Afro Soccer Ethiopia / አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ

Afro Soccer Ethiopia / አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን ፤ አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ክብር ለቀደምት ተጫዋቾቻችንን

የዳዊት ምርጥ 11የሌጀንድ ዳዊት እስጢፋኖስ የምንግዜም ምርጥ 11 ። የዳዊት ምርጫ እንዴት ነው? ሀሳብ አስተያየት ስጡበት (ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)🎁ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው...
09/21/2025

የዳዊት ምርጥ 11

የሌጀንድ ዳዊት እስጢፋኖስ የምንግዜም ምርጥ 11 ። የዳዊት ምርጫ እንዴት ነው? ሀሳብ አስተያየት ስጡበት
(ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)

🎁ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁

የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ🎁🎁🎁🎁
🎁🎁🎁🎁 የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁🎁

ከሻምፒዮኖቹ የእናንተ ምርጥ ማነው?በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ እነዚህ የሴካፋን ዋንጫ ያመጡልን ተጫዋቾች ተጠቃሾች ናቸው ።  ሲጫወቱ ያያችዋቸው ትው...
09/21/2025

ከሻምፒዮኖቹ የእናንተ ምርጥ ማነው?

በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ እነዚህ የሴካፋን ዋንጫ ያመጡልን ተጫዋቾች ተጠቃሾች ናቸው ። ሲጫወቱ ያያችዋቸው ትውስታችሁን አጋሩን ። የምታደንቁት ማንን ነበር? የቡድኑስ ጥንካሬ ምን ነበር?
(ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)

🎁ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁

የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ🎁🎁🎁
🎁🎁🎁 የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁

እነዚህ ሌጀንዶች እነማን ናቸው ?በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ ተጠቃሽ የሆኑት እነዚህ ተጫዋቾች እነማን ናቸው? ሲጫወቱ ያያችዋቸው ትውስታችሁን አጋሩን...
09/20/2025

እነዚህ ሌጀንዶች እነማን ናቸው ?

በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ ተጠቃሽ የሆኑት እነዚህ ተጫዋቾች እነማን ናቸው? ሲጫወቱ ያያችዋቸው ትውስታችሁን አጋሩን
(ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)

🎁ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁

የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ🎁🎁🎁
🎁🎁🎁 የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁

ይህ ሌጀንድ ማነው?በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ አንዱ የሆነው ይህ ተጫዋች ማነው? ሲጫወት ያያችሁት ትውስታችሁን አጋሩን (ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)🎁...
09/20/2025

ይህ ሌጀንድ ማነው?

በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ አንዱ የሆነው ይህ ተጫዋች ማነው? ሲጫወት ያያችሁት ትውስታችሁን አጋሩን
(ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)

🎁ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁

የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ🎁🎁🎁
🎁🎁🎁 የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁

ይህ ሌጀንድ ማነው?በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ አንዱ የሆነው ይህ ተጫዋች ማነው? ሲጫወት ያያችሁት ትውስታችሁን አጋሩን(ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)🎁ኮ...
09/19/2025

ይህ ሌጀንድ ማነው?

በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ አንዱ የሆነው ይህ ተጫዋች ማነው? ሲጫወት ያያችሁት ትውስታችሁን አጋሩን
(ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)

🎁ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁

የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ🎁🎁🎁🎁
🎁🎁🎁🎁 የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁🎁

አሰግድ ተስፋዬ (ጅሬስ፣ ሮማሪዮ፣ ፔሌ)                  (1962-2009)                   አስደናቂ የኳስ ተሰጥኦ የተካነው አሰግድ በዘመኑ ኢትዮጵያውያንን የእግርኳስ...
09/15/2025

አሰግድ ተስፋዬ (ጅሬስ፣ ሮማሪዮ፣ ፔሌ)
(1962-2009)

አስደናቂ የኳስ ተሰጥኦ የተካነው አሰግድ በዘመኑ ኢትዮጵያውያንን የእግርኳስ ታዳሚዎች ጮቤ አስረግጧል። መነሻውን ከድሬ የአሸዋ ሜዳ ያደረገው አሴ
🔸 ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
🔸ለቅዱስ ጊዮርጊስ
🔸ለኢትዮጵያ መድህን
🔸ለኢትዮጵያ ቡና ተጫውቷል

⚽⚽የአስግድ ስኬቶች
👉 በአንድ ውድድር ዘመን አምስት ጊዜ ሀትሪክ በመስራት ባለ ክብረወሰን ነው ፤ በብሔራዊ ቡድን ደረጃም ከምንግዜም ከፍተኛ ጎል አቆጣሪዎች ተርታ አንዱ ሆኗል፡፡

👉ኳስ እያንከባለለ ወደ ግብ ክልል ሲምዘገዘግ ደጋፊው ለመጨፈር ይዘጋጃል ፤ የሚያደርገውን ያውቃሉ እና.....

