Ermiyas Girma

Ermiyas Girma "እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ ትእዛዛትህን ግን አልረሳሁም"
መዝ:- 118 - 141
(3)

👉"በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ" መዝ. 5፥3 👉"My voice shalt Thou hear in the morning, O Lord; in the morning will I dir...
09/08/2026

👉"በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ" መዝ. 5፥3

👉"My voice shalt Thou hear in the morning, O Lord; in the morning will I direct my prayer unto Thee" Ps. 5:3

የረቡዕ ሰይፈ ሥላሴ (መቅድሙና የዘወትሩ ከበታች ተካቷል)አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ። ፩. የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክር...
09/08/2026

የረቡዕ ሰይፈ ሥላሴ (መቅድሙና የዘወትሩ ከበታች ተካቷል)

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ።

፩. የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ይክበር ይመስገን በግልጽና በሥውር ስለሰጠኝ ጸጋ በየሰዓቱ ሁሉ አመሰግነዋለሁ።
፪. አቤቱ በዚች በተባረከች ዕለት ጸሎቴን ትሰማኝና ልመናዬንም ትቀበል ዘንድ በገናንነትህና በአስፈሪነትህ በኃያልነትህና በመለኮትነትህ እለምንሃለሁ አቤቱ ኃጢአቴን ያስተሥርይልኝ ዘንድ የተወደደው ልጅህን ቅዱስ ሥጋውንና ክብር ደሙን ለመቀበል የበቃሁ አድርገኝ።
፫. ፍርሃት በሌለበት ረድኤትህ ጠብቀኝ አቤቱ ሰውነቴን በተንኮል ከሚፈልጓት ተንኮለኞች ሁሉ አድነኝ ትዕቢትን ትምክህትን ቂምና ምቀኝነት ቁጣና በደልን የመሳሰሉትንም ክፋቶች ሁሉ ከእኔ አርቅልኝ።
፬. አቤቱ በጌትነትህ ይቅር ባይነትህና ቸርነት ሥውሩንና ግልጹን ታላቁንና ታናሹን ኃጢአቴን በደሌንም ሁሉ ይቅር በል።
፭. አቤቱ በቅዱስ ወንጌልህ ትእዛዝ መሠረት በጐዳናህ እንድሄድ አድርገኝ አቤቱ የሰይጣንን የልቡን ክፋትና መቃጥኑንም (ወጥመዱን) ከእኔ አርቅልኝ እኔ ባሪያህ ፍጹም ደሀና ምስኪን የተናቅሁና ደካማም ነኝና።
፮. አቤቱ መልካሙን በአደረግኽልኝ ፈንታ የክፋትን መልስ መለስኩልህ የቸርነትህን ጸጋ ሰጠኸኝ እኔ ግን ደግሜ በደልኩ ከክፋቴ እስክመለስ ጠበቅኸኝ በእውነትም ጐዳና መራኸኝ እኔ ግን ከኃጢአቴ አልተመለስኩም።
፯. አሁንም አቤቱ እንደ ቸርነትህ ይቅር እንድትለኝና በክንፈ ረድኤትህም ትሠውረኝ ዘንድ ቅዱስ ፈቃድህን እማልዳለሁ ወይም እጠይቃለሁ።
፰. አቤቱ ጎዳናዬን በሰላምና በደኅንነት አቅና በቸርነትህና በይቅርታህ ከክፉ ነገር ተወግጄ መልካሙን ነገር እንድከተል አድርገኝ።
፱. ለአንተ ክብር ምስጋና ስግደት ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን።
፲. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአነዋወር አንድ በገጽ ሦስት ናቸው፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው።
፲፩. አብ በአካሉ ፍጹም ነው ወልድም በአካሉ ፍጹም ነው መንፈስ ቅዱስም በአካሉ ፍጹም ነው እሊህ ሦስቱ አካላት በመለኮት አንድ ናቸው።
፲፪. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ኃያልና የሚያስፈራ ዓይኑ እንደ እሳት የሚነድ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፫. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የራስ ፀጉሩ እንደበረድ የነፃ እንደ ሰርዲኖስና ኢያሰጲድ ዕንቍ የከበረ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፬. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የመቅደሱ አጥር በእሳት የታጠረ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፭. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር በጠላት ፊት የማይበገር እሱ ጽኑዕ አዳራሽ (ግንብ) ነው።
