03/01/2026
የካሜራ ባለሞያው እስካሁን ድረስ የገባበት አልታወቀም።
ከተሰወረ 140 ቀናት ሆኖታል።
የካሜራ ባለሞያው ወጣት ፊልሞን (ፊላሪ) ነሀሴ 4/ 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በመቐለ ከተማ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ በባጃጅ እየተጓዘ ሳለ ነው የተሰወረው። ከተሰወረ በጥቂት ቀናት ውስጥ ፓሊስ ጉዳዩን ተከታትሎ በአጭር ጊዜ ሁኔታውን እንደሚያሳውቅ ተናግሮ ነበር።ይሁን እንጂ ወጣት የፊልም ባለሙያው ከተሰወረ ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ/ም 140 ቀናት ቢቆጠሩም ፤ ፓሊስ የሚጨበጥ መረጃና ወጤት አላሳወቀም።የካሜራ ባለሞያው ባለትዳርና የሁለት ህፃናት አባት ሲሆን ሰርቶ ሲያስተዳድራቸው የነበሩት ቤተሰቡ ሃዘን አልበቃ ብሏቸው ለችጋር ተጋልጠው " የእርዱን " እጃቸውን ዘርግተዋል።
የወጣት የፊልም ባለሙያው መሰወር እጅግ ያሳሰባቸው ወዳጅ ዘመዶች " ሁሉም ሰብአዊ ፍጡር በፍለጋ ይተባበረን " በማለት ተማፅነዋል። ከአስከፊው የትግራይ ጦርነት በኋላ በክልሉ የሰዎች ስወራና እገታ መባባሱ ይታወቃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