✅አሰግድ ከተጨዋቾች ጋር የነበረው ጥምረት

👉አሸናፊ በጋሻው ቡናን ከመፈረካከስ የታደገበት ቁልፍ ተግባሮቹ አንዱ በክለቡ ውስጥ ብቻውን በቀረበት በዛ ዘግናኝ ወቅት አሰግድን አግባብቶ አሳምኖ ከመድን ወደ ቡና ማምጣቱ ነበር ( አሰግድ ቡናን ሲቀላቀል የቡና ተጫዋቾች ብዛት ሁለት ሆነ ) ፤ ሁለቱ በኳስ ላይም ያለቃላት ይናበቡ ነበር ።
👉አሰግድ እና ካሳዬም ጥምረታቸው እንደ ኢኒየስታ እና ሜሲ ነበር ። ሁለቱም እጅግ አስደናቂ የኳስ ክህሎት አላቸው ።
👉ቴዲ ቦካንዴ የአሰግድን እንቅስቃሴ ለማመን በሚከብድ ደረጃ ፈጥኖ ይረዳል ። አሰግድ አልሀሊ መረብ ላይ ያሳረፋትን የመቀስምት ኳስ በተመጠነ ከፍታ ያውም በጣም ቅርብ ከሆነ ርቀት ያቀበለው ቴዲ ቦካንዴ ነው ።
"በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የምን ጊዜም ምርጧን ጎል ያስቆጠረው አሰግድ ተስፋዬ ነው ፣ አመቻችቶ ያቀበለው ቴዲ ቦካንዴ ከካሳዬ የተሻገረለትን ኳስ ነው ፣ ጎሉ የተቆጠረው በግብፅ ክለብ ላይ ነው " ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ።

ሮናልዶ ፣ ቤል ፣ ሩኒ ...ያስቆጠሯቸውን የመቀስ ምት ጎሎች የኛው አሰግድ ተስፋዬ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሯል - ያውም ከነሱ ዘመን ቀድሞ። ጎሏ የተቆጠረችው በምን ጊዜም ተቀናቃኛችን በግብፅ ክለብ ላይ መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ያኮራል ።
✅አሰግድ እና የቡና ደጋፊዎች
ቡናዎች ጎል ሲጠማቸው ፤ ድል ሲርባቸው የቡድናቸውን ሞተር የሚያጋግሉበት ድንቅ ጥበብ ነበራቸው (የቀድሞዎቹ)። በታፈሰ ዘመን እንዳየነው ሁሉ በአሰግድ ዘመንም ፡


"አሴ አሴ ፡ ጎል ጎል" እያሉ የጎል ማሽናቸውን ባግባቡ ያግሉታል ፤ ማሽኑም የሚፈልጉትን ጎል ያመርትላቸዋል!!!
(አሁን ያለን ደጋፊ አላልንም)

✅አሰግድ ከሜዳ ውጪ
አሰግድ ከሜዳ ውጭ የነበረው ባህሪ ቅንነት የተሞላበት ነው። ተጫዋቾች ሲታመሙ ፣ የኑሮ ችግር ላይ ሲወድቁ፣ወይንም ሲጠፉ ቀድሞ ጠያቂ ፤ ረጂ ፤ አስታዋሽ አሰግድ ነው ፤ ድጋፎችን ያስተባብራል። በፈገግታና በቀልዶቹ እያዋዛ የሚለግሳቸው ምክሮቹም አፅናኝ ናቸው።
👉አሰግድ ባለትዳር እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበር
👉 አሴጋ በተሰኘው አካዳሚ ታዳጊዎችን ያሰለጥን ነበር

⚽የአሰግድ ህልፈት
👉ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ.ም በድንገት በመታጠቢያ ክፍል ውስጥ ወድቆ በተወለደ በ 47 ዓመቱ በሞት የተለየን አሴ የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበር።

የቀደሙትን እያነገስን ፤ አዲሶቹን እያሳደግን ፤ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁 አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ🎁🎁🎁
🎁🎁🎁 የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁

Subscribe to get exclusive benefits:
https://www.facebook.com/100064088501389/subscribenow

እነማን ናቸው ?በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ? ሲጫወቱ ያያችዋቸው ትውስታችሁን አጋሩን(ለምስሉ ጥራት ...
09/15/2025

እነማን ናቸው ?

በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሌጀንዶቻችን ተርታ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ? ሲጫወቱ ያያችዋቸው ትውስታችሁን አጋሩን
(ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)

🎁ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁

የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ🎁🎁🎁🎁
🎁🎁🎁🎁 የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁🎁

Subscribe to get exclusive benefits:
https://www.facebook.com/100064088501389/subscribenow

ዳዊት እስጢፋኖስ ፡ የመሀል መዳው ሞተርደጋማዋ ባሌ ጎባ ለኢትዬጵያ እግርኳስ የድርሻዋን አበርክታለች - ጥበበኛውን ሌጀንድ ዳዊት እስጢፋኖስን ሰታናለችና ።፡ አጋርፋ ተወልዶ አዲስ አበባ እስ...
09/14/2025

ዳዊት እስጢፋኖስ ፡ የመሀል መዳው ሞተር

ደጋማዋ ባሌ ጎባ ለኢትዬጵያ እግርኳስ የድርሻዋን አበርክታለች - ጥበበኛውን ሌጀንድ ዳዊት እስጢፋኖስን ሰታናለችና ።፡ አጋርፋ ተወልዶ አዲስ አበባ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ያደገው ይህ የእግርኳሳችን ፈርጥ ከኢትዮጵያ የምንግዜም ምርጥ አማካይ ተጫዋቾች ተርታ ስሙን በደማቁ ፅፏል ። ዳዊት ኳስ የጀመረው በሰፈር ውስጥ በመጫወት ቀጥሎም በፕሮጀክት በመታቀፍ ሲሆን ጅማሮው ላይ በተከላካይ እና በመስመር ስፍራ ተጫውቷል ።

ክለብ

✅ባንኮች ፡ 1994- 1999 ከ ሲ እስከ ዋናው ቡድን ለ6 አመታት
✅መከላከያ ፡ ከ2000-2002 አጋማሽ እና 2011-2012
✅ደደቢት ፡ ከ2002 አጋማሽ -2003
✅ ኢትዮጵያ ቡና ፡ ከ2003-2007
✅ድሬዳዋ ፡ 2008-2009 እና 2014-2016
✅መብራት ሀይል ፡ ከ2009-2010
✅ፋሲል ከነማ ፡ 2010-2011 አጋማሽ
✅ሰበታ ከተማ ፡ 2012-2013
✅ጅማ አባጅፋር ፡2013-2014

🎁🎁ስኬቶቹ 🎁🎁
🎁 1የኢትዮጵያ ጥሎማለፍ ዋንጫ 2002
🎁1 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ከቡና ጋር
🎁1የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ከቡና ጋር
🎁 1 የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ከመከላከያ ጋር
🎁2 የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ከቡና እና ከመብራት ኃይል ጋር

🎁 ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት
✅ለኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን
✅ ለኢትዬጵያ ብሔራዊ ቡድን 2000-2006
(የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራችን በተሳተፈችባቸው ውድድሮች ላይ በመሰለፍ ሐገራችንን አገልግሏል)
🎁አስደሳቹ ጊዜው
✅ ዳዊት በእግርኳስ ህይወቱ ምርጡን ጊዜ ያሳለፈው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ዋንጫ ባነሳበት እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ባለፈበት ወቅት ነው ።
🎁አሳዛኙ ጊዜው
የሌጀንድ ዳዊት እስጢፋኖስ የእግርኳስ ህይወት አሳዛኙ ወቅት ከሚወደው ክለብ ከኢትዮጵያ ቡና በድንገት የተለየበት ወቅት ነው ።
🎁ኳስ ያቆመው

