Habeshistan Media/ሐበሺስታን ሚዲያ/

Habeshistan Media/ሐበሺስታን ሚዲያ/ �እውነተኛና ያልተዛቡ ታሪኮች
�አጫጭር ፅሁፎችና ትረካዎች
�ጠቃሚ ምክሮች እና አባባሎች
እንዲሁም
�ወቅታዊ ሁናቴዋችና መልዕክቶች
እናጋራችኋለን

❺ "ፍትህ በጉልበት እንደማይለካ ፣ እውነት ከደካሞችና ከጥቂቶች ጋር ቢሆን እንኳ ፣ ጊዜያዊ አሉታዊ ስሌቱን አብረን ተቀብለን ከባለ እውነቱ ጋር መቆምን" የነጃሺ ህይወት ያስተምራል።  በመጨ...
25/10/2023

❺ "ፍትህ በጉልበት እንደማይለካ ፣ እውነት ከደካሞችና ከጥቂቶች ጋር ቢሆን እንኳ ፣ ጊዜያዊ አሉታዊ ስሌቱን አብረን ተቀብለን ከባለ እውነቱ ጋር መቆምን" የነጃሺ ህይወት ያስተምራል።

በመጨረሻው ክፍላችን በአስደናቂው ፍትሀዊ፣ ገለልተኛና ነፃ #ችሎት ላይ #የመሰማት መብትን፣ #ፍትህ የማግኘት መብትን ፣ ከህግ በፊት እኩልነትን እንዲሁም ከሙስና መፅዳትን ፣የተገፉ ሰዎችን በፍቅር የማስጠጋት ባህልን ፣ ለአለም ስላስተዋወቁ ታላቅ መሪ/ንጉስ በማውሳት ለተከታታይ 5 ክፍል ስንወያይበት የነበረውን ቆይታ እናበቃለን።

በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻቸረን ላይ ያገኙናል
Facebook: TikTok: Telegram: YouTube:

Like👍🏼 share📤 subscribe
በማድረግ የዘወትር አጋርነቶን ያሳዩ። 🙏
ፕሮግራሙን ለመከታተል ኮሜንት መስጫ ሳጥን ውስጥ የሚለገኘውን ሊንክ 🔗 ይጫኑ::

«ያለፍትህ ከሄደች መርፌዬ በፍትህ የሄደች ግመሌ» 🖊️ሰሀቦች በሀበሻ ምን ገጠማቸው? ፣ የቁረይሽ ጮሌዎች ነጃሺን የመሸንገል ሙከራ? 📝የንጉስ ነጃሺ ገለልተኛና ፍርሀዊ ችሎት እንዴት ይቃኛል?...
17/10/2023

«ያለፍትህ ከሄደች መርፌዬ በፍትህ የሄደች ግመሌ»

🖊️ሰሀቦች በሀበሻ ምን ገጠማቸው? ፣ የቁረይሽ ጮሌዎች ነጃሺን የመሸንገል ሙከራ? 📝የንጉስ ነጃሺ ገለልተኛና ፍርሀዊ ችሎት እንዴት ይቃኛል? የሚሉ ወሳኝ ነጥቦች በአራተኛው ክፍል ተወየይተንበታል።

🎯ስለሚከታተሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ስለሚያጋሩልን እናመሰግናለን።

አስተያየት መስጫ ሳጥን ውስጥ የሚገኘውን ሊንክ በመጫን ፕሮግራማችንን ይከታተሉ።
የናንተው #ሀበሺስታን
Nejashi Bin Negashi Abdurezack Seid

❸ በሶስተኛው ክፍል ቆይታችን አሁን የስልጣኔ ማማ ላይ እንደተቀመጡ የሚሟግቱ ሀገራት ፤ ስደተኞችን እና ከትውልድ ቀያቸው በግፍ ተሰደው ጥገኝነተ እየጠየቁ ላሉ አካላት እያደረጉ ያለውን አፀፋ...
11/10/2023

