Good things

Good things We are try to informe you the truth about us mean Ethiopia and try to creat new generation.we have to stand together to bring real democracy,peac and love

ጎበዝ ሀገር እየነደደች ነው😭😭😭ኧረረረረ Share አድርጉ ዓለም ይወቀውስልጤ ዞን ሳንኩራ ንቡ ቅዱስ ገብርኤል  ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ ነው። ምን እንደታሰበልን አላወቅንም ገና። በሌላም ...
28/04/2022

ጎበዝ ሀገር እየነደደች ነው😭😭😭

ኧረረረረ Share አድርጉ ዓለም ይወቀው

ስልጤ ዞን ሳንኩራ ንቡ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ ነው። ምን እንደታሰበልን አላወቅንም ገና። በሌላም አካባቢ ያላችሁ እየተሰባሰባችሁ አብያተ ክርስቲያናትን እና ራሳችሁን ጠብቁ !!!

28/04/2022

አሸባሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ብለው ፈርተው ተመለሱ 🥺

እንድ ለእናቱ ሺ ለጠላት የ አድዋው አርቲስት ሚኪዘምቶል በተግባር ነው ይለያል ዘንድሮ
29/07/2021

እንድ ለእናቱ ሺ ለጠላት የ አድዋው አርቲስት ሚኪ
ዘምቶል በተግባር ነው ይለያል ዘንድሮ

11/02/2021

ጌታ ሆይ! አንተ መምህሬ ነህ፣ እጄን ይዘህ በሚሄድበት መንገድ ምራኝ መንገህንም ፣ እንዳውቅ አይነ ልቦናዬን አብራልኝ ።

 #ሼር  #አድርጉላቸውበማርያም በማርያም እያሉ ሲለምኖቸው፣ስድስት ኪሎ አካባቢ በደንብ አስከባሪ ሰዎች አማካኝነት የሚነግዱት ልብስ ተወስዶባቸው በነበረ ወቅት "ስለ ማርያም!" እያሉ ንብረታቸ...
26/01/2021

#ሼር #አድርጉላቸው
በማርያም በማርያም እያሉ ሲለምኖቸው፣

ስድስት ኪሎ አካባቢ በደንብ አስከባሪ ሰዎች አማካኝነት የሚነግዱት ልብስ ተወስዶባቸው በነበረ ወቅት "ስለ ማርያም!" እያሉ ንብረታቸው እንዲመለስላቸው ሲማጸኑ የነበሩት አባት እኝኸ ናቸው ።

ስማቸው #ያሬድ #ያጌ #ሾቴ ይባላል ። የሚኖሩት ሽሮ ሜዳ አካባቢ ማግ ቢዝነስ ሴንተር አጠገብ በሚገኘው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ቁጥር አንድ ወጣት ማዕከል አጠገብ በሚገኘው የኮብልስቶን ቁልቁለት መንገድ ነው ።

#ስልካቸው

0973402448
0900782913

የእመቤታችንን ንጽሕናዋና ቅድስናዋን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንደሚከተለው ነው። “ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም” /መኃ.4፥7/...
13/01/2021

የእመቤታችንን ንጽሕናዋና ቅድስናዋን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንደሚከተለው ነው።

“ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም” /መኃ.4፥7/፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ አምላክ ነው፤ ማደሪያውም ሁሉ ቅዱስ ነው። እግዚአብሔር በበረከትና በረድኤት ያደረባቸው ሰዎች ቦታዎችና ንዋያት ሁሉ ቅዱስ የሚል ቅጽል ይሰጣቸዋል። እመቤታችን ድንግል ማርያም ደግሞ እግዚአብሔር በበረከትና በረድኤት ብቻ ሳይሆን በሥጋም ያደረባት ናትና ቅድስት /ቅድስተ ቅዱሳን ትባላለች፤ ቅድስናዋም በሥጋ፣ በነፍስና በሕሊናዋም ጭምር ነው። ነብዩ ዳዊትም “ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ” መዝ. ፵፭፥፬-፭ በማለት አስቀድሞ በፈጣሪ ዘንድ የተቀደሰች መሆኗን ይናገራል። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም “ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽነሽ የማኅጸንሽም ፍሬ የተባረከነው” ሉቃ. ፩፥፳፰ በማለት ቅድስናዋን መስክሯል።

እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ ላዳነበት ጥበቡ ምስጢር መፈጸሚያ መቅደስ፣ የመለኮት ማደሪያ ለመሆን የበቃች ንጽሕት ቅድስት ናት። ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ተወልዶ ዓለምን ከጥፋት እንደሚያድን "እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደሰዶም በሆንን እንደገሞራም በመሰልን ነበረ፡፡” ኢሳ. 1፥14 ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡ ዘርን የሚለው ቃል ለጊዜው በእግዚአብሔር ርኅራኄ ጨርሶ ከመጥፋት የዳኑትን ቱሩፋንን ቢሆንም (እነዚህም ከጥፋት የዳኑ ደጋግ የእስራኤል ሕዝቦች ናቸው) ፍጻሜው ግን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ለክርስቶስ የተነገረ ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ራሷን በንጽሕናና በቅድስና በማኖር የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ በመሆንዋ ምክንያት ከራስዋ ቅድስና ጋር ታክል መንፈስ ቅዱስ ፍጽምትና ቅድስት እንድትሆን አድርጓታል፡፡ እግዚአብሔር ባወቀ በዚህ ምክንያት ነው እርሷን ለተዋሕዶ የመረጣት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አስተውለን ብንመለከት የእግዚአብሔር ማደሪያ ወይም እግዚአብሔር የመረጣቸው ወይም የእግዚአብሔር ክብር የተገለጠባቸው ቅዱሳን እንዲሁ በከንቱ ቅዱሳን የተባሉ እንዳልሆኑ እንረዳለን፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔርን በመውደድ እርሱ ደስ የሚያሰኘውን ሥራ በመሥራት ራሳቸውን ከዓለም ጉድፍ በመጠበቅ በትልቅ ተጋድሎ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ በእነርሱ እግዚአብሔር ሥራውን ለመሥራት አያፍርም ስለዚህም ቅዱስ ዳዊት “እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተገለጸ እወቁ” መዝ.4፥3 ብሎ በመንፈስ ተሞልቶ መሠከረ፡፡ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “የሚወደኝ ቃሌን ይጠብቃል አባቴም ይወደዋል ወደእርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን” /ዮሐ.14፥24 ብሎ አስተማረን፡፡

ቅድስት እናታችንንም እግዚአብሔር ለተዋሕዶ ሲመርጣት የንጽሕና የቅድስና ሕይወቷን ተመልክቶ ነው፡፡ ቅድስናዋም ከቅዱሳን ሁለ ስለሚበልጥ እግዚአብሔር ለአንዱ የሚያደርገውን ወደፊትም ለሌሎች የማያደርገውን ሥራ በእርሷ ለመሥራት የፈቀደው፡፡ እኛም ኦርቶዶክሳውያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ንጽሕና እንዲህ በማለት እንመሰክራለን፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም በሐልዮ በነቢብ በገቢር ከሚሠራ ኃጢአት ሁለ ንጽሕት ናት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንደሚያስረዳን “ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም” እንዳለ /መኃ.4፥7/፡፡

ይህንን ስንል ኃይለ አርያማዊት ናት ወይም ከሰው ወገን አይደለችም ማለታችን ሳይሆን በአዳምና በሔዋን በኃጢአት መተላለፍ በሰው ሁሉ ላይ ያለው የውድቀት ባሕርይ እርሱም መራብ፣ መጠማት፣ መድከም፣ መሞት እንደማንኛውም ሰው የሚስማማት ሲሆን ነገር ግን ከኃጢአት ሁለ ራሱዋን ጠብቃ የተገኘች ንጽሕት ናት ማለታችን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ቅዱሳን አባቶች ከኃጢአት በቀር ክርስቶስ የሰውን ባሕርይ ባሕርይው አደረገ ብለው ማስተማራቸው፡፡ ራሱም ጌታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋና ነፍስ ተርቧል፥ ደክሟል፥ መከራ ተቀብለል፣ ሞቷል፡፡ ራሱንም የሰው ልጅ ብሎ መጥራቱም የሰውን ባሕርያትን ገንዘቡ እንዳደረገ ለማጠየቅ ነው፡፡ /ዮሐ.3፥14-15/ እግዚአብሔር አምላክ ሰው ሆኖ ሰውን ሊያድን በፈለገ ጊዜ በቅድስና፣ በንጽሕና፣ በታማኝነት፣ በትሕትና፣ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግና በፍቅር በመመላለስ የመልካም ነገር ሁለ ግምጀ ቤት በመሆን እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም ሌላ ሴት አላገኘም ነበር፡፡ እንዲህም ስለሆነ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ /ለቃ.1፥28/ ብሎ ቅዱሱ መልአክ መሠከረላት፡፡

ሲራክም “….ብቻዬን በአድማስ ዞርኩ በውቅያኖስም ዞርኩ በባህርም ማዕበል መካከል ተመላለስኩ…. ከዚህም በኋላ ዕረፍትን ፈለግሁ እንግዲህስ የማንን ሥጋ አዋሐዳለሁ …. በእርሱ ፈቃድ በከበረ በማርያም ማኅፀን ሥጋን ተዋሐድኩ በምኩራብም አስተማርኩ” /ሲራ.24፥1-10/ ብሏል፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው “እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሆኖ ምስራቅንና ምዕራብን ሰሜንና ደቡብን ዳርቻዎችን ሁለ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰ አሸተተም እንደ አንቺ ያለ አላገኘም የአንቺን መዓዛ ወደደ ደምግባትሽንም ወደደ የሚወደውን ልጁንም ወደአንቺ ሰደደ፡፡”ብሎ ከፍጥረታት ሁለ በቅድስና የሚስተካከላት እንደሌለ መስክሯል፡፡ ስለዚህም እኛም ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ንጽሕት ፍጽምት ክብርት ናት ብለን እንመሰክራለን፡

