Amhara Satellite Media Network ASAMN

Amhara Satellite Media Network ASAMN Amhara satellite Media Network
Focus on the social , economic & political
issues of Amhara and Ethiopia at large የ YouTube ቻናላችን >> bit.ly/3nhGJe3

ከስሞች ሁሉ ልቤን የሚያሞቁት በተለይ ዉባንተ አባተ ኮር እና ዞብል አምባ ክፍለጦር አፋብኃ የሚባሉ ስሞች 👌❤የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ ...
19/10/2025

ከስሞች ሁሉ ልቤን የሚያሞቁት በተለይ ዉባንተ አባተ ኮር እና ዞብል አምባ ክፍለጦር አፋብኃ የሚባሉ ስሞች 👌❤
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ታሪካዊቷ ጉና ክፍለጦር፣ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር፣ጣና ገላዉዲወስ ክፍለጦር እና ነበልባሉ ፎገራ ክፍለጦር በደቡባዊው ጎንደር ቀጠና ከፍተኛ ድል ተቀዳጅተዋል።

የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ጉና ክፍለጦር አንበሳዉ እስቴ ዴንሳ ብርጌ፣አንዳቤት ብርጌድ፣ሀገረ ቢዘን ብርጌድ፣መቅደላ ብርጌድ ፣የጉና ክፍለጦር ቃኝ እና መሀንዲስ እንዲሁም የጉና ክፍለጦር አመራሮች እና የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር አመራሮች የተሳተፉበት አዉደዉጊያ ተደርጎ በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል።

ዛሬም እንደ ትናንቱ ታላቅ ድል የፈፀሙት የጉና ክፍለጦር የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ከጧቱ 12:00 ጀምሮ ከአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ፊት ለፊት የጨበጣ አዉደዉጊያ በማድረግ ሶስት የክንክሬት ምሽግ በመሰባበር ጠላትን ሙሉ ለሙሉ ደምስሰዉታል።

አዉደዉጊያዉ በእስቴ መካነየሱስ ከተማ፣በደንጎልት፣በዮቅራሀ እና ጌጣ አድማሱን አስፍቶ የተካሄደ ሲሆን በዮቁራሀ፣ቄጣ እና ደንጎልት የፈረጠጠዉ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል።በዚህ አዉደዉጊያ የሀገረ ቢዛን ብርጌድ እና የአንዳ ቤት ብርጌድ አንድ ሻለቃ በጋራ ተሳትፈዋል።

የጉና ክፍለጦር አመራሮች እና የኮሩ አመራሮች በጋራ በመሆን አዉደዉጊያዉን የመሩት ሲሆን የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ፣የሀገረ ቢዘን እና የአንዳቤት ብርጌድ አመራሮችም ዉጊያን በጥበብ እና ሰንሰለቱን በጠበቀ መልኩ መርተዉታል።

ከከተማዋ ዉጭ የነበረዉን የጠላት ኃይል በማፅዳት በአፋጣኝ እስቴ መካነየሱስ ከተማን የተቆጣጠሩት የጉና አናብስቶች በከተማ የሰፈረዉን እና አመራር ሲጠብቅ የነበረዉን የአገዛዙን ጡት ቆራጭ ቡድን ድባቅ መተዉታል።

መካነየሱስ ከተማን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር የታሰሩ እስረኞችን ማስፈታት የተቻለ ሲሆን ከታሰሩት መካከል አስር ቀን ያልሞላት እመጫት በአገዛዙ በግፍ ታስራ ዛሬ በልጆቾ የበረታ ክንድ ተለቃለች።በተጨማሪም አገዛዙ ስለሚሊሺያ ቀለብ ከዝኖ ያስቀመጠዉ ሎጀስቲክ በጀግኖቹ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ልጆች ቁጥጥር ስር ዉሏል።

በአጠቃላይ በርካታ የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን ሶስት ብሬን እና ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ምርኮ ተደርጓል።ከሞት የተረፈ ከ130 በላይ የጠላት ኃይል ምርኮኛ ተደርጓል።ቁጥሩ ከ100 በላይ የሚሆን የጠላት ኃይል ደግሞ ተደምስሷል።

