Gonder tube / ጎንደር

Gonder tube / ጎንደር ይህ ፔጅ ለህዝብ ድምፅ የምንሆንበት ፈጣን ወቅታዊ መረጃዎች የምናደርስበት የህዝብ ልሳን ነው �

"የአፄ ቴዎድሮስን ታሪክ ወደ ፊልም እስክሪፕት ቀየርኩና ፕሮዲዩስ እንዲደረግ ወደ ሆሊውድ ሄድኩ። አንድ ፕሮዲዩሰር ታሪኩን አንብቦ ወደደውና 'ለምን ዋና ታሪኩን ቴዎድሮስን ሊረዳ በመጣው ፈረ...
29/07/2025

"የአፄ ቴዎድሮስን ታሪክ ወደ ፊልም እስክሪፕት ቀየርኩና ፕሮዲዩስ እንዲደረግ ወደ ሆሊውድ ሄድኩ። አንድ ፕሮዲዩሰር ታሪኩን አንብቦ ወደደውና 'ለምን ዋና ታሪኩን ቴዎድሮስን ሊረዳ በመጣው ፈረንጅ ዙርያ እንዲያጠነጥን አናደርገውም?' አለኝ። እኔም እስክሪፕቱን ተቀብዬው ወጣሁ። ከዚያ በኋላ የሆሊውድን ደጅ ረግጬ አላውቅም"

©ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ

እውነተኛው የአማራ ልጅ አርበኛ በለጠ ሸጋው፤ ስመጥሩው ጀግና በፋኖ ትግል ሂደት ውስጥ አብሪ ኮኮብ ሆኖ ብቅ ማለት የቻለ ልባም ነው። ከ20 ሺህ ብር በላይ በወር ደምወዝ ይቀበልበት የነበረው...
14/07/2025

እውነተኛው የአማራ ልጅ አርበኛ በለጠ ሸጋው፤ ስመጥሩው ጀግና በፋኖ ትግል ሂደት ውስጥ አብሪ ኮኮብ ሆኖ ብቅ ማለት የቻለ ልባም ነው። ከ20 ሺህ ብር በላይ በወር ደምወዝ ይቀበልበት የነበረውን ስራ በመተው ለነፃነት የፈነነው ይህ ጀግና ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ጋር አንድ መስሪያ ቤት ነበር የሚሰራው። በምስራቅ አማራ ፋኖ ውስጥም አንድ ሻምበል ውስጥ ሆነው ታግለዋል። ቀኝ አዝማች ይታገሱ በተሰዋ በሳምንት ውስጥ የ48ተኛ ክፍለ ጦር አንድ ሬጅመንትን በመፈጣጠም ደሙን በብርሀን ፍጥነት የመለሰለት ይህ ጀግና እጅግ በጣም ሀቀኛ እና ጎጠኝነትን የሚጠየፍ መሪ ነው።

ሙስሊም ክርስቲያኑ እጅጉን የሚወደው ታማኝ አርበኛ ሲሆን በወሎ ምድር ከቆላ እስከ ደጋ ዝናን ያተረፈ ወንድማችን ነው። ድሮን ሲሉ ይጠሩታል። ፈጣን ተዋጊ እና አዋጊ ነው።

መሬት ላይ እንደ ዋርካው ልጅ አዋቂው የሚወደው፤ በሚዲያ ያልተነገረለት ነገር ግን አድምቶ ስራ የሰራ ጀግና ነው።

በጎንደር ከተማ ሀምሌ 5 በድምቀት እየተከበረ ነው !!!ለጎንደር ከተማ ህዝብና ለአማራ ህዝብ ሀምሌ 5 በአሉ ድርብ ነው !የኢትዮጵያ ጀግና ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ
11/07/2025

በጎንደር ከተማ ሀምሌ 5 በድምቀት እየተከበረ ነው !!!

ለጎንደር ከተማ ህዝብና ለአማራ ህዝብ ሀምሌ 5 በአሉ ድርብ ነው !

