አዲስ ገፅ/adisegatze

አዲስ ገፅ/adisegatze �ሊነጋ ሲል !

ጨለማው ይበረታል ሰቃይ ፈተናችን ከአቅማችን በላይ ይሆናል ።
ጨለማውን ተጋፍጠን በፅናት እሰከ ቆምን ድረስ የብርሀን ወገግታ ይሰተዋላል !
ህይወት ይቀጥላል ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,✋
አብዱ ገለቱ ነኝ 🙏
(8)

ሰላም አዲስ ገፅ ለእናንተ ይሆናል ፣ ያዝናናል ፣ ያስተምራል ብሎ የሚያስባቸውን ጉዳዮች ወደ እናንተ ያደርሳል። በቴሌግራም t.me/KGSAE ያገኙናል ይቀላቀሉ። አዲስ ገፅ kidsgoalsocceracademy በአሜሪካ እህት ሚዲያ ተቋም ነዉ። ዌብሳይታችንን ይጎብኙ። https://kidsgoalsocceracademy.com/ የታዳጊዎች እግርኳስ አሰልጣኝ ኤሊያስ እንዳለ።

ሰበር ዜና!!ስምምነቱ ተጠናቋል በቅርብ ቀናት ኢዜ የአርሰናል ተጫዋች ይሆናል።
08/20/2025

ሰበር ዜና!!
ስምምነቱ ተጠናቋል በቅርብ ቀናት ኢዜ የአርሰናል ተጫዋች ይሆናል።

ሰበር ዜናአርሰናልና ክርስቲያል ፓላስ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።
08/20/2025

ሰበር ዜና
አርሰናልና ክርስቲያል ፓላስ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።

ምንም ጥርጥር የለዉም ኢዜ አርሰናልን ይመርጣል ከቶትንሃም ይልቅ። ⏳⏳⌛
08/20/2025

ምንም ጥርጥር የለዉም ኢዜ አርሰናልን ይመርጣል ከቶትንሃም ይልቅ። ⏳⏳⌛

ኢዜ ወደ ቀድሞ ክለቡ መመለስ ይፈልጋል። ነገሮች በክለቦች መኻከል እየተደረጉ ይገኛሉ። አርሰናል የካይ ሀቨርትዝን አገልግሎት ለወራት ስለማያገኝ ተጫዋች የማስፈረም ግዴታ ዉስጥ ገብቷል።
08/20/2025

ኢዜ ወደ ቀድሞ ክለቡ መመለስ ይፈልጋል። ነገሮች በክለቦች መኻከል እየተደረጉ ይገኛሉ። አርሰናል የካይ ሀቨርትዝን አገልግሎት ለወራት ስለማያገኝ ተጫዋች የማስፈረም ግዴታ ዉስጥ ገብቷል።

ሰበር ዜናአርሰናል ኢዜን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል። ⌛⌛⌛
08/20/2025

ሰበር ዜና
አርሰናል ኢዜን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል። ⌛⌛⌛

ሰበር ዜናካይ ሀቨርትዝ የጉልበት ጉዳት አጋጥሞታል። ምናልባት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ የምያርቀዉ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል😢
08/20/2025

ሰበር ዜና
ካይ ሀቨርትዝ የጉልበት ጉዳት አጋጥሞታል። ምናልባት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ የምያርቀዉ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል😢

የተለያዩ ሴቶችን ፎቶ ግራፍ ከቴሌግራምና ከቲክቶክ በማውረድ በከፈተው ሀሰተኛ አካውንት እለቃለሁ ብሎ በማስፈራራት ክብርን በማዋረድና የፆታ ግኑኝነት በመጠየቅ የተጠረጠረን ግለሰብ ይዞ ምርመራ...
08/20/2025

የተለያዩ ሴቶችን ፎቶ ግራፍ ከቴሌግራምና ከቲክቶክ በማውረድ በከፈተው ሀሰተኛ አካውንት እለቃለሁ ብሎ በማስፈራራት ክብርን በማዋረድና የፆታ ግኑኝነት በመጠየቅ የተጠረጠረን ግለሰብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ።

ሀምሌ 30 ቀን 20017 ዓ/ም ከምሽቱ 12ሰአት ተኩል ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ብሔረ ፅጌ መናፈሻ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው ወንጀሉ የተፈፀመው።