፲፮. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አግዚአብሔር ጠፈርን ያለምሰሶ መሬትን ያለመሠረት ፈጥሮ ያለድጋፍ በቃል ብቻ ያጸና እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፯. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ሁሉን በየወገኑ የሚገዛ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፰. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር መንግሥቱ የማያልፍ ግዛቱም ለትውልደ ትውልድ (ለዘለዓለም) የሚኖር እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፱. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የሦስትነቱ ሥርዓት የማይለወጥና ለሦስትነቱ ምስጋና የሚገባው እርሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፳. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር በመባርቅት የሚላኩት ነጐድጓድ የሚያመሰግኑት እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፳፩. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ሦስት ሲሆን አንድ አንድ ሲሆን ሦስት የሚሆን እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፳፪. ዓለምን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፫. ቁጣውን በቸርነቱ ባሕር የሚያሰጥማት እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፬. የመቅሠፍቱን እሳት በይቅርታው ውሃ የሚያጠፋ እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፭. የማይቀየም የዋህ ንስሐን የሚወድ እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፮. ኃጢአትን በቸርነቱ ጥላ የሚሸፍን እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፯. አበሳን በቸርነቱ ጉድጓድ የሚደፍን እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፰. በደልን በትዕግሥቱ መጋረጃ የሚጋርድ እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፱. ለእርሱ ለብቻው ምስጋና ይገባል። ለመንግሥቱም እዘዝ ይገባል። ለሦስትነቱ ክብር ይገባል ለከኃሊነቱ ኃይል ይገባል። ለመለኮቱ ሥልጣን ይገባል ለዘላለሙ።
፴. መለኮት በገጽ ሦስት ሲሆን በአንዲት ክሂሎት ሰማይና ምድርን ባሕርንም በውስጧም የሚገኙትን ሁሉ የፈጠረ እሱ ነው።
፴፩. መለኮት በአካል ሦስት ሲሆን መለኮቱ አንድ ነው ስለሆነም በአንድነት ኅብረት ብርሃንን ከጨለማ የለየ እሱ ነው።
፴፪. መለኮት በሥሉስ አካሉ ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር ብሎ አዳምን የፈጠረ እሱ ነው።
፴፫. ዳግመኛም ሥላሴ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ አሉ።
፴፬. የሥላሴ ምክር በጥቅመ ሰናኦር ቋንቋዎችን ለያየ እርሱ ቅሉ አንድነታቸውና ሦስትነታቸውን ሲያጠይቅ ኑ እንውረድና የከለዳውያንን ነገር እንበትንባቸው ብሏልና።
፴፭. ሥላሴ ወይም ሦስትነት ከመለኮቱ የአንድነት አነዋወር ሳይነዋወጽ በሦስት ሰዎች አምሣል በቤተ አብርሃም ተስተናገደ።
፴፮. ይስሐቅን ለመዋጀት በበግ አምሳል ለተመሰለ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፴፯. ከኤሳው ይልቅ የያዕቆብን ሥነ ባሕርይ የመረጠ እንዲሁም በመሰላል ላይ ሆኖ ለተገለጸለት መለኮት መስጋና ይገባል።
፴፰. ሰዋስውም የተባለችው ከመለኮታዊ ፀሐይ ጋር የመለኮት አዳራሽ በማኅፀኗ የተወሰነ የቅድስት ማርያም አምሳል ነው።
፴፱. ለእርስዋ በሰማይና በምድር በባሕርና በቀላያት ሁሉ አገልግሎትና ምስጋና ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን።
፵. ዳግመኛም ጎህ እስኪቀድ ድረስ ለዚህ ለተመረጠ ሰው (ያዕቆብ) በጐበዝ ሰው አምሳል ለተገለጸ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፵፩. በዚህ ጊዜ ስለ ምሥጢረ ትስብእቱ ሲታገለው ሰው አምላክ አምላክ ሰው ለመሆኑ ምስጢር በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እድል ገጠመህ ሲል አመለከተው።
