Affini Media and Communication-አፊኒ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን

  • Home
  • India
  • Delhi
  • Affini Media and Communication-አፊኒ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን

Affini Media and Communication-አፊኒ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን Affini is an independent media aiming to deliver intellectual ideas and alternative ways to create a

ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ ================================ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወ...
18/08/2025

ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ
================================
ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡

በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡

በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ነው ያለው።

ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21 ሺህ 492 ወደ ብር 39 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።

የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 የሚሻሻል መሆኑን ገልጿል።

ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አስታውቋል።

ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል ያለው ኮሚሽኑ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ብሏል።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፦https://www.facebook.com/100069672641659/posts/1084297830569295/?app=fbl

ዜና እረፍት አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት በሙያው ሀገሩን አገልግሏል።ደበበ እሸቱ የመድረክ መ...
17/08/2025

ዜና እረፍት
አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት በሙያው ሀገሩን አገልግሏል።

ደበበ እሸቱ የመድረክ መሪ ፣ የሬዲዩ እና የቴሌቪዥን ድራማና ፊልሞች ተዋናይ እንዲሁም ጋዜጠኛም ነበሩ ።

አፊኒ ሚዲያ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና የአርት ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል!

በኃላፊነት ላይ ያለ የመንግስት ሹመኛ ወይም ተመራጭ ለ   እንዳይታጭ የሚከለክል መመሪያ ወጣ**መመሪያው 8 ዙር ተማሪዎችን ያላስመረቁ እና ሶስተኛ ዲግሪ ወይም (PhD) የማያስተምሩ ከፍተኛ ...
12/08/2025

በኃላፊነት ላይ ያለ የመንግስት ሹመኛ ወይም ተመራጭ ለ እንዳይታጭ የሚከለክል መመሪያ ወጣ

**መመሪያው 8 ዙር ተማሪዎችን ያላስመረቁ እና ሶስተኛ ዲግሪ ወይም (PhD) የማያስተምሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተመራው ይህ መመሪያ በቅርብ ጊዜ የተመሰረቱ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡

በመመሪያው ክፍል ሁለት ላይ የክብር ዶክትሬት የሚሰጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መስፈርትን በተመለከተ የተቀመጠው ድንጋጌ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ለመስጠት ቢያንስ ከ8 ጊዜ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቁ እና የሶስተኛ ዲግሪ የሚሰጡ መሆን እንዳለባቸው ያስገድዳል፡፡

በዚህም መሰረት ሰላሌ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መቅደላ አምባ፣ ራያ፣ ደባርቅ እና መሰል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስምንት ዙር ተማሪዎችን ስላላስመረቁ በመመሪያው መሰረት የክብር ዶክትሬት መሰጠት አይችሉም፡፡

በዚሁ ክፍል ስር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት አገር እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው ሰፍሯል፡፡

በሞያ መስኩ የተለየ ስራ ያበረከተ ከሆነ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል የዘረዘረው መመሪያው መስፍርቱን ካሟሉ ለግለሰብም ይሁን ለቡድን መስጠት እንደሚቻል አመላክቷል፡፡

በሕይወት ላለም ይሁን ለሌለ ሰው ማዕረጉን መስጠት እንደሚቻል የሚፈቅደው ይህ መመሪያው የክብር ዶክትሬት ለማግኘት የማይቻልባቸውን ገደቦችም በክፍል ሁለት አንቀጽ 10 ስር ዘርዝሯል፡፡

በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሰራተኛ፣ የሴኔት አባላት ወይም የአስተዳደር አካላት ከተቋሙ ጋር ያላቸው ቀጥተኛ ግንኙነት እስካላበቃ ድረስ ለክብር ዶክትሬት መታጨት እንደማይችሉ ደንግጓል፡፡

መመሪያው በስራ ላይ ያሉ የመንግስት ሹሞች ወይም ባለስልጣናት ለክብር ዶክትሬት እንዳይታጩም የሚከለክል ነው፡፡

የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ግለሰብ ዶክተር፣ የክብር ዶክተር እና መሰል መጠሪያዎችን ከሰጪው ተቋም ውጪ በየትኛውም ድርጅት ውስጥ መጠቀም እንደማይችሉም ደንግጓል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ዓመት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሽምያ የሚሰጡ የክብር ዶክትሬት ማዕረጎች መመሪያ እስኪወጣ ድረስ እንዲያቆሙ ማዘዙ ይታወሳል፡፡

