ሸዋ Times

ሸዋ Times ሸዋ በኢትዮጵያ ጥንተ ታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያለው ነው!

በትናንትናው ዕለት የአቶ ተፈራ ወንድማገኝን ፎቶግራፍ በፔጃችን ያጋራን ሲሆን ብዙዎች በውስጥ መስመር ሰውየውን ባንዳ ነው በማለት ሲፅፉልን ውለዋል። እኛም እንላለን ተፈራ ህዝባዊ ቅቡልነት የ...
30/07/2025

በትናንትናው ዕለት የአቶ ተፈራ ወንድማገኝን ፎቶግራፍ በፔጃችን ያጋራን ሲሆን ብዙዎች በውስጥ መስመር ሰውየውን ባንዳ ነው በማለት ሲፅፉልን ውለዋል። እኛም እንላለን ተፈራ ህዝባዊ ቅቡልነት የነበረዉ ህዝባዊ መሪ ነበር።

ሌላው ነገር አቶ ተፈራ አሁን ላይ እየሠራ ያለው ሥራ ብዙዎችን እያስለፈለፈ ነው። አንድ ሰው ከነበረበት የሥራ ዘርፍ ሲወጣ ሌላ አማራጭ ፈልጎ ህይወቱን የማስቀጠል ግዴታ እንዳለበት መታወቅ አለበት። ለማንኛውም የተፈራ ስም ሲነሳ የሚደነብር የአማራ ጠላት እንጂ ወዳጅ አይደለም።

ተናፋቂው የሸዋ መሪ!
29/07/2025

ተናፋቂው የሸዋ መሪ!

የምህላ ፀሎት ታወጀ!በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት በተለይ በቆላማ ወረዳዎች ክረምቱ ወቅቱን ጠብቆ ባለመግባቱና የዝናብ እጥረት በመከሰቱ ጸሎተ ምኅላ ታውጇል።ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ...
29/07/2025

የምህላ ፀሎት ታወጀ!

በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት በተለይ በቆላማ ወረዳዎች ክረምቱ ወቅቱን ጠብቆ ባለመግባቱና የዝናብ እጥረት በመከሰቱ ጸሎተ ምኅላ ታውጇል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኹሉም ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተክርስቲያን ከዛሬ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ7 ቀናት የሚቆይ ምኅላ አውጀዋል።

ኹሉም ሕዝበ ክርስቲያን በየአብያተ ክርስቲያናቱ ዘወትር ጠዋት በመገኘት በተሰበረ ልብ ወደእግዚአብሔር እንድጸልይ ብፁዕነታቸው ትናንት ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

ትናንት አዳሩን በወልዲያ መጠነኛ ዝናብ ቢዘንብም በቆላማው ቀበሌዎች፣ በቆቦ፣በአላማጣ እንዲሁም በራያ አዘቦ እስካሁን ዝናብ እንዳለዘነበ አዩዘሀበሻ መዘገቡ የሚታወስ ነው።

የተማራችሁበት ዩኒቨርስቲ ስንተኛ ደረጃ ላይ ነው!? ኮሜንት ላይ ደረጃውን አስቀምጡ!‎የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ — 20251 Addis Ababa University2 University of ...
22/07/2025

የተማራችሁበት ዩኒቨርስቲ ስንተኛ ደረጃ ላይ ነው!? ኮሜንት ላይ ደረጃውን አስቀምጡ!
‎የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ — 2025

1 Addis Ababa University
2 University of Gondar
3 Bahir Dar University
4 Jimma University
5 Mekelle University
6 Hawassa University
7 Haramaya University
8 Adama Science and Technology University
9 Arba Minch University
10 Jigjiga University
11 Addis Ababa Science and Technology University
12 Ambo University
13 Dilla University
14 Unity University
15 Debre Berhan University
16 Wollo University
17 Debre Markos University
18 Wolaita S**o University
19 Madda Walabu University
20 Worabe University
21 Wachamo University
22 Debre Tabor University
23 Wolkite University
24 Ethiopian Civil Service University
25 Arsi University
26 Samara University
27 Assosa University
28 Dire Dawa University
29 Wollega University
30 Mattu University
31 Mizan-Tepi University
32 Kotebe Education University
33 Adigrat University
34 Woldia University
35 Oromia State University
36 Bule Hora University
37 Aksum University
38 Bonga University
39 Rift Valley University
40 Oda Bultum University
41 Raya University
42 Injibara University
43 Selale University
44 Debark University
45 Kebri Dehar University
46 Gambella University
47 Mekdela Amba University
48 Dembi Dolo University
49 Jinka University
50 Borena University
Un Ethiopian Police University

‎(According to UNIRANKS® — Top-Ranked Universities in Ethiopia - 2025)

ታማኙ ፋሲል!
19/07/2025

ታማኙ ፋሲል!