እመቤታችን ንጽሕተ ንጹሕን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተመረጡም የተመረጠች፤ መትሕተ ፈጣሪ፣ መልእልተ ፍጡራን፣ ከፈጣሪ በታች፣ ከፍጡራን በላይ እየተባለች የምትመሰገን ድንቅ ንጽሕናና ቅድስና አላት። የወላዲተ አምላክ ንጽሕናና ቅድስና ልዩ ነው። ‹‹ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፤ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና መላእክት የሚፈሩትን ትጉኃን በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማኀጸኗ ተሸከመችው። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች፣ ከሱራፌልም ትበልጣለች፣ ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና። ›› እያሉ ሊቃውንት ያመሰገኗትም ድንቅ ከሆነ ቅድስናና ንጽሕናዋ የተነሣ ነው። /ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ፤ ራዕ .4፥ 7-9/። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በምስጋናው ‹‹ጸጋን የተመላሽና የደስታ መገኛ ሆይ … ዓይኖቻቸው ስድስት ከሆኑ ከሱራፌል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። እነዚያ ፊታቸውን ይሸፍናሉ። .. ከልጅሽ መለኮት ከሚወጣው እሳት ይድኑ ዘንድ፣ አንቺ ግን ለመለኮት ማደሪያ ሆንሽ የመለኮት ባሕርይም አላቃጠለሽም። የእሳት ነበልባልን ተሸከምሽ ። ›› በማለት ንጽሕናዋን ከመላእክት ንጽሕና ጋር እያነጻጸረ እጹብ ድንቅ እያለ ያመሰግናታል።

የእመቤታችን ቅድስናና ንጽሕና በቅዱሳን አንደበት ሲመሰገን ድንቅ ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ‹‹ምልዕተ ጸጋ›› ቅድስት ኤልሳቤጥ ‹‹የጌታዬ እናት›› እያሉ ያመሰገኗት ምስጋና ድንቅ ነው። ከሰው ወገን እንዲህ ያለውን ምስጋና የተቀበለ የለምና። የእግዚአብሔር እናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም የንጽሕናዋን የቅድስናዋን ድንቅነት ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ‹‹ከቅዱሳን ሁሉ ክብር ይልቅ የማርያም ክብር ይበልጣል …›› ሲል በብዙ ምሳሌ ያመሰገናት ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ‹‹በምን በምን ልመስልሽ›› በማለት ምሳሌ የታጣላት ድንቅ ንጽሕናና ቅድስና ያላት መሆኑን መስክሯል። የንጽሕናዋ የቅድስናዋ ምስክር ስሟ ድንቅ ነው። ማርያም ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ፍጽምት ማለት ነውና። ለጊዜው መልክ ከደም ግባት ያላት ስለሆነ ውበቷ ድንቅ ነው። ‹‹ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤ ነውርም የለብሽም። ›› እንዲል /መኃ.መኃ 4፥ 7/። ሔዋን ንጽሐ ጠባይ ሳያድፍባት እንደነበረችው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥበቃ ከጥንት ጀምሮ በጥንተ ተፈጥሮ ንጽሐ ጠባይ ሳያድፍባት ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ተጠብቃ የኖረች ድንቅ ናት። ነቢዩ ‹‹ንጉሥ ውበትሽን ወደደ›› ያለበት ምክንያቱ ከዚህ ድንቅ ንጽሕናዋ የተነሣ አይደለምን ? ከአካላዊ ውበቷ ይልቅ ውስጣዊ ንጽሕናዋ ቅድስናዋ ምን ይደንቅ! የእመቤታችን ቅድስናና ንጽሕና አፍአዊ ብቻ አይደለም። ንጉሥ እግዚአብሔር የወደደው ውበት እመቤታችንንም ድንቅ የሚያሰኛት ሌላም አለ። ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ልቡናና ንጽሐ ነፍስን አስተባብራ የያዘች ፍጽምት መሆኗ። ስለዚህ ከቅዱስ ዳዊት ጋር ሆነን በአማን ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ፣ በእውነት በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው ልንላት ይገባል። ስለሆነም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ የሚዲያ ባለሙያዋ እንደገለፀችው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢአተኛ የሰው ገላ ውስጥ አርፎ ሳይሆን ከንፁሐን ሁሉ ንፅህት በሆነችው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ነው።

ባቡጂ በቤቱ ፎቶ ተነስቶል እመኑት ያንባል
26/12/2020

ባቡጂ በቤቱ ፎቶ ተነስቶል እመኑት ያንባል

ስዩም
12/11/2020

ስዩም

10/11/2020

Address

Khartoum

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Good things posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category