ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ Quanquayenesh Media

ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ Quanquayenesh Media የቴክኖሎጂ ፈረስ በፈለገበት እንዳይዘውረን በሃይማኖት ልጓም ይዘን የሚጠቅመውን እናስተላልፍበታለን
(1)

https://youtu.be/WEdy0cn3weg?si=LxvbeURyJnPFwbFH
09/11/2025

https://youtu.be/WEdy0cn3weg?si=LxvbeURyJnPFwbFH

ይህ ዩቲዩብ ቻናል የእኔ የዘማሪ መምህር ሉልሰገድ ጌታቸው ቻናል ሲሆን እንደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝነቴና እንደ ሥነ መለኮት ተማሪነቴ ኦርቶዶክሳዊ ይዘታቸ...

09/11/2025

🌷የኢትዮጵያ ስደት፣ የልጆቿም ኀዘን፣ በተለይ ደግሞ የክርስቲያኖች መከራ ተፈጸመ ለማለት ያብቃን።

"ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ"
እንኳን አደረሳችሁ።

በጭካኔ የተገደሉትን ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ያሳርፍልን ሥቃይ ላይ ያሉትን በምሕረት እጁ ይዳስልን፣ የተጨነቁትን በአጽናኙ ቅዱስ መንፈስ ያጽናናልን።

09/11/2025

አስደንጋጭ መረጃ አርሲ

በውስጥ የደረሰን መረጃ :- እኔ በዛው ቦታ ነው ያለሁት መረጃ እንኳን ለማን መስጠት እንዳለብን ተቸግረናል። በአይነ ቁራኛ ነው የምንጠበቀው። እስከዛሬ ድረስ በጀጁ ወረዳ በአንደጎቼ ሁላጨሌ ቀበሌ በኢጉ ጩካ ቀበሌ በሰንቢጤ ፊንጮ ቀበሌ በጉሬ ሙከጉራቻ ቀበሌ በአቡሌ ሙከጉራቻ ቀበሌ በወንጀሎ ወደይመና ቀበሌ እስካሁን ከመቶ በላይ ኦርቶዶክሶች ታርደ,ዋል።ተጨፍጭ,ፈዋል። ከግማሽ በላይ በጅብ ተበልተዋ,ል።

የጀጁን የክርስታያኖች ጭፍጨ,ፋ ማንም መረጃውን ያደረሰ የለም። ከእነዚህ ከታረ,ዱ ክርስቲያኖች መካከል ወንድማማቾች አባትና ልጅ የአጎት የአክስት ቤተሰብ ይበዙበታል ።

እንደዚህ መረጃ መስጠታችን ቢታወቅ መጀመሪያ እርምጃ የሚወስድብን የመንግስት አካል ነው።

የዛሬ 15 ቀን ልክ በዛሬዋ ዕለት የታገቱ ወገኖችን ትናንት ማለትም ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ ም ብር የሚያስገቡበት የመጨረሻዋ ቀን ናት። እያንዳንዱ 600 ሺህ ብር ነው የተጠየቁት ። ምናልባትም ከፍለውም ሊገደ,ሉ ይችላሉ።

ለምሳሌ በአንጎደቼ ቀበሌ 400 ሺህ ብር ከፍሎ የተገ,ደለ ወንድማችን መምህር ግርማ መለሰ ሌላም ስሙን ያላወኩት 280ሺህ ከፍሎ የተገደ,ሉ ናቸው።

በወሸባ በረከት ቀበሌ አንድ ካህን አባት 500ሺህ ብር ከፍለው ተገድ,ለዋል። እሬሳቸ,ውን ጅ,ብ ነው የበላ,ው ።

በአምሽራ መንጋግሳ ሁለት ወንድማማቾች 400ሺህ ብር ከፍለው እንደወጡ ቀርተዋል።

ይሄ ደጋማና ቆላማውን ክፍል ሳይጨምር የወይና ደጋውን ክፍል ነው ።

እንደ ወረዳው ከ500 እስከ 1000 ሺህ ኦርቶዶክሳዊያን ተጨፍጭፈ,ዋል።..............

#ኢትዮጵያ2018 #ሐበሻ #ኢትዮጵያ

07/11/2025
😭 ይህ በቅደስት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በሀገር ታሪክም ውስጥ ከማይረሱ ጥቁር ገጾቻችን አንዱ ነው።ይህ የዝምታችን ውጤት ነው። ይህ ለድክመታችን የቆመ ምስክር ነው። ************...
06/11/2025

😭 ይህ በቅደስት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በሀገር ታሪክም ውስጥ ከማይረሱ ጥቁር ገጾቻችን አንዱ ነው።

ይህ የዝምታችን ውጤት ነው። ይህ ለድክመታችን የቆመ ምስክር ነው።

*******************************************************

"እናቴን አምጡ" የሕፃኑ ታምራት አውግቸው ተማፅኖ።

እናትና አባት ከተጋቡ ወደ አስር ዓመት ገደማ እንዳስቆጠሩ የቅርቦቻቸው ይናገራሉ።

ኑሯቸው በምሥራቅ አርሲ ዞን በጉና ወረዳ ኖኖ ጃዌ ቀበሌ ነውና እንደ ሀገር እና አካበቢ ማኅበረሰብ ሁሉ የዕለት ጉርስ የዓመት ቀለብ የሚያገኙት ደረቁን መሬት አለስልሰው ፣ ከብቶች አርብተው ባገኙት ጥሪት ነው። የሕጻን ታምራት አውጋቸው ወላጆች።