በዚሁ ቀጠና የአንዳ ቤት ብርጌድ አንዳቤት ከተማ በመግባት በጠላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፅሟል።ጠላት በጀግኖቹ የአንዳቤት ብርጌድ ከበባ ዉስጥ ገብቱ ነፍስ ዉጭ ነፍስ ገቢ ሲል ዉሏል።ሌላኛዋ የጉና ክፍለጦር መቅደላ ብርጌድ ወደ እስቴ መካነየሱስ ሲጓዝ በነበረዉ የጡት ቆራጩ የበሰልፅግና ሰራዊት ላይ በሶስት የተጠና ቦታ ደፈጣ በመጣል አብዛኛው ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል።በተጨማሪም በጋሳኝ ከተማ በመግባት በርካታ የሚሊሺያ ኃይል በመደምሰስ ቀሪዉን ደግሞ ምርኮኛ ማድረግ ችለዋል።

በሌላ መረጃ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር፣የጣና ገለዉዲወስ እና የነበልባሉ ፎገራ ክፍለጦር ከደራ ሀሙሲት ከአርብ ከተማ በመዉጣት ወደ እስቴ መካነየሱስ ጉዞ በማድረግ ላይ በነበረዉ የጠላት ኃይል ላይ እርምጃ በመዉሰድ በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዉበታል።ጀግኖቹ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ልጆች ከአርብ ገብያ የወጠዉን ኃይል ድባቅ በመምታት ወደ መጣበት አሳፍረዉ መልሰዉታል።

በዛሬው አዉደዉጊያ ከፍተኛ ድል የተገኛ ሲሆን ከሰሞኑ በአገዛዙ በጭካኔ የታረዱ እህቶቻችን ደም ተመልሷል።በዛሬዉ አዉደዉጊያ አንድነት የታየበት ሲሆን የራስ ተራራው ጉና ክፍለጦር የጠላትን መንገድ በመዝጋት የጠላትን አቅጣጫ ማደናቀፍ ችለዋል።በተጨማሪም የጀኔራል ሀይሌ መለሰ ክፍለጦር በስማዳ ወገዳ ከተማ በመግባት ታላቅ ድል ፈፅሟል።

በዚህ አዉደዉጊያ በርካታ ጀብዶች የተገኙ ሲሆን የድሎችን ዉጤት ከሚመለከተዉ አካል ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Zewudu

የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ ተሻለ ተገደለ! በአፋብኃ አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የአባ ኮስትር ብርጌድ የሰርጂካል ኦፕሬሽን ምድብተኞች ዛሬ ጥቅምት...
16/10/2025

የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ ተሻለ ተገደለ!
በአፋብኃ አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የአባ ኮስትር ብርጌድ የሰርጂካል ኦፕሬሽን ምድብተኞች ዛሬ ጥቅምት 06/2018 ዓ/ም ብቸና ከተማ በመግባት በወሰዱት እርምጃ፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የሆነው አቶ አዲሱ ተሻለን በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ እንዳለ መግደላቸውን መረብ ሚዲያ ከክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በዚህ ሆድ አደርና ለግል ጥቅሙ ሲል የሕዝቡን መከራ እያራዘመ በሚገኝ ካድሬ ላይ እርምጃው የተወሰደው ዛሬ ማለዳ ላይ ሲሆን፡ ከዚህ ቀደም ከተሰጠው ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መማር ያልቻለ ባንዳ ነው ተብሏል።

አመራሩ፡ ለብዙ ጊዚያት የአገዛዙን ተልዕኮ በመቀበል የአማራን ህዝብ ሲያስጨፈጭፍ የነበረ፣በዲማ ቅዱስ ጊወረጊስ ገዳምን ትዛዝ እየሰጠ ጉዳት እንዲደርስ ያደረገ፣የሀዲስ አለማየሁ ሙዚየምን ያቃጠለ እንዲሁም በእነማይ ወረዳ እና ቢቸና ከተማ የፋኖን ቤተሰብ ናቹህ እያለ በእስር፣በእንግልትና መሰል የስቃይ ወጥመድ ሲያንገላታና ሲያሰቃይ የነበረ ቀንደኛ ባንዳ ነው የተባለው የኋላ ታሪኩ ሲፈተሽ።

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በድል ተጠናቀቀ!በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ መስከረም 14/2018 ዓ.ም የተጀመረው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በበርካታ ወታደራዊና...
13/10/2025

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በድል ተጠናቀቀ!

