Meznagnia

Meznagnia Celebrating 10 Years.
(2)

Meznagnia(መዝናኛ) Magazine is a digital and print publication that focuses on lifestyle, news, arts, and entertainment in the Ethiopian, Eritrean, and African communities in the United States.

ትውልደ ኢትዮጵያዊ  እንግሊዛዊው ደራሲና ገጣሚ ለምን ሲሳይ ሆስፒታል ገባ::እውቁ ትውልደ ኢትዮጵያዊ  እንግሊዛዊው ደራሲና ገጣሚ ለምን ሲሳይ ፀጉር ቤት በተቀባው የፀጉር ቀለም ምክንያት ባሳ...
08/22/2026

ትውልደ ኢትዮጵያዊ እንግሊዛዊው ደራሲና ገጣሚ ለምን ሲሳይ ሆስፒታል ገባ::

እውቁ ትውልደ ኢትዮጵያዊ እንግሊዛዊው ደራሲና ገጣሚ ለምን ሲሳይ ፀጉር ቤት በተቀባው የፀጉር ቀለም ምክንያት ባሳየው ከፍተኛ አለርጂ ምላሽ ምክንያት በአስቸኳይ ሆስፒታል ገብቶ የህክምና ክትትል እየተደረገለት መሆኑ ተገለፀ።

በብራድፎርድ ከተማ በሚገኝ አንድ የፀጉር ማስተካከያ ቤት ውስጥ ለምን ሲሳይ ፀጉሩን በመስተካከል በነበረበት ወቅት ፀጉር ቆራጩ “ሙሉ በሙሉ ከተፈጥሮ የተሰራ የፀጉር ቀለም ነው” በማለት እንዲሞክረው ገፉፍቶ የቀባው አዲስ የፀጉር ቀለም ራሱን የሆስፒታል አልጋ ላይ እንዲያገኘው አድርጎታል።

ገጣሚው ፀጉሩን ተስተካክሎና ቀለም ተቀብት ከጨረሰ በኋላ ወደ ቤቱ በሚጓዝበት ወቅት፣ ከፍተኛ የመለብለብ እና የማሳከክ ስሜት እንደጀመረው ጠቅሷል። ከሰዓታት በኋላ ህመሙ እየተባባሰ የራስ ቅሉ፣ ሙሉ ፊቱ እና አንገቱ ላይ ከባድ እብጠት በማጋጠሙ በመጀመሪያ ወደ ፋርማሲስት ዘንድ በመሄድ ቅባትና ፀረ-አለርጂ መድኃኒቶችን ቢወስድም ሁኔታው ይበልጥ እየተባባሰ በመምጣቱ፥ በመጨረሻም ወደ ሆስፒታል ሊያመራ ችሏል።

የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች እንደገለጹት፥ ገጣሚው ከደረሰበት የኬሚካል መመረዝ ምክንያት የደረሰው ጉዳት ሙሉ በሙሉ ድኖ ለማገገም ጥቂት ወራቶችን እንደሚወስድበት ገልፀውለታል። በአሁኑ ወቅት ግን በአስተማማኝ እጅ ላይ ጥሩ የህክምና ክትትል እያገኘ እንደሆነ ታውቋል።

የህክምና ባለሙያዎች ይህንን ክስተት ተከትሎ ለህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በፀጉር ቀለሞች ውስጥ የሚገኘው PPD (Para-phenylenediamine) የተሰኘው ኬሚካል እጅግ አደገኛ የሆነ የአለርጂ ምላሽ ሊያስከትል እንደሚችል አስታውቀዋል። የጤና ዘገባዎች እንደሚያስጠነቅቁት፥ ማንኛውንም የፀጉር ቀለም ከመጠቀማችን በፊት ለ48 ሰዓታት የሚቆይ የቆዳ መሞከሪያ (Patch test) ማድረግ ግዴታ መሆን አለበት። ከዚህ ቀደም መሰል የአለርጂ ክስተቶች እስከ ህይወት ማጣት ያደረሱ የጤና እክሎችን አስከትለዋል።

ፀጉር አስተካካዩ ገጣሚውን የቀባው ቀለም ፈቃድ የሌለው ሆኖ ከተገኘ በፀጉር አስተካካዩ ላይ ፈቃድ የሌለው ምርትን በመጠቀም አደጋ ማድረስ የሚል የሙያ ቸልተኝነት ክስ ሊመሰረትበት ይችላል።