❸ በሶስተኛው ክፍል ቆይታችን አሁን የስልጣኔ ማማ ላይ እንደተቀመጡ የሚሟግቱ ሀገራት ፤ ስደተኞችን እና ከትውልድ ቀያቸው በግፍ ተሰደው ጥገኝነተ እየጠየቁ ላሉ አካላት እያደረጉ ያለውን አፀፋዊ ምላሽ ፤ ከነጃሺ አርኣያዊ እንግዳ ተቀባይነት ጋር አያመሳከረ ቆይታ ያደርጋል ።

📍ስለ ስደተኛነት እና ጥገኝነት ስለሚጠይቁ አካላት ሁኔታ የህግ አንቀፆች እተነሱ ከተባጩ ጋር ያወዳድራል።

📍በኮሜንት ሳጥን ውስጥ የሚገኘውን ሊንክ በጫን ፕሮግራሙን እንዲከታተሉና ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲያጋሩ እንጋብዛለን።

"ምሥራቁ የኛ ነው፣ ምዕራቡም አንዲሁ እየሩሳሌም(አቅሳም) የኛው ነው፣ ድልም የኛ ነው!"ፋቲህ ኤርበካን የዛሬውን የአቅሳ አስገራሚ ውሎ አስመልክቶ ከተናገረው። 🤲ጌታችን ሆይ አንተ የተበደሉት...
07/10/2023

"ምሥራቁ የኛ ነው፣ ምዕራቡም አንዲሁ እየሩሳሌም(አቅሳም) የኛው ነው፣ ድልም የኛ ነው!"
ፋቲህ ኤርበካን የዛሬውን የአቅሳ አስገራሚ ውሎ አስመልክቶ ከተናገረው።
🤲ጌታችን ሆይ አንተ የተበደሉትን እንባ የምታብስ ፣ በዳዬችን በብርቱ የምትይዝ ጌታ ነህ።
እርዳታህን ፣ ሰላምህን. ድልህን ባንተ መንገድ ለሚለፉት ሁሉ ዘውታሪ አድርግልን። 🤲

 #ሀበሻ ለምን ተመረጠች?  #ነጃሺስ? ከባዱ የትግል አማራጭ (ሂጅራ፤ስደት) እነማንን ያካተተ ነበር?  እያለና ሌሎች ጥያቄዎችን እያነሳ  የጀመርነው ውይይት በክፍል ሁለትም ቀጥሏል። የንጉስ...
05/10/2023

#ሀበሻ ለምን ተመረጠች? #ነጃሺስ? ከባዱ የትግል አማራጭ (ሂጅራ፤ስደት) እነማንን ያካተተ ነበር? እያለና ሌሎች ጥያቄዎችን እያነሳ የጀመርነው ውይይት በክፍል ሁለትም ቀጥሏል።

የንጉስ ነጃሺን ሌጋሲ የሚያወሳውን ደማቅ ውይይት ክፍል ② እንድትታደሙ ዘንዳ ወደናንተ አቅርበናል።

ቻናላችንን ሰብስክራብ እያደረጉ ፕሮግራሙ ለሌሎችም እንዲዳረስ ሼር እንዲያደርጉ እንጋብዛለን።🙏

የኮሜንት ሳጥን ውስጥ የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ፕሮግራሙን መከታተል ይችላሉ።

በቱርክ ሀገር በሚኖሩ ተማሪዎች የተጀመረው ሀበሺስታን ሚዲያ ተመልሶ መቷል። በመጀመሪያ መሰናዶውም  #የነጃሺን የፍትሀዊነት ሌጋሲ አሁን እየተተገበሩ ካሉ የአለም አቀፍ ህጎች አንፃር ይቃኛል።...
03/10/2023

በቱርክ ሀገር በሚኖሩ ተማሪዎች የተጀመረው ሀበሺስታን ሚዲያ ተመልሶ መቷል። በመጀመሪያ መሰናዶውም #የነጃሺን የፍትሀዊነት ሌጋሲ አሁን እየተተገበሩ ካሉ የአለም አቀፍ ህጎች አንፃር ይቃኛል።

