Ethiopian

Ethiopian Ethiopian ፔጃችን like እና share አድርጉልን እናመሰግናለን!
ቅድስት ሀገሬ ኢትዮጵያ ለዘላለም ኑሪ!!!!!

የፖሊስ መለዮ ባያችሁ ቁጥር ስለኔ የምትሳቀቁ  ልጆቼ ...የመጨረሻውን ወሰንኩ!በዘመናችሁ ሁሉ ስቃይ ያሸከምኳችሁ የፖሊስ መለዮ ባያችሁ ቁጥር ስለኔ የምትሳቀቁ  ልጆቼ ...አሁንስ ተስፋው ማ...
31/03/2025

የፖሊስ መለዮ ባያችሁ ቁጥር ስለኔ የምትሳቀቁ ልጆቼ ...የመጨረሻውን ወሰንኩ!

በዘመናችሁ ሁሉ ስቃይ ያሸከምኳችሁ የፖሊስ መለዮ ባያችሁ ቁጥር ስለኔ የምትሳቀቁ ልጆቼ ...አሁንስ ተስፋው ማነው? እንደምትሉ አውቃለሁ።

ግዴለም ተስፋዬ እግዚያብሔር ነው። ከብዙ ወጥቻለሁ ነገም ከኔ ጋር ነው! አታስቡ። በተኛችሁበት ጥያችሁ በመሄዴ ብታዝኑም ክፉ አባት ግን አይደለሁም ታውቃላችሁ።

በናተ እድሜ በአንድ የታሪክ ምዕራፍ የተፈጠረ አረመኔ ዘረፈጂ ሃይል የራሱን ልጅን አቅፎ እየኖረ የናተን አባት ግን በሚችለው ሁሉ ተበቀለው በመጨረሻም እናተን ጥዬ እንድወጣ አደረገ። ይኽ አልፋና ኦሜጋ አይደለም በህይወታችሁ ተስፋ እንዳትቆርጡ በፍጹም በችግር ውስጥ መልካም ነገር አለና። በርቱ!

ለወዳጆቼ በሙሉ በጥሩም በመጥፎ ጊዜዎች ስለሰጣችሁን ተስፋ አመሰግናለሁ።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ የወጣትነት እድሜ ከ25 አመታት የልጅነት ትግል ጀምሮ ቀላል አመታትን አላለፍንም።
ትግላችን ይዞት ከመጣው ከብዙ ውጣውረድ በኋላ በውጤት ነፃነት ሳይሆን ሀገር ጥሎ መሰደድ ብቸኛ ምርጫ ሆኖ ተሰድጃለሁ።

በረጅም የትግል ታሪክ ግለ ህይወቴ ወደፊት በጽሁፍ በቃል ለማስፈር እገደዳለሁ የሰው ልጅ መቀበል የሚችለውን መራር ዋጋ በመቀበል ተምሬበታለሁ።

እርግጥ ነው ቦታዬ መሰደድ ባይሆን እመርጥ ነበር ምርጫዬ ይኽ እንዳልሆነ ቢገባኝም እያዘንኩ የወሰንኩት የታሪክ ኩነት ሆኗል። ይኽ አዲስ ነገር ሌላ ምዕራፍ ነው።

ባሳለፍነው በመራራ ትግላችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ሁሉ ከጎኔ የቆማችሁ ወገኖቼ እህት ወንድሞቼ በፈጣሪ ስም አመሰግናለሁ።
የነገ ታሪካችን አካል ናችሁ። ክብር ይስጥልኝ።

ዛሬም በፈተና ውስጥ ብሆንም ከየትኛውም ጊዜ በላይ ትብብራችሁን እሻለሁ። ይኽ የድካሜ ውጤት ፍሬ ማሳያ ነውና። የትግላችን እዳ ነውና።

ከትላንቱ ስርዓት በከፋ ሁኔታ ባለፉት ሰባት አመታት ያሳለፍነው ከባድ ነው ምናልባት በወደፊቱ ትውልድ መማሪያ ቁጭት የሚፈጥር የጥላቻ ጥግ በቀል ከኔ ውጭ ይኽን ያህል ነውረኛ ድርጊት የተፈጸመበት አላውቅም። አንድ ሰውን በዚህ ደረጃ ማሳደድ ምክንያቱም አይገባኝም።

