Ethiopian Drama

Ethiopian Drama Ethiopian Drama, Movies, Music, Comedy and everything Ethiopian.

07/08/2025
"እንዳለሁ አበራለሁ"በእንግሊዝኛ "Shining As I Am" በሚል ርዕስ የወጣውና በአማዞን ላይ "Best Seller" ለመሆን የበቃው የደራሲ ማክዳ አርሺ የህፃናት መፅሃፍ "እንዳለሁ አበራ...
07/08/2025

"እንዳለሁ አበራለሁ"

በእንግሊዝኛ "Shining As I Am" በሚል ርዕስ የወጣውና በአማዞን ላይ "Best Seller" ለመሆን የበቃው የደራሲ ማክዳ አርሺ የህፃናት መፅሃፍ "እንዳለሁ አበራለሁ" በሚል በታገል ሰይፉ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል።

የመፅሃፉ ዋና ትኩረት በህፃናት ላይ ስለ ኦቲዝም ግንዛቤ መፍጠር ሲሆን አንድ ኦቲስቲክ የሆነ ልጅ የአንድ ቀኑን ውሎ ከራሱ አንደበት በሚያሳይ መልኩ የተተረከ ነው። ታሪኩ፣ ህፃናት ኦቲዝም ምን እንደሆነ በቀላልና ግልፅ በሆነ ቋንቋ እንዲረዱ ከማስቻሉም በላይ፣ በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበትና ጥንካሬ ያጎላል።

ደራሲ ማክዳ አርሺ፣ ኦቲስቲክ ልጆች አለምን የሚገነዘቡበት መንገድ ልዩ መሆኑንና ይህም እንደ እርግማን ወይም እብደት ሳይሆን እንደ ተፈጥሯዊ የአእምሮ እድገት ልዩነት ሊታይ እንደሚገባ ታስረዳለች።

ከዚህ ቀደም "የአለም መብራቶች" የተሰኘ ሌላ የህፃናት መፅሐፍ ለንባብ ያበቃችው ደራሲዋ፣ በስራዎቿ በርካታ ሽልማቶችን አግኝታለች።
ይሄው በአይነቱ የተለየ "እንዳለሁ አበራለሁ" መፅሃፍ ነሃሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በልዩ ሁኔታ ተመርቋል።

📸 Markon

“ወደ ማዶ”በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ30 የአለም ሀገራት መድረኮች የሚታይ ወደ ማዶ" አለም አቀፍ የትያትር ጉዞ ሊጀመር ነውበኢትዮጵያ የትያትር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ30 የአለም ሀገራት...
25/07/2025

“ወደ ማዶ”

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ30 የአለም ሀገራት መድረኮች የሚታይ ወደ ማዶ" አለም አቀፍ የትያትር ጉዞ ሊጀመር ነው

በኢትዮጵያ የትያትር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ30 የአለም ሀገራት መድረኮች የሚታይ ወደ ማዶ" አለም አቀፍ የትያትር ጉዞ ሊጀመር እንደሆነ የትያትሩ አዘጋጆቹ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

አንጋፋ ተዋንያን የሚተውኑበት ይህ "ወደ ማዶ" የተሰኘው ትያትር በውጭ ሃገር መድረክ እንደሚመረቅም ተገልጿል፡፡

ይህን እስካሁን ባልተለመደ መልኩ በ30 አለም አቀፍ መድረኮች የሚታይ ትያትርን ፕሮዲውስ ያደረገው ዋካ ፕሮሞሽንና ኢቨንት ነው፡፡

"ወደ ማዶ" የተሰኘው እና ኮሜዲ ዘውግ ያለው ትያትር ን ለመስራት ብዙ አመታትን የፈጀ ሲሆን በትወና ብቃቷ ከፍተኛ የተመልካች ፍቅርና አድናቆት ያላት ሃረገወይን አሰፋን ጨምሮ ሸዋፈራው ደሳለኝ እና የኋላእሸት ዘሪሁን ይተውኑበታል፡፡

በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተደርሶ በሴም አማኑኤል የተዘጋጀው "ወደ ማዶ" ትያትር ማህበራዊ ጉዳዮችን እያነሳ የሚሄድ፤ ሲሆን በሕይወታችን የሚገጥሙን ችግሮች ለማውጣት የሚደረግን ትንቅንቅ የሚያሳይ ነው፡፡

ወደ ማዶ" አለም አቀፍ የትያትር ጉዞ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ አህጉራት በሚገኙ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ከ30 በላይ መድረኮች ይታያል ተብሏል፡፡