ለምን ሲሳይ በዘመናችን የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያሳረፈ ድንቅ ባለቅኔ ነው። በ2012 የለንደን ኦሊምፒክ ይፋዊ ገጣሚ ሆኖ በመመረጥ ታሪክ የሰራ ሲሆን፣ በልጅነቱ በእንግሊዝ የጉዲፈቻና የማህበራዊ እንክብካቤ ስርዓት (Foster care) ውስጥ ያሳለፈውን መራራና ማንነትን የማፈላለግ የህይወት ውጣ ውረድ የከተበበት “My Name Is Why” (ስሜ ለምን ይባላል) የተሰኘው የግል ማስታወሻ መጽሐፉ (Memoir) በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት ከተሸጡ መጻሕፍት (Best-seller) ተርታ ይሰለፋል።

ለምን ሲሳይ በተጨማሪም የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር በመሆን ያገለገለ ሲሆን፥ ለስነ-ጽሁፍ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ ከእንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰብ የላቀ የክብር ማዕረግን ተቀብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ከመላው ዓለም የተውጣጡ አድናቂዎቹ፣ ደራሲያን እና የጥበብ ወዳጆች ፈጣን ማገገምን እየተመኙለት ይገኛሉ።

Daniel Gebremariam

የስፔን የወደፊቷ ንግሥት ወታደራዊ ብቃቷን አረጋገጠችየስፔን ዙፋን ለመረከብ የመጀመሪያ ተሰላፊ የሆነችው የ20 ዓመቷ ልዕልት ሊዮኖር፣ በንጉሳዊ ቤተሰቧ ታሪክ በፓራሹት በመዝለል የመጀመሪያዋ ...
08/22/2026

የስፔን የወደፊቷ ንግሥት ወታደራዊ ብቃቷን አረጋገጠች

የስፔን ዙፋን ለመረከብ የመጀመሪያ ተሰላፊ የሆነችው የ20 ዓመቷ ልዕልት ሊዮኖር፣ በንጉሳዊ ቤተሰቧ ታሪክ በፓራሹት በመዝለል የመጀመሪያዋ በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግባለች።

ስምንት ዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን አቀላጥፋ የምትናገረው ይህች ወጣት ልዕልት፣ የወደፊት የአገሪቱ ርዕሰ ብሔርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆኗ መጠን ለዙፋኑ የሚመጥን አጠቃላይ ወታደራዊ ስልጠና ወስዳለች።

ለሦስት ዓመታት በሀገሪቱ እግረኛ ጦር፣ ባህር ኃይል እና አየር ኃይል ውስጥ ሲሰጥ የነበረውን ጠንካራ ወታደራዊ ስልጠና በስኬት ያጠናቀቀችው ልዕልቷ፣ ምንም ዓይነት ልዩ ክብር ሳይደረግላት ከሌሎች እጩ መኮንኖች ጋር እኩል በምሽት ጭምር አስቸጋሪ የፓራሹት ዝላይዎችን አከናውናለች።

በቅርቡ ያጠናቀቀችው ወታደራዊ ማሰልጠኛ አካል የሆነው የአየር ወለድ ዝግጅት ልዩ ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ በከፍተኛ ከፍታ ላይ ከበረራ አውሮፕላን በፓራሹት በመወንጨፍ በስፔን ንጉሣዊ ቤተሰብ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ተወንጫፊ ለመሆን በቅታለች።

ካለፉት 150 ዓመታት ወዲህ የስፔን የመጀመሪያዋ ነጋሲ ንግስት (Reigning Queen) ለመሆን የምትዘጋጀው ልዕልት ሊዮኖር፣ ይህንን ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና ማጠናቀቋን ተከትሎ በቀጣይ በፖለቲካ ሳይንስ ትምህርቷን እንደምትቀጥል ታውቋል።

ይህ ታሪካዊ እርምጃዋ ዘመናዊና ጠንካራ የአመራር ቁመና እንዳላት ለሕዝቡ ያሳየ ሁነት ተደርጎ ተወስዷል።

ልዕልቲቷ ከዚህ ቀደም በብስክሌት፣ በመርከብ እና በተለያዩ ወታደራዊ አካዳሚዎች ያሳለፈቻቸው የትምህርትና የተግባር ዓመታት የአገሪቱን ዘመናዊ የንጉሣዊ አገዛዝ ሚና በአዲስ መልክ እንደሚቀርጹት ተንታኞች ይገልጻሉ።