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ መስከረም 14/2018 ዓ.ም የተጀመረው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በበርካታ ወታደራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ታጅቦ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተቋጭቷል::

ዘመቻው፣ መስከረም 14/2018 ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት በአምስቱም ኮሮች በተመሳሳይ ሰዓት ውጊያ በመክፈት ከጀመርንበት ቅጽበት አንስቶ የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ፡-

ምስራቅ አማራ ኮር 1፣ ምስራቅ አማራ ኮር 2፣ ላስታ አሳምነው ኮር፣ ልጅ ዕያሱ ኮር፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ የዕዙ ልዩ ዘመቻ እንዲሁም በአንዳንድ ቀጠናዎች በቅንጅት የድርጅታችን አካል የሆኑት ቴዎድሮስ ዕዝ፣ አሳምነው ዕዝ፣ በላይ ዘለቀ ዕዝ እና መላው የሰራዊታችን አባል፣ በየደረጃው የሚገኙ የኃይል አመራሮች እና የዕዛችን ሥራ አስፈጻሚ አመራሮች 24/7 እረፍት አልባ የውጊያ ተሳትፎና አመራር በመስጠት የኀልውና ትግሉን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ማስገባት ተችሏል፡፡

ዘመቻው ታቅዶ ወደተግባር ከተገባበት ጊዜ ጀምሮ የድርጅታችን አፋብኃ ቀጠናዊ አመራሮች የሞራል ድጋፍ ከመስጠት ጀምሮ፤ የዘመቻው አካል በመሆን የጠላትን እንቅስቃሴ በመገደብ አልፎም ባደረግናቸው የጋራ ውጊያዎች፣ የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል መሪ ድርጅት እንደተፈጠረ በተግባር አሳይተናል፡፡

ለ18 ቀናት ያለ እረፍት በዘለቀው ዘመቻ አባ ናደው በርካታ የነፍስ ወከፍ የቡድንና መካናይዝድ ጦር መሳሪያዎችን ከበርካታ ተተኳሽ ጋር እንዲሁም ከ20 በላይ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በምርኮ የተገኘበት ሲሆን፤ ጠላት አምስት ክፍለጦሮቹ የተበተኑበት፤ ውጊያን አቅደው የሚመሩ የውጊያ መሃንዲሶቹን ጨምሮ በርካታ መስመራዊ መኮንኖቹን ያጣበት፤ በመቶዎች የተማረኩበትና በሽዎች ሙትና ቁስለኛ የሆነበት ስኬታማ ዘመቻ እንደነበር በግምገማችን አረጋግጠናል፡፡

የአማራ የኀልውና ትግል ከጀመረበት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ጠላት ካስተናገዳቸው ኪሳራዎቹ እጅግ የከበደውን ኪሳራ በዘመቻ አደም አሊ አስተናግዷል፡፡

ፋኖ በርካታ ወረዳዎችን፣ ከተማ አስተዳደሮችንና ሰፊ ቀጠና የተቆጣጠረበት፣ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በሰፊው የዘረጋበት፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም በቀጣይ እንደ አማራ፣ አፋብኃ በሚያውጀው ዘመቻ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ትልቅ ፍንጭ የሰጠንበት አቅማችንን ለወዳጅ ጠላት ያሳየንበት ልዩ ዘመቻ ነበር፡፡

በጥቅል ግምገማችን በዘመቻው የፋኖ የኀልውና ትግል አዲስ የትግል ምዕራፍ የደረሰበት በመሆኑ በተመዘገበው ድል ሰራዊታችንና ድርጅታችን ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት የሆነው መላው የአማራ ሕዝብና የአማራ ትግል ደጋፊዎች እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

