Gofa Tv

Gofa Tv ይህ የጎፋ ቴሌቪዥን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው። ገፁን ላይክ ፣ ሼርና ኮሜንት በማድረግ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን በየዕለቱ ይከታተሉ!
(1)

27/05/2026

Nu parttey bilxxigina guzhetetha qofan, issotethan, deretetha hashetethaninne gina dichan ubba deretetha go7etetha minthanaw oothishe beettes gishe D/re Baljjige Tasfayey odidosoona.

Hiisa 19/2018 M/

27/05/2026

በጎፋ ዞን በቡልቂ ከተማ የጎፋ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች ማስተዋወቂያ እና የይምረጡን ቅስቀሳ ማጠቃለያ መረሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

27/05/2026

Goofa Zoonen Zaala woradan Meell, Phizgo,Daama,Qorpha,Bato oge projjektte gidida Elssa aasho doomissiya giigisoy dhoqqa kawo oosuwa kaapotti beettida bessan doomettis.
Hiisa 19/2018M/L

27/05/2026

Deretetha baaso oyshota hayzon alissiya zaaro imoy laame kawo qofa gidi D/re Baljjige Tasfayey odidosoona.
Hiisa 19/2018 M/L

ፓርቲያችን በመደመር እሳቤ፣ በአንድነት፣ በህዝብ ተሳትፎ እና በፍትሃዊ ልማት መርሆዎች ተመስርቶ የሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቆራጥነት እየሰራ ይገኛል:-ተስፋዬ በልጅጌ (ዶክተር)ግ...
27/05/2026

ፓርቲያችን በመደመር እሳቤ፣ በአንድነት፣ በህዝብ ተሳትፎ እና በፍትሃዊ ልማት መርሆዎች ተመስርቶ የሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቆራጥነት እየሰራ ይገኛል:-ተስፋዬ በልጅጌ (ዶክተር)

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

በጎፋ ቁጥር አንድ ምርጫ ክልል የተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍና የዕጩ ማስተዋወቂያ መረሃ ግብር የህዝብ አንድነት፣ የለውጥ ተስፋ እና የቀጣይ ብልፅግና ጉዞ የሚያሳይ ደማቅ መድረክ ሆኖ ተካሂዷል።

በኢፌዴሪ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ እንደገለፁት ብልፅግና ፓርቲ በአገራችን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዘርፎች ላይ ያመጣቸው ለውጦች የህዝብን ተስፋ ያጠናከሩ እና የነገዋን ኢትዮጵያ በጠንካራ መሠረት ላይ የሚገነቡ ናቸው ብለዋል።

ቀጥለውም በመሠረተ ልማት፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ እና በወጣቶች ተሳትፎ የተመዘገቡ ስኬቶች የለውጡ ተጨባጭ ማሳያዎች እንደሆኑም አብራርተዋል።

ፓርቲያችን በመደመር እሳቤ፣ በአንድነት፣ በህዝብ ተሳትፎ እና በፍትሃዊ ልማት መርሆዎች ተመስርቶ የሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቆራጥነት እየሰራ የሚገኝ ትልቅ ግዙፍ ፓርቲ ነው ስሉም ተናግረዋል።

የዛሬው የድጋፍ ሰልፍም ህዝባችን ለሰላም፣ ለልማት እና ለቀጣይ ብልፅግና ያለውን ጽኑ አቋም በግልፅ ያሳየበት ነው በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በጎፋ ዞን እየታየ ያለው የልማት እንቅስቃሴ፣ የመሠረተ ልማት መስፋፋት፣ የግብርና ምርታማነት መጨመር እና የወጣቶችና የሴቶች ተሳትፎ መጠናከር የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ፓርቲ መሆኑን በተግባር ያረጋግጣል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በም/ር/መስተዳድር ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የሚያጋጥማትን ችግር በጥበብና በመደመር በመሻገር ኢትዮጵያን ካደጉት ሀገራትም ጋር እኩል ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ያለው ብልፅግና ፓርቲ ነው በማለት ገልፀዋል።