የስፔን ሕዝብም የወደፊቷን ንግሥት በትልቅ አክብሮትና ተስፋ እየተመለከታት ይገኛል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጠቅለያዎቹ ላይ የሚያሰፍረው የአሜሪካው በርገር ቤትበአሜሪካ አገር 424 ቅርንጫፎች ያሉት እና ከ28,000 በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው ዝነኛው የፈጣን ምግብ...
08/22/2026

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጠቅለያዎቹ ላይ የሚያሰፍረው የአሜሪካው በርገር ቤት

በአሜሪካ አገር 424 ቅርንጫፎች ያሉት እና ከ28,000 በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው ዝነኛው የፈጣን ምግብ ሰንሰለት ኢን-ኤንድ-አውት (In-N-Out Burger) በሚሸጣቸው የበርገር ማሸጊያዎች ላይ የሚያትማቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በደንበኞች እና በሲቪል መብት ተሟጋቾች መካከል ሰፊ የሃሳብ መከፋፈል ፈጥረዋል።

ተቋሙ በለስላሳ መጠጥ መያዣ እቃዎች የታችኛው ክፍል እና በበርገር መጠቅለያ ወረቀቶች ላይ እንደ “ዮሐንስ 3:16”፣ “ምሳሌ 3:5”፣ “ምሳሌ 24:16”፣ “ናሆም 1:7”፣ “ሉቃስ 6:35” እና “ራዕይ 3:20” የመሳሰሉ ጥቅሶችን የሚያትምባቸው ሲሆን፣ ይህም አሰራር የተጀመረው ከ46 ዓመት በፊት በድርጅቱ መስራች በነበሩት ሐሪ ስናይደር አማካኝነት የቤተሰቡን የክርስትና እምነት ለማንጸባረቅ ታስቦ ነበር።

የድርጅቱ ደጋፊዎች ማናቸውም የግል ኩባንያ በራሱ ምርት ላይ የፈለገውን ነገር የማድረግ ሙሉ መብት እንዳለውና ጥቅሶቹም ማንንም ደንበኛ እምነት እንዲቀይር እንደማያስገድዱ ይከራከራሉ።

በአንጻሩ ነቃፊዎች ደግሞ ተቋሙ የተለያየ እምነት ያላቸውንና ምንም እምነት የሌላቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን የሚያስተናግድ አገር አቀፍ የንግድ ሰንሰለት በመሆኑ፣ የበርገር መጠቅለያ ወይም የፈሳሽ መያዣ የወረቀት ብርጭቆዎች ላይ የሃይማኖት መልዕክቶች ፈጽሞ መኖር የለባቸውም ሲሉ ይተቻሉ።

የአሁኗ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የመስራቹ የልጅ ልጅ የሆኑት ሊንሲ ስናይደር ይህንን ተግባር እንደ ቤተሰብ መዘከሪያ ቅርስ በመቁጠር ከአቋማቸው ፍንክች እንደማይሉ በተደጋጋሚ የገለጹ ሲሆን፣ በጥቅሶቹ ምክንያት ነቀፌታ እና የተሟጋቾች ግፊት ቢኖርም የኩባንያው ቅርንጫፎች መስፋፋታቸውን እና የድርጅቱ ተወዳጅነት ከመጨመር ወደ ኋላ አላለም።

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የ1.4 ሚሊዮን ዶላር የቅንጦት ሰዓት በስጦታ ተበረከተለትታዋቂው የዓለማችን እግር ኳስ ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የያዕቆብ እና ኩባንያ (Jacob & Co.) መስራች ከሆነው...
08/21/2026

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የ1.4 ሚሊዮን ዶላር የቅንጦት ሰዓት በስጦታ ተበረከተለት

ታዋቂው የዓለማችን እግር ኳስ ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የያዕቆብ እና ኩባንያ (Jacob & Co.) መስራች ከሆነው ከጃኮብ አራቦ (Jacob Arabo) የ1.43 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው እጅግ ዘመናዊና ውድ የቅንጦት ሰዓት በልዩ ስጦታ መልክ እንደደረሰው ተረጋግጧል።

በቅርቡ የተሞሸረው እና ከሚስቱ ጋር የዕረፍት ጊዜውን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ሮናልዶ፣ ይህንን ስጦታ የተቀበለው በጃኮብ አራቦ እጅ በቀጥታ መሆኑ ተገልጿል።