ከምንም በላይ የአማራ ፋኖ ትግል ዓለማቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንደሚያከብር፣ በምርኮኛ አያያዙ ለዓለማቀፉ ማኀበረሰብ በማሳየት ትግላችን ራስን የመከላከል፣ እንዲጠፋ የተፈረደበትን ሕዝብ ኀልውና የማዳን ተልዕኮ እንደሆነ በተግባር ማስመስከር ችለናል፡፡

ነፃ በወጡ ከተሞችና የወረዳ ማዕከላት ደማቅ አቀባበል ያደረገልን ሕዝባችን፣ በተሳትፎው የትግሉ ባለቤትነቱን ዳግም አስመስክሯል!!

የአለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ (International humanitarian law) በሚደነግገው መሠረት ሰብዓዊ ክብራቸውን በጠበቀ ሁኔታ የያዝናቸው የቀድሞ የብልጽግና ሰራዊት አባላት ይህን ምስክራቸውን በዓለማቀፉ ማኀበረሰብ አባላት ፊት መስክረዋል፡፡ ይህ አዲሱ የአማራ ኀልውና ትግል የታሪክ ምዕራፍ ነው፡፡

በቀጣይም እንደ ድርጅት በምናደርጋቸው ዘመቻዎች ለአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ ተገዢ ሆነን እስከ አራት ኪሎ ድረስ እንደምንዘልቅ ዳግም ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

አጠቃላይ ባለፉት 18 ቀናት በዘመቻ አባ ናደው የተመዘገቡ ዝርዝር ቁጥራዊና ሌሎች መረጃዎችን የማጠቃለያ ሪፖርትን ይዘን እንመለሳለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)በሰሞኑ ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በርካታ ሰራዊቱ የተደመሰሰበትና የተማረከበት ብልፅግና ከወለጋ ያመጣው የማዕከላዊ ዕዝ ሰራዊት ከወልድያ እ...
10/10/2025

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)

በሰሞኑ ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በርካታ ሰራዊቱ የተደመሰሰበትና የተማረከበት ብልፅግና ከወለጋ ያመጣው የማዕከላዊ ዕዝ ሰራዊት ከወልድያ እየጠፋ ምኒልክ ዕዝን እየተቀላቀለ ነው::

ሰሞኑን በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከባድ ሽንፈት የገጠመው ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግናየተደመሰሰበትንና የተማረከበትን አምስት ክፍለጦር ሰራዊት ለመተካት ከተለያየ ክልል ያመጣው ምልምል ሰራዊት ወልድያ ከደረሰ በኋላ እየጠፋና እየኮበለለ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለ ሲሆን መስከረም 29/2018 ዓ.ም ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር ሰባት አሳምነው ክፍለጦር ሁለት አጠቃላይ ዘጠኝ የሰራዊቱ አባላት ተቀላቅለዋል:: ኮሎኔል ሞገስ ዘገየን ጨምሮ የምኒልክ ዕዝ የክፍለጦር የኮርና የድርጅት ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል::

ኮብልለው ፋኖን የተቀላቀሉ የማዕከላዊ ዕዝ አባላት የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋትና ወረራ እየፈፀመ ያለው ብልፅግና ሁሉንም ነገሩን አሟጦ አማራ ላይ ወረራ እየፈፀመ ስለሆነ አማራ ሆነን አማራ ላይ ወረራ አንፈፅምም እንዲያውም እድሉን በማግኘታችን ደስተኛ ነን እንታገለዋለን ብለዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
መስከረም 30/2018 አ.ም

በሰሞኑ ዘመቻ አደም አሊ የተደናገጡት የብአዴን የሚዲያ ሰራዊት እና የአፋህድ ሳይበር ቡድን የሚዲያ ጥምረት ፈጥረዉ በጠንካራው የአፋብኃ/ምኒልክ ዕዝ ላይ 'ዘርፈ ብዙ የሀሰት ዘመቻ' እያደረጉ...
10/10/2025