‎የብልፅግና ፓርቲ ሁሉም የማህበረሰቦች እኩል ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥና ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የምንሻገርበት ድልድይ ላይ በመሆናችን የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ አድርገናል በማለት ተናግረዋል።

‎ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ኋላ ቀርነትና ድህነት ተቀርፎ የበለፀገች ኢትዮጵያን በመገንባት ከሌሎች ሀገራት ጋር እኩል ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

ብልፅግና ፓርቲ በስራና በህብረት መኖርን የሚያሳይ አንድነትን ያስመሰከርን ህዝቦች በመሆናችሁ የፓርቲው እውነተኛ ደጋፊ ናችሁ በማለት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ገልፀዋል።

‎የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ፓርቲ መሆኑን ያሳያችሁ ፓርቲው በሀገር ደረጃ የሚገጥሙ ችግሮችን በመደመር ያሳለፋችሁና የትውልድ አሻራን የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል የስንዴ ነዶን በመምረጥ ብልፅግናን ምረጡ ብለዋል።

‎ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር ትልቁ መንገድ መደመር ሲሆን የህዝባችን መተባበርና አንድነት ትልቁ የብልፅግና መዳረሻችን ነው በማለት ተናግረዋል።

በኢፌዴሪ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ በተገኙበት የጎፋ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና ዕጩ ማስተዋወቂያ ...
27/05/2026

በኢፌዴሪ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ በተገኙበት የጎፋ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና ዕጩ ማስተዋወቂያ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

በጎፋ ዞን በቡልቂ ከተማ የጎፋ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች ማስተዋወቂያ እና የይምረጡን ቅስቀሳ ማጠቃለያ መረሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ቃል የ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ ዕጩ ማስተዋወቂያ በከተማ አስተዳደሩ እና በወረዳው በጋራ ቅንጅት የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ የሚገኘው።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ አባላት እና ደጋፊዎች ባለፉት የለውጥ ዓመታት በብልፅግና ፓርቲ መሪነት የተመዘገቡ ድሎችን የሚያወሱ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ለመላው ሙስሊም እምነት ተከታዮች ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉግንቦት 18/2018 ...
26/05/2026

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ለመላው ሙስሊም እምነት ተከታዮች ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1447ኛው ለኢድ አል አድሃ (አረፋ )በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው አረፋ በዓል የመቻቻል፣ የእምነት ጽናት፣ የሰላም እና የአብሮነት እሴቶችን የሚያጎለብት ከፍተኛ መንፈሳዊ ትርጉም ያለው ታላቅ በዓል ነው።

ይህ የከበረ በዓል የመተሳሰብን፣ የመረዳዳትን፣ ለወገን ደራሽ የመሆንን እና የሰላም እሴቶችን በማጠናከር ማህበራዊ አንድነታችንን የበለጠ የሚያጠናክር ነው።

በዚህ የበዓል ወቅት አቅመ ደካሞችን፣ ወላጅ አጥ ህጻናትን፣ አረጋውያንን እና ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን በመርዳት የበዓሉን እውነተኛ መንፈስ እንድናንጸባርቅ በማለት ገልፀዋል።

የአረፋ በዓል የፍቅር፣ የይቅርታ እና የሰላም በዓል በመሆኑ ሁሉም ዜጎች ከጥላቻና ከክፍፍል ርቀው በአንድነት እና በመከባበር እንዲኖሩ አሳስባለሁ።

በሀገራችን የምትፈልገው ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና አንድነት በሁሉም ዜጎች ትብብርና በጋራ ጥረት የሚረጋገጥ በመሆኑ የበዓሉን የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶች አጠናክረን ለተሻለ ሀገር እንድንሰራ ጥሪ እናቀርባለን።

በዓሉ ለመላው የሀገራችን ህዝብ ሰላም፣ ለቤተሰቦች ፍቅርና ደስታ፣ ለወጣቶች ተስፋ፣ ለሀገራችን ደግሞ የተሻለ እድገትና ብልጽግና ይዞ እንዲመጣ ከልብ እንመኛለን።