ለአብነት

1ኛ ይኽ አገዛዝ ወደስልጣን ከመጣ ወዲህ በአምስት ክልል ከተሞች ከ30 በላይ የእስር ቀጠናዎች... ሪከርድ ሆኗል።

2ኛ በትንሹ 21 የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ከፍቶብኛል።

3ኛ ዐቃቢ ህግ በ4 መደበኛ ክስ ፍርድ ቤት ገትሮኛል።

4ኛ ኮሽ ባለቁጥር የ3 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀጥተኛ የእስር ትህዛዝ ተፈጻሚ ተደርጓል።

5ኛ ከ350 ሺህ በላይ የዋስት ገንዘብ ተከፍሏል።

6ኛ በተለምዶ የቅጣት ቦታ የሚባል 3 የጨለማ ክፍሎች ለወራት አቆይቶኛል።

በአጠቃላይ በሰባት አመት የስልጣን ዘመን ውስጥ አራት አመት(4) ለነጋሪ በማይመች ዋጋ አስከፈሎናል።
የሰኔ 16 እርግማን የመጨረሻ ውጤት ህወሓትን የሚናፍቅ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ሙሉ ቤተሰብ በትኜ ከሀገር እንድወጣ ምክንያት ሆኗል። እንደመሸ አይቀርም ነገን ተስፋ አደርጋለሁ።
ፈጣሪ የሚወደውን ይፈትናል ለወዳጆቼ በድጋሚ አመሰግናለሁ። ልጆቼን አደራ! ስንታዬሁ ቸኮል

 #የኦህዴድ እና የኦነግ የእገታ ዶሴ በስሱ ሲገለጥአሳዬ ደርቤ❗️➖➖➖share የሚደረግ1.👉ህዳር 25/2012 ዓ. ም 17 የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በኦነግ...
25/03/2025

#የኦህዴድ እና የኦነግ የእገታ ዶሴ በስሱ ሲገለጥ
አሳዬ ደርቤ❗️
➖➖➖
share የሚደረግ

1.👉ህዳር 25/2012 ዓ. ም 17 የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ታግተው ይኑሩ ይሙቱ ሳይለይ ተረሱ። ቤተሰቦቻቸው በተደጋጋሚ" የመንግስት ያለህ የልጆቻችንን ነገር አንድ በሉን"ቢሉም ሰሚ ሳያገኙ ቀሩ።

2.👉ህዳር 29/2015 በእለተ ሀሙስ ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ አዲስ አበባ በኦዳ ባስ በሚጓዙበት ወቅት በምእራብ ወለጋዋ የጊምቢ ወረዳ ጉሊሶ ቀበሌ ውስጥ 9 የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ታገቱ።
ታጋች ተማሪዎችም
1ኛ. ተማሪ ደጀኔ ያለው - IT department 3ኛ ዓመት ተማሪ
2ኛ. ተማሪ ኪሩቤል መለሰ- Civil department 5ኛ ዓመት ተማሪ
3ኛ. ተማሪ ብርሃኑ አበባው - Civil department 5ኛ ዓመት ተማሪ
4ኛ. ተማሪ ማህሌት ዘላለም - Business management department 3ኛ ዓመት ተማሪ
5ኛ. ተማሪ ሲሳይ ጋሻዬ -psychology department 3ኛ ዓመት ተማሪ
6ኛ. ተማሪ ሰዓዳ ሞሀመድ- Mechanical department 5ኛ ዓመት ተማሪ
7ኛ. ተማሪ ቤዛዊት ተሾመ- Architecture department 5ኛ ዓመት ተማሪ
8ኛ. ተማሪ ብዙአየሁ አረጋ Law department 5ኛ ዓመት ተማሪ መሆናቸው ታውቋል።በተጨማሪም በሥም ያልተጠቀሱ ሌሎች የታገቱ ተማሪዎች እንዳሉ በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘገበ።

3👉 ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በአውቶብሶች ሲጓዙ የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰኔ 25/2016 ዓም በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች መታገታቸውን ቢቢሲ ዘገበ።

