ሰላም የጥበብ እንኑር ቤተሰቦች
በጥበብ እንኑር በአለም ዙሪያ ያፈራልን ፍቅር የሆኑ ሰዎችን ማስተዋወቅ፡፡ ከራሳቸው አልፈው በሌሎች የኑሮ ሂደት እና የመልካምነት መንገስ ሃሳብ የሚወሰዱ፤ በጎነታቸው የሃገር መረከት እንደሆኑ፤ መልካምነታቸው እና በህብረተሰብ ውስጥ ያላቸው አገልግሎት የሃገራችን ኢትዮጵያ ተስፋ እንዳላት የሚሰብኩ እና ማሳያ የሆኑትን አግኝተናል፡፡ የጥበብ እንኑር አላማ ቁልጭ ብሎ የሚታየን እና በረከቶቻችንን አሜን ብለን የምንቀበለው ከኢትዮጵያ ባልደረባችን ናህሚ ኃይሉ አንዷ ናት፡፡ ናህሚዬ ጋር ቨርጂንያ በተገናኘንበት ጥቂት ሰአት ብዙ በረከቶች አወያየችን ፤ እኛም የሃገራቭን ሚዲያ የማያዮቸው፤ ዘማሪያን ያልዘመሩላቸው፤ ሸላሚዎች ያልጎበኟቸው፤ ባለቅኔዎች ያልተቀኙላቸው፤ ሶሻል ሚዲያ ያላሽከረከራቸው ስንት ባለበረከቶች በጥበብ እየኖሩ፤ ሌሎችን እያገለገሉ እንደሆነ አየን፡፡ ናሚንዬ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ ፡፡ ባለሙሉ ጥበብ በመሆንሽ አፋችንም በእጃችን ጭነን ተደመምን ፡፡ ለስጦታው እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ ሁሉም ለበጎ ነው፡፡ ከሆነው ሁሉ አንዳችም ያለእግዚአብሔር ፍቃድ አልሆነም እናም ክብሩን ይውሰድ፡፡
በጥበብ እንኑር፡፡
#VOED we will be back in the near future!!
እንኳን ለቅዱስ ገብረኤል አመታዊ በዓል አደረሳችሁ፡፡
እንደምን አደራችሁ ወገኖች
“I’ll be back. I think I’ll be back soon,”
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅዳሜ ምሽት ላይ በትዊተር ለአራት ደቂቃ የቪዲዮ መልእክት ያካፈሉት የመዝጊያ ነጥባቸው ነው። “እመለሳለሁ በቅርቡ ተመልሼ የምመጣ ይመስለኛል” ተመልሼ የምመጣ ይመስለኛል። አዎን ተመልሰው እንዲመጡ አብዛኛው ሰው ይፀልይላቸዋል። የሃገረ አሜሪካ መሪ ናቸው። ብዙዎችን ያስተዳድራሉ። ይህ ክፉ በሽታ ታላቂቷን ሃገር የእሽቁልቁል የሚያያት ይመስል መፍትሔ በማይገኝለት ሁኔታ እያተራመሰን ይገኛል። እንዲህ አይነት ሰዎች ሲያዙ ደግሞ ብዙዎች ተከታዮቻቸው ቀና ብለው ስርዓትም እንዲይዙ ያደርጋቸዋል። ኮረና አለ ብለው ዛሬ ብዙዎች ጥንቃቄ የሚጀምሩ ሰወችም አሉ። ፣ ፕሬዘደንት ዶናልድ ትራንፕ እንዲህ ብለዋል ሀሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ COVID-19 ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ እና ወደ ዋልተር ሪድ ብሔራዊ ወታደራዊ ሜዲካል ሴንተር ከተወሰደዱ በኋላ ጥሩ ስሜት እንደተሰማው ይናገራሉ ፡፡ ፕሬዘደንት ዶናልድ ትራንፕ በቫልተር ሪድ የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎችን በቪዲዮ መልእክታቸውን ላይ አመስግነዋል ፡፡ ፕሬዘደንት ዶናልድ ትራንፕ ሐሙስ አመሻሽ ላይ ምርመራ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ የዓለም መሪዎችን ላደረጉላቸው ለድጋፋቸውም ምስጋናቸውን አልነፈጉም፡፡ ይማሮት ኮረናውን አጥፍቶ ልቦና ይስጥልን ብያለሁ
ወራዙት የቅዳሜ ወግ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ
እለቱ ቅዳሜ ነው በመልካምነት እንታነፅ ይላል ወራዙት የቅዳሜ ወግ፡፡ መልካምነትን ለመለገስ ሳይሆን በውስጥ ያለውን መልካምነር ለሌሊች አውጥቶ ማብራት፡፡
በወራዙት መድረክ ግልፅ ግልፁ ይነገራል ማንንም ለመጉዳት ሳይሆን አቅጣጫ ለመጠቆም ነው፡፡ አቅጣጫ መጠቆም ደግሞ ከውጭ የሚደውሉትንም ይቀበላል፡፡
ለዚህ ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ስንል መነሻችን ልናደርገው ይገባል፡፡
ተንኳል እና ክፋት ምቀኝነት የተደረመሰበት መድሃኒት ሃያልነቱን ያሳየበት የቀረፀበት ቀን ነው፡፡
በወጣቶቻችን ላይ ያጠላውን ችግር እናያለን፤ በማህበረሰባችን ውስጥ አዛውንቶችን የሚበድሉትን እናጋልጣለን፤ ለሌቦች አናዝንም ስንል ሌብነትን እንቃወማለን፡፡ ታዲያ በዚህ መድረክ ሀገራዊ እና አካባቢያዊ ዳሰሳ ይቀርባል ሃሳቦትን እስቲ ያጋሩ፡፡ https://streamyard.com/vyq7yg9hfk
ወራዙቶች ነን፡፡
ወራዙት ማለት መልካም ወጣት ማለት ነው፡፡ ሰላም ያገናኘን መልካም በዓል
ለሌሎች ሼር ማድረግ አይርሱ፡ ፡https://streamyard.com/vyq7yg9hfk
መረጃ በቨርጂኒያ ለሚገኙ ሁሉ
የቨርጂኒያ እስቴት ሴነተር ማርክ ዎርነር በ09/17/2020 ከሁላችንም ጋር በሃገር ውስጥ እና በውጭ ጉዳይ ውይይት ውይይት ለማድረግ ጋብዘዋል
መረጃ ነው
መረጃ ይሆናችሁ ዘንድ እነሆ አልኩኝ፡፡
በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላን እና ቨርጂኒያ ለምትኖሩ ወገኖች ፡፡ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስራ የለቀቃችሁ ሁሉ Unemployment መሙላት ያለባችሁ ከሆነ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ዋናው ቢሮው በቨርጂኒያ አርሊንግተን የሚገኘው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ማዕከል ውስጥ ACC ውስጥ በመደወል አገልግሎት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ስልኩ 7036850610 Ex 226
ሔለን ገብሩ Helen Shiferaw
በንግድ ስራ ላይ ያላችሁ ሰዎች እና ይህ ችግር በንግድ ስራችሁ ላይ ያደረሰው ጉዳት ካለ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለመወያየት EDG መደወል ትችላላችሁ ፡፡ Enterprise development group በማንኛውም የንግድ ጉዳይ የብድር አገልግሎት እና በዚህ ባለው ችግር ደግሞ በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ እና በሜሪላን የምትገኙትን አብነት አገኘሁን ማነጋገር ትችላላችሁ፡፡
7036850610 Ex 258 ECDC Enterprise Development Group - EDG
ይደውሉ፡