
08/21/2023
ቢሊዬ❤ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዛሬ አየሁሽ
አሁን ምን ማለት እንዳለብኝ ባላውቅም በዚች ቅጽበት የሚሰማኝን ስሜት ግን መናገር እፈልጋለሁ። ገና በመጀመሪያ እንዳየሁሽ ልቤ ስንጥቅ ሲል የነበረኝን ስሜት መቼም በሕይወት እያለሁ አልረሳውም። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የምታደርጊውንና የምትናገሪውን በሙሉ በስስት እከተላለሁ አዳምጣለሁ። ምንም እንኳን ለአንቺ ያለኝን ስሜት ለመግለፅ ትክክለኛ ቦታ ባላገኝም አንቺን ባሰብኩ ጊዜ የሚሰማኝ ስሜት ልዩ በመሆኑ በተደጋጋሚ አስብሻለሁ፤ በቃ ደስ ይለኛላ። ቢሊ 😍 በሁሉም ነገሮችሽ እንደማፈቅርሽ ግን እንደዚህ በአደባባይ ላሳውቅሺ እፈልጋለሁ።