4.👉በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ልዩ ስሙ "አሊዶሮ መውጫ' በተባለ ሥፍራ ታጣቂዎች መጋቢት 8/2017 እኩለ ቀን ላይ የአንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ውስጥ የነበሩ 60 ተሳፋሪዎችን በሙሉ አፍነው ወሰዱ። ከዚያ በአንድ ሰው 1.5 ሚሊዮን ብር ጠየቁ። ምንጭ ቢቢሲ

5.👉 ከቀናት በፊት በተመሳሳይ መልኩ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሊዶሮ አካባቢ በቀን 14/7/2017 አንድ ታታ አውቶብስ ሙሉ 60 ሰው ታገተ። ምንጭ ዋዜማ

6.👉በኦሮሚያ ከልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ከጎርፎ ከተማ ወጣ ብሎ ባለ ሥፍራ፣ ታጣቂዎች ከሶስት ቀን በፊት 10 ሰዓት ገደማ በሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ በፈጸሙት እገታ 40 ያህል ተሳፋሪዎችን አፍነው መውሰዳቸውን ዋዜማ ሬዲዮ ዘገበ።

7.👉በደራ ወረዳ (27/12/015) ኦነግ በሚባለው ታጣቂ ከቆሮ ፣ ከግንደበርበሬ፣ ከራቾና ከሮብገበያ ቀበሌዎች ወደ ወረዳው ዋና ከተማ ጉዶመስቀል ለገበያ ይጓዙ የነበሩ ከ300 በላይ ንፁሃን ገበያተኞች እገታ ተፈጸመባቸው ። በአካባቢው ለኦነግ ድጋፍ እንዲያደርግ የተላከው መከላከያ ተብዬውም ለድርጊቱ ሽፋን በመስጠት ተባባሪ እንደነበር የመረጃ ምንጮች ሲናገሩ ነበር።

8. 👉በ26/12/15) ከሰላይሽ ከተማ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የከተማዋ ነዋሪዎችን ማገቱም በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ ነበር።

9.👉"…ማክሰኞ መስከረም 22/2016 ዓም በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተዋቀረው ሸገር ከተማ ሱሉልታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አዲሱ ኬላ ወይም ቆዳ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ታጣቂዎች 9 ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውንና ለታጋቾቹም ማስለቀቂያ ለእያንዳንዳቸው ታጋቾች በነፍስ ወከፍ 300 ሺህ ብር መጠየቃቸውን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘገበ።
"…እነዚሁ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም በዚሁ በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ በመግባት፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን ወስደው መሰወራቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

10.👉. በ08/11/2015 ከቀኑ 6 ሰአት አካባቢ የሼር ኢትዮጵያ መኪና ሾፌር የሆነው መስፍን በኦሮሚያ ክልል በተለምዶ ዱኒ የሚባል አካባቢ በሶደሬ መስመር ወይን ለመጫን ሄዶ በዚያው ታግቶ ቀረ። የሹፌሮች ድምጽ

11.👉 በ12/03/2015 ከቀኑ 10 ሰአት ከወለንጭቲ መተሃራ መንገድ 55 ላይ 1 የህዝብ ሚኒባስ 1ሃይሉኩስ 3 ተሳቢ ታግተው ሹፌሮች፣ ተሳፋሪዎችና ረዳቶች ተወሰዱ። ምንጭ አልአይን

12.👉 በኦሮሚያ ክልል በወሊሶ ዞን አራት ታዳጊዎች በኦነግ ሽኔ ታግተው አራቱንም ለማስለቀቅ ብር ይጠየቅባቸዋል። ከዚያም የተጠየቀውን ብር ይዘው ወደ ስፍራው ያመሩ ቤተሰቦችም መታገታቸው ሲነገር ነበር።

13.👉በኦሮሚያ ክልል በአሩሲ ዞን ፖሊስ ጣቢያ ፊትለፊት 9 ዐማሮች ይገደላሉ። ከዚያም ዘመድ አዝማድ ከሩቅም ከቅርብም ተጠራርቶ እየተላቀሰ መጥቶ ቀብር ዋለ። ከቀብር መልስም መንገድ ላይ ቀባሪዎቹ እንደገና ታግተው ይወሰዳሉ። እናም በወቅቱ አጋቾቹ አንዱን ታጋች ገድለው በ3ቱ ሲደራደሩ እንደነበር በኢሰመጎ ጭምር ሲዘገብ ነበር።