ሰሀቦች ወደ ሀበሻ ያደረጉትን ጉዞ ከነበረው መነሻ ገፊ ምከኒያቶች ጀምሮ ሂደቶቹን ተግዳሮቶቹን እንዲሁም ተምሳሌታዊ የሆኑ የንጉስ ነጃሺን ተግባራት ያወሳል።
የህግ ባለሙያው እና የፒ. ኤች. ዲ. ተማሪው አብዱረዛቅ ሰዒድ (Abdurezak seid) ከመሀመድ ነጋሽ (Nejashi Bin Negashi) ጋር ያደረጉትን ውይይት እድትከታተሉ እንጋብዛለን።

ፕሮግራሙን ለማግኘት በኮሜንት መስጫ ሳጥኑ ውስጥ የሚገኘውን ሊንክ ይጫኑ።

🇹🇷በቱርክ መንግስት የሚሰጠው አመታዊ የነፃ የትምህርት እድል ምዝገባ (application ) በያዝነው ወር በ Jan. 10 ክፍት የተደረገ ሲሆን እስከ ቀጣዩ ወር Feb. 20 ድረስ የሚቆይ ...
24/01/2023

🇹🇷በቱርክ መንግስት የሚሰጠው አመታዊ የነፃ የትምህርት እድል ምዝገባ (application ) በያዝነው ወር በ Jan. 10 ክፍት የተደረገ ሲሆን እስከ ቀጣዩ ወር Feb. 20 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
👨🏾‍🎓👩🏽‍🏭 ብዙዎች የሚወዳደሩበት ይህ አመታዊ የትምህርት እድል በሺዎች የሚቆጠሩ 🥇🥈አሸናፊዎችን 🇪🇹ኢትዮጲያን ጨምሮ ከሁሉም ሀገራት ተቀብሎ ያስተናግደል።

🏆በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ለምትፈልጉ ተከታዮቻችን ወንድም Duri በyou tube ገፁ ያቀረባቸውን ተከታታይ ፕሮግራሞች እንድትመለከቱ እንጋብዛለን።

🎖️መልካም እድል።
የተወሰኑት ፕሮግራሞች ከዚህ በታች ባሉት ሊንኮች ስር ተያይዟል።

¶| How to apply for Turkey scholarship | as an Ethiopian | Part 1
https://youtu.be/zZpFTineehg

¶| How to apply for Turkey scholarship | as an Ethiopian | Part 2
https://youtu.be/vqDkRZgcr7c

¶| How to write a good letter of intent
https://youtu.be/PfYRhLEXCU4

¶| How to win Turkey scholarship | Tips by Musa Mohammed
https://youtu.be/Qmnst9x39dU

How To Win The Turkish Scholarship | Tips | Seniors Advice - 3 | Ethiopian Students:

https://www.youtube.com/watch?v=RHHGm3pWpHE&t=17s

Scholarship 🔗
Link;
https://www.turkiyeburslari.gov.tr/

Telegram group link:
https://t.me/+5cSNSemjeHY1ZmJk

LIKE SHARE SUBSCRIBE

Raed Duri

How to Write a Good Letter of Intent/Essay | Turkey Scholarship | Ethiopian Students | AmharicFirst video: የቱርክ scholarship application ሊያልቅ 3 ሳምንት ብቻ ቀረው!/ ...

    🤲Hayatını kayıp edenlere Allahtan Rahmet… yaralılara acil şifalar diliyoruz. 🤲   olsun #በቱርክ ኢስታንቡል የቦንብ ፍንዳታ 📝ትላንት ...
14/11/2022

🤲Hayatını kayıp edenlere Allahtan Rahmet… yaralılara acil şifalar diliyoruz. 🤲 olsun
#በቱርክ ኢስታንቡል የቦንብ ፍንዳታ
📝ትላንት በተክሲም ጎዳና ተብሎ በሚጠራው የቱሪስት መዳረሻ ስፍራ በተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 21 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።📌 ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል ፈንጂውን አስቀምጣ ለመሰወር የሞከረችውንም ሴት ተጠርጣሪም ያካትታል።

