02/03/2026
አባት ሁለት ሴት ልጆቹን ዳረ። አንዷን ለገበሬ አንዷን ደሞ ለሸክላ ሰሪ ነበር የዳረው ፤ ከአመት በኋላ ሊዘይራቸው ብሎ ከአገር ወጣ ። ዚያራውን የቤቱ ታላቅ ከሆነችው ለገበሬው ከዳራት ልጁ ጀመረ ፤ እሷም እጅግ በደስታ ተቀበለችው ። "እንዴት ነሽ ኑሮ እንዴት ይዞሻል በምንስ እየኖርሽ ነው" ብሎ ጠየቃት
"ባለቤቴ መሬት ተከራይቶ ነው ያረሰው ፣ እህሉን ደግሞ በብድር ነው የወሰደው አሁን ዘርቶታል ። ዝናብ እየጠበቅን ነው፤ ከዘነበ ኢንሻ አላህ ምርቱ ጥሩ ይሆናል ኑሯችንም ይሻሻላል ፤ ካልዘነበ ግን አደጋ ውስጥ ነን።"አለችው
ከዚያም ወደ ሁለተኛ ልጁ አመራ እሷም በደስታ ተቀበለችው።
"ኑሮ እንዴት ነው በምንስ ነው የምትኖሩት"አላት ።
"ባለቤቴ በብድር ነው የሸክላ አፈር የገዛው ፤ አሁን ብዙ የሸክላ ምርት አዘጋጅቶ መድረቁን እየተጠባበቀ ነው ። በየቀኑ ፀሀይ የሚወጣ ከሆነ ምርቱ ይሄድለታል ፤ በኑሯችን ላይም ለውጥ ይኖራል። የሚዘንብ ከሆነ ግን ሸክላው ይበላሻል ።"አለችው
አባት ልጆቹን ከጎበኘ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ ፤ ቤቱ ሲደርስ የልጆቹ እናት ስለ ሁኔታቸው ጠየቀችው ። እሱም እንዲህ አላት :-
።"
እንግዲህ የዱንያ ነገር እንዲህ ነው ፤ አንዱ የሚፈልገውን ሌላው አይፈልገውም ፤ ላንዱ የሚስማማው ለሌላው አይስማማውም፤ ለአንዱ መሰናክሉ ለሌላው የስኬት መንገዱ ነው። ብናዝንም ብንደሰትም ብናጣም ብናገኝ
አላሃምዱሊሏህ 😍🙏🙏