( ያሬድ እንዳሻው - ሸገር ራዲዮ)

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሲዳማ ቡና  ከለብ ወቅታዊ ሁኔታ አሰመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ለሚዲያዎች ጥሪ አድርጓል ፣ዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት የሲዳማ ቡና ይግባኝ ሙሉ በሙ...
10/08/2025

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሲዳማ ቡና ከለብ ወቅታዊ ሁኔታ አሰመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ለሚዲያዎች ጥሪ አድርጓል ፣

ዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት የሲዳማ ቡና ይግባኝ ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል። ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ሰኞ ነሐሴ 5/2017 ከቀኑ 8:00 ላይ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተዘጋጅቷል።

በመሆኑም የሚዲያ አካላት በስፍራው እና በሰዓቱ ተገኝታችሁ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ እና የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡ በማክበር እንጠይቃለን ሲሉ ገልጿል።
ቀጣዩ የሲዳማ ቡና እጣፈንታ የመላው ህብረተሠብ እና የደጋፊዎች ትኩረት ሆነዋል።

ሲዳማ ባንክ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ብር ተቀማጭ አስመዘገበ ====================የሲዳማ ባንክ አክሲዮን ማህበር በበጀት ዓመቱ 3 ቢሊየን 674 ሚሊዬን በላይ ብር ተቀማጭ ማስ...
04/08/2025

ሲዳማ ባንክ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ብር ተቀማጭ አስመዘገበ
====================

የሲዳማ ባንክ አክሲዮን ማህበር በበጀት ዓመቱ 3 ቢሊየን 674 ሚሊዬን በላይ ብር ተቀማጭ ማስመዝገቡን ገለጸ።

ሲዳማ ባንክ አክሲዮ ማህበር የ2024/25 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ዓመታዊ የሥራ አመራር ጉባዔ በሐዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባዔው ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሐጢያ የሲዳማ ባንክ በአጭር ጊዜ ተወዳዳሪና ተፎካካሪ መሆን የቻለ ባንክ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ባንኩ የዉስጥ አቅሙን አሟጦ በመጠቀም ካፒታሉን እያሳደገ መምጣቱን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ባሳለፍነዉ ዓመት የታየዉ የባንኩ ስኬት ለቀጣይ ዓመት የተሻለ ሥራ እንደምንሰራ አመላካች ነዉ ብለዋል።

የባንኩ ስትራቴጂክ እና ማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንሻ ሚካኤል በበኩላቸው፤ ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ተጨማሪ ተቀማጭ ለመሰብሰብ አቅዶ፥ በአጠቃላይ 3 ቢሊየን 674 ሚሊዬን ብር በመሰብሰብ ከዕቅድ በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰዋል።

2.4 ቢሊዬን ብር ብድር መስጠቱን የጠቀሱት አቶ ወንሻ፤ ከ97 በመቶ በላይ ዕዳ ማስመለስ ቻሉንም ገልፀዋል።

ለደንበኞች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትም በቀጣይ ባንኩን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ለድረግ የሞባይል ባንኪንግ አፕልኬሽን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ይፋ እንደሚደረግም አክለዋል።

ሲዳማ ባንክ ምንም እንኳን ከማይክሮ ፋይናንስ ሙሉ በሙሉ ወደ ባንክ ካደገ አጭር ጊዜ ቢሆንም፤ 333 ሺህ ደምበኞችን ማፍራት መቻሉንም ጠቁመዋል።

{በ0 አመት}Ethiopian Airlines - Vacancy Announcement (For Fresh Graduates)Ethiopian Airlines would like to invite qualified...
02/08/2025

{በ0 አመት}Ethiopian Airlines - Vacancy Announcement (For Fresh Graduates)

Ethiopian Airlines would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following vacant position.

Position 1: Trainee Pilot
Qualification: BSC/BA Degree in Any Field Of Study

Position 2: TRAINEE CABIN CREW
Qualification: a minimum of Ethiopian university entrance exam certificate (EUEEC) with a minimum 200 result.

Position 3: SCHOOL OF MARKETING /SOM/ TRAINEE
Qualification: a minimum of Ethiopian university entrance exam certificate (EUEEC) with a minimum 300 result.