በጎፋ ዞን በኦይዳ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡን ቅስቀሳ ማጠቃለያ ኮንፍራንስ እና የድጋፍ ሰልፍ  ተካሄደ ።ግንቦት 18/2018 ዓ.ምየክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች...
26/05/2026

በጎፋ ዞን በኦይዳ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡን ቅስቀሳ ማጠቃለያ ኮንፍራንስ እና የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ ።

ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ከሁሉም ቀበሌ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች በተገኙበት በጎፋ ዞን በኦይዳ ወረዳ በሸፊቴ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃላያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር ቱርቃቶ ቱርቶ የይምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ኮንፍራንስ እና የድጋፍ ሰልፍ መርሃ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን በጽናት ያቆመ በመደመር መንገድ የተነሳ መዳረሻው የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማውረስ ነው በማለት ሀገራችንን የአፍሪካ ብልፅግና ተምሳሌት የማደረግ ራዕይ ዕውን ለማድረግ፤ እንዲሁም ኢትዮጵያን ወደከፍታ ለማድረስ የተጀመሩ ስራዎች ከዳር ለማድረስ ይሠራል ብሏል።

አክለዉ ህብረ ብሔራዊነትን በማጠናከር ከወንድም ህዝቦች ጋር በማተሳሰር የህዝቡን የመልማት ፍላጎት ጥያቄ ለመመለስ እየሠራ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ለሌሎች ሀገራት የማድረስ እየሠራ የሚገኝ ፓርቲም ነዉ ያሉት ዶ/ር ቱርቃቶ።

የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቦረና ቦላዶ በመድረኩ ፓርቲያችን ብልጽግና የለውጥ ፓርቲ አቃፊና አካታች ነው በማለት ህዝቡ በዛሬው ላሳያዉ የብልጽግና ፓርቲ ውግንነት ልመሰገን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኦይዳ ህዝብ ታታሪ፣እንግዳ አክባሪ፣ታዛዥ ህዝብ መሆኑን በዛሬው ድጋፍ ስልፍ አሳይቶናል፣ ብልጽግናን መምረጥ፣በሠላም፣በልማት ፣በሁሉም ዘርፎች የአፍርካ ተምሳሌት ለማድረግ ከመንግሥት ጎን መሆናቸዉን መስክረዋል።

የኦይዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ታዘቤ ጋትሦ በበኩላቸው ፓርቲያችን ብልፅግና በወንድማማችነትና በእህታማማችነት መርህ ኢትዮጵያን በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት ለሚደረገው ጉዞ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን በትጋት አየሠራ ይገኛል ብሏል።

7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ ነፃ የመራጩን ህዝብ ቅቡልነት እንዲያገኝና ለዲሞክራሲዊ ስርዓት ግንባታ ወሳኝ ሚና ስኖረዉ ዜጎች ህገ መንግስታዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙም ሰፊ እድል ይፈጥራል ነዉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ።

የኦይዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ምትኩ መዳቤ ብልፅግናን መምረጥ ኅብረ ብሔራዊነትና አንድነትን ማጽናት ፤ ሀገርን ካልተቋጨና ካልተግባባ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ችግር ዉስጥ በማዉጣትና ከግጭት እና ጦርነት አዙሪት በማላቀቅ የጸና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓትን ለመገንባት አሻራን ማሳረፍ እንዲሁም የኋላ ቀርነት እና የድህነት ታሪክን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቋጨትም ነዉ ብሏል ፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ላይ የጎፋ ዞን የክልል፣የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የኦይዳ ልዩ ምርጫ ክልል የፌዴራልና የክልል ዕጩ ተወካዮች ፣የአካባቢው ነዋሪዎችና የፓርቲው ደጋፊዎች ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የልማትና የዴሞክራሲ ስኬቶችን በመዘከር ግንቦት 24 ለሚካሄደው ምርጫ ለብልፅግና ያላቸውን ጽኑ አጋርነት አረጋግጧል።