📗በአደጋው 6 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ 80 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
🔴የደህንነት አካላት ፍንዳታው በሀገሪቷ በአሸባሪነት መዝገብ የተመደበው PKK ተብሎ የሚጠራው ቡድን እንደሆነ ገልፀዋል።

📮አደጋው ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሀዘን መግለጫ እየደረሰ ሲሆን፣ ቱርክ በሀገር ውስጥ ሚኒስትሯ በኩል አሜሪካን🇺🇸 ጨምሮ ይህን መሰል ግሩፕ ከጀርባ እየደገፉ ከፊት መጥተው ማስዛዘኛ የሚልኩ ሃገራትን የሀዘን መግለጫዎቻቸውን እንደመቀይቀበሉ ገልፀዋል።
🔶በአሁኑ ሰዓት አደጋው የደረሰበት ቦታ ወደ ቀድሞ ሰላሙ ተመልሶ ለ ጎብኞች ክፍት ተደርጓል።

 #የረሱል ሰ/ዐ/ወ የትዝብት ወቀሳ 🤔🤔🤔''ألا هل بلغت?  اللهم فشهد!''ይህ ቃል ከሰይዳችን የመጨረሻዎቹ የምስክር ቃል ውስጥ አንዱ ነው።ከስር በምስሉ ላይ የምናውቀው Diril...
27/10/2022

#የረሱል ሰ/ዐ/ወ የትዝብት ወቀሳ 🤔🤔🤔
''ألا هل بلغت? اللهم فشهد!''
ይህ ቃል ከሰይዳችን የመጨረሻዎቹ የምስክር ቃል ውስጥ አንዱ ነው።
ከስር በምስሉ ላይ የምናውቀው Diriliş Ertuğrul ተከታታይ ፊልም ላይ የኦቶማን መስራች የሆነውን የጋዚ ኡስማን የታዳጊነት ህይወት በማሳየት የርሱን ሚና የተጫወተው ታዳጊ ተዋናይ ነው።

🍇በአንድ አጋጣሚ ድንገተኛ ጥያቄ ተጠየቀ

🌺 ረሱልን አንድ ጥያቄ የመጠየቅ እድል ብታገኝ ምን ትጠይቃቸዋለህ ተባለ?

እንዲህ ሲል መለሰ ❤‍🩹>
#بلغ #الرسالة #وأدى #الأمانة #ونصح #الأمة #وجاهد #في #سبيل #ربه حق #الجهاد ولم يترك شيئاً
🌖? ያወቅነውን አለመኖራችንስ? ምን ይሉን ይሆን? 🤔🤔🤔

  olsun   በቱርክ አሳዛኙ እለት   በሚባለው ከተማ የድንጋይ ከሰል ማእድን ማውጫ ቁፋሮ ቦታ የደረሰው ፍንዳታ  41  ሰራተኞችን ለሞት የዳረገ ሲሆን 11 ሰራተኞች ደግሞ ከባድ ጉዳት አ...
16/10/2022

olsun በቱርክ አሳዛኙ እለት
በሚባለው ከተማ የድንጋይ ከሰል ማእድን ማውጫ ቁፋሮ ቦታ የደረሰው ፍንዳታ 41 ሰራተኞችን ለሞት የዳረገ ሲሆን 11 ሰራተኞች ደግሞ ከባድ ጉዳት አደርሶ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው። ሌሎች 15 ሰራተኞች ደግሞ ከቁፋሮው ቦታ ለማውጣትርብርብ እየተደረገ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰኣት ሁሉንም ማውጣት ተችሏል። ዘገባው እስከተጠናቀረበት ሰኣት ድረስ ስራው ላይ ከተሰማሩ 110 ሰራተኞች 58 ሰዎች ማዳን ተችሏል።
Bartındaki Şehit olan işcilere allahtan rahmet dileriz, mekanları cennet olsun., Ailelerine başsağlığı, yaralılarımıza acil şifalar dileriz.