REGISTRATION PLACES/ LOCATIONS: –
ADAMA SCIENCE AND TECHNOLOGY UNIVERSITY, ADAMA
ADDIS ABABA, ONLINE
AMBO UNIVERSITY, AMBO
ARBAMINCH UNIVERSITY, ARBAMICH
ASSOSA UNIVERSITY, ASSOSA
BAHIR DAR UNIVERSITY, BAHIR DAR
WOLLO UNIVERSITY, DESSIE
DIRE DAWA UNIVERSITY, DIRE DAWA
GAMBELLA UNIVERSITY, GAMBELLA
GONDAR UNIVERSITY, GONDER
HARAMAYA UNIVERSITY; HARAR CAMPUS, HARAR
HAWASSA AIRPORT, HAWASSA
JIGJIGA UNIVERSITY, JIGJIGA
JIMMA UNIVERSITY, JIMMA
MEKELLE UNIVERSITY, MEKELE
WOLLEGA UNIVERSITY, NEKEMETE
MADDA WALABU UNIVERSITY, ROBE
SEMERA UNIVERSITY, SEMERA
SHASHEMENE POLY TECHNIC COLLEGE, SHASHEMENE
WOLKITE UNIVERSITY, WOLKITE
Required Number: 4000

How to Apply: (ይመልከቱ፤ ፈጥነው ያመልክቱ!)
For details use the link below and apply: 👇👇👇
https://lnkd.in/d3vxX7wr
Registration Date: August 11, 2025, To August 15, 2025
🔗መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ እባክዎ ለወዳጅ-ጓደኛዎ ያጋሩት
Don’t forget to share for your friends

ዶ/ር ግርማ አመንቴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ንግድ ድርጅት የአፍሪካ ሕብርት ቋሚ ተወካይ ሆኖ ተሾሙ ፤==============================አፊኒ ሐምሌ 25፣2017 ዓ...
02/08/2025

ዶ/ር ግርማ አመንቴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ንግድ ድርጅት የአፍሪካ ሕብርት ቋሚ ተወካይ ሆኖ ተሾሙ ፤
==============================
አፊኒ ሐምሌ 25፣2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
የቀድሞ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትርነትን ጨምሮ በተለያዩ መንግስታዊ ሃላፊነቶች ያገለገሉት ዶክተር ግርማ አመንቴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጄኔቫ በሚገኘው የዓለም ንግድ ድርጅት የአፍሪካ ሕብርት ቋሚ ተወካይ ሆነው እንዲያገለግሉ በአፍሪካ ሕብረት መሾማቸው ተረጋግጧል ።

አዲሱ አረጋ በትላንትናው ዕለት በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር የግብርና ሚኒስቴር ሆኖ መሾማቸው ይታወሳል።

This article does not conform to the standards of journalism or academic content. It lacks a solid foundation and is dis...
29/07/2025

This article does not conform to the standards of journalism or academic content.
It lacks a solid foundation and is disconnected from the history and socio-political context of the Sidama people. We categorically reject this misleading narrative. We are aware of those responsible for it, but we urge, the owner of the media outlet, and some members of the Addis Ababa-based team to take the time to provide clarity on this matter.

: Purity and Power: politics still shackled by old ideologies

The Sidama people, known for their distinct cultural identity, gained regional statehood in 2019 after years of struggle. However, the author of this commentary argues that the region's political landscape remains deeply influenced by centuries-old systems—most notably, Wolapho, an ideology of "ritual purity" that determined an individual's access to power, resources, and social status based on their "lineage and clan." He writes, "In modern Sidama politics, Wolapho continues to manifest through favoritism, exclusion, and discrimination, despite the democratic rhetoric adopted by many political parties operating in the region."

The author explains that this ideology, rooted in the 17th century, "evolved from a traditional purification process into a rigid political hierarchy," with the Yemericho clan at the top, while others such as the Hadicho, Aleta, and Hoffa were categorized as "unpurified." He further elaborates that "over time, the political landscape shifted as the Aleta clan challenged the Yemericho," leading to an alliance, while the Hadicho and Hoffa "remained excluded" from this purity-based hierarchy system.

