አብራጎት ፔጅ Abragot page

አብራጎት ፔጅ Abragot page የነቢ ኢሳነይ (አ.ሰ) ዲነ ታጣሙይ ሰብቻ ሸር ኡመተይ አብራጎት

06/12/2024
16/10/2024

"ሁሉም ፀጋ ተወጋጅ ነው የጀነት ሰወች ፀጋ ሲቀር፡ ሁሉም ጭንቀት ተወጋጅ ነው የጀሀነም ሰወች ጭንቀት ሲቀር" (ሀሰኑል በስሪ )

 ! ➠ ስልጤ የመስለጤ #ይዘት➠ የግጥም መድብል #ጸሐፊ➠ ሙባረክ ላሉ  ➠ ጥቅምት 24/2017 ➠  ወራቤ
16/10/2024

!

➠ ስልጤ የመስለጤ

#ይዘት➠ የግጥም መድብል

#ጸሐፊ➠ ሙባረክ ላሉ
➠ ጥቅምት 24/2017
➠ ወራቤ

በወራቤ ከተማ የሚገኘው አቡበክር አስሲዲቅ መስጂድና መድረሳ የ2017 የበጋ ኢስላማዊ ትምህርቶች መክፈቻና የአዲሱን መድረሳ ምረቃ ፕሮግራም እያካሄደ ነው። ፕሮግራሙ ላይ ለአቡቡክር አስስዲቅ ...
12/10/2024

በወራቤ ከተማ የሚገኘው አቡበክር አስሲዲቅ መስጂድና መድረሳ የ2017 የበጋ ኢስላማዊ ትምህርቶች መክፈቻና የአዲሱን መድረሳ ምረቃ ፕሮግራም እያካሄደ ነው።

ፕሮግራሙ ላይ ለአቡቡክር አስስዲቅ መድረሳ ማጠናከሪያ የገቢ አሰባሰብ መርሃ ግብርም እየተከናወነ ነው።

በዚህም ታላቁ አባታችን ሃጂ አብዱልሃዲ 30,000 ብር እና አባታችን ሃጂ ወለላ 1,000 ሪያል በካሽ ለግሰዋል።

ሌሎች ወንድምና እህቶችም የኒያቸውን ያህል ለመድረሳው ማጠናከሪያ ገቢ እያደረጉ ነው።

መስጂድ አቡበክር አስሲዲቅ ላለፉት 20 ያህል ዓመታት ሁለንተናዊ ኢስላማዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ተደጋጋሚ ተማሪዎችን አሰልጥኖ በማስመረቅ በስልጤ ዞን ደረጃ ፈር ቀዳጅ መስጂድና መድረሳ ነው።

መታረም ያለበት እሳቤ~"የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የወንጀላችን መብዛት ነው። ወደ አላህ እንመለስ" በሚባል ጊዜ "ኧረ ከወንጀል ጋር የሚያያዝ አይደለም ፤ የታወቀ ሳይንሳዊ ምክንያት ያለው ...
08/10/2024

መታረም ያለበት እሳቤ
~
"የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የወንጀላችን መብዛት ነው። ወደ አላህ እንመለስ" በሚባል ጊዜ "ኧረ ከወንጀል ጋር የሚያያዝ አይደለም ፤ የታወቀ ሳይንሳዊ ምክንያት ያለው ነው" የሚሉ ሰዎች አሉ። እንጂ የፈጣሪ ስራ አይደለም ነው ድምዳሜያቸው። ለሆነ ክስተት ሳይንሳዊ ትንታኔ ወይም የታወቀ ምክንያት ኖረው ማለት ያ ክስተት የፈጣሪ ስራ አይደለም ማለት አይደለም። በፈጣሪ የሚያምን ሰው ያለሱ መሻት በምድርም ይሁን በሰማይ የሚሆን ነገር እንደሌለ ያምናል። ስለዚህ ዝናቡም፣ ንፋሱም፣ ማእበሉም፣ ድርቁም፣ መብረቁም፣ የመሬት መንቀጥቀጡም፣ የፀሐይ ግርዶሹም፣ ወረርሽኙም፣ ... ሁሉም በአላህ ውሳኔና መሻት የሚፈፀም ነው። ደረስንበትም አልደረስንበትም ከአላህ ውሳኔዎች ጀርባ የሱ ጥበብ አለ።