፵፪. ይህንንም ቃል መሠረት በማድረግ ሁሉን ፈጸመ በወንጌል እንደ ተነገረው የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ተብሏልና።
፵፫. በይሁዳ ዕፃ የአንበሳ ልጅ ተብሎ ለተሰየመ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፵፬. ከተሸጠ ዮሴፍ ጋር ላልተለየ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፵፭. በታላቅ ኃይልና በጽኑ ክንድ ዓሥራ ሁለቱን ነገደ እስራኤል ከባርነት ነፃ ላወጣ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፵፮. እርሱ ቅሉ አብ አሕዛብ በኃይሌ (በማዳኔ) ይተማመናሉ እውነትም በእርሱ ጸንታ ትኖራለች ብሎ እንደ ተናገረ መዝራዕት የተባለም የአብ አንድ ልጁ የሚሆን ወልድ ነው።
፵፯. ዕንጨቱን ባለማቃጠል በዕንጨቱ ላይ በሚታይ ነደ እሳት አምሳል ለሙሴ ለተገለጸለት የእግዚአብሔር መልክተኛ ምስጋና ይገባል።
፵፰. ዕፀ ጳጦስም የተባለችው ድንግል ማርያም ስትሆን መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
፵፱. የአብ ቃል እርሱ መለኮታዊ አካሉ ፍጹም እሳት የሆነ የአምላክነት ባሕርይ ያለው በሐር ግምጃ ላይ ተዋሕዶ የሚያበራ ንጹሕና ጽሩይ ብርሃን ነው።
፶. ወልድ ልጅ በመባል ከባሕርይ አባቱ እግዚአብሔር አብና ከባሕርይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አያንስም።
፶፩. እርሱ አብ በፍጹም አካሉ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል አባት ነውና መለኮታዊ አካሉ እሳተ ነበልባል ነው።
፶፪. አብ አባት በመሆኑ ከባሕርይ ልጁ ከእግዚአብሔር ወልድና ከባሕርይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አይበልጥም።
፶፫. እርሱ መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ነው፤ መለኮታዊ አካሉ ፍጹም እሳት ነው ከአብ ከወልድ ጋር በአገዛዝ አንድ በሥልጣን ትክክል ነው።
፶፬. እሊህ ገዥዎች በገጽ ሦስት በፈቃድ አንድ ናቸው በመለኮትና በማንኛውም ሥነ ባሕርይ ሁሉ ፍጹም ልዩነት የለባቸውም።
፶፭. አንደኛው ከሁለተኛው ሁለተኛው ከሦስተኛው ሳይለይ በመለኮት አንድ ናቸው እንጂ እነሱ አንድ አምላክ ናቸውና።
፶፮. የአብ ህልውና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፶፯. የወልድም ህልውና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፶፰. የመንፈስ ቅዱስም ህልውና ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
፶፱. የአብ መንግሥት ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፷. የወልድ መንግሥት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፷፩. የመንፈስ ቅዱስም መንግሥት ከአብና ከወልድ ጋር ትክክል ነው።
፷፪. የአብ መለኮት ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፷፫. የወልድ መለኮት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፷፬. የመንፈስ ቅዱስም መለኮት ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
፷፭. የአብ ሥልጣን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ጋር አይለይም።
፷፮. የወልድ ሥልጣን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ልዩነት የለበትም።
፷፯. የመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ከአብ ከወልድ ሥልጣን ፈጽሞ አይለይም።
፷፰. የአብ ባሕርይ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፷፱. የወልድ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፸. የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
፸፩. በዚህ በሥላሴ አንድነት ሥሉስ ቅዱስ ስለ ሦስትነታቸው ብለው በየጊዜውና በየሰዓቱ ለዘወትር ፈጽመው ይቅር ይሉኝ ዘንድ እማፀናለሁ ነፍሴንና ሥጋዬንም አደራ አስጠብቃለሁ።
፸፪. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው . . . ላይ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