‎በመሎ ጋዳ ወረዳ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሄደ።‎‎ግንቦት 18/2018 ዓ/ም ‎‎በጎፋ...
26/05/2026

‎በመሎ ጋዳ ወረዳ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሄደ።

‎ግንቦት 18/2018 ዓ/ም

‎በጎፋ ዞን የመሎ ጋዳ ወረዳ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

‎በመርሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚዲያና ህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ኃላፊ እና የመሎ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የክልል ዕጩ ተወካይ ክቡር አቶ ማሩፋ መኩሪያ እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ተኮር ፓርቲ በመሆኑ ህዝቦችን በማዳመጥ ጥያቄዎቻቸዉን ምላሽ በመስጠት የህዝቡ የልማት ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ አየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

‎ከህዝቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረው በወረዳው ህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ምላሽ ለመስጠት እንቀሳቀሳለን ብሏል።

‎የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የመሎ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የክልል ዕጩ ተወካይ ክቡር አቶ ምናሴ ኤልያስ በበኩላቸው ሀገራዊ ትላልቅ የልማት፣ የትብብርና የዲፕሎማሲ ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸዉ፣ ሀገራችንን ካለመችበት የብልጽግና ከፍታ እንድትደርስ መላዉ ህዝብ ድምጽ እንዲሰጥም ጥሪ አድረገው የምርጫ ምልክታችን የሆነውን የስንዴ ነዶ ይምረጡ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎ብልጽግና ፓርቲ ከልማት እቅዶችንና ጅምሮች ባሻገር የሀገራችን ስብራቶች ሊጠግኑ የሚችሉ ተቀባይነት ያላቸዉን ፍትሃዊ አጀንዳዎችን በመያዝ በከፍተኛ ትጋት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግሯል።

‎የመሎ ጋዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዮሴፍ ብርሃኑ እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ እያከናወነ ባለው የሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ የተለያዩ ስኬቶችና በየአካባቢው ተጨባጭ ውጤቶች እንዳሉ በማስረዳት፣ ብልጽግናን መምረጥ የመርሃ-ግብር ጉዳይ ሳይሆን የተጀመሩ ልማቶችን የማስቀጠልና የሀገር አንድነት ማጽናት እንደሆነ ተናግረዋል።

‎የመሎ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የፈደራል ተወካይ ክቡር ኢንጂነር ካሳሁን ሰለሞን ብልጽግና ፓርቲ ከተመሠረተ ጥቂት አመታት ያስቆጠረ ቢሆንም መንግስት የመመስረት እድል ካገኘ ጀምሮ በህዝቦች ዘንድ ሁለንተናዊ ውጤቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልፀው ይህ የምርጫ ማጠቃለያ ሳይሆን የልማት ማብሰሪያ ነው ብሏል።

‎ከህዝቡ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ሰፊ መሆናቸውን አንስተው በቅርቡ ምላሽ እንደሚያገኝ አክለዋል።

‎የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የመሎ ጋዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ አቶ አሰግድ አለማየሁ​ ብልጽግና ፓርቲ ጀምሮ ያጠናቀቃቸዉ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በማከናወን የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ የሚገኝ ህዝብ ተኮር ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል።

‎በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ፓርቲው ባለፉት ዓመታት በሰላም፣ በልማትና በዴሞክራሲ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በማንሳት ለተወዳዳሪዎቹ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

የህብረተሰቡን መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማዳመጥና ከልብ ተረድቶ አጥጋቢ ምላሽ መስጠት የለውጡ መንግስት ዕሳቤ ነው:-ተስፋዬ በልጅጌ (ዶክተር)ግንቦት 18/2018 ዓ.ምበጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ...
26/05/2026

የህብረተሰቡን መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማዳመጥና ከልብ ተረድቶ አጥጋቢ ምላሽ መስጠት የለውጡ መንግስት ዕሳቤ ነው:-ተስፋዬ በልጅጌ (ዶክተር)

ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በበድሮ ኤላ ቀበሌ ከህብረተሰቡ ጋር በልማት እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

በዛሬው ዕለት በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ በበድሮ ኤላ ከተማ ከህዝቡ ጋር በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ያደረጉት ውይይት የለውጡ መንግስት ከህዝብ ጋር በቅርበት የመስራት እና የህዝብ ድምፅን የመስማት ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ተግባራዊ እርምጃ ነው ።

ህዝብን በማዳመጥ፣ ችግሮችን በጋራ በመለየት እና መፍትሔዎችን በተባበረ መንገድ በመቅረጽ ዘላቂ ልማትና መልካም አስተዳደር ማረጋገጥ ይቻላል ስሉ በኢፌድሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ ተናገሩ።

የለውጡ እሳቤ መሠረቱ ህዝብን ማዕከል ያደረገ አስተዳደር፣ ፍትሃዊ አገልግሎት፣ ፈጣን ልማት እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ሲሆን ዛሬ በበድሮ ኤላ የተካሄደው ውይይትም የዚህ አስተሳሰብ እውነተኛ መገለጫ ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ እንደገለፁት ፓርቲያችን ብልፅግና ሰው ተኮር እና ተቀራርቦ በመስራት የአካባቢያችን ልማት በተጠናከረ መንገድ የሚያስቀጥል ፓርቲ በመሆኑ ህዝባችን ለዚህ ፓርቲ አጋር በመሆን አብሮ እንዲሰራ አሳስበዋል።

‎ፓርቲያችን ብልፅግና ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ አሻጋሪ ራዕይዎችን በመሰነድ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ለውጥ እያመጣ ያለውን ፓርቲ እንምረጥ ብለዋል።

የጎፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁን ደምሴ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ በጥቂት አመታት ዘርፈ ብዙ ልማቶችን በሀገር ደረጃ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በዚህ በበድሮ ኤላ ማዘጋጃ ከተማ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ወደ ልማት ተገብቷል ብለዋል።

‎አቶ ይሁን አያይዘው የበድሮ ኤላ ህዝብ በየጊዜው የሚጠይቀውን ጥያቄ እንደ መንግስት እየመለስን በመሆኑ ህዝባችንም 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን ብልፅግና ፓርቲን በመምረጥ የተጀመሩ ልማቶችን ማስቀጠል ይኖርበታል ስሉም አሳስበዋል።

‎የገዜ ጎፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ብርሃኑ በበድሮ ኤላ ማዘጋጃ ከተማ ዛሬ የተገኘነው የህዝባችን መሠረታዊ ጥያቄ የሆነውን የመንገድ ጥገና ስራ በአፋጣኝ እየተሰራ እንዳለና እንዲሁም የመብራት ጥያቄ አጥኝ ቡድን ተልኮ ጥናት አጠናቆ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር ይገባል ብለዋል።

‎በለውጥ መንግስት እሳቤዎች መሪነት ባለፉት ዓመታት የተገኙ ድሎችን ተከታታይነት ባለው መንገድ በህዝብ ግንኙነት ስራዎች ማስተዋወቅና ለህዝብ ግልፅነት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልጿል ።

በጎፋ ዞን በመሎ ጋዳ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር በድምቀት እየተካሄደ ነው።ግንቦት 18/2018 ዓ/ምበጎፋ ዞን በመሎ ጋዳ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ...
26/05/2026

በጎፋ ዞን በመሎ ጋዳ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር በድምቀት እየተካሄደ ነው።

ግንቦት 18/2018 ዓ/ም

በጎፋ ዞን በመሎ ጋዳ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እና ማጠቃለያ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር በዎምባ ከተማ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል ።

በድጋፍ ሰልፉ የመሎ ምርጫ ክልል የፌዴራል፣የክልል ምክር ቤት እጩዎች፣ የክልል፣የዞን፣የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ሀገር ሽማግሌዎች፣የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

Address

Gofa
Monrovia
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofa Tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share