አንተን አየሁ ሞላ የተባለው ተጠርጣሪ ራሱ ባዘጋጀው ሰቦንቱ ኤጀንት ሰርቪስ የሚል ሀሰተኛ የቲክቶክ አካውንት በመክፈት የግለሰቦችን ፈቃደኝነት ሳይጠይቅ ከቴሌግራም፣ ከቲክቶክ እንዲሁም ሴቶችን መንገድ ላይ በሚጓዙበት ወቅት ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረፅ ራሱ በከፈተው አካውንት ላይ አቀናብሮ በመልቀቅ ግለሰቦችን በማስፈራራትና በማስገደድ የፆታ ግኑኝነት ጭምር የሚጠይቅ ግለሰብ መሆኑን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ተከሳሹ ወይዘሮ ሰላማዊት ታደሰን የቤት ተከራይ መስሎ በመቅረብ ስልክ ቁጥሯን በመውሰድ የራሱ ባልሆነ ስልክ ቁጥር በመጠቀም ከቴሌግራም ላይ ፎቶዋን በማውረድና በማቀናበር ግላዊ የፆታ ግኑኝነት ከሷ ጋር እንድትፈፀም ያቀናበረውን ሰነድ በማስፈራሪያነት በመጠቀም ያስገድዳታል። የግል ተበዳይም ባለትዳርና የልጆች እናት ነኝ ይህንን ድርጊት ለመፈፀም ፈቃደኛ አይደለሁም ብትለውም ማስፈራራቱን ባለማቋረጥ ባዘጋጀው ሀሰተኛ የቲክቶክ አካውንት "ሹገር ማሚ" ስለሆነች በእኔ አካውንት ማግኘት ትችላላችሁ በማለት ከአንድ ሺ በላይ ተከታይ ባለው የቲክቶክ አካውንት በማጋራቱ የግል ተበዳይ ለፖሊስ አመልክታለች፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሴቶች እና ህፃናት ወንጀሎች ምርመራ መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።

በተጠርጣሪው ግለሰብ ላይ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የማስፋት ተግባር ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈፀም ካዘጋጃቸው ፎቶዎች ጋር መያዙንም ፖሊስ አስታውሷል፡፡

ዜጎች ከማያውቁት ሰው ጋር በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ምንም ዓይነት ግንኙነት ባለመፍጠር ከመሰል ወንጀሎች ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

አዲስ አበባ ፖሊስ

??.
08/20/2025

??.

በዚህች ቀን ከ13 አመት በፊት መለስ ዜናዉ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
08/20/2025

በዚህች ቀን ከ13 አመት በፊት መለስ ዜናዉ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

ትራምፕ ኔታንያሁን የጦር ጀግና ሲሉ አወደሱ  የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁን የጦር ጀግና ሲሉ አወድሰዋል።ትራምፕ ከወግ አጥባቂው የሬዲ...
08/20/2025

ትራምፕ ኔታንያሁን የጦር ጀግና ሲሉ አወደሱ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁን የጦር ጀግና ሲሉ አወድሰዋል።

ትራምፕ ከወግ አጥባቂው የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ማርክ ሌቪን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኔታንያሁ ጥሩና ጠንካራ የጦርነት ጀግና ነው ብለዋል።

በሰኔ ወር ትራምፕ የኔታንያሁ የሙስና ክስ ውድቅ እንዲሆን የጠየቁ ሲሆን፤ ተቀናቃኞቹ እስር ቤት ሊጥሉት እየሞከሩ ነው በማለት ተናግረዋል።

እ.ኤ.አ ከ2020 ጀምሮ በችሎት ክሳቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት ኔታንያሁ፣ በስልጣን ላይ እያሉ የወንጀል ክስ የገጠማቸው የመጀመሪያው የእስራኤል መሪ ናቸው።

ባለፈው ህዳር ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በኔታንያሁ እና በቀድሞው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ በጋዛ የጦር ወንጀል ፈፅመዋል በማለት የእስር ማዘዣ ማውጣቱ የሚታወስ ነው።

የህፃናት ሆድ ድርቀት አሳሳቢ የሚሆነው መቼ ነው❓ የሆድ ድርቀት አብዛኛውን ጊዜ በትናንሽም ሆነ በትላልቅ ህፃናት ላይ የሚከሰት እና በጊዜ ሂደት ከህፃናቱም ባለፈ ወላጆችን የሚያስጨንቅ የጤና...
08/19/2025