ሰላተልጋኢብ በቅርበት መታደም ያልቻሉ የኢማሙ የሩቅ  ተከታዮች።ፋናቸው አለምን ያዳረሰው ታላቁ መሪ፣ የተበዳዮች ድምፅና አባት ፣ የሚዛናዊነት የትግል እና የተሀድሶው ጠቢብ ወደ እውነተኛውና ...
27/09/2022

ሰላተልጋኢብ በቅርበት መታደም ያልቻሉ የኢማሙ የሩቅ ተከታዮች።

ፋናቸው አለምን ያዳረሰው ታላቁ መሪ፣ የተበዳዮች ድምፅና አባት ፣ የሚዛናዊነት የትግል እና የተሀድሶው ጠቢብ ወደ እውነተኛውና አይቀሬው መንገድ ሲያቀኑ በሺዎች ሚቆጠሩ ሽኝታቸው ላይ ሲካፈሉ፤ ምንም እንኳ በአካል ቢርቋቸው የቅርብ ያህል የሚያዉቋቸው እና በፍቅራቸው የወደቁ አእላፍ ተከታዮቻቸው በአቅራቢያ መስጂዶቻቸው ሰላተል ጋይብ በመስገድ ከመልካም ዱዓዎቻቸው አድርሰውላቸዋል።

በቱርክ በብዙ ከተሞች በዋነኝነት በኢስታንቡሉ ፋቲህ ጃሚ እና የአንካራዉ ሀጂ ባይራም ጃሚ ዋነኞቹ ናቸው። በመስጂደል አቅሳ እንዲሁም በተለያዩ የአውሮፓ እና የአፍሪካ ሌሎችም ሀገራት ተጠቃሺዎች ናቸው። በተቃራኒው የትውልድ ቀያቸው ያሉ ወዳጆቻቸው ይህን እድል ባያገኙም (በሌሉበት የሞት ፍርድ ያዘዘው አገዛዝ ሰላተል ጀናዛም እንዳይሰገድ አዟል ተብሎ እየዘተዘገበ ይገኛል)

ሸይኽ አእምሮን ከፈጣሪ ራእይ፣ ሸሪዓዊ ድንጋጌን ከተጨባጭ ብያኔ፣ እውቀትን ከሀይማኖት ፣ አምልኮትን ከእምነት ፣ አስተሳሰብን ከስነምግባር ፣ ሀሳብን ከተግባር የማረቅ ብሂልን የሚያሳዩ ሚዛናዊ አካሄዶችን በጥናት እና ምርምር የሰደሩ፤ የመብት ማጉደል እና ድንበርርን ማለፍ መሀል ያለውን ፍትሀዊና ሚዛናዊ መንገድን ያሳዩ ፤ሁሉም ማህበረሰብ ባለበት ተጨባጭ አማኝ መሆን የሚችልበት መንገድ ሁሉ ያመላከቱ፣ ለብዙዎች በእስልምና ለለማረክ ሰበብ የሆኑ፣ የነብዩን ሰ/ዐ/ወ የእውቀት ውርስ በልኩ ሰድረው ለቀጣዩ ትውልድ ያስረከቡ፣ በደለኛን ከአፍላነት እስከ እርጅና ፊት ለፊት በወጥ አቋም የተጋፈጡ አይተኬ የለውጥ መሀንዲስ ነበሩ።
.. እውነትም >
እንዲህ ብለው ነበር… ንዝረት በሚጥርው ኝግግራቸው ላይ. (የእርግጠኝነቴ)ብርሃን በልቤ፤ ልቤም በጌታዬ እጅ ነው። ጌታዬም አጋዤና ረዳቴ ነው።
በእምነቴ ገመድ ላይ ፀንቼ እዘልቃለሁ፤ ለዲኔ ህያውነት በፈገግታ ሞትን እቀበላለሁ»

