ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ "

  • Home
  • Qatar
  • Doha
  • ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ "

ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው  " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ " 💚💛❤️ አምላኬ ኳታር ቅድስት ሥላሴን ሳልጨርስ የትም አትውሰደኝ ::

11/12/2025

✋ ኖኤልዬ እግዚአብሔር ያሳድግሽ !!

🎁 ኖኤልዬ የኔ ቆንጆ ልጅ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መድኃኒት የሆነውን ባርኮ የሚያሳድገውን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን ተቀብለሽ 10 ኛ ዓመትሽን አከበርሽ እንኳን ተወ...
11/12/2025

🎁 ኖኤልዬ የኔ ቆንጆ ልጅ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መድኃኒት የሆነውን ባርኮ የሚያሳድገውን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን ተቀብለሽ 10 ኛ ዓመትሽን አከበርሽ እንኳን ተወለድሽልኝ ልዑል እግዚአብሔር ለቁም ነገር ያብቃሽ!!

✋የNORWAY ውቢቷ BERGEN ከተማ
10/12/2025

✋የNORWAY ውቢቷ BERGEN ከተማ

10/12/2025

🇩🇪 በጀርመን ፍራንክፈርት የሚዘጋጀውን የገና ኤክስፖ በጣም ወድጄዋለው በቅርብ ያላችሁ ኑ ጎብኙት በጣም ትወዱታላችሁ !!

08/12/2025

✋የኔ ማርያምዬ እናቴ እወድሻለው
✋እናንተም በሏት
⛪️ የታሕሳስ 3 በዓታ ማርያምን በጀርመን ክሮንበርግ ደብረ ኃይል ቅድስት በዓታ ለማርያም ቅዱስ ኡራኤል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አርብ በቅዳሴ ቅዳሜ ከ13 ሰዓት ጀምሮ በዋዜማ ቅዳሜ ለእሁድ ማታ ከ22 ሰዓት ጀምሮ በማኅሌት ጠዋት በቅዳሴ እና በዑደት በደመቀ በዚያ እናክብር ::

✋ዛሬ ይቤሉ እስራኤል ሰንበትን በጀርመን ክሮንበርግ ደብረ ኃይል ቅድስት በዓታ ለማርያም ቅዱስ ኡራኤል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን በነበረኝ አገልግሎት በቅዳሴ በስብከት በዝማሬ ተባረኩኝ የ...
07/12/2025

✋ዛሬ ይቤሉ እስራኤል ሰንበትን በጀርመን ክሮንበርግ ደብረ ኃይል ቅድስት በዓታ ለማርያም ቅዱስ ኡራኤል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን በነበረኝ አገልግሎት በቅዳሴ በስብከት በዝማሬ ተባረኩኝ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኃይል ቀሲስ ኢሳኢያስ ትጉኅ እረኛ ተወዳጅ አባት በአንድ አመት ውስጥ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ ያሳዩትን ታላቅ ለውጥ አይቼ አድንቂያለው ቄሰ ገበዝ ግሩም ያልተነበበው መጽሐፍ ነዎት ሁሌም ጫወታዎትን አልጠግበውም ሊቀ ዲያቆናት ዳኒዬ ትሕትናን ከሙያ ጋር አስተባብሮ የያዘ ዲያቆን ወንደሰን እንግዳ አክባሪ ብርቱ መምህር እና ተተኪ ዲያቆናት ልጆቻችንን በየአመቱ ማይባቸው ለውጥ እጹብ ያሰኛል የደብሩ ሰበካ ጉባኤ የሕንጻ አሠሪዎች የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ሁላችሁንም እጅግ እወዳችኃለው ሳምንት ደግሞ እናታችንን በዓታን ለማክበር ሽር ጉድ እያላችሁ ነው እግዚአብሔር ያከናውንላችሁ !!

✋የእህቶቼ መኖሪያ  ሀገረ ጀርመን በሠላም ገብቻለው ሁሉንም ቤተሰቦቼን በሠላም አጊኝቻቸዋለው ይህንን ያደረገልኝ አምላኬ ክብር ምስጋና ይድረሰው ::
06/12/2025

✋የእህቶቼ መኖሪያ ሀገረ ጀርመን በሠላም ገብቻለው ሁሉንም ቤተሰቦቼን በሠላም አጊኝቻቸዋለው ይህንን ያደረገልኝ አምላኬ ክብር ምስጋና ይድረሰው ::

🤣 አብዛኛው ለንደን ያለ ሠው ኳስ አያይም እኔን ጨምሮ ባለኝ ጊዜ ባየሁት እና ባስተዋልኩት እንኳን አርሰናል ኢመሬትስ ስቴድየሙ ሥር እንኳን ያሉት ምን እየተኪያሄደ እንደሆነ ማያውቁ ብዙ ናቸ...
06/12/2025