የዚህ ብላቴና ቤተሰቦች በክርስትና ሕይወታቸውም ቢሆን ቤተክርስቲያንን ሳይሱሙና የፈጠራቸውን ሳይማልዱ ውለው አያድሩም። እንደ ቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መጾም ፣ መጸለይና ማስቀደስ ግዴታ መሆኑን በተግባር መፈፀማቸውንም መረጃውን ከነገሩን ከቅርቦቻቸው ሰምተናል።

የታምራት ቤተሰቦች በቀያቸው በነበሩበት ወቅት በትዳር አንድ ወንድና አንድ ሴት ልጅ አፍርተዋል ።

አበው እንደሚሉት የቀንም ጎዶሎ አለና በምሥራቅ አርሲ ዞን በጉና ወረዳ ኖኖ ጃዌ ቀበሌ በሚገኘው የመኖሪያ ቀያቸው ሐሙስ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ ሀገር ሰላም ቀየው አማን ብለው በተኙበት ሰዓትን ቆጥሮ ለመግደል የሚፋጠን እግርና እጅ ከለሊቱ 6:00 ላይ ወደ ኦርቶዶክሳዉያኑ ቤት አመራ።

ሞት በራቸውን ያንኳኳው የታምራት አውግቸው ቤተሰቦችና ጎረቤቶቻቸው በድቅድቅ ሌሊት እየተገፈተሩ ከቤታቸው በማስወጣት ከደጃፋቸው በሚገኘው ሜዳ ላይ ደርድረው አንበረከኳቸው።

በወቅቱ ብላቴናው ከእናቱ ጀርባ ላይ እንደነበር ያዩ ምስክሮች ነግረውናል።

ታዲያ የታምራት እናት እና አስራ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች በዘነበባቸው ተኩስ ሕይወታቸውን ማትረፍ ሳይችሉ እስከ ወዲያኛው ላይመለሱ አሸለቡ።

በሰዓቱ ሕፃን ታምራት ከመሬት ወድቃ የእናትነት ትንፋሿ ሲርቀው እናቱ ከወደቀችበት እንድትነሳ ይማፀናት ጀመር።

ይህንን የሰሙ እነዛ የታጠቁ ኃይሎች ልጅነቱ ሳያሳሳቸው ወገኖቹ የቀመሱትን ጥይት እነሆ ሲሉ ተኮሱበት።

ሕፃን ታምራት አውግቸውም በደረሰበት ጉዳት መቋቋም አቅቶት ከእናትና ከብዙ ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን አጠገብ ወደቀ።

በሰዓቱ የሚደርስላቸው ባለመኖሩ የብላቴናው እግር ላይ ያሉት የደም ስሮች ተፈጥሯዊ የደም መዘዋወራቸውን ለማከናወን ተሳናቸው።

አይነጋ የለምና በአስክሬን መሀል ራሳቸውን ከአገኙት መካከል አንዲት የ8 ዓመት ታዳጊ የሰው ያለህ እያለች ትጣራ ጀመር።

አካባቢ ከማታ ይልቅ በጥቂቱም ቀን የተሻለ ነውና ሕፃናቱን ወደ ሕክምና፣ ቤተሰቦቻቸውን ደግሞ አፈር ለማቅመስ በአካባቢው ወደ ሚገኘው አጥቢያ አመሩ።

በሕፃናቱ ላይ በደረሰው ከባድ ጉዳት አዳማ ለሕክምና ቢመጡም የታዳጊ ታምራት ጉዳት እጅጉን በማየሉ ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሊመጣ ችሏል።

ሕፃን ታምራት ከእግሩ ባሻገር ሌሎች የሰውነቱ አካላት ላይ ጉዳት ስለደረሰበት የሕክምና እርዳታ ሊደረግለት ችሏል።

ይሁን እንጂ የደረሰበት ጉዳት ከባድ በመሆኑ በሆስፒታሉ የሕክምና ባለ ሙያዎች ትእዛዝ መሰረት ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 አንድ እግሩ ሊቆረጥ ችሏል።

ይህ ብላቴና ከእግሩ መቆረጥ በተጨማሪ በቤተሰቡ ናፍቆት እየተሰቃየ ይገኛል ሲሉ አስታማሚዎቹ ይናገራሉ።

የሕመም ስቃዩን የአልቻለው ይህ ታዳጊ በአሁኑ ወቅትም "እናቴን አምጡ እያለ" ክፉኛ እንደሚያለቅስና ከፍተኛ ስነ ልቡናዊ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የሕፃን ታምራት ቤተሰቦች እና ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን ቤተክርስቲያንን ብለው በአካባቢው ባለመራቃቸው ይህ አይነት አሰቃቂ ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚሉት አስታማሚዎቹ ከጥቃቱ የተረፉትን ሕፃናት ልጆችን የመንከባከብ እና የማሳደግ ኃላፊነት የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ነው ይላሉ።