የድርጅቱ መስራች አራቦ ሰዓቱን ለሮናልዶ በሰጠበት ወቅት በማህበራዊ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት “በአቅራቢያው ስለነበርኩ ለአንዱና ለብቸኛው ክሪስቲያኖ ይህንን ሰዓት በግንባር ቀርቤ ለማበርከት ወሰንኩ” ማለቱ ታውቋል።

ሰዓቱ “Twin Turbo Furious Baguette” የሚባል ሞዴል ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ከ18 ካራት ነጭ ወርቅ የተሰራ ነው። በውስጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ በደቂቃ የሚሽከረከሩ አልማዞች (Baguette-cut diamonds) እና እጅግ ረቂቅ የሆኑ ሜካኒካዊ ሲስተሞችን አካቶ ይዟል። ይህ የሰዓት ሞዴል በዓለም ላይ የተመረተው ለ18 ሰዎች ብቻ በመሆኑ እጅግ ብርቅዬና ውድ ያደርገዋል።

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከያዕቆብ እና ኩባንያ (Jacob & Co.) ጋር የረጅም ጊዜ የወዳጅነትና የንግድ አጋርነት ያለው ሲሆን፣ ከዚህ ቀደምም በስሙ የተሰየሙ ልዩ የሰዓት ምርቶች (CR7 Collection) ለገበያ መቅረባቸው ይታወሳል።

ይህ አዲስ ስጦታም የሮናልዶን እጅግ ውድ እና አስደናቂ የሰዓት ክምችት የበለጠ ያሳደገው ሆኗል።

በአሰቃቂ የተኩስ አደጋ የጓደኛውን ሕይወት ያጠፋው የ12 ዓመት ታዳጊ ፍርድ ቤት ቀረበ በዋሽንግተን ዲሲ የ13 ዓመቱን ታዳጊ አህመድ ሚምስን በሽጉጥ ተኩሶ በመግደል ነፍስ  በማጥፋት ወንጀል ...
08/21/2026

በአሰቃቂ የተኩስ አደጋ የጓደኛውን ሕይወት ያጠፋው የ12 ዓመት ታዳጊ ፍርድ ቤት ቀረበ

በዋሽንግተን ዲሲ የ13 ዓመቱን ታዳጊ አህመድ ሚምስን በሽጉጥ ተኩሶ በመግደል ነፍስ በማጥፋት ወንጀል የተከሰሰው የ12 ዓመት ታዳጊ ሐሙስ ዕለት በዲሲ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

በችሎቱ ሂደት ላይ ታዳጊው ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት ያለቀሰ ሲሆን፣ እናቱ ከፍርድ ቤቱ ውጭ ሆና በቪዲዮ መገናኛ አማካኝነት ሂደቱን በከፍተኛ ሐዘን ስትከታተል ተስተውላለች።

በታዳጊው ላይ የጦር መሣሪያ ካለፈቃድ መታጠቅ ፣ የሰውን ህይወት በቸልተኝነት ማጥፋት እንዲሁም ተጨማሪ የጦር መሣሪያ ይዞታ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበታል።

የዋሺንግተን ዲሲ ፖሊስ መምሪያ (MPD) ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ አሳዛኙ የተኩስ አደጋ የተፈጸመው ባለፈው አገስት 11 ቀን በሰሜን ምስራቅ ዋሽንግተን 1600 ሮዝዴል ስትሪት (1600 block of Rosedale Street, NE) በተባለ አካባቢ ነው።

ከተጠርጣሪው ታዳጊ የተገኘው የቃል ምስክርነት እንደሚያመለክተው፣ ጓደኛው ከእርሱ ጋር ለመጫወት አዘውትሮ እንደሚያደርገው ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንደመጣና አብረው መጫወት እንደጀመሩ ገልፆ፣ በጨዋታቸው መሀከል የወንድሙ ሽጉጥ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ እንደተመለከተ እና ሽጉጡን አንስቶ እየፎከረና እየዘለለ በነበረበት ወቅት ሸጉጡ በድንገት ባርቆ ጓደኛውን እንደገደለው አመልክቷል።