በአላህ የሚያምን አካል ትልልቅ መቅሰፍቶች ቀርቶ ትንንሽ ፈተናዎች ሲገጥሙት እንኳ የራሱን ድክመት ይመለከታል። ሰበቡ ወንጀሌ ሊሆን ይችላል ብሎ ወደ ጌታው ይመለሳል። እውነታውም እንደዚያ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَمَاۤ أَصَـٰبَكُم مِّن مُّصِیبَةࣲ فَبِمَا كَسَبَتۡ أَیۡدِیكُمۡ وَیَعۡفُوا۟ عَن كَثِیرࣲ }
"ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሰሩት (ሃጢኣት) ምክንያት ነው። ከብዙውም ይቅር ይላል።" [አሹራ፡ 30]
=

@ Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦

06/10/2024

ሰላት ውስጥ ኢማምን መቅደም ያለው አደጋ👇
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

አንዳንድ ሰዎች ከኢማም ጋር አብረው ኢማም ሁነው የሚያሰግዱ ይመስላል።
በጣም አደጋ ያለው ትኩረት የተነፈገ ብዙ ሰው እየፈፀመው ያለ ስህተት !

ኢማሙ እማም ሆኖ ስያሰግድ መቅደምም ይሁን በጣም ወደ ሗላ መቅረት አይፈቀድም። አንዳንድ ሰዎች ከተክቢረተል ኢህራም ጀምረው እስከ ማሰላመት ከኢማሙ ጋር እኩኩል የሚፈፅመውን ከራሱ አብረው የሚፈፅሙ አንዳንድ ሰዎች እንደውም ቀድመውትም የሚጓዙ ኣሉ። ይህን ተግባር ነብዩ ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም በጥብቅ ያወገዙትና ትልቅ የሆነ ዛቻም ያለበት ኢማሙን ተከትለው የሚሰግዱ አንዳንድ ሰዎች የሚፈፅሙት ትልቅ የሆነ ስህተት ነው።

ነብዩ ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም እንዲህ ይላሉ።👇

ኢማምን ቀድሞት ራሱን ቀና የሚያደርግ ሰው አለህ ራሱን የአህያ ራስ ወይም ድምፁን የአህያ ድምፅ እንዳያደርግበት ሊፈራ የገባል ብሏሉ

📚( ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

በሌላም ሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ👇

" ኢማም እኮ ኢማም የተደረገው እንዲመሩበት ነው።"

📚(ቡኻሪ ፡ 688 ሙስሊም 417 ዘግበውታል)

አደራ አደራ አብዛኛው ሰው የሚፈፅመው ስህተት ስለሆነ ለሌሎችም እናስተላልፈው።

የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ እውቀቶችን ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ነክተው ጆይን በማለት ይቀላቀሉ👇👇👇👇👇👇👇👇👇

20/09/2024

ወንድማችንን እንደግፈው

እዚሁ መንደር ያለ ወንድማችን ነው።ታታሪ ሰራተኝነት መገለጫው ነው።ከአመት በፊት ሸገር ሲቲ ቤት ፈረሳ ሲጀምር ብዙ አመት ለፍቶ የገነባው ቤት ፈረሰ።ወንድማችን በወቅቱ ሀዘኑን ዋጥ አድርጎ ቤት ፈረሳውን ተከትሎ አደባባይ የወጡ ወገኖቹን ከችግር ለመታደግ የተከራየው ቤት ላይ ሰዎችን ከማስጠለል ጀምሮ የሚያውቃቸውን ሰዎች እያስቸገረ የሚቋቋሙበትን ስራ ለማስጀመር ደፋ ቀና ይል ነበር።ወራት ነጎዱ ወንድማችን በአላህ ፈቃድ የፈረሰብኝን ቤት ነገ በላቤ ሰርቼ እተካዋለሁ ብሎ መልፋቱን ቀጠለ።አሁን ደግሞ የቤተሰቡን ህይወት የሚያናጋ ሌላ ዱብ እዳ መጣበት።ለኮሊደር ልማቱ ይፈለጋል በሚል የስራ ቦታው ፈረሰ።ለአመታት እረፍት የማያውቁ እጆቹ ስራ ፈተው ቤት መቀመጥ እጣቸው ሆነ።
ስራ ፈቶ ቤት ከመቀመጡ በላይ ሰርቼ እከፍለዋለሁ ብሎ የተበደረውን የ650 ሺህ ብር እዳ መክፈል ዳገት ሆነበት።እጁ ላይ የቀረውን 400 ሺህ ብር ለአበዳሪው ከፍሎ 250 ሺህ ብሩን ለመክፈል የአንድ ሳምንት ተጨማሪ ጊዜ ጠየቀ። ነገር ግን እጁ ላይ ቤሳቤስቲ እንኳ አልቀረውም።ወንድማችን ለቀናት እንቅልፍ አጥቶ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል። በዚህ ከቀጠለ የጤናውም ነገር አሳሳቢ ነው።