እስከመጨረሻው እጣቸው ለአመኑበት ኖሩለት አመኑ ፣ ሰሩ፣ ለፉ፣ ታገሉ አታገሉ፣ ታሰሩ፣ ተሰደዱ፣ ተንከራተቱ።

እንዳለው ያ ታላቁ ሰው።

በእዝነቱ ይቀበላቸው።
ከመልካም ዘመን_አይሽሬ ሁለንተናዊ ስራዎቻቸው የምንጠቀም ያድርገን።
ሰላም እና እርጋታችንን ያብዛልን።

 #ሂጅራ 🌄ለእምነት እና ለዓላማ ሲባል ወደ አዲስ አድማስ የሚደረግ አስቸጋሪና አይቀሬ የሆነ ጉዞ ነው።  #ሂጅራ 🎇በአላህ ላይ የማመን ፣የእውነተኝነት እና የታዛዥነት ፣የትእግስተኝነት እና ...
30/07/2022

#ሂጅራ 🌄ለእምነት እና ለዓላማ ሲባል ወደ አዲስ አድማስ የሚደረግ አስቸጋሪና አይቀሬ የሆነ ጉዞ ነው።

#ሂጅራ 🎇በአላህ ላይ የማመን ፣የእውነተኝነት እና የታዛዥነት ፣የትእግስተኝነት እና የፅናት ምልክት ነው።

#ሂጅራ 🎆 ተውሂድን ሙጥኝ ማለት እና ሽርክን መራቅ ነው።

#ስደት 🌌ከውሸት የመራቅ እና ወደ እውነት የመመለስ አርማ ነው።
(የቱርክ🇹🇷 ሚንበሮች 1444ኛውን የነብዩና ሙሀመድ ስደት ሲያወሱ)
#የአማን #የሰላም #የፀጋ #የስኬት ያድርግልን
🇪🇹 هجرة #

21/07/2022

አላህን ማናገር ስትፈልግ…

🌕ሀጃጆቹን በቤቱ የተቀረነውን በቤታችን ላከበረና ላላቀ ፈጣሪ ጥራት ይገባው።🌺ለኛ በዓረፋ ፆም ሲኖረንለነርሱ(ለሁጃጆች) በዓረፋ መቆምን ተሰጡ… 🌹ለኛ ተክቢራ አለን ለነርሱ ተልቢያ… 🪷ለነርሱ...
08/07/2022

🌕ሀጃጆቹን በቤቱ የተቀረነውን በቤታችን ላከበረና ላላቀ ፈጣሪ ጥራት ይገባው።
🌺ለኛ በዓረፋ ፆም ሲኖረን
ለነርሱ(ለሁጃጆች) በዓረፋ መቆምን ተሰጡ…
🌹ለኛ ተክቢራ አለን ለነርሱ ተልቢያ…
🪷ለነርሱ ሀድይ ለኛ ኡድሂያ…

🤲ሀጃጆቹን በቤቱ የተቀረነውን በቤታችን ላከበረና ላላቀ ፈጣሪ ጥራት ይገባው።🤲
እለቱ ሀጃዎች ተቆጥረው ሚለመኑበት፣ ወቅቱም በግልፅ ተቀባይነት ያለበት ነው።
🤲ስለ ሁለቱም ዓለም ጉዳዮቻችንን በዝርዝር እንለምነው።

بالتوفيق
كل عام وأنتم بخير!!! 💚💕

ለትርፋማው ንግድ ከዱንያ ቀናቶች ሁላ በላጭ የሆኑትን ቀናት እንዴት እንጠቀም?! እጅግ በጣም ቀላል የሆኑ  የአላህን ተውፊቅ እና የኛን ትንሽ ቁርጠኝነት የሚፈልጉ ትንሽ ሀሳቦችን እንጠቁም። ...
29/06/2022

ለትርፋማው ንግድ ከዱንያ ቀናቶች ሁላ በላጭ የሆኑትን ቀናት እንዴት እንጠቀም?!

