Ladisa Kebele Chief Administration

Ladisa Kebele Chief Administration Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ladisa Kebele Chief Administration, Social Media Agency, North Jakarta.
(1)

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ሰላምና ፀጥታን እና በ100 ቀናት ውስጥ በህዝብ ተሳትፎ የሚሰሩ የልማት ዙርያ ፖሊስ፣ ደንብ አስከባሪዎች፣ እና አጠቃላይ ከሁለቱ ቀጠና ህዝብ...
31/12/2025

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ሰላምና ፀጥታን እና በ100 ቀናት ውስጥ በህዝብ ተሳትፎ የሚሰሩ የልማት ዙርያ ፖሊስ፣ ደንብ አስከባሪዎች፣ እና አጠቃላይ ከሁለቱ ቀጠና ህዝብ ጋር ሰፋ ያለ የውይይት እና ምክክር መድረክ ተካሄዷል

ጉ/ላድሳ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም

በመድረኩ በጭንብል ተሸፍነው በሰው አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደረሱ አካላት ከወዲሁ ሊገቱ እንደሚገባ እና በዓሉ ከመድረሱ በፍት እንዲሁ መወያየት አስፈላጊ እንደሆነና ተገልጿል።

ህዝቡ በሰላም ወቶ በሰላም እንዲገባና የየዕለት ተግባር እንዲወጣ ለማድረግ ፀጥታ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩም በአጽንኦት ተመላክቷል።

በቀጣይ የሚከበሩ የገና በዓል ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከበር የፀጥታ ተቋማት በቅንጅት እንዲሰሩ በሀሳብ ተነስተው በየቀጠናው የፀጥታ አጋዥ ኃይሎችን እና የሮንድ ስራ የማጠናከር ሥራ መሰራት እንዳለበት ተነስቷል።

ህዝብ ለህዝብ ትስስር የሚያጠናክር በህዝብ ተሳትፎ በየደረጃው የሚሰሩ የልማት ስራዎችን በማጠናከር በቅንጅት እንደምሰራም ተነስቷል።

የጸጥታ እና የልማት ስራዎች በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመራ ጠንካራ የፓርቲ መዋቅር ለመፍጠርና የህዝቡን መሰረታዊ ችግሮች ለመቅረፍ ከመድረኩ በስፋት ተነስተዋል።

በመድረኩ የቀበሌ ዋና አሰተዳደር አቶ ደሳለኝ ዳንሳ የቀበሌው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤፌሶን ኤርምያስ እና የፀጥታ አካላትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ያለበት ደረጃ በአራዳ ክፍለ ከተማ በጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ በ02  ቀጠና ላይ ምርታማነትን በማሳደግ ተረጂነትን ታሪክ ለማድረግ በመደረግ ላይ ባለው ጥረት፤ የበጋ መስኖ ...
31/12/2025

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ያለበት ደረጃ

በአራዳ ክፍለ ከተማ በጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ በ02 ቀጠና ላይ ምርታማነትን በማሳደግ ተረጂነትን ታሪክ ለማድረግ በመደረግ ላይ ባለው ጥረት፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተሞክሮን በማስፋት ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበረና እየደረጀ የመጣው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተመኩሮ፤ ግብርናን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ አርሶ አደሩ በየአካባቢው ያሉ የውሃ አማራጮችን ተጠቅሞ በአመት ሦሥቴ እንዲያመርት በማስቻል ተጠቃሚነቱን ከማረጋገጥ ባሻገር ለታለመው የብልፅግና ራዕይ ስኬት የድርሻውን በማበርከት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

የበጋ መስኖ ልማት የአርሶ አደሩን የስራ ባህል በመቀየርና በኩታ ገጠም የማልማት ልምድን በማስፋት ምርታማነትን በማሳደጉ ረገድ አዲስ አብዮት ማምጣት ብቻ ሳይሆን ከስንዴ በተጨማሪ ሌሎች በገበያ ተፈላጊ ምርቶች በማምረት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማሳደግ ላይ ይገኛል፡፡

በዕለቱ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ዋና አስተዳደር አቶ ዳሳለኝ ዳንሳ፣ የቀበሌው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤፈሶን ኤርምያስን ጨምሮ የቀበሌው አስተባባሪዎች እና የቀጠና አመራሮች ተገኝቷል።