ለሰዎች ደራሽ የሆነውን ወንድማችን ከጭንቀት መታደግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000651036406
ሹክራየ ሱልጣን(የባለቤቱ አካውንት ነው)

05/09/2024

⚠️ሞት ሁሌ አድስ እንግዳ!!

መካሪ እኮ የለም ትልቅ እንደ ሞት
አንኳኩቶ ይገባል ድንገት ወደ ቤት
ሲመጣ አያማክር በድንገት ከች ነዉ
እቅድ ሲደረድር የተዘናጋዉ ሰዉ
ከመጣ ብኋላ መላሽ የሌለዉ
ችላ ባይ የሆነዉ የኔ ቢጤ ሰዉ
ያኔ ይባንናል የተዘናጋዉ

በደስታ እየኖሩ ድንገት ይመጣና
የደረሰባት ነፍስ ጠጋ ይላትና
የተላኩኝም ነኝ ከላይ ከረበና
እያለ ይላታል እዉነት ይዟልና፣

አጀል ከደረሠ የለም ወደ ኋላ
ኸይርን አልሠራሁም አይቻል ብኋላ
ቆራጡ ከመጣ ጥፍጥና ቆራጩ
የሚያድነን የለም ፍጡራን ቢንጫጩ፣

ጨለማዉ ሲመጣ ትልቁ እንግዳዉ
የማይለመደዉ ሁል ጊዜ አድስ ነዉ
ከእንግዶችም በላይ ትልቁ እንግዳ ነዉ
ቀላል ይመሥለናል ሌሎች ቤት ስናየዉ

ነገር ግን ሲመጣ በዬ ሁሉም ቤት
ያለ ድንጋጤ ያለዉም ጭንቀት
ብርቱ የሆነ ነዉ የማይቀረዉ ሞት
ዱንያ አንዱን አክብራ አንዱን እያስጠማች፡
ሰው ሆይ ልብ እንግዛ ለዚህች ምድር ዘማች፡
እባክህ አስተውል ስማኝ የነገ ሟች!?

ነፍስ ያላትን ፍጥረት ሁሏንም ያጉዛል፡
በማንም ፍጡር ላይ ሽብርን ይነዛል፡
ጀናዛ ተብሎ ሁሉም ይገነዛል፡
ትልቅ አይል ትንሽ ፈሪም አይለይ ጀግና፡
ሁሉንም በተራው ያጉዘናል ገና...

እድሜ አይገድብ ፆታ አይመርጥም ቁንጅና፡
አይፈራም ትልቅ ሰው አያከብር እርጅና፡
ሰውን በአቋሙ በስራው አይመዝን፡
ለሴትም ለወንድም ለወጣት አያዝን፡

ምንም ሀብታም ቢሆን ገንዘቡ ቢቆለል፡
ልመና አያስቆመው በጉቦ አይደለል፡
በአሏህ ከታዘዘ ከተላከ ለኛ፡
መኪና አሽከርካሪ ቢሆን ከብት እረኛ፡

እጂግ የከፋ ሰው ወይ ደግሞ ኸይረኛ፡
ይፈፅማል ትዕዛዝ ሞት የፍትህ ዳኛ፡
መልካም ሥራ ሰርተን ካልሆነን ለአኺራ
ከአፈር በታች ገብተን ስለ እኛ ቢወራ
ስምችን ቢነሳ በአለም ላይ ቢጠራ