በሰሞኑ ዘመቻ አደም አሊ የተደናገጡት የብአዴን የሚዲያ ሰራዊት እና የአፋህድ ሳይበር ቡድን የሚዲያ ጥምረት ፈጥረዉ በጠንካራው የአፋብኃ/ምኒልክ ዕዝ ላይ 'ዘርፈ ብዙ የሀሰት ዘመቻ' እያደረጉ ይገኛሉ።

የአማራ 'ትርፍ አንጀት የሆነው ብአዴን እና ጭንጋፉ አፋህድ' በእርግጥም በቅርቡ የመሬት ጥምረት ፈጥረው እንደሚመጡ አያጠራጥርም።

ምንም ቢሆን 'የነፋስ ላይ ገለባ' በመሆናቸው በመሬት በምናደርገው ሁለንተናዊ ተጋድሎ ተነዉ ይጠፋሉ።

ሆኖም ግን ከብአዴን ቀጥሎ አፋህድ የሚባል ቡድን 'የአማራ ህዝብ መርገምት' ሆኖ በታሪካችን ዉስጥ በጥቁር ነጥብ ተመዝግቦ ያልፋል።

በብአዴኖቹ እነ ተመስገን ጥሩነህ የመረጃና ደህንነት ተልዕኮና ስምሪት ተሰጥቷቸው በትግላችን የሰረጉት እነ መስፍን ከፋለዉ(በእዉነተኛ ስሙ፦ ተስፉ) እና ሌሎችም ሰርጎ ገቦች ከላኪዎቻቸዉ ጋር ላይመለሱ ይጠፋሉ።

ማሳሰቢያ፦ አፋህድ ስል ወሎ ላይ በእነ መስፍን ከፋለ የሚመራውን የአፋህድ ቅርንጫፍ ተቅበዝባዥ ቡድን ብቻ ማለቴ እንደሆነ ይታወቅልኝ።

አማራነት ይለምልም!

ፎቶ፦ ታላላቆቹ የዕዛችን አርበኞች የአምባሰሉ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ

የድል ዜና!!! የአ/ፋ/ብ/ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ገሞራዉ ብርጌድ ትንታጓ የደጀን ሻለቃ ወደ ጃዊ ፈንድቃ ከተማ በመግባት በጠላት ላይ ሰባዊ እና ቁሳዊ...
08/10/2025

የድል ዜና!!!
የአ/ፋ/ብ/ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ገሞራዉ ብርጌድ ትንታጓ የደጀን ሻለቃ ወደ ጃዊ ፈንድቃ ከተማ በመግባት በጠላት ላይ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዋል።

በቀን 27/01/2018 ዓ.ም አይበገሬዎቹ የደጀን ሻለቃ ባደረጉት ኦፕሬሽን በርካታ የጠላት ኃይል መደምሰስ ሲችሉ አንድ የጠላት ተሽከርካሪ ማርከዋል።
ስቦ መምታት በሚለዉ መርህ መሰረት የወገን ጦር ወደ ኋላ በማፈግፈግ ስልታዊ ኦፕሬሽን ተጠቅሟል። ጠላት ልክፍት እንደያዘዉ ዉሻ ተክለፍልፎ ወደ ትክሊ ቀጠና ለመግባት ሲሞክር በደጀን ሻለቃ እና ኤፍሬም ሻለቃ እንዲሁም በገሞራዉ ብርጌድ ልዩ ተወርዋሪ አባላት የደፈጣ ጠንካራ ምት አስተናግዶ አስከሬኑን እና ቁስለኛዉን እያዝረከረከ ወደ መሀል ጃዊ ከተማ ፈርጥጧል።

"አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ"
አ/ፋ/ብ/ኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

ፋኖ ያዕቆብ ጌታሁን
መስከረም 27/01/2018 ዓ.ም

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)ዛሬ የተመሰረተው ዋ ሲል ክፍለጦር እና የጎፍ ክፍለጦር እንዲሁም ደቡብ አማራ አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያቆብ ኮር አሃዶች በጥምረት ወረኢሉ ከተማን ተቆጣ...
08/10/2025

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)
ዛሬ የተመሰረተው ዋ ሲል ክፍለጦር እና የጎፍ ክፍለጦር እንዲሁም ደቡብ አማራ አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያቆብ ኮር አሃዶች በጥምረት ወረኢሉ ከተማን ተቆጣጠሩ::

