ከኢንተርኔት ያውርዱ Back truck, Kali Linux ወይም Arch Linux
ከነዚህ OS አንዱን መጠቀም በቂ ነው


step 1: ከላይ Download ያደረጋችሁትን Operating System በ Flash Disk Boot ማድረግ
step 2: Flash Disk ላይ የጫነዉን Operating System F12 በማስነሳት
step 3: System 32 ዉስጥ በመግባት Sethc የሚለዉን ስም በመቀየር ወደ CMD መቀየርና ኮምፒተሮን shutdown ማድረግና Boot ያደረግነዉን Flash Disk መንቀል
step 4: ኮምፒተሮን መክፈትና Password ሲጠይቀን Shift 5 ጊዜ በመጫን
step 5: CMD Command ሲመጣ Net user %username% በማለት የምንፈልገዉን Password ማስገባት

like or share በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ

ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ?1፡ በስልኮዎ ውሰጥ ያሉ ፐሮግራሞቸ ልከፍት ይላሉ2፡ በ ሚሞሪ ካርድዎ እና በስልክዎ ውስጥ ያሉ የራስዎ ፋይሎች ራሳቸውን ይቀይራሉ በተለይ ደ...
11/03/2024

ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ?

1፡ በስልኮዎ ውሰጥ ያሉ ፐሮግራሞቸ ልከፍት ይላሉ
2፡ በ ሚሞሪ ካርድዎ እና በስልክዎ ውስጥ ያሉ የራስዎ ፋይሎች ራሳቸውን ይቀይራሉ በተለይ ደግሞ
በቫይረስ የተጠቃውስልክዎ ከሆነ ፋይሎችን አልያ ሶፍትዌሮችን ለመክፈት ሲሞክሩ application not
supported or file dasn’t exist የሚል
ሜሴጅ ሊመጣ ይችላል
3፡ የ ሰልክዎ የባትሪ ጉልበት በጣመ እየደከመ ይመጣለ ይሀ ምልክት ግነ በኖርማል ስልኮች ላይም
ሊስተዋል ይችላል ያ የሚሆነው ደግሞ የሚጠቀሙት ባትሪ ኦርጅናል ባለመሆኑና በሌሎችም ችግሮች
ሊሆን ይችላል ለምሳሌ የስልክዎ ባትሪ
ኮኔክተር ችግር ካለበት ባትሪዎን ቶሎ ቶሎ ይጨርስበወታል (ስለዚክና መሰል ጉዳዮች በሌላ ፕሮግራም
ላይ በሰፊው እንጨዋወታለን)
4: ምናልባት ስልክ ደውለው እያናገሩ እያለ አልያ ደግሞ ገና እየደወሉ እያለ ስልክዎ ይቋረጣል :
(ይህም ሌላ ምክነያትሊኖረው ይችላል ለምሳሌ የስልክዎ ስክሪን ችግር
ካለበትና ስልክዎ ባጋጣሚ የሚጠፋ ከሆነ፣የባትሪዎ ችግርም ሊሆን ይችላል|)
5: በስልክዎ ላይ በጫኑት አፕልኬሽን እየተጠቀሙ እያሉ ፕሮግራሙ በራሱ ጊዜ ሊዘጋበዎ ይችላል
6: እንደ አጠቃላይ ልናየው የምንችለው ደግሞ የስልክዎ ነገራቶችን በፍጥነት የመከወን ብቃት እጅጉን
ይቀንሳል ተሰላችተ እስከመወርወር ድረስ ሊያናድድዎም ይችላለ
ስለምለክቶቹ ይህን ያክል ካልን እንዴት መከላከል እንዳለብንና እንዴትስ ሁነቱ ከተከሰተ በኋላ
ማስወገድ እንደምንችል አንዳንድ ነገራቶችን እንጥቀስ
1፡ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ እያለ ከሆነ ክስተቱ የተፈጠረው ስልክዎን ወዲያውኑ አጥፍተው ያብሩት/
ያስነሱት ይህን ማድረግዎ ኦንላይን የተለቀቁ ቫይረሶች በስልክዎ ላይ ለውጥ ማምጣት እንዳይችሉ
ይረዳወ ዘንድ ነው
2: የተጠራጠሩትን ፕሮግራም ከሞባይልዎ ሾርትከት ላይ ለማጥፋት ይሞክሩ ይህ አልሆን ካለ
3: ከስልክዎ ውሰጥ setting የሚለውን በተን ተጭነው app የሚለውን ጠቅ ሲያደርጉ ብዙ
ፕሮግራሞች ይታያሉ ከነኛ መካከልእርስዎ የተጠራጠሩትን ያጥፉት select and then press uninstall
4: ከ setting ሳይወጡ ወደሆላ በመመለስ security የሚለውን ይምረጡ ከዚክ ጋ device
adminstartore የሚለውን ይጫኑትና በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉትን በሙሉ አጥፍተው
ስልክዎን ሪስታርት ያድርጉት ምናልባት ስልክዎ ቫይረስ ከሌለው ይህኛው አማራጭ በ ቼክ ቦክስ
cheekbox ቲክ የተደረጉ ፕሮግራሞችን ላያመጣ ይችላል

Watch on tiktok
27/02/2024

Watch on tiktok

Watch, follow, and discover more trending content.

የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ከመጠን በላይ ሙቀት ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች90 በመቶ የሚሆኑት የላፕቶፕ ኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ላፕቶፕፓቸውከመጠን በላይ እንደሚሞቅ ይናገራሉ።ይህ ከመጠን በላይ የሆነ...
27/02/2024

የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ከመጠን በላይ ሙቀት ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች
90 በመቶ የሚሆኑት የላፕቶፕ ኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ላፕቶፕፓቸው
ከመጠን በላይ እንደሚሞቅ ይናገራሉ።
ይህ ከመጠን በላይ የሆነ ሙቀትም ላፕቶፓችን በትክክል እንዳይሰራ እና
በውስጡ ያሉ ማሽኖች እንዲበላሹ ሊያደርግም ይችላል።
ቀጥሎ የተዘረዘሩት እና ላፕቶፓችን ከመጠን በላይ እንዳይሞቅ ሊያደርጉ
የሚችሉ ምክሮችን በመተግበር የላፕቶፓችንን እድሜ ለማራዘም እንችላለን።
1. የሃይል አጠቃቀም፦ በብዛት በላፕቶፕ ላይ ስንሰራ ላፕቶፓችንን ቻርጅ ላይ
በመሰካት ሰንጠቀም ከፍተኛ የሆነ ሀይል እንዲጠቀም ስለሚያደርግ ላፕ
ቶፓችን ከመጠን በላይ እንዲሞቅ ያድርጋል።
ይህንን ለመከላከልም በላፕቶፕ ኮምፒውተራችን ታስክ ባር ላይ ያሉ ሀይል
ለመቆጠብ የሚያስችሉ አማራጮች በመምረጥ ሀይል እንዲቆጥብ በማድረግ
ላፕ ቶፓቸን ከመጠን በላይ እንዳይሞቅ ማድረግ ይመከራል።
2. በአየር መንፊያ / Air Compressor/ ላፕቶፓችን ውስጥ የሚገባን አቧራ
ማፅዳት፦ አቧራ ባለበት አካባቢ የምንሰራ ከሆነ ላፕቶፓችን ባሉት ቀዳዳዎች
አቧራ ገብቶ በመድፈን ከመጠን በላይ እንዲሞቅ ያደርገዋል።
ስለዚህም ላፕቶፓችንን በየጊዜው በአየር መንፊያ ማሽን / Air
Compressor/ በመጠቀም በየጊዜው በማፅዳት የላፕቶፓችንን እድሜ
ማራዘም እንችላለን።
3. የምናስቀምጥበትን ቦታ መምረጥ፦ በበዛት ላፕቶፕ ለመጠቀም
እንዲያመቸን አልጋችን ላይ እንጠቀመላን።
ለስላሳ ነገሮች ከላፕቶፑ የሚወጣ ሙቀት እንዳይወጣ በማደረግ ሙቀቱን
ወደ ላፕቶፑ እንዲመለስ በማድረግ የላፕቶፑ ውስጠኛው አካል በሙቀት
እንዲጎዳ ያድርጋል።
ስለዚህም ላፕቶፕ በምንጠቀምበት ጊዜ እንደ ጠረጴዛ ያሉ ጠፍጣፋ ነገሮች
ላይ በማደረግ መጠቀም ይመከራል።
4. ላፕቶፕ ኮምፒውዩተሩን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት፦ የላፐቶፕ
ኮምፒውተራችንን በማንጠቀምበት ሰዓት ሙሉ ለሙሉ በማጥፋተ
ማሰቀመጥም ላፕቶፓቸን ከመጠን በላይ እንዳይሞቅ ያደርጋል።
ላፕቶፑን አንደገና እጠቀምበታለን ብለን ሙሉ ለሙሉ ሳናጠፋ ወይም
ስታንድባይ ላይ የምናሰቀምጥ ከሆነ ላፐቶፑን ከመጠን በላየ የሆነ ሙቀት
ሊሞቅ ይችላል።
ስለዚህ ላፕቶፓቸን ከመጠን በላይ እንዳይሞቅ በማንጠቀምበት ሰዓት ሙሉ
ለሙሉ ማጥፋት ይመከራል።

በኮምፒውተራችን ወይም (USB) በፍላሻችን ውስጥ የተደበቁ(hidden) ፋይሎችን እንዴት ማግኘት እንችላለን?እንዳስቀመጥናቸው እርግጠኛ የሆናቸውፋይሎችእና ፎልደሮች ተደብቀው ነገር ግን ከእይታ...
23/02/2024

በኮምፒውተራችን ወይም (USB) በፍላሻችን ውስጥ የተደበቁ
(hidden) ፋይሎችን እንዴት ማግኘት እንችላለን?እንዳስቀመጥና
ቸው እርግጠኛ የሆናቸው
ፋይሎችእና ፎልደሮች ተደብቀው ነገር ግን ከእይታችን ሊሰወሩ
ይችላሉ፡፡ ይህ በሚያጋጥመን ጊዜ ኮምፒውተራችን እንዲያሳየን
የሚደርገውን ቅንብር በማስተካከል
እንድንመለከት ያስችለናል ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቅደም ተከተል
የተቀመጡትንመንገዶች በመከተል የኮምፒውተርዎን ቅንብር
ያስተካክሉ፡ -
1. Start የሚለው ምልክት በመጀመርሪያ እንመርጣለን
2 በመቀጠል ኮንትሮል ፓናል (control panel)
3. ከሚቀርቡለን ምርጫ ውስጥ Appearance and
Personalizationየሚለው ላይ ክሊክ እናደርጋለን
4. ቪው (view) የሚለውን እንጫናለን ከዚያ አድቫንስድ ሴቲንግ
(advancing setting) እናገኛለን
5. በመጨረሻም Show hidden files, folders,
anddrives ክሊክ ካደረግን በኋላ ok የሚለውን መርጠን
እናጠናቅቃለን፡፡
Or
start >run >cmd> f:attrib -r -s -h /s /d we can use this
please like or share it

Address

London

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ስለ ቴክኖሎጅ about tech posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share