TGEthiopianBroadcasting

TGEthiopianBroadcasting TG Ethiopian Broadcasting, LLC is a media company based in Alexandria, Virginia (United States). TG

TG stands for the late Dr. Artist Tilahun Gessesse who is the King of Ethiopian music

Congratulations to all the graduates! 🎓👏Your hard work, dedication, and perseverance have brought you to this proud mome...
06/14/2026

Congratulations to all the graduates! 🎓👏
Your hard work, dedication, and perseverance have brought you to this proud moment. This achievement is not just the end of one chapter, but the beginning of a bright new journey filled with opportunities, growth, and success.
May your future be full of purpose, confidence, and great accomplishments. We are so proud of you and excited to see all the amazing things you will do.

A special congratulations to my niece Melat Asnake and my nephew Ermias Asnake. We are especially proud of you both!
Congratulations, Class of 2026!
Mesfin Bezu

Today, Sunday, at 12:00 PM Washington, DC time, please follow one of the links below to listen to our live radio broadcast from Fairfax, Virginia.
www.fcac.org/tv/channel-30
www.fcac.org/wrld-international-radio

የወገኖቻችን ጥቃት የሚቆመው መቼ ይሆን?በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ አስቃቂ የግድያ ጥቃት ተፈጽሞአል። መንግስት አ...
06/03/2026

የወገኖቻችን ጥቃት የሚቆመው መቼ ይሆን?
በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ አስቃቂ የግድያ ጥቃት ተፈጽሞአል። መንግስት አልባ በሆኑት አገሮች ላይ እንኳን እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ግድያ ሲፈጸም አይሰማም። መንግስት ባለባት ሀገር ኢትዮጵያ እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም መስማቱ የበለጠ ልብ ይሰብራል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። የፌዴራል መንግስትስ ምን ይላል? የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አባታዊ የኀዘን መልእክት እንደሚከተለው ነው።

ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
‹‹ወረሰዩ አብድንቲሆሙ ለአግብርቲከ መብልዐ ለአዕዋፈ ሰማይ፣ ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም፦ የአገልጋዮችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።››
(መዝሙረ ዳዊት ፸፰፥፪)
በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።
የእምነት ነፃነት ተደፍሮ መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለበት፣ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተዘረፈበት በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት ነው።
የሰላም፣ የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ መከራ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በምታጽናናበት በዚህ ወቅት ራሷ በፈተና ውስጥ ሆና ከመቸገሯም በላይ በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል።
በመሆኑም ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።
በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር ሁል ጊዜ የምትቆም መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኀዘን ሰዓት አምላካችን በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍሶቻቸውን በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን በማለት አባታዊ የኀዘን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Eid Mubarak!ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ-አል-አድሃ( ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም የዒድ-አል-አድሃ በዓል!We warml...
05/27/2026

Eid Mubarak!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ-አል-አድሃ( ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም የዒድ-አል-አድሃ በዓል!
We warmly wish you and your families a blessed Eid al-Adha filled with peace, joy, love, and togetherness. May this special celebration bring happiness to your homes and strengthen the spirit of kindness, generosity, and respect among us all.
Wishing you a beautiful and blessed Eid.
Mesfin Bezu
TG Ethiopian

Congratulations!አሁንም ኩራታችንየኢትዮጵያ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በታላቅ ድምቀት አክብሮአል።From the heart of Africa to...
05/24/2026

Congratulations!
አሁንም ኩራታችን
የኢትዮጵያ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በታላቅ ድምቀት አክብሮአል።
From the heart of Africa to the skies of the world, Ethiopian Airlines carries more than passengers — it carries heritage, excellence, and the spirit of connection. For eight decades, Ethiopian Airlines has turned distance into connection and journeys into unforgettable stories.
Congratulations to Ethiopian Airlines on 80 years of excellence, innovation, and connection. From proudly representing Africa in the skies to connecting people, cultures, and destinations across the world, Ethiopian Airlines is a true symbol of vision, resilience, and success. May Ethiopian Airlines continue to soar higher, inspire generations, and carry the spirit of Africa to every corner of the globe.
Congratulations!
Mesfin Bezu
TG Ethiopian

Address

PO Box 11061
Alexandria, VA
22312

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TGEthiopianBroadcasting posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to TGEthiopianBroadcasting:

Share