14.👉 "…በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን ኩዩ ወረዳ በምትገኘው ምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 19/2015 ዓም ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በማኅሌተ ጽጌ ላይ ሳሉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አንድ ዲያቆን ገድለው ካገቷቸው 11 የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች መካከል ለሦስቱ በድርድር ገንዘብ ተከፍሎ ሲለቀቁ 8 ካህናት ግን ታግተው ቀርተው ነበር። የሚገርመው ነገር ታዲያ አደራዳሪው የኦሮሚያ ፖሊስ ሲሆን ብሩ የሚገባው ደግሞ በኦሮሚያ ባንክ ነው አሉ።

15. 👉በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ዞን አዴ ደንጎሩ ወረዳ ቱሉ ገና ወይም አንገርጉትን ላይ ጥር 11 /2012 ዓ'ም የጥምቀት በዓል ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ለምን ይዛችሁ ወጥታችሁ ተብለው 30 የሚደርሱ የአማራ ብሄር ተወላጆች ታፍነው ተወስደው የት እንደደረሱ ሳይታወቅ መቅረቱን በአማራ ድምጽ ሲዘገብ ነበር።

16.👉በቀን 26/03/2015 ዓ.ም በሆሳዕና ከተማ ማንነታቸውን ባልተወቁ ሰዎች በግምት 9:00 ሰዓት አከባቢ 9 ተማሪ 1ዱ ከዋቸሞ አጠቃላይ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት ስሆን ቀሪዎቹ ከWorld bright ትምህርት ቤት/ በመኪና አፍኖ ወደ ያልታወቀ ቦታ መወሰዳቸው ተገለፀ!

17.👉እሮብ ማታ እንጪኒ እና ዳንጎቴ መንገድ ሌሊት ላይ ከሰል ድንጋይ ጭነዉ ሲመጡ 8 ሹፌሮች መታገታቸው በሹፌሮች ድምጽ ተዘገበ።

18.👉 በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረሊባኖስ አከባቢ ወደ ያያ ጉሌሌ ለገበያ ሲጓዙ የነበሩ አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ 50 ሰዎች ግድም የሚሆኑ ነጋዴዎች ሳዲኒ ብዮ ከሚባል የያያ ጉለሌ ወረዳ ታፍነው ተወሰዱ። ሕዝቡም ሰልፍ ወጥቶ ተቃወመ።

19.👉በምሥራቅ አርሲ ዞን በሮቤ ዲደዓ ወረዳ ጄና ገደምሳ ገበሬ ማኅበር ቀበሌ ውስ ጥ በልዩ ስሙ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን አከባቢ ከቀኑ 11:00 ላይ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የግድያና የእገታ ጥቃት ተፈጽሟል። በጥቃቱም አቶ ጣፋ በቀላ የሚባሉ ኦርቶዶክሳዊ ሲገደሉ፣ዲ/ን ገዛኸኝ ለማ ፣ከተማ ካሳ፣ጋሻሁንና ደሲ የተባሉት ደግሞ ታግተው መወሰዳቸውን የማሕበረ ቅዱሳን ሚዲያ ዘገበ።

20.👉 አምና በ2016 ዓመተ ምሕረት በአዲስ አበባ የሚሰሩና በኦሮሚያ የሚኖሩ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች በሰማያዊው የፐብሊክ ሰርቪስ ተጭነው ወደ ቤታቸው እየሄዱ ሳለ ታጣቂዎች ሹፌሩን ገድለው በውስጥ ያገኟቸውን አማርኛ ተናጋሪ ሲቪል ሰርቫንቶች አግተው ወሰዱ።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል።
#ምንጭ እየጠቀሱ post ወይንም share ያድርጉት።

አገዛዙ የጠላፊ ጠበቃ አይደለም። ራሱ አገዛዙ ጠላፊ ነው። አገዛዙ የደፋሪ ጠበቃ አይደለም። ራሱ አገዛዙ ደፋሪ ነው። ለአመታት ታፍነው የተወሰዱት ተማሪዎች ጉዳይን ሲያድበሰብስ ኖሮ አሁን ይፋ...
25/03/2025