ዳዊት እስጢፋኖስ ጫማውን የሰቀለው 2017ዓም ነው ። ብዙ መጫወት እየቻለ ኳስ ያቆመበት ምክንያት የሀገራችን እግርኳስ የብሄር ፤ የእምነት ፤ የአካባቢ ጎጠኝነት እየተንሰራፋበት በመምጣቱ እና በዚህ ውስጥ መቀጠል ስላልፈለገ ነው ። ዳዊት እስጢፋኖስ ጠንካራ አቋም እና መልካም ስብእና የተላበሰ እንደሆነ የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክራሉ ። ኳስ ካቆመ በኋላ የራሱ የእግርኳስ ፕሮጀክት ላይ እየሰራ ይገኛል - ተተኪ ተጫዋቾችን ለማፍራት 🎁 በቀጣይም በአሰልጣኝነት ለመምጣት አስፈላጊ ዝግጅት ላይ ይገኛል ።
ባለ ትዳር እና የአራት ልጆች አባት የሆነው ይህ የእግርኳሳችን ባለውለታ በአዲስ አበባ እየኖረ ይገኛል ።
⚽ሌጀንድ ዳዊት የመረጠውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምንግዜም ምርጥ 11 በቅርቡ እናቀርበዋለን ።

ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁

የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ 🎁🎁🎁
🎁🎁🎁የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁

በላይነህ አስቻለው: በላያ ሌጀንድ በላያ ጥም ቆራጭ አጥቂ ነው ፡ ይህ አይረሴ የእግርኳሳችን ክስተት  አዲሱ ገበያ ፤ ጉቶ ሜዳ ፤ እና ዘበኛ ሰፈር ተወልዶ ያደገባቸው እና የእግርኳስ ታሪኩ ...
09/11/2025

በላይነህ አስቻለው: በላያ

ሌጀንድ በላያ ጥም ቆራጭ አጥቂ ነው ፡ ይህ አይረሴ የእግርኳሳችን ክስተት አዲሱ ገበያ ፤ ጉቶ ሜዳ ፤ እና ዘበኛ ሰፈር ተወልዶ ያደገባቸው እና የእግርኳስ ታሪኩ መነሻዎቹ ናቸው ። የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈበት የጨርቅ ኳስ የህይወት መስመሩ ሆነ ፤ በተለይ ጌትዬ አስቻለው የተባለው ታላቅ ወንድሙ የመድን ተጫዋች መሆኑ በክለብ ደረጃ የመድንን ማሊያ ለብሶ መጫወት ህልሙ እንዲሆን ምክንያት ሆኖታል ። በብዙ ጥረቱ ህልሙን አሳክቶ 1982 መድንን ቢቀላቀልም ከአንድ አመት በላይ ሊቆይ አልቻለም ፤ 1983 ፖሊስን ተቀላቀለ ። እድሜው ለጋ ቢሆንም ከአንጋፋዎቹ ከነ ተስፋዬ ፈጠነ እና ሙሴ ሃይለማርያም ጋር ተሰልፎ ውድድሩን በከፍተኛ ጎል አግቢነት ይመራ ጀመር ።የኳስ ችሎታው ልዩ ነበርና የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ሳይቀሩ በአድናቆት አጨበጨቡለት ። ሆኖም በዚሁ አመት ውድድሩ በመቋረጡ የበላያ የጎል ማግባት ግስጋሴ ተገታ ።
በላያ 1985 ወደ መድን ተመልሶ እስከ 1989 ድረስ ድንቅ ብቃቱን አሳየ ።

🎁አስደናቂ ስኬቶቹ 🎁
🎁ከመድን ጋር 2 ዋንጫ ሻምፒዮን ሆኗል(የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ)

🎁 ከኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድኑ ጋር የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆኗል
🎁የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል (ኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱንም በሰመዖን አባይ በአንድ ጎል ተበልጦ ነው ያጣው)
🎁ከመሀል ሜዳ ጋና ብሄራዊ ቡድን ላይ እጅግ ማራኪ ጎል አስቆጥሯል👌

🎁በብሄራዊ ቡድን በሁሉም እርከን ተጫውቷል
✅ የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን
✅ የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን
✅የኢትዮጵያ ዋናው ብሄራዊ ቡድን

🎁አብሯቸው ከተጫወታቸው ሌጀንዶች ተጠቃሾቹ
✅ሙሉጌታ ከበደ
✅ደሳለኝ ገብረጊዮርጊስ
✅ተስፋዬ ኦርጌቾ
✅አሰግድ ተስፋዬ
✅ኤሊያስ ጁሀር
✅አሸናፊ ሲሳይ
✅ፍሰህ በጋሻው
✅ጉልማ
✅ብሩክ ካንቶና

