EthioTube Current events, breaking news, entertainment, exclusive interviews, variety shows & much more on Ethiopia. Watch All Things Ethiopia.

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረኮንፌዴሬሽን ...
07/14/2025

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረ

ኮንፌዴሬሽን ይህን ያለው በቅርብ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
ከገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሰራተኛው ለመቁረጥ የቀረበው ሃሳብ ውስብስብ የዋጋ ንረትን እና የድህነት መጠንን ያላገናዘብ ከመሆኑም በላይ ማጭበርበር ሳይኖር በአግባቡ ከደሞዙ ግብር የሚከፍለውን ሰራተኛ ከችግር የሚውጣ ሳይሆን ችግር ውስጥ የሚከት እንደሆነ የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ተናግረዋል፡፡
ሰራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ወጪዎች ስላሉበት ነው ብለዋል፡፡
ተቀጣሪው ሰራተኛ ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲሉ ያስረዱት አቶ ካሳሁን እውነት ለመናገር አንድ ሰው በ5 ሺ ብር ደሞዝ ቤት ኪራይ ይከፍላል ፣ ይበላል፣ ልብስ ይለብሳል ፣ ህክምና ይሄዳል ብለዋል፡፡
ህክምናውን እንተው እየጸለየ ይኑር ፤ቤት ኪራይውንም እንተወው በበረንዳ በሰዎች ላይ በጥገኝነት ይኑር ግን በቀን አንድ ጊዜ እየበላ መኖር የለበትም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አንድ ድርጅት ከትርፉ 35 በመቶ ግብር ይከፍላል ያሉት የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ሰራተኛውም 35 በመቶ ይከፍላል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ነጋዴውም፣ ድርጅቱም ከትርፉ ነው እኮ 35 በመቶ የሚከፍለው ሲሉ ያስረዱት አቶ ካሳሁን ሰራተኛው ግን ከትርፉ ሳይሆን ከሚበላው ላይ ነው የሚከፍለው ይህ እንዴት ነው? እኩል ይሆናል ብለዋል፡፡
ስለሰዎች ስናስብ ልማት ለማስቀጠል ነው ያሉት አቶ ካሳሁን ልማት ያለ ሰው ሰው ያለ ልማት ሊኖሩ አይችሉም ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ስለዚህም የሰራተኛውንም ጫና የመንግስትን ዓላማ ታሳቢ ያደረገ የግብር ምጣኔ መጣል አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አሁን በማሻሻያው የግብር መነሻ 2000 ሺ ብር ሲሆን ምን ታሳቢ ተደርጎ ነው? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አንድ ስልት ሲሰራ ሰውን ማኖር አለበት ያሉት አቶ ከሳሁን ይህ መነሻ ግን ታሳቢ አላደረገም ብለዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው እንደገና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር ቢመካከር ሲሉ የጠየቁት አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኑሮን አልቻሉም፤ ቋሚ ኮሚቴው ፍቃደኛ ከሆነ ከስራ ሲውጡ ፌስታል ይዘው ሆቴል አካባቢ ቆመው ሲለምኑ አብረን ማየት እንችላለን ብሏል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር በኩሉ አዋጁ በይድረስ ይድረስ የተዘጋጀ ሳይሆን ሁለት ዓመት ጥናት ተሰርቶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው ብሏል፡፡
2000 ብር መነሻ የተደረገበት ምክንያት ደግሞ የመክፈል አቅማችን ዝቅተኛ ስለሆነ ነው ሲል አስረድቷል፡፡
መነሻን ከዚህ ከፍ ለማድረግ ቢፈለግ አገሪቱ ያላት ገቢ አይፈቅድም ወደፊት ገቢው እያደገ ሲሄድ ግን መነሻን ከፍ ማድረግ እንደሚችል የገንዘብ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍቃዱ ሆረታ የኑሮ ውድነቱ ግብር በመክፍል ብቻ የመጣ እንዳልሆነ ተናግረው በኢትዮጵያ ብቻም ያለ ችግር አይደለም ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ድኤታው ከውጭ የምናስገባቸውን መዳበሪያ ፣ ነዳጅ እና መሰል ግብዓቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሰዎች ላይ ጫና ይፍጥራል ብለዋል፡፡
ይህን ችግር ለመፍታት ደግሞ መንግስት ደሞዝ መጨመሩን የተናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው መንግስት አቅም በፈቀደ መሰረት ድጋፍ አድርጓል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በገቢ ግብር ላይ ያለውም ጫናውን መቀነስ ነው እንጂ ማጥፋ እንዳልሆነ የተናገሩት አቶ ፍቃዱ ሆረታ በነባሩ አዋጅ ላይ መነሳትን ብናመለከት 600 ነው ወደ 2000 ያደገው በውይይት ተደርጎበት ነው ብለዋል፡፡
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የሞያ ማህበራት ተሳትፎ የተደረገ ማሻሻያ እንጂ ዝም ብሎ የመጣ ቁጥር እንዳልሆነም የገንዘብ ሚኒስቴር ተናግረዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር መነሻው ከተቀጣሪ ሰራተኛ አሁን ካቀረብነው ከፍ ካለ መንግስት ከፍተኛ ገቢ እንደሚያጣ ተናግሮ በተለይ በክልሎች ገቢ ላይ የበረታ ጫና እንደሚያሳድር ተናግሯል፡፡

