
07/22/2025
(Naod Tube) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስመራ ቤተመንግስት ከተናገሩ ከሁለት ቀን በኋላ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከየትኛውም አቅጣጫ የሚሰነዘርበትን ትንኮሳ ለመመከት በሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጅማ በነበረ ወታደራዊ ስነ ስርዓት ላይ ተናገሩ።
ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ፣ የሠራዊቱ ዋነኛ ተልዕኮ የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር መሆኑን አስታውሰው፣ ይህንን ኃላፊነቱን ለመወጣትም ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ ነው ብለዋል። "ኢትዮጵያዊያን የጀግንነትና የአይበገሬነት ስነ-ልቦና ያለን ህዝቦች መሆናችንን ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው" ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፣ ሠራዊቱ የሀገርን ክብር ጠብቆ ለማቆየት ዛሬም እንደትናንቱ ጽኑ አቋም እንዳለው ገልጸዋል።
ጅማ፣ ኢትዮጵያ::