Tocha Primary Hospital

Tocha Primary Hospital This is official telegram page of Tocha primary hospital which is located @ SWEPRS Dawuro Zone Tocha Woreda.

 #የቶጫ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የወርሃ መጋቢት  CASH Campaign በፎቶ!  # Great respect for all our staffs !
18/03/2023

#የቶጫ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የወርሃ መጋቢት CASH Campaign በፎቶ!
# Great respect for all our staffs !

Medications with near expire date @ Tocha primary hospital. Any health institutions that  have  shortage of the listed d...
01/01/2023

Medications with near expire date @ Tocha primary hospital. Any health institutions that have shortage of the listed drugs, it is possible to share.

21/12/2022
 #ዛሬ በወርሃ ታህሳስ የመጀመሪያ ዓርብ በየወሩ ወር በገባ በመጀመሪያው ዓርብ የሚካሄደውን የጽዳት ዘመቻ በሚደንቅ አንድነት አካሂደናል ። ከሙያ ግዴታችው በተጨማሪ ሆስፒታሉን ጽዱና ማራኪ ለ...
16/12/2022

#ዛሬ በወርሃ ታህሳስ የመጀመሪያ ዓርብ በየወሩ ወር በገባ በመጀመሪያው ዓርብ የሚካሄደውን የጽዳት ዘመቻ በሚደንቅ አንድነት አካሂደናል ። ከሙያ ግዴታችው በተጨማሪ ሆስፒታሉን ጽዱና ማራኪ ለታካሚዎች ሚቹ ለማድረግ ዝቅ ብላችሁ ለምታገለግሉ የጤና ባለሙያዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች ትልቅ ክብር አለን!!!

Today (06/04/2015 E.C) We conducted 2015 1st round governing board meeting of Tocha primary hospital. All the board memb...
15/12/2022

Today (06/04/2015 E.C) We conducted 2015 1st round governing board meeting of Tocha primary hospital. All the board members including ( i.e the chairman of the board Dawuro Zone chief adminstrator H.E Desta Demissie (Phd Fellow), Dawuro zone Health Department head H.E Mr. Wosen Chemesse , Tocha woreda Chief admin and Vice chairman of the board H.E Mr Tadele Taye) are presented on the meeting. Decisions were made on Various ajendas and hospital reform activities..

በሀሰተኛ የሕክምና ት/ት ማስረጃ ተቀጥሮ የኹለት ሰዎች ህይወት ለሞት የዳረገው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በ5 ሺሕ ብር ተቀጣ======= #=======ቅዳሜ ኀዳር 17 ቀን 2015 (...
26/11/2022

በሀሰተኛ የሕክምና ት/ት ማስረጃ ተቀጥሮ የኹለት ሰዎች ህይወት ለሞት የዳረገው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በ5 ሺሕ ብር ተቀጣ
======= #=======

ቅዳሜ ኀዳር 17 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የጃዊ ሆስፒታል ቅጥር ሰራተኛ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው የሀሰት ዶ/ር ጌትነት ወንድ አወቅ የተባለው ተከሳሽ በድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ሳይማር በሜዲስን የዶክትሬት ዲግሪ እንደተማረ በማስመሰል በሀሰት በተዘጋጀ የዶክትሬት ሰርቲፊኬት የትምህርት ማስረጃ አቅርቧል።

በአብክመ ጤና ቢሮ ከ4/2/2014-4/2/2019 የሚያገለግል የሚል የሀሰት የሙያ ፈቃድ በመያዝ በአብክመ ጤና ቢሮ ሥር ባሉት ሆስፒታሎች በማችንግ ፈንድ ኘሮግራም በ(Junior General Medical practitioner) የቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድሮ 50% በማምጣት በደረጃ 14 ብር 9056 እየተከፈለው ሲሰራም እንደነበር ተገልጿል።

በህክምና የእውቀት ችግር ምክንያት በተፈጠረ ስህተት ሟች የተመኝ አምላክ የተባለችውን የ7 ወር ህፃን እና ሟች የኔወርቅ ደሳለው የተባለችውን የ25 ዓመት ወጣት ለሞት የዳረገ መሆኑምን ተመላክቷል።

በፈፀመው የሙስና ወንጀል መንግሥታዊ ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሀሰት መለወጥ ወይም በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ሙስና ወንጀል በዐ/ህግ ክስ ቀርቦበት በቀን 15/3/2015 ባስቻለው ዳንግላ ተዘዋዋሪ ችሎት በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 5,000 መቀጣቱን ከአዊ ብሔረሰብ ዞን ፍትሕ መምሪያ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Via Addis Maleda

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች___________የጤና ሚኒስቴር በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ጤና መኮንን፣ ሚድዋይፈሪ፣ ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስ...
24/11/2022

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች
___________

የጤና ሚኒስቴር በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ጤና መኮንን፣ ሚድዋይፈሪ፣ ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን፣ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ፣ ሳይካትሪ ነርሲንግ፣ ኢመርጀንሲ & ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ፣ ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ እና ፔዲያትሪክ ነርሲንግ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና ከህዳር 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ የonline ምዝገባ እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል። ሆኖም ከተመዛኞች የትምህርት ማስረጃ ማጣራት (Authentication) ጋር በተያያዘ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች የተፈጠረውን ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት የonline ምዝገባው እስከ ህዳር 23/2015 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፣ ተመዛኞች በተጠቀሱት ቀናት ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275936/ 0118275337 መደወል ይቻላል፡፡