አርበኛ መክብብ ኦልቀባ ማን ነው?በምስሉ ላይ የሚታየው ወጣት መክብብ ኦልቀባ ይባላል። በኢትዮጵያ የታሪክ ሰነድ ላይ ብዙም ካልተወሱ የአድዋ ጀግኖች መካከል ፊታውራሪ ኦልቀባ ረጋሳ አንዱ ናቸ...
19/07/2025

አርበኛ መክብብ ኦልቀባ ማን ነው?

በምስሉ ላይ የሚታየው ወጣት መክብብ ኦልቀባ ይባላል።

በኢትዮጵያ የታሪክ ሰነድ ላይ ብዙም ካልተወሱ የአድዋ ጀግኖች መካከል ፊታውራሪ ኦልቀባ ረጋሳ አንዱ ናቸው። መክብብ የፊታውራሪ ኦልቀባ ልጅ ሲሆን የካቲት 12፣ 1929 አብረሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስግድሞ ግራዝያኒ ላይ የወረወሩትን የፈንጂ ባሩድ ፈጭቶ ቀላጭ ቀጥቅጦና ፈንጂውን ሰርቶ የሰጣቸው እሱ ነበር። መክብብ ያኔ የገዳም ሰፈር ልጅና የ20 ዓመት ወጣት ነበር።

ልበ ቅኑ ዶ/ር ፍቃደ አጉዋር እውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው!የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪሙ እና ከመደበኛ ስራቸው ውጭ ባሻገር ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም አቋቁመው በበጎ ...
19/07/2025

ልበ ቅኑ ዶ/ር ፍቃደ አጉዋር እውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው!

የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪሙ እና ከመደበኛ ስራቸው ውጭ ባሻገር ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም አቋቁመው በበጎ ፈቃድ የልብ ህሙማንን በመርዳት የሚታወቁት በጎንደር ዩኒቨርስቱ የተመረቁት ዶ/ር ፈቀደ አጉዋር ጎንደር ዩኒቨርስቲ ለቀድሞ ተማሪዎቹ እውቅና በሰጠበት እለት የአልሙናይ አዋርድ ተሸላሚ አድርጎ ሸልሟቸዋል።

የእንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወ ኤልያስ ቤተክርስቲያን!
19/07/2025

የእንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወ ኤልያስ ቤተክርስቲያን!

በ 1983 ዓ.ም እስራኤል በዘመቻ ሰለሞን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ሀገር የተጓዘው ቤተ-እስራኤላውያን (ፈላሻ) ህፃን በሎድ ቤን ጉሪዮን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በአሻንጉሊት እ...
16/07/2025

በ 1983 ዓ.ም እስራኤል በዘመቻ ሰለሞን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ሀገር የተጓዘው ቤተ-እስራኤላውያን (ፈላሻ) ህፃን በሎድ ቤን ጉሪዮን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በአሻንጉሊት እየተጫወተ ይታያል።

ሸዋ ደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን!
12/07/2025

ሸዋ ደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን!

የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የጉምሩክ ከተማ!"ጠላት መጣ መሰል ተንጫጩ ወፎቹ፣ ጀግኖች ይጠሩልን አልዩ አምባዎቹ!" ተብሎ የተገጠመላት፣ የበረሃዋ ገነት በመባል የምትታወቀው ውቢቷ አልዩ አምባ ዛሬ...
11/07/2025

የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የጉምሩክ ከተማ!

"ጠላት መጣ መሰል ተንጫጩ ወፎቹ፣
ጀግኖች ይጠሩልን አልዩ አምባዎቹ!"

ተብሎ የተገጠመላት፣ የበረሃዋ ገነት በመባል የምትታወቀው ውቢቷ አልዩ አምባ ዛሬም በታሪኳ ትዘከራለች። የአንኮበር ታሪክ ሲነሳ፣ የስምጥ ሸለቆ አካል የኾነችው እና የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ የንግድ ማዕከል የነበረችው አልዩ አምባ ሁሌም ትጠቀሳለች።

በሸዋ አንኮበር ወረዳ የምትገኘው አልዩ አምባ የተመሠረተችው በ1266 ዓ.ም እንደኾነም ይነገራል ስያሜዋንም ያገኘችው "አልየ" ከተባለ የአካባቢው ነጋዴ እንደኾነ ታሪክ ይነግረናል።