እጅግ በጣም ቀላል የሆኑ የአላህን ተውፊቅ እና የኛን ትንሽ ቁርጠኝነት የሚፈልጉ ትንሽ ሀሳቦችን እንጠቁም።

1/ ኒያን በማጥራት ከአላህ ጋር ያለንን መንፈሳዊ ግንኙነት ለማሳደግ እውነተኛ ቆራጥነት።
"ለአላህ እውነተኛ የሆነ ሀሳቡን እውን ያደርግለታል"

2/ እውነተኛ ንሰሀ ፣ የሂዳያ መንገድ ከተውበት ይጀምራልና። ስህቶቻችን ቆጥረን ይቅርታ ጠይቀን፣ በሰራነው ተፀፅተን ፣ ላንመለስበትም ቆርጠን መንገዱን መጀመር ይጠበቅብናል።

3/ አምስት ወቅት ሰላቶችን ለአላህ በሚገባው መልኩ ለጉድለታችን በሚያስፈልገን ልኩ ወቅቱን ጠብቀን መፈፀም።
«በላጩ መልካም ስራ ሰላትን በወቅቱ መፈፀም ነው »

4/ 12ቱ በላጭ የሆኑ የቀብሊያና ባዕዲያ ሱናዎችን ማዘውተር
እኚህ ሰላቶች ግዴታ ሰላቶቻችንን የሚጠግኑልን ከመሆናቸውም ጋር ጠብቆ ለሰገደው ሰው "ጀነት ላይ ቤትን እንደሚገነባለት" ቃለ ተገብቶለታል።
(ከሱብሂ በፊት 2፣ ከዙህር በፊት 4 ፣ከዙህር ቡሃላ 2፣ ከመግሪብ ቡሃላ 2፣ ከዒሻ ቡኻላ 2 ብቻ።)

5/ የሌሊት ስግደት
በሌሊቱ በየትኛውም ክፍል አነስተኛ አንድ ረከዓን ለመስገድ መታገል።
"ሰዎች በተኙ ጊዜ ስገዱ
ጀነትንም ሰላማዊ ማረፊያቹ አድርጉ" የሚለው ነብያዊ አስተምህሮ ውስጥ መች ነው ምካተተው ብሎ ነፍሲያን መጠየቅ።

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ፣ የቱርክ 🇹🇷 መንግስት ፕሬዝዳንት  #ኤርዶ*ኣንን ጨምሮ ብዙ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ባለስልጣናት በተገኙበት ፣ ብዙ ዑለማእ እና ዱዓት በታደሙበት እ...
24/06/2022

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ፣
የቱርክ 🇹🇷 መንግስት ፕሬዝዳንት #ኤርዶ*ኣንን ጨምሮ ብዙ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ባለስልጣናት በተገኙበት ፣ ብዙ ዑለማእ እና ዱዓት በታደሙበት እና ንግግር ባደረጉበት በ #ኢስታንቡል ታላቁ #መህመትፋቲህ መስጂድ ላይ ዛሬ ጁን 24/2022
🌙ለ ታላቁ ሊቅ ሸይኽ #ማሕሙድ ኤፌንዲ ዱዓ ተደርጎ ሰላተል ጀናዛ ተሰግዶ የክብር ሽኝት ተደርጓል።
🌑 ሼኽ ሜህሜት ኤፌንዲ በ93 ዓመታቸው (በአንድ ልጃቸው ገለፃ በ95) ይህን አለም የተሰናበቱ ሲሆን።
🌖ገና በልጅነት እድሜ በ16 አመታቸው በብዙ የዒልም ዘርፎች የማስተማር ኢጃዛን በማግኘት ነበር የዳዕዋውን ትግል ሀ ብለው የጀመሩት።
🌖እነሆ አንድ ምእተ አመትን በቀረበ መልኩ ብዙ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች መሀል አልፈው ሸይኽ ማሕሙድ አፈንዲ በዓለም ዙሪያ በርካታ ተማሪዎች አፍረታዋል፣ ቅናቻ መንገድን አሳይተዋል፣ አላህን አስተዋውቀዋል፣ ለብዙዎች የሂዳያ ሰበብ ሆነዋል። በጀርመን በአሜሪካ በሌሎችም ሀገራት በተለይም የፋርስ ዓረብኛ እና ቱርክኛ ቋንቋ ብቁነታቸው ጋር ዳዕዋውን ለማሰራጨት በብዙ ሀገራት ታግለዋል።
🌕ሁሉም በአንድ ድምፅ እንደሚመሰክርላቸው ብዙ የመንግስታት መለዋወጥ ጫና አስደርጎ ከአቋማቸው ሳያዘናጋቸው እውነተኛ ዑለማኡ ረባኒ በመሆን እውነትን ይዘው በሺዎች የሚቆጠሩ ዑለሞችን እና ሁፋዞችን አፍርተዋል።