የኢትዮጵያ ጀግና ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ

የተወለደችው በጎንደር፣ ደራ ፎገራ አውራጃ፣ ልዩ ስሟ ሀሙሲት በምትባል አነስተኛ መንደር ነው። በቤተሰቦቿ የሥራ ዝውውር ምክንያት ለአጭር ጊዜ አሰላ ከዛም አዲስ አበባ ኖራለች። በትምህርቷ በ...
30/06/2025

የተወለደችው በጎንደር፣ ደራ ፎገራ አውራጃ፣ ልዩ ስሟ ሀሙሲት በምትባል አነስተኛ መንደር ነው። በቤተሰቦቿ የሥራ ዝውውር ምክንያት ለአጭር ጊዜ አሰላ ከዛም አዲስ አበባ ኖራለች። በትምህርቷ በጣም ጎበዝ (ቀለም) ከሚባሉት ተማሪዎች ተርታ የምትመደብ ተማሪ ነበረች።

ለሙዚቃ በነበራት ከፍተኛ ፍቅርና ፍላጎት ድምፃዊ ለመሆን ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ በመሄድ ያደረገችው የመጀመሪያ ሙከራ "ድምፃዊ መሆን አትችይም" በሚል መራር ውሳኔ ተደመደመ።

እንደማስተዛዘኛ ግን በተወዛዋዠነት እድሏን እንድትሞክር ተፈቅዶላት ፖሊስ ኦርኬስትራን ለ7ወር በተወዛዋዥነት በነፃ በማገልገል ኪነጥበብን ተቀላቀለች።

ከ7 ወር ግልጋሎት በኋላም በነፃ ዝውውር ወደ አንጋፋው የሀገር ፍቅር ቲያትርቤት በመዘዋወር ከ1965 እስከ 1967 ዓ.ም በተወዛዋዠነት አገለገለች።

በዚህ እልህ አስጨራሽና ተስፋ አስቆራጭ ሂደት ሙያዋን የጀመረችው አይበገሬዋ ድምፃዊት የመጀመሪያ የሙዚቃ ሸክላዋን በተመለከተ አሳታሚው የታንጎ ሙዚቃ ቤት ባለቤት ባንድ ወቅት እንዲህ በሚል ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

"አስቴርን በሸክላ ለማስቀረፅ ስመርጣት ድምጿ አይሰማም ከሚል ስጋት "ይቅርብህ" ያሉኝ ሰዎች ብዙ ነበሩ። እኔ ግን ቁጥር 1 ስራዋን በድፍረት አሳትሜ አወጣሁት። ያው እንደተፈራውም ተቀባይነቱ ቀዝቃዛ ነበረ። ሰዎችን ስጠይቃቸው "ድምጿ ጥሩ ነው ምን እንደምትል ግን አይሰማም "ይሉኝ ነበር።

እናም አስቴርም በወቅቱ "በቃ እኔ ሙዚቃ አይሆንልኝም" ብላ ተስፋ ቆረጠች። እኔ ግን እሷ ትልቅ ቦታ የምትደርስ ድምፃዊ እንደምትሆን እርግጠኛ ስለሆንኩኝ እልህ ውስጥ ገብቼ አስቴርንም አበረታትቼ ፣ የድርሰት ማጥኛ ቤት አዘጋጅቼ ፤ ውብሸት ፍሰሀን ጨምሬ ረጅም ጊዜ በፈጀ ጥናት በባህል መሳሪያዎች የታጀበ ስራቸውን አሳትሜ አወጣው።

ተቀባይነቱ ዳር ከዳር ከመሆኑም በላይ ያኔ ያልተደመጠው የመጀመሪያ ስራዋ ሁሉ እንደገና እንደ አዲስ ይፈለግና ይሰማ ጀመር። ሀገሩ ሁሉ አስቴር ይል ጀመር።" በማለት ያስታውሰዋል ኘሮዲውሰር አሊ አብደላ፤ የታንጎ ሙዚቃ ቤት ባለቤት።

በዚህ መልኩ የአይበገሬነት ጉዞዋን የጀመረችው አስቴር አወቀ ግማሽ ክፍለን ዘመን በሚጠጋው የሙዚቃ ዘመኗ ...

