ET Muslim Defense

ET Muslim Defense we dream for tomorrow is to overcome z ummah's hatred with good morals & get out of conspiracy politics

Welcome to voice of ummah if you follow us you get more news, blogging , information, news, are available in or page. for more information visit our website -- www.agamsatimes.com

ሳዑዲ አረቢያ "ሙስሊሞች ኢየሩሳሌምን በፍፁም አይተዉም" የሚለውን ዓረፍተ ነገር ከ11ኛ ክፍል የአረብኛ መማሪያ መጽሐፏ አስወግዳለች።ይህም "የጽዮናዊ ጠላት" የሚለውን ቃል በ"የእስራኤል ወራ...
08/16/2026

ሳዑዲ አረቢያ "ሙስሊሞች ኢየሩሳሌምን በፍፁም አይተዉም" የሚለውን ዓረፍተ ነገር ከ11ኛ ክፍል የአረብኛ መማሪያ መጽሐፏ አስወግዳለች።

ይህም "የጽዮናዊ ጠላት" የሚለውን ቃል በ"የእስራኤል ወራሪ" የተካው የራዕይ 2030 የሥርዓተ ትምህርት ማሻሻያ አካል ነው።

MBS በራዕይ 2030 ፕሮጀክት ከፂዮናዊያን ጋር ያለውን ወዳጅነት እና የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር የሳዑዲ ኢስላማዊ እሴቶች ማፅዳት ቀጥሏል። የሀገሪቱ የእውቀት ባለቤቶችም በዝምታቸው ተግባሩን ሀላል አድርገዋል።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

ፔንታጎን በወታደራዊ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ክርስትናን እና የምዕራባውያንን ሥልጣኔ ትምህርትን የሚያጎላ ኮርስ እያስተዋወቀ መሆኑን AP ዘግቧል።ይህ እርምጃ ፒት ሄግሴት ወደ 160 የሚጠጉ የፔ...
08/16/2026

ፔንታጎን በወታደራዊ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ክርስትናን እና የምዕራባውያንን ሥልጣኔ ትምህርትን የሚያጎላ ኮርስ እያስተዋወቀ መሆኑን AP ዘግቧል።

ይህ እርምጃ ፒት ሄግሴት ወደ 160 የሚጠጉ የፔንታጎን ትምህርት ቤቶችን የበለጠ ክርስቲያን ፂዮናዊ አርበኛ ለማድረግ የያዘውን እቅድ አካል ነው።

መማሪያ መጽሐፋቹ የምዕራባውያን ሥልጣኔን ከክርስትና ጋር በቅርበት በማዛመድ እስልምናን ዓመፀኛ አድርጎ ለመሳል እና እንደ ክሩሴድ ያሉ ጦርነቶች በመሸፋፈን ታሪክን ለማዛባት አላማ ያላቸው መሆኑን ተቺዎች ገልጸዋል።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

08/16/2026

ትንሹን ግልገል አይተህ ትንቀዋለህ...
ነገር ግን በውስጡ ኃያል አንበሳ አለ...

ይህ የ16 ዓመቱ ሰማዕት ተዋጊ ሱሃይብ ለባድ ቀላል መሳሪያውን ይዞ ከባድ የታጠቀ የጠላት ተሽከርካሪን የተጋፈጠበትን ክስተት የሚያሳይ ትዕይንት ነው።

ሱሃይብ በእጁ መሳሪያ ይዞ አልተወለደም።

ህዳር 19/2023 ወራሪው ሃይል ከጋዛ ከተማ በስተምስራቅ በሚገኘው አል-ዳራጅ ሰፈር ውስጥ የሚገኘውን የቤተሰቦቹን ቤት በቦምብ ደበደበ።

ሱሃይብ በጥቃቱ ሌሎች የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ እናቱን፣ እህቱን ናስራን እናሶስት ወንድሞቹን ሙሐመድ፣ ሃኒ እና አነስን አጣ።

ሱሃይብ የቤተሰቡ ታናሽ አባል ነበር እና የቤተሰቡ መጥፋት በእጅጉ ጎድቶታል።

በኋላም በጦርነቱ ወቅት አልቃሳም ብርጌዶችን ተቀለቅሎ ሰማዕት ሆኖ እስኪያልፍ ድረስ በትግል ሜዳ ላይ ጠላት ጋር እየተፋለመ አሳልፏል። በመጨረሻም በትግል ሜዳ ላይ ሰማዕት ሆኖ አለፈ።