የትያትሩ ይፋዊ የመክፈቻ መርሃ ግብር ታላላቅ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የጥበብ ወዳጅ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በነሐሴ ወር በአፍሪካ የተለያዩ ሃገራት ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም እስካሁን ባልተለመደ መልኩ ትያትሩ በሚታይባቸው ሀገራትና መድረኮች ከትያትሩ ጎን ለጎን ለ"የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል" የገቢ ማሰባሰቢያ እንደሚካሄድም ተነግሯል፡፡ ይህንንም በጎ አላማ ለማሳካት ከማዕከሉ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ትያትሩን ፕሮዲውስ ያደረገው ዋካ ፕሮሞሽንና ኤቨንት በኪነ ጥበቡ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የረጅም ጊዜ ልምድ የካበተ ሲሆን ትያትርና ፊልሞችን ጨምሮ የተለያዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት ይታወቃል፡፡

22/07/2025

የበረሮ ወተት ከላም ወተት በ3 እጥፍ የበለጠ ጤናማ ነው - በፕላኔቷ ላይ በጣም ገንቢ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች አንዱ ነው_ ጥናት

በአዲስ ጥናት መሰረት የበረሮ ወተት በፕሮቲን፣ በቅባት እና በስኳር የበለፀገ ሲሆን ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉንም አሚኖ አሲዶች ይዟል።

በተጨማሪም በረሮዎችን ማቆየት ርካሽ እንደሆነ እና በአካባቢ ላይ በጣም ያነሰ ጉዳት እንደሚያደርሱ ተጠቅሷል። ይህ ግኝት ለወደፊት የምግብ ፈጠራዎች ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል - የበረሮ ወተት በመደብሮች ውስጥ መሸጥ ሊጀምር ይችላል።

ጠቃሚ መረጃእናት ባንክ ለእናት መላ የትምህርት ቤት  ክፍያ ሥርዓት ( Unicash) ተጠቃሚ ለሆኑ ት/ቤቶች ያቀረበው አገልግሎት ምንድን ነው?የክፍያ ሥርዓቱ ( uni cash) የትምህርት ክ...
15/07/2025

ጠቃሚ መረጃ

እናት ባንክ ለእናት መላ የትምህርት ቤት ክፍያ ሥርዓት ( Unicash) ተጠቃሚ ለሆኑ ት/ቤቶች ያቀረበው አገልግሎት ምንድን ነው?

የክፍያ ሥርዓቱ ( uni cash) የትምህርት ክፍያን ለመቀበል፣ ተማሪዎችን ለመመዝገብ፣ የተማሪዎችን መረጃ ለማስተዳደር፣ የፋይናንስ ሪፖርት ለማዘጋጀት፣ ከተማሪ ወላጆች ጋር ያለውን ግንኙነትን ለማሳለጥ፣ የጉዞና የመጽሐፍ ግዢ ክፍያን በቀላሉ ለመፈጸም ያስችላል፡፡
በዚህ አሰራር ተጠቃሚ ለሆኑ የግል የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ መምህራን እና ሌሎች ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤትና የመኪና መግዣ አዲስ የብድር አገልግሎት ማመቻቸቱን አስታውቋል።
ባንኩ የተሟላ፣ ቀልጣፋ እና ምቹ የባንክ አገልግሎት ለሁሉም ማህበረሰብ ማቅረብ አንዱ አሰራር ሲሆን፤ ይህኛው የብድር አገልግሎት በትምህርቱ ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎችን ለመደገፍ እና ተጠቃሚ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል፡፡
ከተዘጋጁት የብድር አይነቶች መካከል:-

1.የአጭር ጊዜ ብድር (የግል ብድር)
2.የደመወዝ ቅድመ ክፍያ ብድር
3.የመኪና ብድር
4.የቤት መግዣ ብድር ናቸው።
የብድር አገልግሎቱ ለደንበኞች ተመጣጣኝ የወለድ መጠን፣ አነስተኛ የመያዣ መስፈርት፣ የመክፈል አቅምን መሰረት በማድረግ የክፍያ ጊዜ አማራጮችን አቅርቧል።

ፍትህ ለቀነኒ በለንደን!!
11/07/2025

ፍትህ ለቀነኒ በለንደን!!

10/07/2025
ሰበር ዜናለአንዱአለም የተሰጠው ሽልማት ተነጠቀ!
05/07/2025

ሰበር ዜና

ለአንዱአለም የተሰጠው ሽልማት ተነጠቀ!

አሳዛኝ ዜና 💔ከ2 ሳምንት በፊት ተሞሽሮ ነበር።
03/07/2025

አሳዛኝ ዜና 💔

ከ2 ሳምንት በፊት ተሞሽሮ ነበር።

“የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ “ህይወት አድኖ ህይወቱን የሰዋው ዮናታን
01/07/2025

“የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ “
ህይወት አድኖ ህይወቱን የሰዋው ዮናታን

Address

London

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Drama posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share