የግጥም ማዕበል

የግጥም ማዕበል የተዋቡ ግጥሞችንና አነዳንድ ኮንትሮባንድ ሃሳቦችን ለማንሸ?

11/18/2025

ክበጅ ያላት ነብስ

ላባ ሆና መ’ታ፣
አለት ሆነች ፀንታ
ፀዳል ሆነች ፈክታ

Abreham Seyoum

10/28/2025

እኔ ጉልት ስውል ጉልት ይውላሉ
እኔ አሣ ሳሰግር አሣ ያሰግራሉ
እኔ ፍራሽ ሳድስ ፍራሽ ያድሳሉ
ብቻ አመድ ብሸጥም አመድ ይሸጣሉ።

ይሄ ሁሉ ሆኖም…
ምቅኞች አይደሉም
"ሀበሾች ምቅኞች" ብላችሁ አትበሉ
እኔ ዛፍ ስተክል መቼ ዛፍ ተከሉ?

ኑረዲን ዒሳ

09/27/2025

የሠማይ መከፈት

በሠማይ መከፈት፣
ውሃና ቁንጅና ወደምድር ዘንበው ፤
አብቃቅልት፣አዝዕርት፣
አዕዋፍ፣እንስሣቱ……
ፍጥረት ሁሉ ‘ረጥበው፤
ነቃሁ።
ጢስ በማገ ጥዋት
በወረዛ ዛፍ ላይ፣ጠል ባንጠለጠለ፣
ብርዝ መሳይ ብርሃን፣
በዛፍ ብብት አልፎ፤
በጐጆዎች አናት፣
በከብቶች ሻኛ ላይ ሥዕል እየሣለ፤
ነቃሁ።
የወፎቹ ‘ኮንሰርት’
ይናኛል፤በመስኮት።
አታሞዋ ጉጉት፣
ሞፈር ቆራጩ ጋር አብራ ስትጐሠም፣
ማህሌት መሰለ፤
የወፎች ድምጽ ወጥቶ እንደገና መክሠም።
በወረዛ ታዛ
ፀሀይዋ ጠርራ፣ቆፈን እስቲባረር፣
ምት እየጠበቀ
አብሮ ይሰለፋል፤የጉርጦች መንጫረር።

ሃኖስን ቢያክልም የመላዕክታን መክፈት፣
አጥርቶ ያሣያል፤የራስ ሽንቁር ደረት።
……………………………………………
ይሄን ሁሉ መጌጥ
ይሄን ሁሉ ውበት
እንኳን አልሰማሁት ፤በጠቢብ መተርክ ወይም በመለኮት፣
ተመስገን አናጢ፤ስትችል ያላቆምካት፣ ቤቴን ያለመስኮት።

ኑረዲን ዒሣ/ያልታተመ/

Address

Atlanta, GA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የግጥም ማዕበል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share