በጫካ ህግ የሚመራው የግብዞች አለም ይህን ሙሉ ቤተስቡን በውራሪ ሀይል አጥቶ ለራሱ ህልውና ነፍጥ ያነሳ ታዳጊን ዛሬም አሸባሪ ብሎ ይጠራዋል።

አላህ ስራውን ይዉደድለት ፣ በጀነትም ከፍ ያለውን ደረጃ ይወፍቀው።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

08/15/2026

🇮🇷/🇶🇦 የኢራን ጦር በመጋቢት ወር ዶሃ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በተሳካ ሁኔታ ቦምብ ጥለው ወደ ኢራን ሲመለሱ ከነበሩ 4 የሱ-24 አብራሪዎች 3ቱ ጃቫድ ሳልሂ፣ አብዱልመጂድ ዳሽቲያን እና ኦምራን ቤህሩሺያን ጄቶቻቸው በአየር መከላከያ ስርዓት ተመትተው በሰላም መውጣታቸውን እና በኳታር መንግሥት ቁጥጥር ሰር እንደሚገኙ በይፋ አስታውቋል።

የኢራን ጦር ኃይሎች የጠፉ ወታደሮች አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀነራል ሰይድ ሙሀመድ የኳታር መንግስት እስረኞቹ አሁን ስላሉበት ሁኔታ ለቀይ መስቀል እንዲያሳውቅ እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲያነጋግሩ የሚያስችላቸውን የጄኔቫ ኮንቬንሽን አንቀፅ 70 እና 78ን እንዲያከብር ጠይቀዋል።

ከአራቱ አብራሪዎች አንዱ አብራሪ መጂድ ካዜሚ በዘመቻው ስማዕት መሆኑን እና አስከሩ በክብር መቀበሩን የኢራን ጦር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኳታር ሶስቱ የኢራን አብራሪዎች በህይወት መያዛቸውን አስመልክቶ የኢራን ጦር ያውጣውን መግለጫ የካደች ሲሆን አስክሬን ለማግኘት ፍለጋ ቢደረግም ምንም ነገር አልተገኘም ብላለች።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

08/15/2026

🇮🇷🚀🇺🇸🇮🇱 ኢራን በቅርቡ በተከሰተው ጦርነት ወቅት የተመቱ የአሜሪካ እና የእስራኤል አውሮፕላኖች እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ፍርስራሾችን ሰፊ ስብስብ ይፋ አድርጋለች።

ስብስቡ ድብቅ በሆነ IRGC ኤሮስፔስ ሀይል የአየር መከላከያ ጦር ሰፈር ውስጥ ታይቷል።

በጦርነቱ ወቅት ከ171 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች የተመቱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል MQ-9 ሪፐርስ ፣ ሄርሜስ 900 እና ሄርሜስ 450 ይገኙበታል።

አንዳንድ ስው አልባ አውሮፕላኖች አብዛኛው ክፍላቸው ሳይበላሹ በኢራን እጅ ገብተዋል።

የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ስብስቦቹን ባሳየበት ወቅት የኤሎን ማስክ 'ስታርሊንክ' ኩባንያ መሳሪያዎች በአሜሪካ ወታደራዊ ድሮኖች ውስጥ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ የሚያሳይ ማስረጃ አቅርቧል።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

🇮🇷🇦🇪 በሆርሙዝ ባህር ሰርጥ ውስጥ ከኢራን መመሪያ ውጭ ሲንቀሳቀስ የነበረ የኤሚሬት ነዳጅ ጫኝ መርከብ "AL WATAN" በIRGC ባህር ሀይል ዕርምጃ ተወስዶበታል።የብሪታንያ ባህር ንግድ ኦ...
08/15/2026

🇮🇷🇦🇪 በሆርሙዝ ባህር ሰርጥ ውስጥ ከኢራን መመሪያ ውጭ ሲንቀሳቀስ የነበረ የኤሚሬት ነዳጅ ጫኝ መርከብ "AL WATAN" በIRGC ባህር ሀይል ዕርምጃ ተወስዶበታል።

የብሪታንያ ባህር ንግድ ኦፕሬሽን (UKMTO) ባወጣው የመርከቡ ሰራተኞች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን እና ሰለጉዳቱ መጠን ምንም አይነት ግምገማ አለመደረጉን ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