አገዛዙ የጠላፊ ጠበቃ አይደለም። ራሱ አገዛዙ ጠላፊ ነው። አገዛዙ የደፋሪ ጠበቃ አይደለም። ራሱ አገዛዙ ደፋሪ ነው። ለአመታት ታፍነው የተወሰዱት ተማሪዎች ጉዳይን ሲያድበሰብስ ኖሮ አሁን ይፋ ሲወጣ ቪዲዮ በማስወረድ ወንጀልን ለመደበቅ ጥረት እያደረገ ነው። ድንገት እውነቱ ስለወጣባቸው ደንግጠው ነው።

ይህ እውነት አማራ ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ቁልጭ አድርጎ ከማሳየት ውጭ ሌላ በህዝብ መካከልም ሆነ የሚያመጣው ችግር የለም። ችግሩ ለጠላፊዎቹ ነው። ችግሩ ለደፋሪዎቹ ነው። ችግር የሚሆነው ቤተ መንግስት ሆነውም ጫካ ያሉትን ቀጥረው ለሚያሰሩት አረመኔዎች ነው። ችግሩ በሀሰት ትርክት አማራን ሲነክሱ መዋልን ፖሊሲ ላደረጉት እርጉሞች ነው። ችግሩ አማራን ማጥቃት አላማ ላደረጉ ባለጊዜዎች ነው። ችግሩ ጫካ ላይ ገዳይና ደፋሪን የፕሮጀክት ተቋራጭ አድርገው አማራን የማሰቃየት አስፈፃማዎች፣ የመቶ አመት የሀሰት ትርክት አመንዣኪዎች ነው።

የአማራ ሰቆቃ ፍንትው ያለ እውነት ሆኖ ሊደብቁት አልቻሉም። ጫካ ወስደው ከእነ እውነታቸው ቀበርናቸው ሲሉ እውነት ፈጥጦ ሲወጣ በአደባባይ ለሚሊዮኖች የደረሰውን ወደማስጠፋት ሄዱ። ምክንያቱ ጫካ ላለ ታጣቂ አዝነው አይደለም። የህዝብ ግጭት ስለሚያስነሳ አይደለም። አስበው የሰሩት ወንጀል ስለሆነ ነው። አሁንም በየቀኑ ከአውራ ጎዳና ላይ ሙሉ ተሳፋሪ ጠልፈው የሚሰሩት ይህንኑ ነው። የሀሰት ትርክት ጎርሰው ቤተ መንግስት የገቡት የአገዛዙ አካላት በየቀኑ የሚደሰቱበት የእያንዳንዱ አማራ ስቃይ ነው።

ለመደበቅ እየጣሩ ያሉት የአንድ ወቅት ክስተትን አይደለም። እየሰሩት ያለ፣ በቀጣይ በተለያየ መንገድ የሚሰሩትን ነው። ለመደበቅ እየጣሩ ያሉት የታገቱ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን በደል አይደለም። አጠቃላይ በህዝብ ላይ ያቀዱትና፣ የሰሩት፣ እየሰሩት ያለ ነው። እየደበቁት ያለው የኦነግ ወዘተ ጉዳይ አይደለም። ተስማምተው የሚሰሩት ፀረ አማራ የጋራ ዘመቻን ነው። ለመደበቅ እየሞከሩ ያሉት በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ፀረ አማራ ፍኖተ ካርታቸውን ነው።

ግን እውነት ነው! ለመደበቅ ቢጥሩት ድንገት አደባባይ ይወጣል! ያውም በራሳቸው ዩኒቨርሲቲ፣ የህክምና ተቋማት፣ በህዝብ በስፋት በሚያየው ሚዲያ! Getachew shifersw

🤔
07/03/2025

🤔

እቴ ወይ ልዋል(2)ከደረትሽ መሀል  ናፈቀችኝ ጎንደር(2) የእነ አሞራው ሀገር   በቅዳሴው ቦታ ቀለሀ ሲዘምር እንዴት ሰንብተሻል እናትዋ ጎንደር እናትዋ ብልሽ ትንፋሽዋ ብልሽአካልዋ ብልሽመቼ...
15/01/2025