መሣሪያው ተኩሶ የአህመድን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ ታዳጊው በከፍተኛ ድንጋጤ በመዋጥ የአህመድን አስከሬን ከቤት ውስጥ ጎትቶ በማውጣት በሕዝብ መሄጃ እግረኛ መንገድ ላይ እንደጣለው አምኗል።ከአደጋው ከሦስት ቀናት በኋላ፣ ታዳጊው እና ቤተሰቡ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ሜትሮፖሊታን ፖሊስ መምሪያ በመሄድ እጃቸውን ሰጥተዋል።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ ቤተሰቡ ስለ ክስተቱ ሦስት የተለያዩ የእምነት ቃል መግለጫዎችን የሰጡ ሲሆን፣ በመጨረሻም ድርጊቱ ድንገተኛ አደጋ መሆኑን በሚገልጸው ሦስተኛው መግለጫ ላይ ጸንተዋል። ባለሥልጣናት ይህንን ሦስተኛ የቃል ምስክርነት የተቀበሉት ሲሆን፣ ሕፃኑም እውነታው እርሱ መሆኑን ለመርማሪዎች አረጋግጧል።

የአህመድ ሚምስ አያት ወይዘሮ ሞኒካ ሚምስ የልጅ ልጃቸውን ሲያስታውሱ፣ “ውጭ መውጣትን እና ከጓደኞቹ ጋር መጫወትን የሚወድ በጣም የዋህ እና ቅን ልጅ ነበር” ብለዋል። አያት አክለውም፣ “ይህ በእርሱ ላይ በመፈጸሙ እጅግ ደንግጫለሁ፣ ተጎድቻለሁም። በጣም ደግ ልጅ ነበር፤ ሌሎችን መርዳት ይወድ ነበር። በእውነት መልካም ልጅ ነው፤ በፍጹም ረብሻ ውስጥ የሚገኝ አይነት ልጅ አልነበረም” ሲሉ በሐዘን ገልጸዋል።

የዲሲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተባባሪ ዳኛ ስቲቨን ዌልነር የ12 ዓመቱ ታዳጊ ለሕብረተሰቡ ደህንነት አስጊ ነው ሲሉ በሰጡት ውሳኔ፣ ታዳጊው በዲሲ የወጣቶች እስር ቤት ማእከል ዉስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲቆይ አዘዋል። በተጨማሪም በሚቀጥለው ሳምንት ለሚኖረው የፍርድ ቤት ችሎት እስኪቀርብ ድረስ የአእምሮ ጤና ምርመራ እንዲደረግለት ዳኛው ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

Daniel Gebremariam

የደቡብ ኮሪያ ጠንቋዮች AI ገብያችንን ክፋኛ ቀንሶብናል ብለው አማረሩ። በቴክኖሎጂ ምጥቀት ቀዳሚ ከሆኑት የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ደቡብ ኮሪያ፣ የቅርብ ጊዜው የአርቴፊሻል ...
08/20/2026

የደቡብ ኮሪያ ጠንቋዮች AI ገብያችንን ክፋኛ ቀንሶብናል ብለው አማረሩ።

በቴክኖሎጂ ምጥቀት ቀዳሚ ከሆኑት የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ደቡብ ኮሪያ፣ የቅርብ ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዕድገት የዘመናት ታሪክ ባለው የባህላዊ ዕድል ትንበያ (ጥንቆላ) ኢንደስትሪ ላይ ከፍተኛ አደጋ እየደቀነ መሆኑ ተሰማ።

በአገሪቱ የሚገኙ ታዋቂ ዕድል ተንባዮችና ጠንቋዮች ወደ እነርሱ ይመጡ የነበሩ ደንበኞቻቸው ፊታቸውን ወደ AI ቴክኖሎጂ በማዞራቸው ምክንያት ሥራቸው ክፉኛ እንደ ተቀዛቀዘባቸው በምሬት በመግለጽ ላይ ናቸው።

በዋና ከተማዋ ሴኡል ዳርቻ በሚገኘውና በባህላዊ ዕድል ተንባዮች (ጠንቋዮች) መንደርነቱ በሚታወቀው ‘ሚያ መንደር’ ውስጥ አሁን ላይ የደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።

ቀደም ባሉ ዓመታት የደቡብ ኮሪያ ነዋሪዎች ስለ ጤናቸው፣ ትዳር፣ ፍቅር፣ ገንዘብ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ለመጠየቅ ወደዚህ መንደር በብዛት ይጎርፉ ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ አብዛኞቹ ዜጎች በአካል ወደ መንደሩ ከመሄድ ይልቅ በኢንተርኔት አማካኝነት እንደ ChatGPT እና Gemini ያሉ የ-AI መተግበሪያዎችን በመጠቀም ዕድላቸውን መተንበይ መምረጣቸው ተገልጿል።