የህፃናት ሆድ ድርቀት አሳሳቢ የሚሆነው መቼ ነው❓

የሆድ ድርቀት አብዛኛውን ጊዜ በትናንሽም ሆነ በትላልቅ ህፃናት ላይ የሚከሰት እና በጊዜ ሂደት ከህፃናቱም ባለፈ ወላጆችን የሚያስጨንቅ የጤና እክል ነው።

አብዛኛውን ጊዜ በቀላሉ በራሱ ከሚስተካከከል እንዲሁም አልፎ አልፎ ለህክምናም አዳጋች የሚሆን ሁኔታን በመፍጠር ህፃናት ላይ አካላዊም ሆነ የስነ ልቦናዊ ችግርን ማለትም የለተለት እንቅስቃሴ ፣ የትምህርት የመማር ሂደትን ፣ እንዲሁም የማህራዊ ሕይወታቸው ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተፅእኖ ያሳድርባቸዋል።

ህፃናት እንደ የእድሜያቸው የተለያየ የካካ ጊዜ እንዲሁም ካካ የሚሉበት የቀን ልዩነት የተለያየ ስለሆነ ካካ የሚያደርጉበት ቀናቶች ስለረዘመ ብቻ በትክክል የሆድ ድርቀት አለባቸው ማለት አይደለም ።

በአጠቃላይ በህፃናት ላይ የሚከሰት የሆድ ድርቀት ምክንያቶቹ በዋነኝነት በሁለት ይከፈላሉ ።

1️⃣ኛው ከ 90% በላይ ህፃናት ላይ የሚሰተዋል ከአመጋገብ ፣ ከሚውሉበት አካባቢ እንዲሁም የለተለት ኑሮ ጋር በተያያዘ የሚከሰት የሆድ ድርቀት ሲሆን ማለትም ይህ ሁኔታ የሚከሰተው
✔️ የእናት ጡት ወተት ሲቆም ወይም ሲቀንስና የጣሳ ወተት ሲጀምሩ
✔️ ከ6 ወር በኋላ ተጨማሪ ምግቦችን ሲጀምሩ
✔️ ትምህርት ቤት ገብተው መማር ሲጀምሩ
✔️ መኖሪያ ቦታ ሲቀየሩና የአካባቢው ሁኔታ አዲስ ሲሆንባቸው
✔️ የላም ወተት መጠቀመም ሲጀምሩ
✔️ በቂ የሆነ ውሀ አለመጠጣት እና
✔️ ተያይዞ የፊንጢጣ ስንጥቃት ሲያጋጥማቸው ነው።

አንድ ህፃን ከዚህ ችግር ጋር በተያያዘ የተከሰተ የሆድ ድርቀት አለበት ለማለት እነዚህ ከጠቀስኳቸው ስድስት ነጥቦች ቢያንስ ሁለት እና ከዛ በላይ ምልክቶችን ለአንድ ወር ወይም ከዛ በላይ ሊኖሩት ይገባል እነሱም

❶ በሳምንት ውስጥ ሁለት እና ከዛ በታች ካካ የሚያደርግ ከሆነ

❷ ካካ በሚያደርግ ሰአት የመጨነቅ እና የህመም ስሜት ካለው

❸ ካካው የደረቀ እና ውፍረቱ ከወትሮው በተለየ ተለቅ ያለ ከሆነ

❹ ፖፖ ላይ ካካ ማድረግ ለምዶ ነገርግን ቢያንስ እላዩ ላይ በሳምንት አንድ ቀን ካካ ካደረገ

❺ በፊንጢጣ ወይም በራጅ ምርመራ የታችኛው የአንጀት ክፍሉ ላይ የካካ መከማቸት ከታየ እና

❻ ህመሙን ፍራቻ ካካ እያለበት ካካን ያለአግባብ መያዝ ወይም ላለማውጣት መታገል ናቸው ።

2️⃣ኛው ከአንጀት አፈጣጠር ችግር ፣ ከሆርሞን እና የሰውነት ንጥረነገር መዛባት፣ ከሚወሰዱት መድሀኒቶች ወይም ከነርቭ ችግር ጋር በተያያዘ የሚከሰት የሆድ ድርቀት ችግር ነው ።