🇹🇷🇺🇸 ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ለአልጀዚራ፡- ትራምፕ F-35 ተዋጊ አውሮፕላኖችን ለመሽጥ ቃል ገብቶልናል፣ እሱ ቃል ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ እየጠበቅን ነው።ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም...
08/15/2026

🇹🇷🇺🇸 ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ለአልጀዚራ፡- ትራምፕ F-35 ተዋጊ አውሮፕላኖችን ለመሽጥ ቃል ገብቶልናል፣ እሱ ቃል ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ እየጠበቅን ነው።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

ሂዝቦላህ፡- እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሲቪሎች ላይ የፈጸመችውን ጭፍጨፋ እናወግዛለን እንዲሁም እስራኤል እና አሜሪካን ለተባባሰው እና ለተፈጸሙት ጥቃቶች ተጠያቂ እናደርጋለን።️በአሜሪካ ዋስ...
08/15/2026

ሂዝቦላህ፡- እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሲቪሎች ላይ የፈጸመችውን ጭፍጨፋ እናወግዛለን እንዲሁም እስራኤል እና አሜሪካን ለተባባሰው እና ለተፈጸሙት ጥቃቶች ተጠያቂ እናደርጋለን።

️በአሜሪካ ዋስትናዎች እና ሽምግልና ላይ መተማመን የሽንፈት ስምምነት እንደሆነ እና አሜሪካ በእስራኤል ጥቃቶች ውስጥ ተሳታፊ መሆኗን እናረጋግጣለን።

️የሊባኖስን ሉዓላዊነት እና ደህንነት የሚያዳክም የፖለቲካ አካሄድ አደጋን እናስጠነቅቃለን። እና የሊባኖስ ባለስልጣናት የድርድሩን ሂደት እንዲገመግሙ ጥሪ እናቀርባለን።

የጠላት ሀይል ጥቃቶቹን ፣ የሚፈፅማቸውን የስምምነት ጥሰቶች እና የወረራ ድርጊት ለመፈጸም የሚያደርገው ሙከራን ሊቀጥል እንደማይችል እና ሊባኖስን ፣ ሕዝቧን ፣ ሉዓላዊነቷን እና ብሔራዊ ክብሯን ለመከላከል ተገቢውን እርምጃ እንደምንወስድ በሚገባ መረዳት አለበት።

-----

የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በደቡብ ሊባኖስ በአንሳር እና በዴይር አል-ዛህራኒ ከተሞች ላይ እስራኤል በፈፀመችው ሁለት የአየር ጥቃቶች ምክንያት 11 ንፁሃን መገደላቸውን እና 19 የሚሆኑ መቁስላቸውን አስታውቋል።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

🇺🇸⚡️🇮🇷 የኢራን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ ለትራምፕ ንግግር የሰጡት ምላሽ፡-የሆርሙዝ ሰርጥ የኢራን ግዛት ነበር ፣ አሁንም የኢራን ግዛት ነው፣ እና ሁልጊዜም የኢራን ግዛ...
08/15/2026

🇺🇸⚡️🇮🇷 የኢራን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ ለትራምፕ ንግግር የሰጡት ምላሽ፡-

የሆርሙዝ ሰርጥ የኢራን ግዛት ነበር ፣ አሁንም የኢራን ግዛት ነው፣ እና ሁልጊዜም የኢራን ግዛት ሆኖ ይቀጥላል።

ይህ ሰርጥ የሚዘጋው እና የሚከፈተው በኢራን ትዕዛዝ ብቻ ነው።

እርስዎ [ትራምፕ] የሽንፈትን እውነታ እስካልተቀበሉ እና ምናባዊ ቅዠቶችዎን እስካላቆሙ ድረስ ኢራን ሰርጡን የመዝጋት ትዕዛዟን ማስፈፀም ትቀጥላለች።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

08/15/2026

🇺🇸⚡️🇮🇷 ትራምፕ፡- በቅርቡ የሆርሙዝ ሰርጥ የአሜሪካ ግዛት መሆኑን እገልጻለሁ።

ለተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎች ቴሌግራም
👇👇👇

t.me/Etmusliminsider

Address

Road
Alexandria, VA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ET Muslim Defense posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ET Muslim Defense:

Shortcuts

Share