በዚሁ መንደር ውስጥ ከቀሩት ጥቂት ዕድል ተንባዮች መካከል አንዷ የሆኑት የ86 ዓመቷ አዛውንት ሶንግ ኦ-ሱን ሁኔታውን ሲያስረዱ፣ እሳቸው አሁንም ከዘመናዊው የኢንተርኔት ዓለም ርቀው እንደሚኖሩና ዕድልን ለመተንበይ “አራቱ የዕጣ ፈንታ ምሰሶዎች” (Saju) የሚባለውን የኮሪያ ጥንታዊ ኮከብ ቆጠራ ዘዴ በብሬይል መጽሐፍ እያነበቡ እንደሚጠነቁሉ ገልጸዋል።

አዛውንቷ ባለፉት 40 ዓመታት ያካበቱት ይህ የሰዎች ስነ-ልቦና የመረዳትና የማማከር ልምድ AI በቀላሉ ሊተካው የማይችለው የላቀ ሰብአዊ ችሎታ መሆኑን በጽኑ ያምናሉ። “በሕይወት የመኖር ተስፋ ቆርጠው ለመሞት እንኳ ወደ እኔ የመጡ ሰዎችን አሳምኜና አጽናንቼ ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ አድርጌያለሁ” ሲሉም የሥራቸውን ማኅበራዊ ፋይዳ ያስረዳሉ።

ይሁን እንጂ የኢኮኖሚው እውነታ ሌላ ሆኗል። ቀደም ሲል በአካባቢው ከ 70 እስከ 80 የሚደርሱ ጠንቋዮች በሥራ ላይ የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ቁጥራቸው ከ20 በታች ዝቅ ብሏል። እንደ ‘ኢንኖፎሬስት’ (Innoforest) የተባለው የደቡብ ኮሪያ የጀማሪ ኩባንያዎች ትንተና ድርጅት መረጃ መሠረት፣ በአገሪቱ ያለው የዕድል ትንበያ ገበያ እጅግ ግዙፍና በ 2024 ብቻ በግምት 986 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የደረሰ ቢሆንም፣ አብዛኛው የገበያ ድርሻ ግን ወደ ዘመናዊ መተግበሪያዎች እየተዛወረ ነው።

ለዚህ ሽግግር ዋነኛው ምክንያት የዋጋና የቅልጥፍና ጉዳይ መሆኑ ይነገራል። የ-AI መተግበሪያዎች አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በነጻ ወይም በጣም በዝቅተኛ ክፍያ በሰከንዶች ውስጥ የሚሰጡ ሲሆን፣ በአንጻሩ እንደ ወይዘሮ ሶንግ ያሉ ባህላዊ ባለሙያዎች ለአንድ የዕድል ትንበያ ክፍለ-ጊዜ እስከ 35 ዶላር ገደማ ያስከፍላሉ። ይህ የዋጋ ልዩነትና የቴክኖሎጂው ተደራሽነት፣ ወጣቱ የኮሪያ ትውልድ ከባህላዊው መንደር ይልቅ ስማርት ፎኑን እንዲመርጥ ማድረጉን የዘርፉ ታዛቢዎች ገልጸዋል።

45% - 55% የሚጠጉ ደቡብ ኮርያውያን በህይወት ዘመናቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ የህይወት እጣ ፋንታቸው እንዲተነበይላቸው በመፈለግ ወደ ዕድል ተንባዮች (ጠንቋዮች) ቤት ያመራሉ።

Daniel Gebremariam

በአትላንታ ሰዎችን ለመረዳት ስትል ህይወቷ ያለፈው ወጣት አሜን ኪሮስ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል::በአትላንታ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን ለመታደግ በምታደርገው የሰብ...
08/20/2026

በአትላንታ ሰዎችን ለመረዳት ስትል ህይወቷ ያለፈው ወጣት አሜን ኪሮስ
የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል::

በአትላንታ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን ለመታደግ በምታደርገው የሰብዓዊነት ጥረት ላይ ሳለች ባልታሰበ አደጋ ህይወቷ ያለፈው የ23 ዓመቷ ወጣት አሜን ኪሮስ የሽኝት እና የሕይወት መታሰቢያ መርሃ-ግብር ዛሬ ሐሙስ ኦገስት 20 ቀን ከቀኑ 2:00pm ሰዓት ጀምሮ በአትላንታ በሚገኘው H.M. Patterson & Son-Oglethorpe Hill Chapel እንደሚፈጸም ቤተሰቦቿ አስታወቁ።