አንድ የሸክላ ሙዚቃና 25 የሙዚቃ ካሴቶችን በግሏ፣ አንድ የሙዚቃ ካሴት ከድምፃዊ ውብሸት ፍስሀ ጋር በጋራ፣ ከድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ጋር" መች እንዲህ "የተሰኘ አንድ ዜማ በቅብብል፣ "እንኖራለን ገና" በሚል በኤች አይ ቪ ዙሪያ የተሰራ የጋራ አልበም፣ ለሚሊንየም የተጫወተችው ነጠላ ዜማ፣ የኛ ከተባሉ የሙዚቃ ቡድኖች ጋር በጋራ አንድ ዜማ ተጫውታለች።

አስቴር በስራዋ የሀገሯን ሰዎች ብቻ ሳይሆን የውጭ ሀገር ሰዎችን ጆሮዎችም የሳበች ሲሆን ከሲቢኤስ (CBS) ኮርፖሬሽን ጋር የሰባት አመት ኮንትራት እንደነበራት ተገልፇል። በተመሳሳይም ከሌላ ከእንግሊዝ ሀገር ካምፓኒ ጋር ሌላ ኮንትራት ተዋውላ ስራዎቿን አበርክታለች።

በታዋቂው ታይም (TIME) መፅሄት ላይ አዲስ አይነት የሙዚቃ ስልት ዘርፍ ትልቅ አድናቆት እና ክብር ተሰጥቷታል። ከዚህም ባሻገር "ካቡ" የተሰኘው አልበሟ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1990 በ "CMJ New Music Charts" ላይ ለአራት ሳምንታት ከፍተኛ ቦታ (Top Position) ላይ እንዲሁም በ "Billboard's World Music Charts" ላይ ለአስር ሳምንታት (Top Ten of Billboard's World Music Charts) ላይ ቆይቷል።

አስቴር ወደ ኢትዮጵያ መጥታ ትልልቅ የሙዚቃ ዝግጅቶችን በጃንሜዳ፣ አዲስ አበባ ስታድየም፣ ሸራተን አዲስ እና ሚሊኒየም አዳራሽ አድርጋለች። ከዚህ ባሻገር በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን የረሃብ አደጋ ሰለባዎች ለመርዳት በተደረገው ጥረት ወደ ሃገሯ በመምጣት በሙያዋ አስተዋፅኦ አበርክታለች።

የራስሽን ዘፈን ስትሰሚ ምን ይሠማሻል ተብላ ተጠይቃ "ተለዋዋጭ ነው፣ በወጣትነት ጊዜዬ በጣም አፍር ነበር፤ የኔን ዘፈን ካዘፈንሽ ያንቺ መኪና ውስጥ አልገባም ነበር፣ የኔን ዘፈን ካዘፈንሽ እቤትሽ አልመጣም ነበር። ምክንያቱን ሁሌም በሰማሁ ቁጥር ይህን እንዲህ ማድረግ ነበረብኝ የምላቸው ስሜቶች ይሰሙኝ ነበር።" ብላለች።

አስቴር ራሷን "አስቴር አወቀ በጣም ደግ፣ ስስ ቆዳ ያላት እና ትልቅ ለመሆን የምትፈልግ ሴት ናት። መፈቀርም ማፍቀርም የምትፈልግ ናት። ሌላ ትርጉም ሊሰጣት አይገባም ከተፈቀረች ይበቃታል። ሌላ ነገር አትፈልግም" ብላ ትገልፃታለች።

አስቴር አወቀ አንድ ሴት ልጅ ያላት ሲሆን የግል ህይወቷን ከሰው ሸሸግ አድርጋ የምትኖር እና ከአደባባይ ይልቅ የግል ሰው እንደሆነች፣ ትልቅ የመድረክ ፍርሃት እንዳለባትም ትናገራለች።

ባለድንቅ ተሰጥኦዋ እና እንደ ህፃን ልጅ የቅን ልብ ባለቤቷ አስቴር አወቀ

* የዜማ ደራሲ
* የግጥም ደራሲ
* በቅንብር የምትሳተፍ
* የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች

በተጨማሪም ኑሮዋን በአሜሪካን ሀገር ካደረገች ጀምሮ ደግሞ የተዋጣላት ዲዛይነር በመሆን ለረጅም አመት የሀገሯን ባህል አስተዋውቃለች። መድረክ ላይ የምታደርጋቸው ውብ የባህል ልብሶች በራሷ ዲዛይን የተደረጉ ናቸው።

በታላቁ ዋልድባ ገዳም ሱባኤ ተጀምሯል ።የታላቁ ገዳም ዋልድባ መነኮሳት የ6 ወር ሱባዔ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፣፡፡፡፡፡፡፡የዋልድባ ገዳም አባቶች በየአመቱ ከሰኔ 21 እስከ ህዳር የሚያደ...
29/06/2025