(ምንጭ፦ ሸገር ሬዲዮ - ያሬድ እንዳሻው)

"ፌሚኒስቶችን ምቃወም አይነት ሰው ነበርሁ" - ጆርዲን በዛብህ የሴታዊት መቀነት መሰናዶ የዚህ ሳምንት እንግዳ። እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። | Meqenet Show - A Setaweet con...
07/14/2025

"ፌሚኒስቶችን ምቃወም አይነት ሰው ነበርሁ" - ጆርዲን በዛብህ የሴታዊት መቀነት መሰናዶ የዚህ ሳምንት እንግዳ። እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። | Meqenet Show - A Setaweet conversation with Jordin Bezabih

ለመመልከት 👇
https://youtu.be/kY8rTcn1g9I

ቸልሲ የአለም የክለብ ዋንጫ አሸናፊ 🏆🏅
07/13/2025

ቸልሲ የአለም የክለብ ዋንጫ አሸናፊ 🏆🏅

በአለም የክለብ ዋንጫ ፍፃሜ ያልታሰበው እየሆነ ነው። ብዙዎች ዋንጫ ያነሳል ብለው የገመቱት ፒኤስጂ በመጀመሪያው አጋማሽ በቸልሲ 3ለ0 እየተመራ ነው።ፒኤስጂ በ2ኛው አጋማሽ መመለስ ይችል ይሆ...
07/13/2025

በአለም የክለብ ዋንጫ ፍፃሜ ያልታሰበው እየሆነ ነው። ብዙዎች ዋንጫ ያነሳል ብለው የገመቱት ፒኤስጂ በመጀመሪያው አጋማሽ በቸልሲ 3ለ0 እየተመራ ነው።

ፒኤስጂ በ2ኛው አጋማሽ መመለስ ይችል ይሆን? 🤔

07/13/2025

Former Nigerian President Muhammadu Buhari has died at the age of 82 in a London clinic, where he had been receiving medical treatment since April.

A former military ruler turned democratically elected leader, Buhari made history in 2015 by becoming the first opposition candidate to defeat an incumbent.

His presidency, marked by promises to tackle corruption and insecurity, was often overshadowed by health concerns.

ከጥቂት ሰአታት በኋላ የሚካሄደውን የአለም የክለብ ዋንጫ ማን ያሸንፋል?- ፒኤስጂ- ቸልሲ
07/13/2025

ከጥቂት ሰአታት በኋላ የሚካሄደውን የአለም የክለብ ዋንጫ ማን ያሸንፋል?

- ፒኤስጂ
- ቸልሲ

የቤት ሰራተኛዋን ገድለው ሁለት ህፃናትን አግተው  10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ አጋቾችን በቁጥጥር ስር አውሎ ህፃናቱን ለቤተሰቦቻቸው ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ***...
07/13/2025

የቤት ሰራተኛዋን ገድለው ሁለት ህፃናትን አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ አጋቾችን በቁጥጥር ስር አውሎ ህፃናቱን ለቤተሰቦቻቸው ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ
***

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 05 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የወሩ ማብቂያ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አለም ባንክ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ከቀኑ 11፡45 ሠዓት ላይ የቤት ሰራተኛ የሆነችውን ሀብታሟ ወርቁ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በስለት ተወግታ መሞቷን እና እህትማማች የሆኑ የአስርና የሰባት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃን እምነት አሽናፊ እና ጄሪ አሽናፊ መጥፋታቸው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ሪፖርት ይደሰርሰዋል፡፡

ጠቅላይ መምሪያው የፎረንሲክ፣ የምርመራ እና የክትትል ቡድን አባላትን በማደራጀት ወንጀል ወደተፈፀመበት ስፍራ ከሄዱ በኃላ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ሥራው መጀመሩን የጠቅላይ መምሪያው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ገልፀዋል፡፡

የሟች ማንነት እንጂ የገዳይ ማንነት አለመታወቁ፣ ሀብታምን ማን ገደላት ? ህፃናቱስ የት ተሰውሩ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እና ወንጀል ፈፃሚውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንዲሁም የጠፉትን ህፃናት ለማግኘት ክትትሉ በቀጠለበት ሒደት መንግስቱ ደላሳ የተባለ ግለሰብ ለህፃናቱን ወላጅ እናት ለወ/ሮ ሃዊ ዮሴፍ ስልክ በመደወል ህፃናቱን ማገቱን 10 ሚሊዮን ብር ካልተሰጠው ልጆቹን እንደሚገድላቸው እንዲሁም ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቀች በህፃናቱ ላይ የከፋ እርምጃ እንደሚወስድ የሚገልፅ መልእክት ያስተላልፋል፡፡

