31/01/2026
በጣም አሳዛኝ ሞት!
ትናንት ማታ በቤቴ ተኝቼ ነበር። ቤቴ ከመግባቴ አንድ ሰዓት ገደማ በፊት አንድ ፀባይ ሰናይ የሆነ ጎሮቤቴ (የሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ጤና ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር እንድሪያስ ማርቆስ) ከዩንቨርሲቲው ስብሰባ ሲመለስ በጋራ መኖሪያ ቤታችን ኮርደር ላይ ስንተላለፍ ተገናኝተን ደስ በሚል አኳኋን ሰላምታ ሰጥቶኝ ሰላም ተባብለን ነበር ወደየቤታችን የገባነው።
ከተገናኘን በኋላ ልክ በግምት አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ አከባቢ ልዩነት ባለቤቴ ጋደም ካልኩበት በአስቸኳይ እንድወጣና ወደ እሱ ቤት እንድደርስ አስጠራችኝ። እኔም ግራ እየተጋባው ወደ ባልደረባችን ቤት ደረስኩ። ስደርስ ባለቤቱና አራት ጨቅላ ህጻናቱ በድንጋጠ ያለቅሳሉ። ጩሄቱን ሰምተው ቀድመው የደረሱ ጎሮቤቶችና ባለቤቴ ግራ ተጓብተዋል። ዶክተሩ ተዝለፍልፎ በሶፋው ላይ ፀጥ ብሏል።
በርካታ ጎሮቤቶችም የጩሄት ድምፅ ሰምተው ተጨምረው መጡ። በፍጥነት ተሸክመን ከፎቁ አወረድን፤ መኪናዬን በፍጥነት አዘጋጅቼ በከፍተኛ ፍጥነት አዳሬ ሆስፕታል አደረስን። ዶክተሩ ግን መጀመሪያም የለም፤ሄዷል😥
ዶክተሮች በፍጥነት እርዳታ ለመስጠት ሞከሩ፤ ነገር ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም። መጀመሪያም እንደሞተ ነገሩን😥
አሟሟቱን ከባለቤቱ አንደበት፦
"ምንም አይነት ህመም አልነበረበትም፤ ከዩንቨርሲቲው ስብሰባ ተመልሶ፣ ምግቡን በልቶ፣ ከልጆቹ ጋር ተጫውቶ ፀሎት እያደረጉ እያለ ለትንሽ ደቅቃ ተንቀጠቀጠና በተኛበት ሶፉ ላይ ፀጥ ብሎ ቀረ። በጭንቅላቱና በደረቱ ላይ ውሃ ደፋን; ግን ፀጥ ብሎ ሲቀር ነው የጮህነው" አለችን።
ከሌሊቱ 6 ሰዓት ገደማ የዶክተሩን አስክሬን እንደሚሆን አድርገን ወደ ቤት ስንመለስ ጨቅላ ልጆቹ አባታችን ይመለሳል በሚል እሳቤ በቤታቸው ደጅ ቁጭ ብለው በዝምታ የሚመጣውን ሁሉ ያያሉ😥
በህይወቴ እንዲህ አይነት ሀዘን ተሰምቶኝ አያውቅም😭😭!...ቁጭ ብለው የሚጠባበቁትን ልጀች ፊት ለማየት አቅም አጣን! ከባለቤቴ ጋር ሆኔን በፍጥነት ቤታችን ገብተን አለቀስን። መተኛት አልቻልንም። ምን ብለን እናስገባቸው?😭!?...እንደምንም ደፈር ብዬ፦
"ህክምናው ስለሚቆይ ገብታችሁ ተኙ" ብዬ እንዲገቡና እንዲተኛ አደረኳቸው። ለኛ ግን እስከ ሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት እንቅልፍ አለን...
ሰው ከንቱ!
ፈጣሪ ለቤቴሰቦች ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ
RIP😭
Source Dr Tessema Elias