🎁አይረሴ ገጠመኞቹን ከራሱ አንደበት 🎁
ልጅ እያለሁ አባቴ ቀለበት ስጦታ ሰጥቶኛል ፤ ይህ ቀለበት ከጣቴ ወልቆ አያውቅም ነበር ፤ ስጫወትም በፋሻ ጠቅልዬ ነበር ሜዳ ምገባው ፤ ጣልያን ከመጣሁ በኋላ አንድ ጨዋታ ላይ ቀለበቱን እንዳወልቅ አስገደዱኝ ፤ እናም በብዙ ትግል በፒንሳ ከጣቴ ላይ ወጣ ፤ እና እያለቀስኩ የተጫወትኩትን አይረሳኝም። የሆነ አካሌ የተቆረጠ ያህል ነው የተሰማኝ ።
ሌላው ኡጋንዳ የሆነውን... ብሄራዊ ቡድኑ ኡጋንዳ ምሽት ላይ ደረስን ፤ እርቦን ስለነበር ፓስታ ሰጡን ፤ በጣም ጣፍጦን በላን ፤ በነጋታው ዞር ዞር ስንል ገበያ ስፍራ ነፍሳቶች ተጠባብሰው ለምግብነት ሲሸጡ አየን ፤ ማታ የበላነው ምግብም ስላየነው እንደዛ የጣፈጠን ከምን ቢሰራ ነው ❓ብለን ጠየቅን ፤ ...ከአንበጣ ፥ ከፌንጣ እንደተሰራ ነገሩን! ምን እንሁን ❓ ከዛን በኋላ የእነሱን ምግብ መብላት አቃተን ፤ በቆሎ እና በበሶ ብቻ ቆይተን ከሌለን ክብደት ላይ ኪሎ ቀንሰን ተመለስን ።
🎁ኳስ ያቆመው መቼ ነው?
በላያ እና ኳስ አሁንም አልተለያዩም ፤ ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ ጣሊያን ባሉ የተለያዩ ከተሞች ክለቦች ለበርካታ አመታት ተጫውቷል ፤"ከመጫወቴም በላይ የጣሊያኖችን ታክቲክ በደንብ ተምሬበታለሁ " ሲልም ለቀጣይ የአሰልጣኝነት ህልሙ መሳካት ቁልፍ ግብአት እንዳገኘበት ይናገራል ።" እኛ ሀገር የቴክኒክ ችሎታችን ምርጥ ነው ፤ ታክቲክ ላይ ግን ብዙ ይቀረናል ። "
ትዳር መስርቶ የሁለት ሴት ልጆች አባት ለመሆን የበቃው በላያ በአሁን ሰዓት አሜሪካ ሜሪላንድ በደስታ እየኖረ ይገኛል ።
🎁ቀጣይ ፍላጎቱ🎁
ለ20 አመታት ያክል በጣሊያን በመጫወት የጣሊያኖችን ታክቲክ በተግባር ያወቀው በላያ የኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በአሰልጣኝነት አሻራውን ማሳረፍ ይፈልጋል ፤ ይህ በዘመኑ የተጨበጨበለት ጥም ቆራጭ አጥቂ የኢትዮጵያ ክለቦችም ሆኑ ብሄራዊ ቡድን እድሉን ቢሰጡት የገዘፈ ልምዱን እና እውቀቱን ያተርፉበታል ።
ልዩ መልእክት
" መላው የእግርኳስ ቤተሰብ ፥ ስላከበራችሁኝ አመሰግናለሁ ፤ ብዙ ሳላስደስታችሁ መራቄ ቢቆጨኝም ሁሌም ከልቤ አላችሁ ፤ እወዳቸዋለሁ ።ፈጣሪ ሰላም ያብዛልን።
በላይነህ አስቻለው (በላያ) ከሜሪላንድ "

የበላያን የምንግዜም ምርጥ 11 እሁድ እናቀርበዋለን 🙏
መልካሙ ወንድማችን ዮሀንስ አያሌው ክበርልን 🙏🙏

✅ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁
የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን ፤ አዲሶቹን እያሳደግን ፤ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ 🎁🎁🎁
🎁🎁🎁የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁

Address

Alexandria, VA

Telephone

+251704149670

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afro Soccer Ethiopia / አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Afro Soccer Ethiopia / አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ:

Share

Category

Afro Soccer Ethiopia

Promotes Ethiopian Football players’ Talent , Gives Transfer Information Services , (Foreign Clubs , Ethiopian Clubs , Agents , Managers , Scouts )