24/10/2025
ይህ በፎቶ የሚትመለከቱት የማንችስተር ሲት ተጫዋች ዶኮ አንድ ወቅት ከበተሰቡ ጋር በአንድ አፖርታማ ውስጥ ተከራተው ይኖሩ ነበር፡፡ የተከራዩበት ቤት ሳያስቡት ተሸጠ የገዛው ግለሰብ ጥቁሮችን የሚጠላ ሰው በመሆኑ እነርሱን ከምኖሩበት ቤት ቶሎ እንድለቁለት ጠየቃቸው እነርሱም እባክህን እየከፈልን እንኑርበት በማለት ይለምኑታል ሰውየው ግን በግድ ከቤቱ አስወጣቸው።ከጊዜ ቆይታ በኋላ ያ ከክራይ ቤት በግድ ውጣ ተብሎ የወጣው ዶኮ የታላቅ ክለብ ተጫዋች ሆኖ ብዙ ገንዘብ ባገኘ ጊዜ:- ያነ ከቤቱ ያስወጣቸው ሰው ያንን ተከራይተው ይኖሩበት የነበረውን በግድ የወጡበትን ቤት ልሸጥ እንደሆነ ሰማ፡፡ ቤቱን ዶኮ ገዛው ከዚያም በኋላ ቤት ለሌላቸው ለድሆች ያንን ቤት በነጻ ስጦታ ሰጣቸው። ተጫዋቹ ስናገር በህይወቴ የተደሰትኩበት ትልቁ ስከቴ ነው ብሏል፡፡
በሀገራችን በብዙ ከተሞችና በከተማችንም አንዳንድ አከራዮች ተካዮቻችሁን የሚትበድሉ ሳት እላፍ አትገባም እያላችሁ ሰዎች በቤተክርስቲያን ጉዳይ ብያረፍዱ ብያመሹ ግብ የሚትቆልፉ: አምፑል በራ ብላችሁ ቆጣር የሚታጠፉ፡አንድ ጀርካን ውሃ ይበቃሃል በማለት የውሃ ቆጣር የሚትዘጉ፡ሽንት ቤት በቀን ሁለቴ ብቻ ትጠቀማላችሁ የሚትሉ የተከራይን ቤት መኝታ ቤቱን ጭምር የሚትበረብሩ ከተከራይ እጅ ገንዘቡን እየተቀበላችሁ በነጻ እንደሰጠ ሰው እረፍት የሚትነሱ የተከራይ በተሰብ በድንገት ልጠይቅ ብመጣ አይናችሁ የሚቀላ ምን ሆናችኋል? ብትመለሱ ይሻላችኋል:: ሰው ገንዘቡን ከፍሎ እናንተ በግለሰቡ ገንዘብ መልካም ኑሮ እየኖራችሁ ግለሰቡ ገንዘቡን እየከፈለ ግን እየተሸማቀቀ ለምን ይኖራል? አንድ ቀን ለእርሱም ቀን ይመጣለታል ወይ ከእናንተ የተሻለ ቤት ወይ ከእናንተ ከተማ በተሻለ ከተማ ልኖረው እንደምችል አስቡ ሰውን አታስመሪሩ፡፡
ይህንን ስል ሁላችሁም የእግር ኳስ ተጫዋች ትሆናላችሁ እያልኩ አይደለም የዶኮ በረከት በእግሩ ላይ ነበረ፡፡የአንዳንዶቻችሁ በእጃችሁ፡በአንደበታችሁ፡በአእምሯአችሁ ወዘተ ልሆን ይችላል፡፡ባለብዙ መንገድ የሆነው እግዚአብሔር
ቤት የለላችሁ በክራይ የሚትጨነቁ እግዚአብሔር ቤት ይስጣችሁ።
አስተማርነው ካላችሁ ሼር አድርጉ፡፡