ባለፈው እሁድ ኦገስት 17 ቀን ጎህ ሲቀድ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ከተሽከርካሪዋ ወርዳ በነበረበት ቅፅበት፣ በከፍተኛ ፍጥነት በመጣ ሌላ መኪና ተገጭታ ህይወቷ ያለፈው ወጣት አሜን፤ እስከ ህይወቷ ፍፃሜ ድረስ ለሌሎች መኖርን የመረጠች እና የሞቷም

ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በአትላንታ ጆርጂያ የተወለዳቸው አሜን ሁልጊዜም ፈገግታ ከፊቷ የማይጠፋ፣ በደስታ የተሞላችና ቅን አሳቢ ነበረች።

“እችላለሁ” በሚለው ጠንካራ መንፈሷ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ችግር ውስጥ ለወደቁ ሰዎች ጆሮዋን ሰጥታ የማዳመጥ እና የመድረስ መልካም ባህሪዋ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል። ሰዎችን በጥልቀት እና በአዎንታዊ መልኩ የመንካት የተለየ ፀጋ ነበራት።

ቤተሰቦቿም ወዳጅ ዘመዶቿ ዛሬ በሚከናወነው የሽኝት መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት ሀዘናቸውን እንዲካፈሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሪንስ ሃሪ ከመላ ቤተሰቡ ጋር አሜሪካንን ለቀው ኑሯቸውንበእንግሊዝ ሀገር ሊያደርጉ እንደሆነ ተሰማ::የሳሴክስ መስፍን እና መስፍኒት ፕሪንስ ሃሪ እና ባለቤታቸው መገን ማርክል በዚህ ወር መገ...
08/20/2026

ፕሪንስ ሃሪ ከመላ ቤተሰቡ ጋር አሜሪካንን ለቀው ኑሯቸውን
በእንግሊዝ ሀገር ሊያደርጉ እንደሆነ ተሰማ::

የሳሴክስ መስፍን እና መስፍኒት ፕሪንስ ሃሪ እና ባለቤታቸው መገን ማርክል በዚህ ወር መገባደጃ ላይ ከኖሩባት አሜሪካ በመነሳት ቋሚ መኖሪያቸውን ወደ እንግሊዝ (ዩናይትድ ኪንግደም) ሊያደርጉ መሆኑን ይፋዊ ምንጮች ዘግበዋል። እንደ ዘ ዴይሊ ቴሌግራፍ እና ዘ ሰን ጋዜጦች ዘገባ ከሆነ ባልና ሚስቱ ከለንደን ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ የግል እና የንጉሣዊ ቤተሰብ ይዞታ ባልሆነ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይኖራሉ።

የባለትዳሮቹ ልጆች የሆኑት የ7 ዓመቱ ፕሪንስ አርቺ እና የ5 ዓመቷ ፕሪንሰስ ሊሊቤት በመጪው መስከረም (ሴፕቴምበር) ወር በብሪታንያ ትምህርት ቤት ገብተው ለመማር መመዝገባቸው ታውቋል።

ይህ እርምጃ ቤተሰቡ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ረጅም ጊዜ ለመቀመጥ ማቀዳቸውን ትልቅ ማረጋገጫ ተደርጎ ተወስዷል።

የሳሴክስ መስፍን እና መስፍኒት ከ2019 መገባደጃ አካባቢ ጀምሮእንግሊዝን ለቀው ወደ ካናዳ በማቅናትኑሯቸውን በቫንኩቨር ከተማ መስርተው ነበር። ከ2021 መጀመሪያ ጀምሮ ደግሞወደ አሜሪካን ሀገር ሎስ አንጀለስ ከተማ ጠቅልለው በመግባት ህይወታቸውን ሲመሩ መቆየታቸው ይታወቃል።

ንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ ስለ ልጃቸው እና ስለ ቤተሰቡ ወደ እንግሊዝ የመመለስ እቅድ ባለፈው እሁድ የተነገራቸው ሲሆን፣ የልጅ ልጆቻቸውን በቅርብ ለማየት የሚችሉበትን አጋጣሚ በመፈጠሩ እና ልጃቸው እና ቤተሰቡ ወደ እንግሊዝ በመመለሳቸውበደስታ እንደተቀበሉት ተገልጿል።