የሠራነዉ ስራ ከሆነ ገለባ
ለአኺራ ካልሆነ ለኛ ምን ሊረባ
ጨለማዉ ተገፎ ቀብር ካላበራ
ምን ሊጠቅም ወሬ ዝናሥ ምንሊሠራ

ደስታን አያገኝም ከአንተ የሸሸ
ይቅር በለኝ ብዬ መጣሁ ተመልሸ
ይቅር ባይ ነህና ከሁሉም በላይ
እጆቸን አንስቸ ዳግም ወደ ላይ
ይቅርታን ጠየኩህ ሀያሉ ጌታዬ
አስጨነቀኝ እና የመጨረሻዬ

ኻቲማዉ ሲያምር ነዉ ስኬታማ ማለት
ኸይር ስራ ሰርቶ ወንጀል ተምሮለት
ይሔ ነዉ ትልቅ ሰዉ ስኬታማ ማለት
ከአዛብ ተጠብቆ የገባ ከጀነት።

01/09/2024

“አንዳችሁ ከደጃፉ/ከበሩ የሚፈስ የወንዝ ውሃ ቢኖርና በቀን አምስት ጊዜ ቢታጠብበት አንዳች ቆሻሻ ይቀርበታልን?”
"ምንም እድፍ አይኖርበትም" አሉ ሶሃቦች
"ይህ እንግዲህ አላህ ሐጢአቶችን የምያብስባቸው የአምስቱ ሶላቶች ምሳሌ ነው።" ቡኻሪ እና ሙስሊም

29/08/2024

‼️ስንቱን አጅር አባከንን?

«ሁለት ቃላት ለምላስ ቀላሎች ናቸው ፤ሚዛን ላይ ከባዶች ናቸው፤አላህ ዘንድ ተወዳጆች ናችው፤ ሱብሃነላሂ ወቢሀምዲሂ ሱብሃነላሂል አዚም(የሚሉት ናቸው) »።

28/08/2024

ሉቅማን፡ "ከሰው ሁሉ መጥፎ ማነው?" ተብለው ተጠየቁ። "ጥፋት እየፈፀመ ሰዎች ቢያዩት ደንታ የሌለው ነው" አሉ።
[አዙህድ፣ አሕመድ]

📢 አስደሳች ዜና | بشرى سارة ልዩ የዒልም ኮርስ በወራቤ ከተማእነሆ በአይነቱ ልዩ የሆነ የዒልም ኮርስ ከፊታችን እሮብ ነሃሴ 22/2016 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት በወራቤ ከተማ ይካሄ...
27/08/2024

📢 አስደሳች ዜና | بشرى سارة

ልዩ የዒልም ኮርስ በወራቤ ከተማ

እነሆ በአይነቱ ልዩ የሆነ የዒልም ኮርስ ከፊታችን እሮብ ነሃሴ 22/2016 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት በወራቤ ከተማ ይካሄዳል።

በዓቂዳ፣ ፊቅህ፣ ኡሱሉል-ፊቅህ እና በሌሎችም
ወሳኝ የእውቀት ዘርፎች ያተኮሩ ት/ቶች በተለያዩ ከሀገር ውጭ(ከሱዳን እና ሱዑዲ) በመጡ ታላላቅ መሻይኾች የሚሰጥ ሲሆን በስልጤ ዞን እና አጎራባች ዞኖች የምትገኙ ዒልም ፈላጊዎች እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን ።

ከውጭ ከሚመጡ ተጋባዥ መሻይኾች መካከል:
❶ ዶ/ር አብዱረሕማን ሃሚድ አል-ናቢት
❷ ዶ/ር ኸሊል ሃሚድ ኸሊል
እና ሌሎችም

እንዲሁም ከሀገር ውስጥ በርካታ ታላላቅ መሻይኾች እና ዱዓቶች የሚሳተፉ ይሆናል።

🕌 ወራቤ ከተማ አቡበክር መስጅድ
📆 ከረቡዕ ነሃሴ 22 - 25/2016 ዓ.ል

https://t.me/fewaidworabe

Address

Mecca

Telephone

+251913722699

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አብራጎት ፔጅ Abragot page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አብራጎት ፔጅ Abragot page:

Share

Category