
06/16/2025
የኢትዮጵያን ስም በሰበብ በአስባቡ መጥራት የሚወደው ጋሽ ትራምፕ
"...ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ እየገደበች በነበረው ግዙፍ ግድብ ምክንያት ኢትዮጵያና ግብፅ ሊገቡበት የነበረውን ትልቅ ጦርነት እኔ ጣልቃ በመግባት አስቀርቼዋለሁ... ልክ ኢሄን እንዳሳካሁት ሁሉ የኢራንና እስራኤልንም ጦርነት አስቀራለሁ " ሲል ሳያፍር ተናግሯል !
በማደራደር ሰበብ የኢትዮጵያን እጅ ለመጠምዘዝ ሞክሮ ሳይችል ሲቀር ግብፅ ግድቡን ታፈነዳዋለች እስከማለት ፀባጫሪ ለግብፆች" ግድቡን ምቱት" አይነት ንግግር በአደባባይ እስከ መናገር ደረጃ የደረሰበትን ግዜ መቼስ ኢትዮጵያዊያን አይረሱም ።
የሆነው ሆነና በብዙ ተነግሮ ማያልቅ መስዕዋትነት እነሆ ኢትዮጵያ ታላቁን የአፍሪካ ግዙፍና ታሪካዊ ግድብ ልታስመርቅ ሽርጉድ ማለት ጀምራለችና ክሬዱቱን ለመውሰድ መሞከሩ ከማናደድ ይልቅ የሚያስቅ ፣ የኢትዮጵያዊያንንም አይበገሬነት ያረጋገጠ ተደርጎ ይወሰዳል ።
FMN