ታህሳስ 22/2018
ጉሩሞ ላዲሳ

በወላይታ ሶዶ ከተማ የ100 ቀናት ስራዎች ዕቅድ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ታህሳስ 17/2018 ዓ.ምየወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገዬ ...
26/12/2025

በወላይታ ሶዶ ከተማ የ100 ቀናት ስራዎች ዕቅድ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል

ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም

የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገዬ ጳዉሎስ ያለፈው የ90 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ ።

ቀጣይ የ100 ቀናት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ዕቅድ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች አፈፃፀም እና የቀጣይ ወራት ስራዎች ኦረንቴሽን ዙሪያ በወላይታ ሶዶ ከተማ የክፍለ ከተማ አስፈጻሚዎችና የቀበሊያት አመራሮች በተገኙበት ቦታ በመመከር ላይ ይገኛሉ ።

በያዝነዉ 2018 በጀት ዓመት በሁሉም የሰላም፤ የልማት እና የመልካም አስተዳደር መስኮች የተመዘገቡ አስደናቂ ውጤቶችን በማላቅ ብሎም በክፍለ ከተማ ያሉ ፀጋዎችን ገልጦ በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል የከተማችን ነዋሪዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የከተማ መንግስት ዋነኛ ትኩረት መሆኑ ተጠቅሷል ።

በተለይ በዋና ዋና የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ በማተኮር የከተማችን የ2018 የልማት ዕቅድ በዳሰሱበት ወቅት፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረግ ሽግግርን የሚያፀኑ እና ለከተማ የሰላምና የብልጽግና ግብ ስኬት አቅም የሚፈጥሩ ዝርዝር የትኩረት አቅጣጫዎችን ማመላከታቸው የሚታወስ ነው፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም ባለፉ ጊዜያት በየዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትንና የተገኙ ውጤቶችን በዝርዝር በመገምገም፤ በበጀት ዓመቱ ለታለመው ግብ ስኬት በቀጣይ በመደበኛና በንቅናቄ በትኩረት ሊከናወኑ የሚገቡ ተግባራትን በመለየት አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩም የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገዬ ጳዉሎስን ጨምሮ የከተማ አስተባባሪ አካላት፣ የከተማ ማዕከል አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማ አስፈጻሚዎችና የቀበሌ አስተዳዳሪዎችና ሌሎቸ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በአራዳ ክፍለ ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ አስተዳደር ላይ 2ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ አካሄደዋል በዚህ መሠረት የተለያዩ የቀበሌ አስተዳደር ላይ የቀበሌ ዋና አስተዳደር እና...
24/12/2025

በአራዳ ክፍለ ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ አስተዳደር ላይ 2ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ አካሄደዋል

በዚህ መሠረት የተለያዩ የቀበሌ አስተዳደር ላይ የቀበሌ ዋና አስተዳደር እና አመራሮችን ሹመት በማጸደቅ መደበኛ ጉባኤ
ተጠናቋል።

ወላይታ ሶዶ፣ ህዳር 15/2018 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ አስተዳደር ላይ 2ኛ ዙር 13ኛ ስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ አዳዲስ የቀበሌው አመራሮችን ሹመት አጽድቋል።

በመደበኛ ጉባኤው ላይ የቀበሌው ሙሉ ምክር ቤት አባላት በተገኙበት የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም የወራዊ ክንውን ሪፖርትና ቀጣይ ወር እቅድ ተግባራትና የቀበሌ አስተዳደር እቅድ ክንውን ሪፖርት ቀርቧል።

በየአካባቢው ከሰላምና ጸጥታ ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት የጸጥታው ሀይል ህብረተሰቡን አሳትፈው በቀጠናው የሚሰሩ የልማት እና መልካም አስተዳደር ስራዎችን ትኩረት አድርጎ እንዲያከናውን ከምክር ቤት አባላት ተጠይቋል

በእለቱ
1. አቶ ደሳለኝ ዳንሳ በአራዳ ክ/ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ ዋና አስተዳደር
2. አቶ ኤፌሶን ኤርምያስ የአራዳ ክ/ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
3. አቶ ብልሁ ብርሃኑ የአራዳ ክ/ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ አስተዳደር አጠቃላይ ኢኮኖሚ ዘርፍ እና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
4. ክቡር አቶ እንዳለ እልካ የአራዳ ክ/ከተማ የጉሩሞ ላዲሳ ቀበሌ አስተዳደር የህዝብ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ ተሰጥተው ተጠናቋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች"በሚል መሪ ቃል ክ/ከተማ አቀፍ የህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ኮንፈራንስ ላይ የከተማችን የመንግስት ረ...
20/12/2025

በወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች"በሚል መሪ ቃል ክ/ከተማ አቀፍ የህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ኮንፈራንስ ላይ የከተማችን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አገኙሁ ጰጥሮስ ባሉበት መድረኩ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል!!

"ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል":- አቶ ከፍያለው ተፈሪበወላይታ ሶዶ ከተማ የልማትና መልካም አስተዳደር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈ...
13/12/2025

"ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል":- አቶ ከፍያለው ተፈሪ

በወላይታ ሶዶ ከተማ የልማትና መልካም አስተዳደር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈሪ በኮንፈረንሱ መክፈቻ መንግሥት ከለውጡ ወዲህ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን ሀገራችንን ከመበተን በማዳን በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።

የቁጭታች ውጤት የሆነው የህዳሴ መጠናቀቁን፣ ስንዴን ኤክስፖርት ማድረግ መጀመሩን፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን ማልማት መጀመራችን፣ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮች እንዲሁም ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴዎችን በማስፋት በተሠሩ ሥራዎች በርካታ ውጤቶች ታይተዋል ብለዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ እንደሚገኝም የጠቆሙት ኃላፊው አገልግሎት በቴክኖሎጂ በመታገዝ በመስጠት የተገልጋይ እንግልት ለማስቀረት ተሠርቷልም ብለዋል።

በርካታ ሀገራዊ ድሎች የተመዘገቡት ህዝባችን ከመንግስት ጎን በመቆሙ የተመዘገቡ በመሆኑ ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ ተናግረው የምናልመውን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚቻለው በቅንጅትና በትብብር ስንሠራ ነው ብለዋል።

የሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲቤ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም የሶዶ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች ተቻችለው በፍቅር የሚኖሩባት ከተማ ናት ሲሉ ተናግረው በርካታ ህዝባችንን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች እየተሠሩ እንደሆነ አብራርተዋል።

የመጡ ለውጦች የከተማው ህዝብ ከመንግሥት ጎን በመቆም የመጡ በመሆኑ አመስግነው በኮንፈረንሱ ለከተማችን ለውጥ እና ብልጽግና የሚጠቅሙ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

13/12/2025
በወላይታ ሶዶ ከተማ ለመካከለኛ አመራሮች ስሰጥ የነበረው የሶስተኛ ዙር ስልጠና በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል ወላይታ ሶዶ፦ህዳር 30/2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ "በመደመር መንግስት እይታ፣...
09/12/2025

በወላይታ ሶዶ ከተማ ለመካከለኛ አመራሮች ስሰጥ የነበረው የሶስተኛ ዙር ስልጠና በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል

ወላይታ ሶዶ፦ህዳር 30/2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ "በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ለመካከለኛ አመራሮች ስሰጥ የነበረው የሶስተኛ ዙር ስልጠና በዛሬው ዕለት ግብን በመምታት ይጠናቀቃል ።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡርት ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም ለከተማ መካከለኛ አመራሮች የስራ መመሪያ እየሰጡ ይገኛል።

ላለፉት ስምንት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና የከተማ የአመራሩን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማሳደግ በወላይታ ሶዶ ከተማ የተጀመሩ ለውጦች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑ ወ/ሮ እታገኝ አመላክቷል ።

ብልጽግና ፓርቲ ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን ለመሸጋገር ያነገበውን ግብ በስኬት መጠናቀቅ የቻለ መሆኑን ያመለከቱ ከንቲባ የወላይታ ሶዶ ከተማ አመራሩ አንድ አመት እንደ አምስት አመት በብርቱ ትጋት በአፍሪካ ተምሳሌታዊ ሀገር ለማሻገር እንዲያስችል የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት ማጎልበት እንደሚገባ አመላክቷል ።

ስልጠናዉ በሀገር ደረጃ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ በቁልፍ ሴክተሮች ላይ ዉጤት የማምጣትና አመራሩ ዕይታ የማስፋት ሚና እንደሚኖረውም ተጠቅሷል።

በስልጠናው በመደመር መንግስት እይታ የግብርና፣ የገጠር መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ የሚሉ ርዕሶች ላይ ጥልቅ ዉይይት ተካሂዷል።

ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን የተግባርና የንድፈ-ሃሳብ ዕዉቀት በየክፍለ ከተማ እና በየቀበሌ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር በሁሉም ዘርፎች እመርታ ለማስመዝገብ እንደሚተጉ ይጠበቃል።

በስልጠናው ከ 172 በላይ የከተማ መካከለኛ አመራሮች መሳተፍ ችለዋል።

በስልጠና ማጠቃለያ ላይ የወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግሥት ዋና ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገዬ ጳውሎስ፣ የከተማ ም/ከንቲባና ሥራና ክህሎት መምሪያ ሀላፊ አቶ መንግስቱ ትግሮን ጨምሮ የመንግሥት ረዳት ተጠሪዎች ፣የከተማ አጠቃላይ አመራሮች ፣ የክፍለ ከተማ አስፈፃሚዎችና አመራሮች እንዲሁም የቀበሌ አመራሮች መሳተፍ ችለዋል።



Wolaita S**o City Prosperity Party Branch Office

የጋራ በሚያደርጉ እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ አንድ በመሆን የጋራ አቋም በመያዝ በቅንጅት መሥራት ይገባል፦አቶ ዝናቡ ተክሌወላይታ ሶዶ ህዳር፣ 29/2018 ዓ.ም በ...
08/12/2025

የጋራ በሚያደርጉ እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ አንድ በመሆን የጋራ አቋም በመያዝ በቅንጅት መሥራት ይገባል፦አቶ ዝናቡ ተክሌ

ወላይታ ሶዶ ህዳር፣ 29/2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ የአራዳ ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ትውውቅ እና ቀሪ የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች ዙርያ ላይ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በትውውቁ ወቅት የአራዳ ክ/ከተማ ዋና አስፈፃሚ አቶ ዝናቡ ተክሌ እንደገለፁት በከተማው በሚሰሩ የመንግሥትና ፓርቲ ተግባራት ዙሪያ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣትና ተግባሩን በውጤት አሳጅበው መመራት አስመልክተው ነው የትውውቅ መድረክ ያካሄዱት።

በከተማው የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠልና ህዝቡን ለማገልገል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸው አንድነታችን ላይ በማትኮር፣ በመቀራረብ በመስራት፣ ችግሮችን በመፍታትና ከማዕበል የሚወረዱ ተልዕኮን በብቃት በመወጣት ውጤታማ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ስሉ አቶ ዝናቡ ተናግሯል።

የአራዳ ክፍሌ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ደስታዬ ዳርጮ በትውውቅ ሰዓት አመራሩ ተጀምረው እየተሰሩ ያሉ የፓርቲና የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን አጠናክረው እንድያስቀጥሉ መልዕክት አስተላልፎ አዳግ የሆነው የህዝብ ጥያቄ ሁሉም ባለድርሻ በቅንጅት መስራት እንዳለበት ተናግሯል።

በመድረኩ የአራዳ ክፍሌ ከተማ አጠቃላይ አመራሮችን ጨምሮ የአስራ አንዱ የቀበሌ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ጋር በዲጂታል  ቁጠባ እና የብድር አገልግሎት ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ የውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ህዳር 29/0...
08/12/2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ጋር በዲጂታል ቁጠባ እና የብድር አገልግሎት ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ የውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ህዳር 29/03/2018 ዓ/ም ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማሪያም እንደገለፁት የተቀላጠፈ እና ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎትን ለመስጠት ከኢትዮጵያ ንግድ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ክብርት ከንቲባዋ አክለውም ዛሬ በተፈረመው መግባቢያ ሰነድ መሰረት የከተማው የመንግስት ሰራተኞች ሲቢኢ በእጄ የዲጂታል የብድር አገልግሎት እንዲጠቀሙ ያስችላል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመንግስት ሰራተኞች የብድር አገልግሎትን እንዲያገኙ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አማራጭ ይዞ መቅረቡን በባንኩ የወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የመጡት አቶ ተስፋልደት በላይ ገልፀዋል፡፡

በውል ስምምነቱ የፊርማ ስነ ስርአት ላይ የወላይታ ሶዶ ከተማ የፋይናንስ እና ፕላን መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሰማ ታንቱ እና የባንኩ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Address

North Jakarta

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ladisa Kebele Chief Administration posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share