
08/01/2025
የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት ሌሎች ተሞክሮ ሊቀስሙበት የሚገባ የስራ ክፍል ነው ሲሉ ስራ አስኪያጁ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ ጠቆሙ!
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት የተቋሙን አስረኛ አመት የምስረታ በዓል እና የ2017 የህክምና አመት የማትጊያ ፕሮግራም አካሂዷል።
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ የተቋሙ ላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት በርካታ ሀገር አቀፍና ክልል አቀፍ እውቅናዎች የተገኙበት ተግባር ማከናወኑን በመግለጽ ሌሎች የስራ ክፍሎችም ከዳይሬክቶሬቱ ልምድ ሊወስዱ እንደሚገባ በፕሮግራሙ ባደረጉት ንግግር ጠቁመዋል።
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብዲ ዋነንጎ በበኩላቸው ዳይሬክቶሬቱ በጂን-ኤክስፐርት ያገኘውን እውቅና/accreditation/ ወደ ሌሎች ዘርፎችም ለማስፋፋት እያደረገ ያለውን ጥረት በማድነቅ የተቋሙ ማኔጅመንት ድጋፍ ከጎናቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
በመድረኩ የሆስፒታሉ የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በህረዲን ዳሪ የዳይሬክቶሬቱን የአስር አመት ጉዞ የሚያሳይ ሰነድ ሲያቀርቡ በአንድ የላቦራቶሪ ማሽን የተጀመረው ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ በመምጣት መቶ በመቶ ሊባል በሚችል ደረጃ የላቦራቶሪ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በጂን-ኤክስፐርት የተገኘውን እውቅናም/accreditation/ እንደ ሄማቶሎጂ እና ኬሚስትሪ በመሳሰሉ ዘርፎችም ለማግኘት እንደታቀደ ዳይሬክተሩ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
በመድረኩ የተቋሙ የማኔጅመንት አካላት፣ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በ2017 የህክምና አመት የተሻለ አፈጻጸም ነበራቸው ለተባሉ ባለሙያዎች እና ዴስኮች እውቅና ተበርክቶላቸዋል።