Doch Infotainment

Doch Infotainment Welcome to Doch Tube, where entertainment meets information! Follow us on YouTube, TikTok, Facebook, and Telegram for engaging and insightful content.

27/05/2025

ከዛሬው እለት እንጀምራለን

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች ከዛሬው እለት ጀምሮ ማቅረብ የምንጀምር ይሆናል።

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በሚባል ደረጃ ከህዝብ የሚነሱና በመንግሥታዊ ተቋማቱና መዋቅሮች የሚሸፋፈኑ ጉዳዮች ላይ እናተኩራለን።

ማንኛውም ሰው ጥቆማና መረጃ ሲኖረው በቴሌግራም Bot አድራሻችን t.me/southwestmedianetworkbot መላክና አብሮን በትብብር መሥራት ይችላል።

መረጃ ሳይዛነፍ አደባባይ ላይ ይሰጣል!
አብራችሁን ቆዩ!

Hawassa❤
31/01/2025

Hawassa❤

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!
06/01/2025

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!

ለምለሟ ምድር አዲሲቱ የተስፋ አድማስእንኳን አደረሰሽ!Doch Infotainment Say 'No' to RACISM
06/01/2025

ለምለሟ ምድር አዲሲቱ የተስፋ አድማስ
እንኳን አደረሰሽ!

Doch Infotainment
Say 'No' to RACISM

የቀጠናው ግዙፍ የኢኮኖሚ ማዕከል ሚዛን አማን የቀጠናው ግዙፍ ከተማ ነች። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ። በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ምን አልባትም በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ...
05/01/2025

የቀጠናው ግዙፍ የኢኮኖሚ ማዕከል

ሚዛን አማን የቀጠናው ግዙፍ ከተማ ነች። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ። በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ምን አልባትም በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በክልሉ ተወዳዳሪ ከተማ ላይኖራት ወደ ሌላኛው ከፍታ ሊተኩሳት ይችላል።

በአሁኑ ወቅትም ቢሆን የክልሉ የኢኮኖሚ ማዕከል ነች። በነቀኑ በከተማዋ የሚወጡ አዳዲስ ቢዝነሶች፣ የሚበቅሉ ፎቆችና በመንግሥት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች እንዲሁም ህብረብሔራዊ ውቅሯ ያመጣላት ጠንካራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የከተማዋ ልማት ከሚታየውም በላይ ከፍ እንዲል ያስቻለም የሚያችልም ነው።

በየጊዜው ለከተማ አስተዳደሩ የሚቀርቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ከተማዋ ለኢንቬስትመንት ምን ያህል ምቹ ነች ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጥና ነገዋን አመላካች ነውና ይህንኑ መቀላቀል ብልጠት ነው።

ከሰሞኑ የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ለማስተናገድ ሽር ጉድ የምትል ከተማዋ የመኪናና የሰው እንቅስቃሴ ከነበራት ድምቀት ደረጃውን ከፍ ያደረገው ይመስላል። የገናውም ዋዜማ አድምቋታል።

በየጊዜው ዶች የክልሉን አከባቢዎች ይቃኛል!

ዶች!

ሳያስገድድህ ጠብመንጃ ሳይደቅን ራስህን አስትቶ የራሱ ያደርግሃል- የቤንች ህዝብ በህይወት ዘመኔ እጅግ ከምደሰትበት "እሰይ" ከምልበት ነገር አንዱ እጅግ ከምወደውና ከማከብረው የቤንች ህዝብ ...
04/01/2025

ሳያስገድድህ ጠብመንጃ ሳይደቅን ራስህን አስትቶ የራሱ ያደርግሃል- የቤንች ህዝብ

በህይወት ዘመኔ እጅግ ከምደሰትበት "እሰይ" ከምልበት ነገር አንዱ እጅግ ከምወደውና ከማከብረው የቤንች ህዝብ መካከል እንድወለድ ፈጣሪ መፍቀዱ ነው።

ብዙ ስለ ህዝብ መናገር አስብና ቃላት አቅም የሚኖራቸው አይመስለኝም። በእርግጥም ቃላት አቅመቢስነታቸውን ያረጋገጥኩትም በዚሁ ለህዝቡ ያለኝን ፍቅር መግለጥ ሲሳናቸው ነው።

ቤንች "ማን ነህ" አይልህም። "ጎሳህ ከማን ነው ነገድህስ ከየት ነው" ብሎ ጊዜ አያጠፋም። ሰውነትህ በቂው ነውና አብሮህ ሰው ሆኖ ሰውነትህን ተቀብሎና ወዶህ ይኖራል። ይህ ሰዎች የነገሩኝ አልያም ያነበብኩት አይደለም። የተቀበልኩትና ዘመኔን ሙሉ የኖርኩት እንጂ።

ህዝቡ ጠብመንጃ ሳይደቅንብህ ፤ ሳያስገድድህም በፍቅሩ ረቶህ "እኔነት" የምትለቅን አንተነት አስክዶህ "እሱነት" ያልከውን የራሱን ማንነት አላብሶ ራስህን አስክዶ እሱነቱን እንድትኖር ያደርግሃል። ሳይሰብክህ "እንዲህ ነኝ" ሳይልህ ይህቁንስ ኖሮ አሳይቶህ "እንዲህ ነው" ብለህ እንድታፈቅረውና በፍቅሩም ታስረህ እንድትኖር ያደርግሃል።

እንዳልኳችሁ ቃላት አቅመቢስ ናቸው። እኔም እንጃ የቃላት አቅሜን። እናም እኔ ስለምወደው ትልቅ ህዝብ በፅሁፍ ሳይሆን በቪዲዮ መጥቼ እናወጋለን። ጠብቁኝ።

ዶች ነኝ!

ዲጋም ይስቲ ቢስት ባሬሽን አታዴ!?

Address

Скопје

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Doch Infotainment posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category