
12/01/2024
ኢትዮጵያ በ5 ቢሊየን ፓውንድ "ሜጋ ኤርፖርት ሲቲ" በመገንባት ላይ ትገኛለች። ተጠናቆ ስራ ሲጀምርም በአፍሪካ ግዙፉና በአለም ካሉ እጅግ ቢዚ ኤርፖርቶች አንዱ ይሆናል።
ከአዲስ አበባ በ25 ማይል ርቀት ላይ በቢሾፍቱ አቅራቢያ የሚገነባው አዲሱ ኤርፖርት በ2029 ሲጠናቀቅ በአመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግዳል። ተርሚናል እና አራት ማኮብኮቢያ/ማረፊያ ራንዌዮች ይኖሩታል።
ከባህር ጠለል በላይ 2,334 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፋዊ የአቪዬሽን ማዕከልነቷን እያረጋገጠ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ መጨናነቅ ገጥሞታል።
የሚገነባው "የሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ይህን ችግር ከማቃለል ባለፈ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ያሳድጋል፣ ሀገሪቱን በአለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ዋና ተዋናይነት ያስቀምጣል። አዲሱ ተቋም እንደ ዱባይ እና ሄትሮው ያሉ አለምአቀፍ አየር ማረፊያዎችን ለመወዳደር ያለመ ነው።