የንጉስ ሚካኤል ኮር አሃድ የሆነውና ዛሬ መስከረም 27/2018 ዓ.ም የተመሰረተው ዋ ሲል ክፍለጦር እና የልጅ እያሱ ኮር አሃድ የሆነው የጎፍ ክፍለጦር እንዲሁም ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያቆብ ኮር አሃዶች በጥምረት ወረ ኢሉ ከተማን ተቆጣጥረዋል:: በተጨማሪም የጎፍ ክፍለጦር ካቤ እና ሰኞ ገበያ ከተማን ተቆጣጥረዋል::

ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
መስከረም 27/2018 አ.ም

የተመሰገን ጥሩነህ ንግግር ሰምቼ ታምሜ ነው ያደርሁት!አሁን ትንሽ መለስ ስላደረገልኝ አንዳንድ ነገር ልበል፣ በባንዳው ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ተላላኪ ነው ተብለህ የተሰ...
06/10/2025

የተመሰገን ጥሩነህ ንግግር ሰምቼ ታምሜ ነው ያደርሁት!

አሁን ትንሽ መለስ ስላደረገልኝ አንዳንድ ነገር ልበል፣ በባንዳው ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ተላላኪ ነው ተብለህ የተሰደብኽው አማራ እረ እንዴት ነህ? አማን ነው ወይ? ወንዙ፣ ሸንተራሮ፣ ተራራው ኮረብታው እንዴት ነው? ስድቡ ተስማማህ ወይ? እረ አይበቃም ወይ?

ለዚህ ምላሽህስ ምንድነው⁉️

ይሄን ጉዳይ በአግባቡ ካፒታላይዝ እናደርገዋለን፣ ፋኖ ከምን አይነት ሰዎች ጋር እየታገለ እንዳለና እነዚህ ሰዎች አማራን ወክለው የሚያስጨፈጨፉት እስከመቼ ነው?!

ታላቁ የአማራ ሕዝብስ በተላላኪዎች ተላላኪ ተብሎ ተሰድቦ ዝም ይላል ወይ?

ፋኖስ ይሄን ጉዳይ እንዴት ነው የሚመለከተው?

ሕዝብን እንደ ሕዝብ መስደብስ ይቻላል ወይ?

የአማራ ሕዝብ ከችግኝ ጣቢያ ጥበቃ ተነስቶ እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርነት በስሙ የወከለ ሰው የአማራ ሕዝብን መሳደብ ይቻላል ወይ?

ትናንት አለምነው መኮነን ዛሬ ደግሞ ተመስገን ጥሩነህ እየሰደበን እንዴትስ እንቀጥላለን?

የእውነት ያማል፣ ነደድሁ!

Amberbr

በምዕራብ ወሎ መካነሰላም ቀጠና የተጀመረው የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ እና ቴዎድሮስ ዕዝ የዉጊያ ጥምረት አገዛዙን በእጅጉ አስጨንቆታል።በዘመቻ 'አደም አሊ/አባ ናደዉ' ክፉኛ ተመትቶ የተደናገጠው ...
05/10/2025

በምዕራብ ወሎ መካነሰላም ቀጠና የተጀመረው የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ እና ቴዎድሮስ ዕዝ የዉጊያ ጥምረት አገዛዙን በእጅጉ አስጨንቆታል።

በዘመቻ 'አደም አሊ/አባ ናደዉ' ክፉኛ ተመትቶ የተደናገጠው ይህ አገዛዝ ሀይማኖታዊ አጀንዳ ከፈጠረ በኋላ ሁለቱ ዕዞችን በአጀንዳው ጉዳይ እርስበርስ የሚካሰሱ መስሎት እየዳከረ ነው።

መታወቅ ያለበት ነገር፦
1. የሁለቱ ወንድማማች ዕዞች የዉጊያ ትስስር (የጋራ ዉጊያ) እና ተቋማዊ ግንኙነት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን በቀጠናው ወሳኝ በመሆኑ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

