05/07/2025
                                            ቼልሲ በዓለም ክለቦች ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ክለቦች ዋንጫ ቼልሲ የብራዚሉን ፓልሜራስ 2 ለ 1 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
ሌሊት 10 ሰዓት ላይ በተደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ፥ የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ፓልመር እና ጉስቶ አስቆጥረዋል።
የፓልሜራስን ብቸኛ ግብ ኢስቲቫኦ ያስቆጠረ ሲሆን፥ ተጫዋቹ ባለፈው ክረምት ለቼልሲ ከፈረመ በኋላ ለአንድ አመት በፓልሜራስ እንዲቆይ ሁለቱ ክለቦች መስማማታቸው ይታወሳል።
ከቀናት በፊት ከብራይነት ቼልሲን የተቀላቀለው ዦአዎ ፔድሮ ለሰማያዊዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል።
በሌላ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር የብራዚሉ ፍሉሚኔንሴ ከሳዑዲ ፕሮ ሊጉ አል ሂላል ጋር ያደረጉት ጨዋታ በፍሉሚኔንሴ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ቼልሲ የፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን በግማሽ ፍጻሜው ፍሉሚኔንሴን ይገጥማል።                                        
 
                                                                                                     
                                                                                                     
                                         
   
   
   
   
     
   
   
  