ከአዲስ አበባ 187 ኪሎ ሜትር፣ ከደብረ ብርሃን 57 ኪሎ ሜትር፣ ከአንኮበር ወረዳ ዋና ከተማ ጎረቤላ ደግሞ 15 ኪሎ ሜትር ትርቃለች ይህችው ድንቅ ስፍራ። አልዩ አምባ ለረዥም ርቀት ንግድ (ሲራራ ንግድ) ምቹ በመኾኗ በወቅቱ እስከ ዘይላ ወደብ ድረስ ተዘርግቶ የነበረው የሲራራ ንግድ ማዕከል በመኾንም አገልግላለች።

በ1834 እና 1835 ዓ.ም በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የኾነው የቀረጥ ውል በአልዩ አምባ ገበያ መሠረት ተፈርሟል። በአጼ ምኒልክ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረጥ መሥሪያ ቤት ሲከፈት በአልዩ አምባ የጉምሩክ ጽሕፈት ቤት ሥራውን የጀመረ ሲኾን ከዘይላ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ የንግድ ዕቃዎች ላይ የቀረጥ ክፍያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረባት ከተማም ነች።

ከ1ሺህ 500 እስከ 1ሺህ 700 የሚጠጉ ግመሎች የሀገር ውስጥ ሸቀጦችን ወደ ውጭ ያጓጉዙባት እንደነበርም ይነገራል። በአሁኑ ወቅት የአማራ፣ የአፋር እና የአርጎባ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች በፍቅር እና በአንድነት የሚኖሩባት ድንቅ ቦታም ናት አልዩ አምባ።

በ19ኛው ክፍለ ዘመን የንግድ ማዕከል በነበረችበት ወቅት አራት መግቢያ እና መውጫ በሮች የነበሯት ይህችው ድንቅ ስፍራ በሮቿም አዋሽ በር (ጨው፣ ሻይና ሌሎች ሸቀጦች ከዘይላ ወደብ የሚገቡበት) እና ጨኖ በር በመባል የሚታወቀው በር ሌላው መግቢያ በር ነው።

ይህችው ድንቅ ስፍራ መውጫ በሮችም ነበሯት ይኸውም አንኮበር በር (ከመሀል ሀገር እስከ ሰሜን ዕቃዎች የሚላኩበት) እና ምንጃር በር (ወደ ደቡብ ሸቀጦች የሚላኩበት) ናቸው።

አልዩ አምባ ከፐርሺያ፣ ከሕንድ እና ከአረብ ሀገሮች የሚመጡ በርካታ የውጭ ዜጎች ይኖሩባት እንደነበርም ጎብኝዎች ጽፈዋል። ስልክ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ከእንጦጦ እስከ አልዩ አምባ ድረስ መስመር ተዘርግቶለት ነበር፤ እስካሁንም "ስልክ አምባ" የሚባል ሰፈር መኖሩ የዚሁ ማሳያ ነው።

አሁን ላይም አልዩ አምባ የንግድ እንቅስቃሴ በሰፊው የሚካሄድባት ታሪካዊ ከተማም ናት።

በዲላ ዩንቨርስቲ ሰመራ ካምፓስ የተማራችሁ የእመቤቴ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እርዳትዋ ልመንዋ የደገፋችሁ ሲከፋን ምንፅናናባት ስንደስት በእልልታ የዘመርንባት ስንጣም በደጅዋ ቁጭ በለን ያሳለፍን...
10/07/2025

በዲላ ዩንቨርስቲ ሰመራ ካምፓስ የተማራችሁ የእመቤቴ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እርዳትዋ ልመንዋ የደገፋችሁ ሲከፋን ምንፅናናባት ስንደስት በእልልታ የዘመርንባት ስንጣም በደጅዋ ቁጭ በለን ያሳለፍንባት ብዙ የሆነችልን እናታችን የኪዳነ ምህረት ሕንፃ ለፍፃሜ በቅቶ እንድናይ እግዚሃብሔር ይርዳን።

የሁላችንምን እርዳታና ድጋፍ ያስፈልጋል!

አንድ ካሬ ቆርቆሮ ለአንድ ሰው!

"አንድ ብሎኬት ለአንድ ተማሪ" የነበረው አይነት ልዩ መንፈሳዊ challenge እነሆ ተደገመ "አንድ ካሬ ቆርቆሮ ለአንድ ሰው " በመንፈሳዊ ቅናት ለዲላዋ ኪዳነምሕረት challenge እንቀላቀል።

ጸሎት ሠሚዋ በmid Final exam ለተጨነቅን የተረጋጋንባት፣ ለጾም ለንስሐ፣ ኪዳን ቅዳሴ ለተጋንባት ቅድስት ቤተክርስቲያን ለፍፃሜ እናድርሳት!

የአንድ ካሬ ቆርቆሮ ዋጋ 1440 ብር ብቻ!

1000084396609
ዋለሜ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ

Address

Nazareth

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሸዋ Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category