03/01/2026
አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ ስላደረገችው ወታደራዊ ጥቃት ማወቅ ያለብዎ ነጥቦች!!
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው ቅዳሜ ማለዳ ላይ "ተይዘው ከአገር እንዲወጡ ተደርገዋል" ብለዋል። ይህም በዓለም ዙሪያ ፈጣን ስጋትን የቀሰቀሰውን የአሜሪካን "መጠነ-ሰፊ ጥቃት" ያረጋገጠ መግለጫ ሆኗል።
የአሜሪካ ጦር ልዩ ግብረ-ኃይል (Delta Force) ማዱሮን የመያዙን ዘመቻ ማከናወኑን ባለሥልጣናት ለሲቢኤስ (CBS) ኒውስ ገልጸዋል።
Ethioinfo
አንድ የሪፐብሊካን ሴናተር እንደተናገሩት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ማዱሮ ከአመታት በፊት ክስ ተመስርቶባቸው በነበረበት አሜሪካ ውስጥ የወንጀል ክስ እንደሚመሰረትባቸው ጠቁመዋል።
ሩቢዮ "በቬንዙዌላ ተጨማሪ እርምጃ ይወሰዳል ብዬ አልጠብቅም" ማለታቸውንም ሴናተሩ ገልጸዋል። የትራምፕ አስተዳደር ማዱሮን በዕፅ ዝውውር እና አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ ቡድኖች ጋር በመስራት ለረጅም ጊዜ ሲከስ የቆየ ቢሆንም፣ ማዱሮ ግን ክሱን ያስተባብላሉ።
ጥቃቱ የተፈጸመው አሜሪካ በቀጠናው ለወራት ያደረገችውን ወታደራዊ ዝግጅት ተከትሎ ሲሆን፣ "ዩኤስኤስ ጄራልድ አር ፎርድ" (USS Gerald R. Ford) የተሰኘችው የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ እና ሌሎች በርካታ የጦር መርከቦች በካሪቢያን ባህር ላይ ሰፍረው ነበር።
ባለፉት ሳምንታት አሜሪካ በቬንዙዌላ አቅራቢያ ሁለት የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን የተቆጣጠረች ሲሆን፣ አስተዳደሩ "ዕፅ ጭነዋል" ባላቸው ከ30 በላይ ጀልባዎች ላይም ጥቃት ሰንዝሯል።
በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ጀልባዎቹ ዕፅ የሚጭኑበት የወደብ አካባቢ" ያሉትን ስፍራዎች መምታታቸውን ገልጸዋል።
ተፈላጊው ግለሰብ በተያዘበት ወቅት "በጥብቅ ይጠበቅ" እንደነበር የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ሌሊቱን የተከናወነውን ኦፕሬሽን በማድነቅ አንድም የአሜሪካ ወታደር እንዳልተገደለ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቅዳሜ ጠዋት በ "Fox and Friends" ፕሮግራም ላይ ሲናገሩ "እንደ እውነቱ ከሆነ ቦታው ልክ እንደ ምሽግ ነበር" ብለዋል።
"ማንም ሰው አለመገደሉ አስገራሚ ነው። ጥቂት ሰዎች ተመተው ነበር፣ ነገር ግን ተመልሰዋል፤ አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ስለሚታሰብ ማንም አልተገደለም ማለት እችላለሁ።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም አሜሪካ የቬንዙዌላውን ኦፕሬሽን ከቀናት በፊት ልታከናውን አቅዳ የነበረ ቢሆንም፣ የአየር ሁኔታው አመቺ እንዳልነበር ገልጸዋል።
"ይህንን ለማድረግ ያሰብነው ከናራት በፊት ነበር፣ ነገር ግን የአየር ሁኔታው ፍጹም አልነበረም" ብለዋል ትራምፕ። "ከዚያም በድንገት (ሰማዩ) ሲጠራ እርምጃውን ወስደናል ብለዋል።
What to know about the U.S. military strikes on Venezuela
President Trump said Venezuelan President Nicolás Maduro and his wife were "captured and flown out of the Country" early Saturday morning, confirming a "large scale strike" by the U.S. that drew quick condemnation and concern from across the globe.
The U.S. Army's Delta Force, an elite special forces unit, carried out the operation to capture Maduro, officials told CBS News.
A Republican senator said Secretary of State Marco Rubio had indicated that Maduro would face cri