በታላቁ ዋልድባ ገዳም ሱባኤ ተጀምሯል ።
የታላቁ ገዳም ዋልድባ መነኮሳት የ6 ወር ሱባዔ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፣፡፡፡፡፡፡፡
የዋልድባ ገዳም አባቶች በየአመቱ ከሰኔ 21 እስከ ህዳር የሚያደርጉትን ጸሎት እና ሱባዔ ተጀምሯል።
አባቶቻችን ለ6 ወርሃት በህብረትና በግል ለሀገር ሰላም ለህዝብ ፍቅር ስጥልን እያሉ እየፀለዩ ከውጭው ማህበረሰብ ጋር ሳይገናኙ በበዓታቸው ተወስነው የሚፀልዩበት ወቅት ነው።
"እመቤታችን "
በኪደተ እግሯ ከባረከቻቸው ቦታዎች አንዱ መሆኑ :የዋልድባ ገዳም እመቤታችን ወደኢትዮጵያ በስደቷ ጊዜ መጥታ የአረፈችበት ቦታ እና ፣ጌታችን በሕፃንነቱ ትንቢት ከተናገረላቸው ቦታዎች አንዱ ነው።በኢትዮጵያዊው ጻድቅ በአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ተጋድሎ እህል አይብቀልብሽ፣ኃጢአት አይሻገርብሽ የሚል ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።የተመሰረተውም በ485 ዓ.ም

እግዚአብሔር። አምላክ የአባቶቻችንን ጸሎት ልመናቸውን ይስማልን

ከሰኔ 21 እስከ ህዳር 24 ቀን እንዲሁም እስከ ልደት(ታህሣሥ 29) ይቆያል ።

ፀጋው የበዛላቸውና ለአስቻላቸው ደግሞ በአርምሞ ከሰው ጋር ሳይነጋገሩ እድሜ ልካቸውን ሱባኤ ገብተው በበአት ይኖራሉ :;
በረከታቸውን ያድለን ጸሎታቸው ይርዳን :አሜን
Lalibela

ይህም ላንቺ ነው እምዬ😭💔
19/06/2025

ይህም ላንቺ ነው እምዬ😭💔

እውነተኛ የህዝብ ወኪል ታጋዮች
12/06/2025

እውነተኛ የህዝብ ወኪል ታጋዮች

ተመልከት የዘንድሮውን የ8ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ
10/06/2025

ተመልከት የዘንድሮውን የ8ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና

አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ

ምን አይነት የስልጣን ጥመኛ ብትሆን ነው ከገዳያችን ጃዋር ጋር ተቀምጠህ ምታወራ የአማራ ህዝብ የህልውና እየታገለ ልደትህን እያከበርክ ፎቶ ትለቃለህ !የአማራ ህዝብ በየቀኑ በድሮን እያለቀ በ...
08/06/2025

ምን አይነት የስልጣን ጥመኛ ብትሆን ነው ከገዳያችን ጃዋር ጋር ተቀምጠህ ምታወራ

የአማራ ህዝብ የህልውና እየታገለ ልደትህን እያከበርክ ፎቶ ትለቃለህ !

የአማራ ህዝብ በየቀኑ በድሮን እያለቀ በየቀኑ እየወጣህ ለግል ስምህ ተጨንቀህ የማያልቅ መግለጫ ትሰጥለህ !

ለዚህ ሁሉ እልቂት መነሻ ከሆኑት ህውሀትና የኦነግ የጡት ልጅ ከሆነው ጃዋር ጋር ተቀምጠህ ታወራለህ !

አንተ የማንም ተወካይ አይደለህም ! ለስልጣን ጥም የምትሮጥ የስልጣን ጥመኛ ነህ !

አማራ የሚታገለው ለህልውና እንጂ ለስልጣን አይደለም !

አንተ የፎቶ አርበኛ ነህ !!

አንተ የፓለቲካ እውቀት ሆነ የአካዳሚ እውቀት ያሌለህ ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ትልቅ ጠንቅ የሆንክ አረም ነን !

እንደ ብልፅግና ሁሉ እስከመጨረሻው እንታገልሀለን !

ድል ለአማራ ህዝባዊ ሰራዊት

Address

Gonder

Telephone

+251918731796

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gonder tube / ጎንደር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share