🤣 አብዛኛው ለንደን ያለ ሠው ኳስ አያይም እኔን ጨምሮ ባለኝ ጊዜ ባየሁት እና ባስተዋልኩት እንኳን አርሰናል ኢመሬትስ ስቴድየሙ ሥር እንኳን ያሉት ምን እየተኪያሄደ እንደሆነ ማያውቁ ብዙ ናቸው ግን ኢትዮጵያ እና ሌላ አለም ያለ ነው አብሮ ከኳሷ ጋር ሲንቀረቀብ የሚውለው ተጫዋቾቹ አንድ ሲጠልዙ ሚልዮን ዶላር ነው እኛ ግን ላይፋችንን ስንጠልዝ እኑላለን::
👉እያልኩ ያለሁት ኳስ አትዩ ሳይሆን ልክ እንደ ኳሱ ለእያንዳንዱ ጉዳያችን አጀንዳችን እና ዓላማችን ትኩረት ብንሰጠው የት በደረስን የሚል አስተያየት አለኝ ::
🔥እናንተስ ምን ትላላችሁ ?

✋ የለንደኗን ጸሐይ ጽርሐ ጽዮንን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቴ ባርካኝ የሁላችሁም አሻራ የሆነውን  ፍሬያችሁን እና የእናቴን ክብር አይቼ በክብር እና በደስታ ተመልሻለው ::✋ይህንን ላሳካች...
06/12/2025

✋ የለንደኗን ጸሐይ ጽርሐ ጽዮንን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቴ ባርካኝ የሁላችሁም አሻራ የሆነውን ፍሬያችሁን እና የእናቴን ክብር አይቼ በክብር እና በደስታ ተመልሻለው ::
✋ይህንን ላሳካችሁ በለንደን እና አካባቢው ያላችሁ በአጠቃላይ ከብፁዕ አባታችን ጀምሮ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች የአድባራት አስተዳዳሪዎች ማኅበረ ካህናት እና ማኅበረ ምእመናን እና እጅግ የምወድህ ወንድሜ ኮሜድያን እሸቱ ወንድሜ ሸዋንጌ ትልቁ ፕሮጀክታችሁ ስለተፈጸመ እና ስለተመረቀ በተለይም ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ የድንግል ማርያም ፍቅር በልባቸው አድሮ ኢትዮጵያ ድረስ መጥተው ጣዕሟን ተምረው ፍቅሯን በልቦናቸው አሳድረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለንደን ላይ መስርተው የእመ አምላክን ታቦት ለ50 ዓመታት ጠብቀው አቆይተው የሰጠናቸውን አደራ በሚያደንቅ ኃላፊነት ተወጥተው አዛኝቷን በመንበሯ እንድታርፍ ላደረጉት ለካሪቢያውያን አባቶቻችን ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ ::
ግን.............
😓 ጽርሐ ጽዮን እናቴን ተሰናብቼ ከለንደን ስወጣ አንድ በጣም ያሳሰበኝ ጉዳይ አለ ለእናንተም እነግራችኃለው በቪዲዮ እመጣለው::

01/12/2025

✋እንቁዎቻችን ደስታቸውን ሲገልጹ ስሙ ::
👂 ውይ ውይ ኸ ኸ እመቤቴ እንደው ምሥጋና ይድረስሽ ስትል ሰማችኃት ????
👉እናንተስ ምን አላችሁ ?????? አጥለቅልቁት

30/11/2025

❤️ ማርያም ማርያም ሳትሉ አትለፉ 😍
😍 የሷ ስም ሲነሳ ለሚያቃጥላቸው ሠዎች አድርሱልኝ ምንም EDIT ያልተደረገ video ለቅቄላችኃለው
❤️ የእመ አምላክ የወላዲተ አምላክ ታቦት ለ50 ዓመታት ከኖረችበት ቤት በክብር ወጥታ ለንደን በጣም የተጨናነቀ ሲቲ መንገድ አዘግታ ወደ መንበረ ክብሯ ገብታለች ::
✋ወንድሜ ኮሜድያን እሸቱ እንኳን ደስ አለህ
✋ወንድሜ ሸዋንጌ እንኳን ደስ አለህ
✋በመላው አለም ያላችሁ የእመ ብርሐን ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ!!

29/11/2025

😍 የመልአከ ጽዮን ቀሲስ ተስፋ ሚካኤል በረከት ይደርብን የላቲን አሜሪካ ሠው ሁነው ለ50 አመታት በቤታቸው ታቦተ ጽዮንን እቅፍ ሽሽግ አርገው ያቆዩ ታጥቀው ያገለገሉአት ድንቅ አባት በረከታቸው ይደርብን !!

Address

Doha
90945

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ " posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ ":

Share