
10/10/2025
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ በገጠር ኮሪደር ኢንሼቲቭ ያስገነቡትን ሞዴል የገጠር መንደር አስመርቀዋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፣ የክልልና የዞን የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።