
11/12/2024
"የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስነ አይምሮ ብስለት"
እነዚህን በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ሁለት ግለሰቦችን የሚያገናኛቸው ጥቂት ነገሮችንና የሚለያቸውን ሀያሌ ክፍተቶች እስቲ በመጠኑ እንመልከት። በመጀመሪያ ደረጃ ከምስሉ በስተ-ቀኝ ያለው ምስል የምንመለከተው ብዙዎችን በሚገርም ሁኔታ በተለይ ኢትዮጵያዊያን የማህበረሰብ ድህረ-ገፅ ተጠቃሚዎችን ስነ-አእምሮ መቆጣጠር የቻለና በብዙዎች ጭንቅላት ውስጥ ያለ ምንም ግብግብ የሰረፀ የዓመቱ ተፅህኖ ፈጣሪ አቶ ዮናስን ነው። ከምስሉ በስተግራ ደግሞ የዓለማችን የሳይኮሎጂ ሊቅ እና ኒውሮሎጅስት (የነርቭ) ሀኪም የኦስትሪያ ተወላጅና ጅዊሻዊ ዘር ያለበት ድንቅ ሰውን ማንበብ እንዴት እንደሚቻል ለዓለማችን (የሳይኮ አናሊስስ) ጥበብ የለገሰን ታላቅ ጠቢብ ሲግመንድ ፍሮይድን ነው። እነዚህን ግለሰቦች በየፈርጃቸው የፈፀሙት የየራሳቸው መንገድ የባህሪ መገለጫ ፣የእውቀት ደረጃ፣የማንነት ኩኔታ እና የአኗኗር ዘይቤ ፍፁም የተለያዩ ግለሰቦች ናቸው። ሆኖም ግን ሁለቱንም የሚያገናኛቸው ሰውነት አልያም ፍጡር መሆናቸው ሁለቱም በተለገሳቸው እውቀት ተፅህኖ መፍጠር መቻላቸው ነው።መቼም አቶ ዮናስን በመልካም ምግባሩ የሚፈርጀው እንደሌለ ብዙዎች ቢናገሩም ቅሉ የተናጋሪውንም የአእምሮ ትኩረት መሳቡ ያስደንቃል።ስለዚህ ትንሽም ይሁን በብዙ የአድማጩን የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚው ቅድመ ርዕስ ሳይሆን ያለፈበት ግዜ አልነበረም።ይሄ የሚያመለክተው ዮናስ አሁን ደግሞ ምን ሊል ይሆንል? የሚል ጥያቄ ያነገቡ በድህረ ገፃቸው እርሱን ለመስማት ይጔጔሉ እጅግ ቦታ ይሰጣሉ።ዮናስ በአንዱ ባይሳካለት ርዕስ እየቀያየረ ትኩረትን ሲወጥር ህዝቡን እንደፈለገ ሲስበው ይታያል ለምሳሌ በፖለቲካው ሲሰለች በሀይማኖት እያለ አድማጩን ይዞታል። ታድያ ምነው ከሲግመንድ ታላቅ ጠቢብ ጋር ምን አገናኛቸው ትሉ ይሆናል? ከሚያገናኛቸው ነገር አንዱ ሲግመንድ የታካሚውን አእምሮ ለመግዛት ትኩረቱን ለመሳብ ብዙ የሳይኮሎጂ የህክምና መላ ምቶች ይጠቀማል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ እርሱን እንዲጠሉት የተለያየ የተወሳሰበ መንገድ ይጠቀማል ምክንያቱም የሰው ልጅ በጥላቻ ውስጥ ትክክለኛ መውደድ እና ስበት መለየት ስለሚቻል ነው። የአቶ ዮናስም አካሄድ ብዙዎቻችን የማፈልገውን አክት በመጫወት ጥላቻ እንዲያድርብን ካደረገ በኋላ የሚፈልገውን ትኩረት ካገኘ በኋላ የፈለገውን መልዕክት ቢያስተላልፍ እንዲደመጡለት አድርጔል። በዌብሳይት ድህረ-ገፁ ላይ የሚለቃቸውን ቪዲዮ መልዕክቶች ቢያንስ ብዙሀኑ ይከታተሉታል .....ደግሞስ በጥላቻና በቧልትም ይሁን ምልከታውን እንድናይለት ተገደናል። የስነ-አእምሮን ክትትል ወይም ትኩረት ከሚስቡ ነገሮች አንዱ ጥላቻ መሆኑን እጅጉን ተጠቅሞበታል። በዚህ እጅግ አደንቀዋለው። ምን አልባት ሲግመንድ የሳይኮ አናሊስስ ሜትዶችን ይጠቀም የነበረው ሰውን ለማከም ሲሆን ዮናስ ደግሞ የሰውን ጭንቅላት ለመመረዝ መሆኑ ልዩነታቸውን ያሰፋዋል...........