እቴ ወይ ልዋል(2)
ከደረትሽ መሀል
ናፈቀችኝ ጎንደር(2)
የእነ አሞራው ሀገር

በቅዳሴው ቦታ ቀለሀ ሲዘምር
እንዴት ሰንብተሻል እናትዋ ጎንደር
እናትዋ ብልሽ
ትንፋሽዋ ብልሽ
አካልዋ ብልሽ
መቼ ደረስኩልሽ

ሹርባ ሆኗል ጎፈሬው
እንደ መይሳው ሊያደርገው
ያ ጎንደሬው
ምነው ገብርየን ቢያረገኝ
አሞራው ውብነህ ቢያረገኝ
ከፊት እንድገኝ

አሞራው ከአሞራ(4)

ያየም ሰው ይናገር የነበረም ያውጋ
ተጋጥሟል ይባላል አሞራው ከአሞራ
ጎንደር ጀግና ትውለድ ታሳድግ ፀንሳ
እንደአሞራው ውብነህ ስሙ ማይረሳ
ሀገርና እምነቱን ከእራሱ አስበልጦ
ለጠላት ያለቅሳል ውዳሴውን ገልጦ

ጎንደር ጎንደር ደስ ይበልሽ
ደም መላሽ አርበኛው አሞራው መጣልሽ
የሰው ነው የሰው የሰው አመሉ
ማን መጣ ቢሏችሁ ጎንደሬው ነው በሉ

አሞራው ከአሞራ
ኢትዬጵያን ሊያገባት አብጠሊሷን ቀዶ

ልጇ ደረሰላት ሞት ወዶና ፈቅዶ
ወይ አንች እናታለም ወይ አንች መበለት
እንድሜ ብርክ ሲይዘው ልጅ ይሆናል ጎልበት
ወልቃይት ጠገዴ አጅሬ ጃኖራ
ምን አይነት ፍርድ ነው አሞራው ከአሞራ
አሞራው ከአሞራ(3)

ሲሆን መጡ መጡ እንባል ነበረ
እንሂድባቸው ማሸነፍ ካልቀረ
ደሞ ተዚ ተዚህ ተወዲያ ተወዲህ
ጎንደር ከአንች በፊት ያድርገኝ ተንግዲህ
እናትዋ ጎንደር እጅ የዘረጋችው
ዘነበች መሸሻን ወልዳ የሳመችው
ምድር ቀዝቀዝ ሲል ተላይ እያሞቀው
ይኸው ቀብረር ብሎ አሞራው ጠበቀው
አሞራው ጠበቀው

ሀገር እንደዋዛ ናፍቆት እንደዋዛ
የእነ አሞራው ሀገር የመይሳው ካሳ
አዘዞ ድማዛ

የጃንተከል ዋርካው ወደ መሬት ዘሟል
እንኳን ያደገብሽ ያየሽ በአይኑ ታሟል
እናትዋ ጎንደር

ተይ ደሜ(3)
በላ ልበልሀ እንካንጅ ተቀበል
አሞራው ተነሳ ከእንግዲህ ዝም አትበል
የአለም ፀሀይ እታባ ፊትሽ አይቀየር
የተጠማው በልቶ ለብሶ ጠግቦ ቢያድር
ከተኮሰ ማይስት ጀግና ክንደ ብርቱ
ያ የአርበኛው ምንጣፍ ያ ምጅምር ገጡ
የጦሩ መሳፍንት ፈሪሀ እግዜር ያለው
ከጦር መሀል ሲሄድ ይመስላል ክንፍ ያለው
አሞራው ከአሞራ(8)
አሞራ ምት ለምዶ አካሌ ተቆጣ
ልሂድ ወንድነቴን አሳድሸው ልምጣ
ከዳሽን ላይ ፈልቆ ቀድታ የጠጣችው
የነካትን ሁሉ አቃጥላ ፈጀችው
ከሱዳን ገዳሪፍ ተስቦ እንደ ሰርዶ
ኢትዬጵያን ሰቀላት ያን ሰንደቅ አውርዶ
የአበቅየለሽ ልጆች ዳር እስከዳር ኩሩ
ጎንደር ጀግና አታጣም አትጠራጠሩ(3)
አሞራው ከአሞራ (2)

Address

Newport

Telephone

07447298788

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian:

Share