
30/08/2025
#ተወልዶ ያደገው ፈረንሳይ ለጋሲዮን ነው። ዲያቆን ነው። ዶክተር ነው፤ የዓይን ሐኪም። ጎንደር ዩኒቨርስቲ እያከመ ያስተምር ነበር፦ ለሁለት ዓመት። ...ከዚያ ወደ አዲስ አበባ መጣ፤ በአውሮፕላን አብራሪነት ተመረቀ። አሁን ረዳት ፓይለት ነው።
#ይህ ወጣት ናትናኤል ስንታየሁ ይባላል። ዲያቆን፣ ዶክተር፣ ፓይለት ናትናኤል ስለ ልጅነቱ እንዲህ ይናገራል ።
"ከትንሽነቴ ጀምሮ ሶስቱንም መሆን እመኝ ነበር፤ ዲያቆን፣ ዶክተር እና ፓይለት። ከትምህርት ጊዜዬ ውጪ ውሎዬ እዛው ስለሆነ፣ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ገነተ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዲያቆን ሆንኩ። እናቴ ጤና ጣቢያ ነው የምትሰራው፤ እዚያ ሥራ ቦታዋ ይዛኝ ትሄድ ነበር። ሐኪሞቹን እያየሁ እነሱን መሆን ተመኘሁ። አባቴ ደግሞ ሁሌም የአየር መንገድን ሠላምታ መፅሔት ይዞ ይመጣል። እሱን እያየሁ፤ እያነበብኩ፣ ፓይለት መሆን ተመኘሁ። ፓይለት ሆንኩ፦ አሁን ረዳት አብራሪ ነኝ።...."
ለዲያቆን ዶክተር ፓይለት ናትናኤል መልካም እድል ተመኙለት