ወንድማቸው ፕሪንስ ዊሊያም እና ባለቤታቸው ኬት ሚድልተንም ይህንን እቅድ አስቀድመው እንዲያውቁት ተደርጓል።

ጥንዶቹ በ2020 ከለንደን ንጉሣዊ ቤተሰብ የሥራ ኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወሳል። አሁን ወደ ሀገር ቤት ቢመለሱም እንደ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል በይፋዊ የሥራ ክንውኖች ላይ የመሳተፍ እቅድ የሌላቸው ሲሆን፣ እንደማንኛውም የግል ዜጋ ሕይወታቸውን እንደሚመሩ ተረጋግጧል።

Meznagnia Media

የቴሌሙንዶ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊና አራት አሜሪካውያን በኬንያ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው አለፈበኬንያ ሰሜን ምዕራብ ክፍል በሚገኝ አንድ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ በደረሰ...
08/19/2026

የቴሌሙንዶ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊና አራት አሜሪካውያን በኬንያ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

በኬንያ ሰሜን ምዕራብ ክፍል በሚገኝ አንድ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የታዋቂው የቴሌሙንዶ (Telemundo) የቴሌቪዥን ጣቢያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊን ጨምሮ አምስት አሜሪካውያንና አንድ ኬንያዊ ፓይለት ሕይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው የተከሰተው በቱርካና ሐይቅ ላይ በሚገኘው ማዕከላዊ ደሴት ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ነው።

የአሜሪካውያን ቡድን በኬንያ ታዋቂ የቱሪስት መዳረሻዎችን በመጎብኘት ላይ የነበሩ ቱሪስቶች እንደነበሩ ታውቋል።
ሄሊኮፕተሯ እሁድ ምሽት ላይ ከአየር ማረፊያ ከተነሳች ከጥቂት ጊዜያት በኋላ መከስከሷ ታውቋል። ፍለጋ ያደረጉ የነፍስ አድን ቡድኖች ሰኞ ማለዳ ላይ የሟቾችን አስከሬን እና የሄሊኮፕተሯን ስብርባሪ አግኝተዋል።

በአሜሪካ ፍሎሪዳ መሰረቱን ያደረገው ታዋቂው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቴሌሙንዶ ምክትል ፕሬዝዳንት በአደጋው ሕይወታቸው ካለፉት መካከል ዋናው ነው። ሌሎቹ አራት የሞቱት ሰዎች ደግሞ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የቅርብ ጓደኞቹ እና የጉዞው ተባባሪዎች ናቸው። ማሪየስ ማጉዋ የተባለ ከፍተኛ የማብረር ልምድ ያለው ኬንያዊ የሄሊኮፕተ አብራሪ ም በአደጋው ህይወቱን ።

የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ አስቸኳይ ምርመራ ጀምሯል። ይሁን እንጂ አደጋው በተከሰተበት ወቅት በአካባቢው የነበረው የአየር ሁኔታ አስቸጋሪ እንደነበር ተገልጿል።

የቴሌሙንዶ የሚዲያ ተቋም ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ “ካርሎስ ፔራልታ ለድርጅታችን ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ታላቅ መሪ ነበር” በማለት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ተመኝቷል።

በኬንያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም ለሟች ቤተሰቦች አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

Salem Magazine

✨ 🇪🇹 የኢትዮጵያ አዲስ አመት ክብረበዓል ከሞንጎምሪ ኮሌጅ 🇪🇹 ✨We would love for you to join us as we celebrate the Ethiopian New Year with a...
08/19/2026

✨ 🇪🇹 የኢትዮጵያ አዲስ አመት ክብረበዓል ከሞንጎምሪ ኮሌጅ 🇪🇹 ✨

We would love for you to join us as we celebrate the Ethiopian New Year with a wonderful day of culture, community, and connection! Bring your family and friends to experience rich traditions while exploring incredible educational and career pathways.

📅 Saturday, August 29, 2026
⏰ 11:00 a.m. – 3:00 p.m.
📍 Montgomery College

What to Expect:
🎶 Live Ethiopian cultural music and entertainment
🛍️ Ethiopian cultural vendors and artisan markets
☕ Traditional Ethiopian coffee ceremony
🤝 Community resource tables and cultural exhibits
🎉 Family-friendly activities and opportunities to connect and network
📚 Montgomery College Workforce Development and Continuing Education (WDCE) and EOC information tables

Whether you are reconnecting with your culture, discovering something new, or exploring educational and workforce opportunities at Montgomery College, there will be something for everyone! 💛💚❤️

👇 Tag a friend in the comments who needs to come with you!

Montgomery College

Address

50 Pickitt
Alexandria, VA
22312

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meznagnia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Meznagnia:

Shortcuts

Share