የሆድ ድርቀቱን መንስኤ ከሁለቱ የቱ እንደሆነ ለማወቅ ከመወለዱ ጀምሮ አሁን እስካለበት እድሜ ድረስ የህፃኑን የጤና ታሪክ ማጥናት እና የአካላዊ ምርመራ ወይም እንዳስፈላጊነቱ ተጨማሪ የላብራቶሪ እና የራጅ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።

⚠️ የህፃናት የሆድ ድርቀት አሳሳቢ የሚሆነው መቼ ነው ❓

✔️ ህፃኑ ከተወለደ በኋላ የመጀመሪያ ካካ ያለው ከሁለት ቀን በኋላ ከሆነ
✔️ በተያያዘ ከእድገታቸው ጋር የሰውነት ክብደት የማይጨምር ከሆነ
✔️ ድርቀቱ የተከሰተው ህፃኑ ከተወለደበት የመጀመሪያ አንድ ወር ጀምሮ ከሆነ
✔️ ተያይዞ ቢጫ ወይም አረንጓዴ የቀላቀለ ማስመለስ ካለ
✔️ የተጋነነ የሆድ መነፍት እና ትኩሳት ካለ
✔️ በአካላዊ ምርመራ ሲታይ የፊንጢጣ አፈጣጠር ችግር ወይም የጀርባ አከርካሪ ነርቭ ችግር
ካለ
👉 ለየት ያለ ተጨማሪ የሆነ ምርመራ እና ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።

✅ ህክምናው

የህፃናት የሆድ ድርቀት እንደ የምክንያቱ እና እንደ የሆድ ድርቀቱ ጥንካሬ እንዲሁም ምልክቱ እንደቆየበት የጊዜ ርዝመት የተለያዩ ህክምናዎች ይደረጋሉ።

የሆድ ድርቀቱ መንስኤ ከአንጀት አፈጣጠር ችግር ፣ ከሆርሞን እና የሰውነት ንጥረነገር መዛባት፣ ከሚወሰዱ መድሀኒቶች ወይም ከነርቭ ችግር ጋር የተያያዘ ከሆነ እንደተገኘው መንስኤ ትክክለኛ ህክምና በመድሀኒት ፣ በአንጀት እጥበት እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ የቀዶ ህክምና በማድረግ ይታከማል።

ነገርግን መንስኤው እነዚህ የጠቀስኳቸው ችግሮች እንዳልሆኑ ከተረጋገጠ የሚሰጠው ህክምና እንደ የሆድ ድርቀቱ ጥንካሬ ይለያያል።

ቀለል ያለ አይነት ከሆነ አመጋገብን በማስተካከል እና ከወትሮው ተጨማሪ ፈሳሽ ነገር በብዛት እንዲወስዱ በማድረግ እንዲሁም እድሜያቸው ከሁለት አመት በላይ ከሆነ ፖፖ ላይ ካካ እንዲያደርጉ በማስተማር እና በማበረታታት እንዲታከም ይደረጋል።

በዚህ መንገድ የሆድ ድርቀቱ ለውጥ ከሌለው ወይም በምርመራ ሲታይ የሆድ ድርቀቱ ጠንከር ያለ ከሆነ ደግሞ ከላይ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ የሰገራ ማለስለሻ መድሀኒት በመስጠት እና በፊንጢጣ በኩል ሞቅ ያለ ንፁህ ፈሳሽ በማስገባት የደረቀውን ካካ አለስልሶ እና አጥቦ እንዲወጣ በማድረግ ይታከማል።

ከዛም እንዳስፈላጊነቱ የሰገራ ማለስለሻ መድሀኒቱን በማስቀጠል የሆድ ድርቀቱ እስከሚድን ድረስ በክትትል እንዲታከም ይደረጋል ማለት ነው።

ማጣቀሻ
1. Coran Pediatric Surgery 7th Edition
2. American Pediatric Surgical Association Guideline

ዶ/ር ዮናታን ከተማ : በቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ቀዶ ህክምና ሬዚደንት ሀኪም

ሰላምና ጤና በያላችሁበት ይሁን!

ሰናይ ምሽት🥰
08/19/2025

ሰናይ ምሽት🥰

Address

Hyattsville, MD

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዲስ ገፅ/adisegatze posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አዲስ ገፅ/adisegatze:

Share