የእናቶች ሞት ቅኝት ኮሚቴዎች ውሎ እና ውሳኔ********************************** #በቀን 07/03/2015 ዓ.ም ከጧቱ 2:00 አከባቢ በቶጫ ወረዳ  #ሸንዳ  ቀበሌ  #ያር...
24/11/2022

የእናቶች ሞት ቅኝት ኮሚቴዎች ውሎ እና ውሳኔ
**********************************
#በቀን 07/03/2015 ዓ.ም ከጧቱ 2:00 አከባቢ በቶጫ ወረዳ #ሸንዳ ቀበሌ #ያርዳ መንደር በቤት ውስጥ በመውለድ አንዲት እናት በወሊድ ምክንያት ህይወቷ አልፏል።
#በዚህም መነሻ የቶጫ መ/ደ/ሆስፒታል የእናቶች ሞት ቅኝት ኮሚቴ በቀን 14/03/2015 ዓም በቦታው በመገኘት ሁኔታውን ለማጣራት ሙከራ አድርጓል።
#የ20 ዓመት እናት ወ/ሮ #ማርታ ኡሼኖ በሸንዳ ቀበሌ ያርዳ መንደር ከሌሊቱ 8:30 አከባቢ ቤት ከወለደች በኋላ በደም መፍሰስ ችግር ከጧቱ 2:00 አከባቢ ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል ይላሉ ባለቤቷ አቶ #ታዬ ከበደ ። ወላዷ ነዋሪነቷ በታርጫ ከተማ በመሆኑ ህይወቷ ከማለፉ ጥቅት ቀናት በፊት ለወሊድ ወደ ባለቤቷ ቤተሰቦች የመጣች ሲሆን የወላዷን መምጣት በቀበሌ ለሚገኙ ባለሙያዎች አለማሳወቃቸውን ይገልፃሉ።

#የሞቷ መንስኤ ከወሊድ በኋላ በተከሰተው ደም መፍሰስ ሲሆን ይህም የእንግዴ ልጅ ሳይወጣ በመቅረቱ ነው። i.e PPH 2 to Retained placenta.
#ለሞቷ አጋዥ የሆኑ ነገሮች:-
***************
✔ወሊዱ ቤት ውስጥ መሆን
✔የእርግዝና ክትትል አለማድረግ
✔የክህሎት ችግር
✔መንገድ ችግር
✔ለወሊድ ዝግጅት አለማድረግ
✔አቅራቢያ ላይ ጤና ተቋም ያለመኖር

የኮሚቴዎች ውሳኔ
**********
#የእናቶች ሞትን ዜሮ ለማድረግ/ለመቀነስ
👉አሁን የተጀመረውን የሴቶች ልማት ቡድን መልሶ ማደራጀት ንቅናቄን በማጠናከር የመውለጃ ጊዜ የተቃረበ ሁሉም እናቶች ወደ ሆስፒታሉ እናቶች ማቆያ እንዲመጡ ማድረግ
👉ከሌላ ቦታ የሚመጡትን ነፍሰ ጡር እናቶች በአስቸኳይ በልማት ቡድን መሪዎች በኩል በቀበሌ ላሉ ባለሙያዎች ማሳወቅ
👉በወረዳው ያለውን ከፍተኛ የመንገድ ችግር ለመቅረፍ የወረዳ መንግስት የጀመረውን የመንገድ ስራ ንቅናቄን በመደገፍ የአምቡላንስ መግቢያ በሁሉም ቀበሌ እንዲሰራ ማድረግ
👉ባህላዊ አምቡላንስ (ቃሬዛ) ከጣውላ ወይም ከቆዳ ሰርተው በየልማት ቡድናቸው እንዲያስቀምጡ፣
👉ጤና ትምህርት አሰጣጥን ማጠናከር
👉በጤና ኬላዎች መሠረታዊ የሆኑ ግብዓቶች(N/S,oxytocin,fridge) እንዲሟሉ ማድረግ፣
👉ሪፌራልን ወቅታዊ ማድረግ
👉የባለሙያ ድጋፍን ማጠናከር

#በመጨረሻም የተወለደው ህፃን ወደ ወላጅ እናቱ ቤተሰቦች አከባቢ ተወስዶ #በገሳ Village of Hope የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል በጥሩ ጤንነት እንደሚገኝ ተገልጾልናል።
ግልባጭ
ለዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ
ለዳውሮ ዞን ሴ/ወ/ህ/መምሪያ
ታርጫ
ለቶጫ ወረዳ ዋና አስ/ር
ለቶጫ ወረዳ ሴ/ወ/ህ/ጽ/ቤት
ለቶጫ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት
ቶጫ

አንድም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም!

Endereço

Tocha

Website

Notificações

Seja o primeiro a receber as novidades e deixe-nos enviar-lhe um email quando Tocha Primary Hospital publica notícias e promoções. O seu endereço de email não será utilizado para qualquer outro propósito, e pode cancelar a subscrição a qualquer momento.

Compartilhar