በተለይም ለብላቴናው ሰው ሰራሽ እግር ፣ ወደ ጤናው ሲመለስ ትምህርትና መሰል እገዛዎችን ከቤተክርስቲያንና ከምእመናን እንጠብቃለን ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በተመሳሳይ የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው የ8 ዓመቷ ታዳጊ የእነ ታምራት የቅርብ ጎረቤት ስትሆን በአሁኑ ወቅት በአዳማ ሕክምና እየተከታተለች ትገኛለች።

በአርሲ ሀገረ ስብከት በርካታ ኦርቶዶክሳዉያን በጭንቅ ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው ላሉት ልንደርስላቸው ለተጎዱት ድጋፍ ልናደርግላቸው ይገባል መልእክታቸው ነው።

የታምራት አባት ከዚያች ምሽት በኋላ የት እንደሚገኙ ማወቅ እንደማይቻል እና እህቱ ደግሞ ቤተሰብ ጋር መሆኗን ሰምተናል።

መረጃው EOTCMK TV ነው።

አሁንም አልነጋም የከበደው ሌሊትአርሲ ላይ ያለው የኦርቶዶክስ እልቂት ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዳ በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የተፈጸ...
05/11/2025

አሁንም አልነጋም የከበደው ሌሊት
አርሲ ላይ ያለው የኦርቶዶክስ እልቂት
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዳ በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የተፈጸመውን ግድያን በተመለከተ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ማብራሪያ ሰጥቶናል።
በዚሁ መሠረት በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ልዩ ስሙ ጋዶ ቅ/ጊዮርጊስ በተባለ ቦታ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ በአጨዳ ላይ በነበሩ 5 ግለስቦች ላይ ጭካኔ የተመላበት ግድያ መፈጸሙን የመርቲ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በቁጥር 033/2018 በቀን 25/02/2018 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ለሀገረ ስብከቱ አሳውቋል።
ሀገረ ስብከቱም ክስተቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረስ በመሆኑ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያደርግልን ጠይቋል።
በተያያዘ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባኤ በክስተቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ እንዲዋቀር ወስኖ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል ።

04/11/2025

♦️የኢትዮጵያ ፮ቱ ፓትርያርኮች....

ቃለ ሕይወት ያሰማልን መጋቤ ሐዲስ ኤፍሬም ተስፋ

♦️ተወዳጁና ትሑቱ የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍሬ የሆነው አርቲስት ዋሲሁን በላይ በትናንትናው ምሽት በሚሰራበት በብሔራዊ ቲያትር "አልንበረከክም" የሚል ድንቅ መጽሐፍ አስመረቀ።ዋስዬ በሁሉ...
04/11/2025

♦️ተወዳጁና ትሑቱ የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍሬ የሆነው አርቲስት ዋሲሁን በላይ በትናንትናው ምሽት በሚሰራበት በብሔራዊ ቲያትር "አልንበረከክም" የሚል ድንቅ መጽሐፍ አስመረቀ።

ዋስዬ በሁሉ ይወደዳል፣ ስብእናው ያስቀናል። ተወልዶ ያደገው በዚያው በፒያሳ በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ አካባቢ ነውና አሁን ለደረሰበት ሙያ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት ኮትኩታ ስላሳደገችው ስለ ሰማዕቱ እና ስለ እመቤታችን ተናግሮ አይጠግብም።

ከዚህም አንጻር ለብዙ ታላላቆች ዘማርያን ያበረከተው ግጥሞች አሁንም በየዓውደ ምሕረቱ ይዘመራሉ "ተዋሕዶ ሃይማኖቴ" የዘማሪት አዜብ ከበደ እንዲሁም ለዘማሪት ሲስተር ሕይወት እና ለሌሎችም ግጥም በመስጠት ይታወቃል።

በትናንትናው ምሽት አክባሪዎቹ በርከት ብለው በብሔራዊ ቲያትር ፍቅራቸውን ገለጹለት። በተለይ ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ልጆች የእመቤታችንን ሥዕል በስጦታ ሲያቀርቡለት በዕንባ ነበር የተቀበላት። እኛም በልዩ ደስታ የምትወዳት እናት እመብርሃን አትለይህ ብለን መልካም ምኞታችንን ገለጽን።

♦️ለልደት በዓል ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌምምዝገባችን እየተጠናቀቀ ነው 0978777888// 0977170707ቋንቋዬ ነሽ እና ኤል አኮቴት
03/11/2025

♦️ለልደት በዓል ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም
ምዝገባችን እየተጠናቀቀ ነው 0978777888// 0977170707
ቋንቋዬ ነሽ እና ኤል አኮቴት

Adress

Asogatan 79 I Stockholm
Stockholm
11829

Webbplats

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ Quanquayenesh Media postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Kontakta Affären

Skicka ett meddelande till ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ Quanquayenesh Media:

Dela