2. ለአገዛዙ አስፈፃሚ ሆኖ የሚሰራም ይሁን የወገነ አካል ማንኛውም ኃይማኖት ላይ ቢደበቅ ተቀባይነት የለውም። ሲኖሩ የመንግስት ካድሬ ሲሞቱ ኃይማኖተኛ መሆን አይቻልም።

3. የአገዛዙ አገልጋይ ግለሰብ የትኛውንም እምነት ይከተል የአማራ ህዝብ ጠላት መሆኑ ታዉቆ እርምጃው ይወሰድበታል።

4. ሁለቱ ዕዞች የአንድ ድርጅት ቅርንጫፎች በመሆናቸው እና በቀጠናው በሚደረግ የጋራ ዉጊያ ላይ አንዱ ዕዝ በሚወስደው 'ማንኛውም እርምጃ ሁሉ' ሌላኛውም ሃላፊነት ይወስዳል።

5. ፋኖ አለማቀፍ የጦርነት ህጎችን ፈፅሞ የሚያከብር የህልውና ታጋይ በመሆኑ ለትኛውም ሀይማኖታዊ ተቋም እና አማኞች አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረገ መጥቷል። አሁንም ያደርጋል። በተለይም የኢትዮጵያ ሃብት ጭምር የሆኑትን የእስልምና እና የክርስትና እምነቶችን አብዝቶ ይጠብቃል።

አማራነት ይለምልም!

ጥብቅ መረጃ!   ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሰሞኑን በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት ላለመቀበል ፋኖ የተዋጋኝ ብቻውን አይደለም ከትግ...
02/10/2025

ጥብቅ መረጃ! ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሰሞኑን በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት ላለመቀበል ፋኖ የተዋጋኝ ብቻውን አይደለም ከትግራይና ከኤርትራ ሃይሎች ጋር ሆኖ ነው እና ሌሎችም ምክንያቶችን ሲደረድር ሰንብቷል::

ፋኖ ከፈጣሪው በታች ትጥቁም ስንቁም ሁሉ ነገሩ በውስጥም በውጭም ያለ የአማራ ህዝብ መሆኑ የአደባባይ ሐቅ ነው:: ፋኖ ከፈጣሪው በታች ራሱን ችሎ የቆመ ነው:: ተኩሱም አሸናፊነቱም ድል አድራጊነቱም የአባት የአያት የቅድመ አያቶቹ በአጠቃላይ ስሪቱ ነው::

ነገር ግን አብይ አህመድ ሽንፈቱን ላለመቀበል "ፋኖ ከትግራይና ከኤርትራ ሃይሎች ጋር ሆኖ ነው የወጋኝ" እያለ በሚዲያ ሚሊሻዎቹ በኩል ሲያለቅስ የሰነበተ መሆኑ ይታወቃል:: የማልቀስ መብቱም የተጠበቀ ነው::

ከዚህ ጋር ተያይዞም ፋኖ የወጋኝ ከትግራይና ከኤርትራ ሃይሎች ጋር ሆኖ ነው የሚለውን ለቅሶውንና ውንጀላውን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለማጀብ ምንም ፋኖ ባልተማረከበት ሁኔታ ሐራ መሬት እየተባለ ከሚጣራው ቦታ የጌታቸው ረዳ ቡድን አባል የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ታጣቂዎችን በማምጣት "ፋኖ ጋር ሆነን ስንዋጋ ወልድያ ዙሪያ በመከላከያ ተማረክን" እንዲሉ በማድረግ ዛሬ መስከረም 22/2018 ዓ.ም ደሴ ከተማ ፋና ቲቪ ቀረፃ እያካሄደ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል::

ስለሆነም ፋኖ በብልፅግናው ቡድን በሃሰት ፕሮፓጋንዳና ውንጀላ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች ቢደረደሩ የጀመረውን የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ለድል ከማብቃት የሚያደናቅፈውና የሚያግደው አንዳችም ሁኔታ እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መስከረም 22/2018 ዓ.ም

አርበኛ Abebe Fentaw
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሕ/ግ ኃላፊ

Address

London

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Satellite Media Network ASAMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amhara Satellite Media Network ASAMN:

Share

Category