15/12/2025
ማንም በልጅ ህመም አይፈተን !
ከዚህ ቀደም የቄራ ሰላም መስጂድ ጀመዓ ሁሉ በመልካም ስሟ የሚያውቃት እህታችን ሰሚራ ልጇ ሀኒፍ ወደ ቱርክ ሀገር ሄዶ በደጋግ ሰዎች እገዛ እና ርብርብ ከነበሩበት ህመሞች መካከል አንደኛውን ታክሞ ነበር ከአንድ አመት በኃላ ተመልሰሽ አምጪው ብለዋት ወደ ሀገር የተመለሰው።
ለተከታታይ ሁለት አመት በጣም ደህና ሲሆን እና ለውጥ ሲያመጣ እናት ሰሚራም ልጄ ደህና ነው ድጋሚ ለመውሰድም አቅም የለኝም ብላ የሀገር ውስጥ ህክምና ብቻ እየተከታተለች ቆይታ ነበር።
ነገር ግን አሁን ላይ በድጋሚ ወደ ውጪ ሄዶ ህክምና ማድረግ እንዳለበት በሀገር ውስጥ ክትትል የሚያደርጉለት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች ቦርድ ነግረዋታል።
እህታችን ሰሚራ ከዚህ በፊት እኛን ወንድም እህቶችዋን እገዛ ጠይቃ ልጇን አሳክማ ስለነበር አሁንም በድጋሚ ሰው አላስቸግርም አላህ እንዳደረገው ይሁን ስትል አንድ ሀኪም እንዲህ አላት። "ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያው ህክምና ስትመጪ እና ህክምናውን ከባድ እንደሆነ ስነግርሽ አላህ አለ ጥሎ አይጥለኝም ልጄ ይድናል የአቅሜን አደርጋለሁ" ብለሽ ነበር ምነው አሁን ከአላህ ተስፋ ቆረጥሽ በማለት ሲናገራት እህታችን በድጋሚ እናንተ ደጋግ እህት ወንድሞቿ ፊት የተጠየቀችውን 4,000,000 (አራት ሚሊየን ብር) እገዛ ለመጠየቅ ተገዳለች።
ሁላችንም የአቅማችንን እገዛ በማድረግ ልጇን እናትርፍላት።
አላህ ኒያችሁን ይሙላላችሁ እህት ወንድሞች
1000433513758 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
116309998 አቢሲኒያ
014311316960600 አዋሽ
(ሰሚራ ኑርሰፋ)
+251 90 462 3864