
30/09/2025
የደም ማነስ (Anemia) መንስኤ: ምልክቶች እና መፍትሔዎች
✅ በርካቶች ከደም ማነስ ይልቅ ስለ ደም ግፊት እና ደም ብዛት ማውራት ይቀናቸዋል። ይሁን እንጅ ደም ማነስም ከደም ብዛት ያልተናነስ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል። አንዳንድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ ተቀምጠው ቆይተው ሲነሱ አልያም ተመግበው ከመቀመጫዎ ሲነሱና ረዘም ላለ ጊዜ ሲቆሙ የማዞር አጋጣሚ ይከሰታል። መሰል አጋጣሚዎች ደግሞ ከደም ማነስ ጋር የተያያዙ ሊሆኑ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሰዎች ለደም ግፊት የሚሰጡትን ትኩረት ያክል ለደም ማነስም ሊሰጡ እንደሚገባም ይመክራሉ።
✅ የደም ማነስ በሽታ የሚከሰተው በሰውነታችን ውስጥ በቂ የቀይ ደም ህዋሳት ወይም ሄሞግሎቢን በማይኖርበት ጊዜ ነው ።
የደም ማነስ የምንለው በወንዶች ሄሞግሎቢን መጠን ከ13.5gram/100ml በታች ሲሆን በሴቶች ደግሞ ከ12gram/100ml በታች ሲሆን ነው።
✅ ቀይ የደም ህዋሳት ኦክስጅንን ከሳንባ ወደ ሰውነታችን ክፍሎች ያጓጉዛሉ። ሰለዚህ የቀይ ደም ህዋሳት እጥረት ወደ ሰውነታችን ህዋሳት በቂ ኦክስጅን እንዳይደርስ ምክንያት ይሆናል።
✅ ደም ማነስ በቀይ የደም ህዋስ መጠን መሠረት በሦስት ይከፈላል እነርሱም ፦
➡1-የቀይ ደም ህዋስ መጠን ከተለመደው በታች ሲሆን የሚከሰት ነው መንስኤውም የአይረን እጥረት ወይም በዘር ምክንያት ሊሆን ይችላል።
➡ 2 -የቀይ ደም ህዋስ በመጠን የተለመደውን ያክል ሆኖ በቁጥር ሲያስ ነው መንስኤው ከዘላቂ በሽታዎች ጋር የተያያዘ የደም መፍሰስ ወይም የኩላሊት ሕመም ነው።
➡ 3 -የቀይ ደም ህዋስ ከተለመደው በላይ ሲሆን ነው መንስኤው ደግሞ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት እና የአልኮል መጠጥ ነው።
✅ የደም ማነስ መንስኤዎች የቀይ የደም ህዋሳት በአግባቡ አለመመረት እና ከፍተኛ የደም መፍሰስ ናቸው ።
✅ የደም ማነስ ምልክቶች፦
➡- ድካም እና የአቅም ማነስ
➡- ፈጣን የልብ ምት በተለይ እንቅስቃሴ በምናረግበት ጊዜ
➡- የአየር እጥረት እና እራስ ምታት በተለይ እንቅስቃሴ በምናረግበት ጊዜ
➡ - የትኩረት ማነስ
➡ - የቆዳ መገርጣት
➡ - የእግር መሸማቀቅ እና
➡- የእንቅልፍ እጦት ናቸዉ ።
✅የ ደም ማነስ መፍትሔዎች እንደ መነሻ ምክንያታቸው ይወሰናሉ እነርሱም፦
➡ 1-በአይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
➡ 2-የደም ፍሰት የሚያስከትሉ እንደ የጨጓራ ቁስለት ያሉ በሽታዎች በአግባቡ መታከም
➡ 3-በ የቫይታሚን ቢ12 የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
➡ 4-የአልኮል እና ሱስ አስያዥ መጠጦችን መቀነስ እና
➡ 5-የሕክምና ክትትል ማድረግ ናቸዉ።
#ደምማነስ
Bete Amhara Media ቤተ አምሐራ ሚድያ /BAM