According to the article, several political parties in Sidama, despite their stated goals, continue to uphold this ongoing division in this modern age. The Sidama Liberation Movement ( ), for instance, includes "Wolaphote" (purification) in its name, reflecting “a lingering attachment to exclusionary tribal ideology. The Sidama People's Democratic Organization ( ), formed under the , also "institutionalized division by adopting the divisive ideology." Despite its integration-focused Medemer philosophy, the Prosperity Party has struggled to implement real change, as "local appointments and resource distribution continue to reflect ancestral hierarchies."

The author emphasizes that "the persistence of purification (Wolapho) ideology across Sidama's political spectrum represents more than historical curiosity; it constitutes a fundamental barrier to democratic governance and comprehensive development." For genuine change, he urges political parties to "explicitly reject purification ideology by publicly renouncing tribal hierarchies and establishing internal safeguards against tribal favoritism."

https://addisstandard.com/?p=51589

የሀዘን መግለጫ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ተክሉ፤ በዛሬው ዕለት በ17/11/2017 ዓ.ም በድንገተኛ ሞት ከዚህች ዓለም በሞት  ተለይተዋል።አቶ ሙሉነህ ተ...
24/07/2025

የሀዘን መግለጫ

የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ተክሉ፤ በዛሬው ዕለት በ17/11/2017 ዓ.ም በድንገተኛ ሞት ከዚህች ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ሙሉነህ ተክሉ፤ በሥራቸውና በአካዳሚክ ዕውቀታቸው ወደር የሌላቸው ትጉህ ሰራተኛና አገልጋይ እንደነበሩ የሙያ አጋሮቹና የሥራ ባልደረቦቹ ይናገራሉ።

የህዝብ አገልጋይነትን በመምህርነት የጀመሩት አቶ ሙሉነህ ተክሉ፤ በአለታ ወንዶ መለስኛ ትምህርት ቤት፤ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሠናዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ሆነው እንዲሁም በሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መምህር ሆነው ትውልድን የመቅረፅ አደራ እንደተወጡ ይነገራል።

አቶ ሙሉነህ ተክሉ በአመራርነት ተመድበር በአለታ ጩኮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ለተወሰኑ ጊዜያቶችም እንደሰሩ ይታወቃል።

በዛሬው እለት በድንገተኛ ሞት ከዚህች ዓለም እስከተለዩ ድረስ፤ በሲዳማ ክልል የዞን መዋቅር ከተዘረጋ ጀምሮ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው በከፍተኛ የአመራር ብቃትና አቅም ሲመሩ እንደነበሩ የታሪክ ማህደራቸው ያሳያል።

አሚኮ ለቤተሰብ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናት እንዲሆን ይመኛል።

አፊኒ_ሚዲያና_ኮሙኒኬሽን

ትኩስ እና እውነተኛ መረጃዎችን ለማግኘት ይከታተላሉ
ዩቲዩብ:https://youtube.com/channel/UCzxVCZUtW-XmosukNkCXZEA
telegram:https://t.me/affinimedia

ከዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ማዕረግ የሚመረቁ ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመስተማር  ከፈቀዱ ስልጠና ወስደው መምህር እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ከ2018 ጀምሮ ወደ ስራ...
24/07/2025

ከዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ማዕረግ የሚመረቁ ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመስተማር ከፈቀዱ ስልጠና ወስደው መምህር እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ከ2018 ጀምሮ ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም በሚል ወደ ስራ ይገባል የተባለው አሰራር የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚታየውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ ይረዳል ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር፡፡ይህ የተባለው የክረምት ልዩ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማሻሻያ ስልጠና ለማስጀመር በማሰብ ከ30 ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራን እየተሰጠ ያለው ስልጠና በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ድኤታ አየለች እሸቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተፈጥሮ ሳይንስ መምህራን ስልጠና ያልተካፈሉ መምህራን፣ የማህበራዊ ሳይንስ መምህራን፣ የስራና ተግባር ትምህርት መምህራን በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ ብለዋል፡፡ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው ስልጠና ልምድ አግኝተናል ያሉት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ለ2ኛ ጊዜ የሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ስልጠና መምህራኑ በሚያስተምሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ተዘጋጅተናል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2018 ጀምሮ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚታየው የመምህራን እጥረት ለመቅረፍና ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ በማሰብ አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም አዘጋጅቷል ያሉት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር ‎የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) ናቸው፡፡