🤲አላህ ባማረው አቀባበሉ በእዝነቱ እንዲያካብባቸው ለኛም ፈተና እና ችግሮቻችን አንስቶልን ሰላም እና ደስታን እንዲሰጠን አብዝተን እንለምናለን።

🌟150,000 ኡስታዞችን, በ 90,000. መስጂዶች እና, 40,000 የቁርኣን መማሪያ መድረሳዎች አሰናድቶ ኑ የልጆቻችንን ወደፊት አለም በቁርኣን ኑር እናብራ ሲል በየመስጂድ ሚንበሮቹ 🇹🇷 ...
17/06/2022

🌟150,000 ኡስታዞችን, በ 90,000. መስጂዶች እና, 40,000 የቁርኣን መማሪያ መድረሳዎች አሰናድቶ ኑ የልጆቻችንን ወደፊት አለም በቁርኣን ኑር እናብራ ሲል በየመስጂድ ሚንበሮቹ 🇹🇷 የቱርክ ሀይማኖት ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪ አድርጓል።

✨✨"በንፁህ እና በጠራ ተፈጥሮ የተወለዱትን የአይን ማረፊያ ልጆቻችን አላህን በማላቅ ፣ በአምልኮ ፍቅር ንቃተ ህሊና በማሳደግ መልካም ሰዎች እና ቆንጆ ሙስሊም አድርጎ ማብቃት የኛ ኃላፊነት ነው።" ሲሉ አስታውሰዋል።

አክለውም« ⚽🏀 በስሩ ከሚገኘው የወጣቶች እና ህፃናት መምሪያ ጋር በመተባበር ግማሽ ቀኑን ከቁርኣን እና የዲን ትምህርቶች ጋር ግማሽ ቀኑን ደግሞ ከ እስፖርት (🏈🎳)እና መዝናኛዎች ጋር ለማሳለፍ ዝግጅቱን አጠናቋል ሲል » አስተዋውቀዋል

✨✨በኛስ ሀገር ስንት መስጂዶች ስንት መድረሳዎች ከመዝናኛ ማእከላት ጋር በመሆን ለልጆቻችን ቁርአንን ለማውረስ ተዘጋጅተው እየጠበቁ ይሆን?

«geçmiş bayram mübarek olsun» «ያለፈው በዓል የተባረከ ይሁንልን» እንደማለት ስለ  #ጥርስ ኪራይ ፣  #የእዳ ደብተር፣  #ካርኮር የተባለውን ጨዋታ፣  #የረመዳን ዱፍ እና ...
23/05/2022

«geçmiş bayram mübarek olsun» «ያለፈው በዓል የተባረከ ይሁንልን» እንደማለት
ስለ #ጥርስ ኪራይ ፣ #የእዳ ደብተር፣ #ካርኮር የተባለውን ጨዋታ፣ #የረመዳን ዱፍ እና መድፍ እንዲሁም ሌሎች ባህል እና ልምዶችን እናስቃኛቹሀለን። ሊንኩን በመጫን ይከታተሉ።
መልካም ጊዜ ከሰላምታ ጋር።
https://youtu.be/nGagWNnG_yM

Address

Sıhhıye

Telephone

+905466442138

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habeshistan Media/ሐበሺስታን ሚዲያ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Habeshistan Media/ሐበሺስታን ሚዲያ/:

Share