ህፃናቱ ከዚህ ቀደም አጋቹን ስለሚያውቁትና የደገሰላቸውን የሞት ድግስ ባለማወቃቸው ያለ ጭንቀት ሲጫወቱ እና ልጆቹ እርሱ ጋር መሆናቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ ለወ/ሮ ሃዊ ይልካል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር ባደረጉት የክትትል ሥራ የፖሊስ አባላት ቀንና ሌሊት ባደረጉት ያላሰለሰ ክትትል አጋቹን እና ሌሎች ተባባሪዎቹን ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በቁጥጥር ስር በማዋል ሁለቱንም ህፃናት በአዳማ ከተማ ልዩ ቦታው ቦሌ ሰፈር እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ታግተው ከተቀመጡበት ቤት በሠላም ማስለቀቁን ኮማንደር ማርቆስ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣዎችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የህፃናቱ ወላጅ እናት ወ/ሮ ሃዊ ዮሴፍ እና አባታቸው አቶ አሸናፊ ጫኔ እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት በእጅጉ ተጨንቀው እንደነበር ተናግረው የአዲስ አበባ ፖሊስ እና ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ጥረት ልጆቻቸውን በሰላም በማግኘታቸው በፀጥታ አካላት ተግባር ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከታቸውን ለዚህም በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ስም ኮማንደር ማርቆስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

መሰል ችግር ሲያጋጥም ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ፖሊስ አስታውቆ ነገር ግን ልዩ ልዩ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ስለ ወንጀሉ መረጃ ማሰራጨት ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ምቹ ሆኔታን እንደሚፈጥር ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢው ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የፓርላማ አባላት ማትጊያና ጥቅማ ጥቅም እንዲስተካከልላቸው ጥያቄ አቀረቡ  - ከግድያ በስተቀር ሁሉን ዓይነት ምርመራ የሚፈቅደው አዋጅ ተሰርዟል  - ‹‹አዋጁ ውስጥ ያለው ድንጋጌ እንዲቀር ብ...
07/10/2025

የፓርላማ አባላት ማትጊያና ጥቅማ ጥቅም እንዲስተካከልላቸው ጥያቄ አቀረቡ

- ከግድያ በስተቀር ሁሉን ዓይነት ምርመራ የሚፈቅደው አዋጅ ተሰርዟል
- ‹‹አዋጁ ውስጥ ያለው ድንጋጌ እንዲቀር ብከራከርም የፓርቲ ዲሲፕሊን በመሆኑ አዋጁን አፅድቄያለሁ›› - የብልፅግና ፓርቲ የፓርላማ አባል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚሰጣቸው ማትጊያና ጥቅማ ጥቅም በቂ ባለመሆኑ ይስተካከል ሲሉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ፓርላማው በአራተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄደው የዓመቱ ማጠቃለያ ሁለተኛ ልዩ ስብሳባ፣ የምክር ቤቱን የ2017 ዓ.ም. አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡
የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ለምክር ቤት አባላት በሎጂስቲክስና በትራንስፖርት አቅርቦት የታዩ መልካም ጅምሮች መኖራቸውን፣ እንዲሁም የአባላትን አቅም የሚገነቡ ፕሮግራሞች በማዘጋጀት በሕግ አወጣጥ፣ በቁጥጥርና ክትትል፣ በውክልና ሥራና በዲፕሎማሲ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን ተናግረዋል።

(ምንጭ፡ ሪፖርተር)

አይበገሬው ፒኤስጂ! ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን በፊፋ የክለብ አለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ላይ 4ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ አልፈዋል። እሁድ ለዋንጫ ከቸልሲ ጋር የሚገጥሙ ይሆናል። ዋንጫውን...
07/09/2025

አይበገሬው ፒኤስጂ!

ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን በፊፋ የክለብ አለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ላይ 4ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ አልፈዋል። እሁድ ለዋንጫ ከቸልሲ ጋር የሚገጥሙ ይሆናል።

ዋንጫውን ማን ያነሳዋል? 🤔

07/07/2025
የሴታዊት መቀነት መሰናዶ የዚህ ሳምንት እንግዳ ተቋም አማረ እና ሀና አማረ ናቸው። እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። | Meqenet Show - A Setaweet conversation with Teq...
07/06/2025

የሴታዊት መቀነት መሰናዶ የዚህ ሳምንት እንግዳ ተቋም አማረ እና ሀና አማረ ናቸው። እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። | Meqenet Show - A Setaweet conversation with Tequam Amare & Hanna Amare

ለመመልከት 👇
https://youtu.be/2XwhvJy8jVE

Address

Baileys Crossroads, VA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioTube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EthioTube:

Share