በከፍተኛ ነጥብ ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች መምህር የመሆን ፍላጎች ካላቸው ትምህርት ሚኒስቴር የሚያዘጋጀውን ፈተና ካለፉ የሚፈለገው ስልጠና ተሰጥቷቸው በመምህርነት እንዲሰማሩ ይደረጋል ብለዋል፡፡ለዚህ ፕሮግራም ጅማሮ አሁን ላይ 6 ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ሰምተናል፡፡

በዘንድሮው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማሻሻያ ስልጠና 84,000 ሰልጣኞች ይካፈላሉ፡፡ከ30 ዩኒቨርሲቲዎች 630 የሚሆኑ መምህራን ስልጠናውን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡ስልጠናው ሀምሌ 28 ይጀመራል፡፡

Sheger

''በዓሉን ምክንያት በማድረግ ምንም አይነት የአልጋ ዋጋ ጭማሪ አላየንም ''የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ====================፣፣፣፣፣፣፣በዓሉን ምክንያት በማድረ...
24/07/2025

''በዓሉን ምክንያት በማድረግ ምንም አይነት የአልጋ ዋጋ ጭማሪ አላየንም ''የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ
====================፣፣፣፣፣፣፣

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከ400 በላይ አልጋ ቤቶች ላይ ፍተሻ አድርገናል ምንም የዋጋ ጭማሪ አላየንም ሲል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ

ሐዋሳ ከተማ በየአመቱ ለሚከበረው የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ግርማ ሜቲዎስ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሪት የከተማዋ 95 በመቶ በካሜራ ቁጥጥር ስር መሆኑን እና የከተማ ነዋሪም ሆነ ሁሉም የፀጥታ አካላት በአሉ በሰላም ተከብሮ እስኪጠናቀቅ በጋራ እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

የከተማዋን ሰላም መነሻ በማድረግ የቱሪዝም ፍሰቱ እየጨመረ በመምጣቱን ይህንኑ እድል በአግባቡ መጠቀም ይጠበቃል ብለዋል።በበዓሉ ወቅት ለሞባይል ንጥቅያና ለመሳሰሉ ጉዳዮች በተለመደው ጊዜያዊ ችሎት ችግሩ በፍጥነት እንዲፈታ መርማሪ አቃቢ ህግ እና ዳኞች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓልን ሆነ በአዘቦቱ ቀን ለክልልም ሆነ ለከተማዋ ክብርና ገጽታ ህዝቡ የተለመደ የእንግዳ አቀባበል ልምዱን እንዲተገብር መልዕክት ያስተላለፉት ረዳት ኮሚሽነር ግርማ የንግዱ ማህበረሰብ ሆቴሎች፣ አልጋቤቶች፣ ታክሲና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያለምንም የዋጋ ጭማሪ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ውይይት ተደርጋል ብለዋል።

ሆኖም የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ አንዳንድ ተቋማት መኖራቸውን በተለያየ መንገድ እየሰማን ነው ያሉት ረዳት ኮሚሽነር ግርማ ይህንንም ለማጣራት እሮብ ማታ ከ400 በላይ አልጋ ቤቶች ላይ ፍተሻ መደረጉን እና የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ቤቶች አለማግኘቱን አስታውቀዋል።በዚህም የተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ላይ የዋጋ ጭማሪ መኖሩ የሚሰረጩ መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው ተብሏል።የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረበአል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያየአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሀገራችንን ክብር እና ገፅታ ከፍ በሚያደርግ መልኩ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በ...
18/07/2025

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሀገራችንን ክብር እና ገፅታ ከፍ በሚያደርግ መልኩ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀገራችሁን ለማገልገል ለምትፈልጉ በጎ ፈቃደኞች ከእንግዶች አቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው መርሃ ግብር ላይ በጎ ፈቃደኛ የፕሮቶኮል ካዴቶችን አሰልጥኖ ዓመታዊ ስብሰባው እስኪጠናቀቅ ድረስ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ለማሰማራት ይፈልጋል።

የምዝገባ ሊንክ፡ https://forms.gle/34PxUgPV2bgcZCbU9
MFAEthiopia Amharic የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Address

Delhi
1234

Telephone

+251996858227

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Affini Media and Communication-አፊኒ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Affini Media and Communication-አፊኒ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን:

Share