
17/02/2025
የካቲት 10 2017
ኢትዮ ቴሌኮም‼️
ኢትዮ ቴሌኮም ለረጅም ግዜ በግዝፈቱ በአንደኛ ደረጃ ተይዞ የነበረውን የ ኤምቲኤን MTN ኩባንያ ደረጃን መንጠቁ ተሰማ።
ኩባንያው በ MTN ተይዞ የነበረውን ደረጃ ተቀብሎ
ከ አፍሪካ አንደኛ ደረጃ መያዙ ተነግሯል።
ኩባንያው ለአመታት የ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ መቆየቱ ይታወቃል።
ዛሬ ደግሞ ከ አፍሪካ 1ኛ ከአለም ደግሞ 16ተኛ ደረጃን መያዙን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ከ 5 ቀን በፊት የስድሰት ወሩን የስራ አፈፃፀም ይፋ ያደረገው ኩባንያው ይህ ሪፖርት በተሰማ ግዜ የሁለተኛ ደረጃን መያዙ ተሰምቷል።
ይህን ሪፖርት ያወጣው ዓለም አቀፉ የሞባይል ኮሙኒኬሽን ስርአት ማኅበር ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ነው።
ኢትዮዽያ በድጅታል አለም የበኩሏን ድርሻ እንዲኖራትና ተመልካች እንዳትሆን የተስፋፋው የቴሌኮም መሰረተ ልማት ለዚሁ ውጤት አግዟል ተብሏል።
11.2 ሚሊየን ደንበኞች በአፍሪካ የ 5ጂ ተጠቃሚዎች እንዳሉ የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ኢትዮዽያም የራሷ ድርሻ እንዲኖራት እየሰራን ነው ብለዋል።
በሞባይል መኒ ቴሌ ብር በ ሶስት አመት ውስጥ 3.5 ትሪሊየን ብር መገላበጡን የተናገሩት ፍሬህይወት ታምሩ ኩባንያው ይህን በማድረጉ እንዲሁም የደንበኞች ተሞክሮና ፍላጎት በማሳደጉ ከፊት እንዲሆን አግዞታል ብለዋል።
ወሬው የተሰማው ኩባንያው የ 5ጂን አምስተኛ ትውልድ ኢንተርኔት አገልግሎት ወደ ጅማ በወሰደበት ግዜ ነው።
አዲስ አበባን ጨምሮ 12 ከተሞች 5ጂ አግኝተዋል