11/07/2025
ዶክተር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ "በተሻለ ክብርና ከፍታ አፍሪካን የማገልገል ዕድል አገኘሁ"ሲሉ ተናገሩ።
የቀድሞው የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አፍሪካን በይበልጥም ሀገራቸውን "በተሻለ ክብርና ከፍታ የማገልገል ዕድል" ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ዶክተር ጴጥሮስ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ "ከተመኩ አይቀር በእግዚአብሔር ነው" ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ባህር ማዶ የሚገኙት የቀድሞ ፕሬዝዳንቱ በቅርብ ቀን ወደ ሃገራቸው እንደሚመለሱ የጠቀሱ ሲሆን ያገኙት "ዕድል" ምን እንደሆነ በቅርቡ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሙሉ ፅሁፋቸው እንዲህ ቀርቧል፦
"ውድ ወገኖቼ!
በቅንነት ያገለገልኩት አምላኬ አሁን ተዓምር ሰርቶልኛል። ማንም፣ ምንም በማይቀለብሰው መልኩ፣
ልያስብ እንኳ በማይችለው መልኩ ተደርጎልኛል።
ከተመኩ አይቀር መመካት በእግዚአብሔር ብቻ ነው።
ትላንት ከአፈር ያነሳኋቸው፣ ዛሬ ጀርባቸውን ስሰጡኝ፣ ጓደኞቼ ናቸው ያልኳቸው ስልኬን መመለስ ፈርተውና አፍረው ስዘጉብኝ......
እግዚአብሔር ግን ደረቱን ሰጠኝ፣ ተዋጋልኝ፣ አሸናፊም አደረገኝ።
በአደባባይ የማመሰግነው ወድጄ አይደለም ! በውለታው ተገድጄ ነው።
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሀገሬ እመለሳለሁ።
በተሻለ ክብርና ከፍታ አፍሪካን፣ በተለይም ሀገሬን የማገለግልበትን በር ዛሬ እግዚአብሔር ከፍቶልኛል።
ክብር ለልጅነቴ አምላክ! እሰግድለታለሁ።
አመልከዋለሁ።
አገለግለዋለሁ።
እነሆ ነገሩ ተገለበጠ።"
ዶች