ተአምር፦

፩. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው . . . ላይ ለዘላለሙ ይደርና ሥሉስ ቅዱስ ያደረጉት ተአምራት ይህ ነው።
፪. እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ጸድቅ ሰው በፍልስጤም አገር ነበረ።
፫. እሱም ቅዱሳት መጻሕፍትን የመጻፍ ችሎታ ነበረው በጽሕፈት ዐዋቂነቱም ከሌሎች ጸሐፊዎች ሁሉ በጣም ብልጫ ያለው ነበረ።
፬. ከዕለታት ባንደኛው ቀን በበጐ ሥራው የተደነቀ አንድ አገረ ገዥ መጥቶ አንተ ደገኛ የሆንክ ወንድሜ ሆይ ክቡር የሚሆን ሰይፈ ሥላሴ የሚባል መጽሐፍ ትጽፍልኝ ዘንድ ወዳንተ መጥቻለሁ በማለት ጸሐፊውን ጠየቀውና እሺ በጐ አሰኘው።
፭. መጽሐፉንም በሚጽፍለት ጊዜ በአፃፃፉ ሥላሴን ደስ ለማሰኘት የሥሉስ ቅዱስን ስም እጅግ በሚያበራ የወርቅ ቀለም ይጽፍለት ነበር።
፮. ሥራውንም በዚህ ዓይነት ቀጥሎ ሳለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
፯. እነሆ መላእክት ክንፋቸውን በመዘርጋት የዚህን የጸሐፊ ነፍስ ለመቀበል ወደሱ መጡ።
፰. መላእክትም ከሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ባቀረቡት ጊዜ የሰማይና የምድር ገዥዎች ሥላሴ እንዲህ አሉት።
፱. አንተ ጸሐፊ በሕይወትህ ሳለህ ስማችንን አስጊጠህ እንደ ጻፍክ ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት ና ግባ አሉት።
፲. ሥላሴም ይህን ካሉት በኋላ መላእክት ተሸክመው ወስደው ከእግረ መንበር አደረሱትና ረቂቅና ለመስማት እጅግ አስደናቂ የሆነ የሥላሴን ምስጢር አስተማሩት።
፲፩. ዳግመኛም እኒሁ መላእክት አንተ ጸሐፊ ሆይ በወርቅ ዓምድ ላይ የተጻፈውን ስምህን ታይ ዘንድ ና እንውሰድህ አሉት።
፲፪. ጸሐፊውም ስሙን በተመለከተ ጊዜ ፈጽሞ ተደሰተ ቀጥሎም ገዥዎቼ ሥላሴ ሆይ ምን ሥራ ሠራሁላችሁና ነው የማይመጣጠነኝና ተገቢዬም ያይደለ ዋጋ የሰጣችሁኝ በማለት ተናገረ።
፲፫. ዳግመኛም ሥሉስ ቅዱስ አንተ መልካም ጸሐፊ አንተስ መልካሙን ሁሉ አደረግህልን ካንተ በኩል የቀረ ነገር የለም በሕይወትህ ሳለህ ቅዱስ መጽሐፍን በምትጽፍበት ጊዜ ለስማችን ታላቅ ክብር ሰጥተኸዋልና አሉት።
፲፬. ይህንም ካሉት በኋላ የብርሃን መጐናጸፊያ አጐናጽፈው የወርቅ ዘውድ አቀዳጁትና ዕዝራና ሄኖክ ኤልያስም በሕይወታቸው ካሉበት በተድላ ገነት አስቀመጡት።
፲፭. የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ እንግዲህ ሥላሴ በሰማይ በሕይወት አዳራሽ ያስገቡን ዘንድ ስማቸውን እናክብር ከፍ ከፍም እናድርግ።
፲፮. ዳግመኛም አሸናፊ ለሚሆን ስማቸው እንገዛ የእሳት ሰይፋቸውን መዘው ባሉ መላእክት እጅ ይጠብቁንና ከድንገተኛ ሞት ይሠውሩን ዘንድ።
፲፯. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው ከ . . . ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

***************

የሰይፈ ሥላሴ መቅድም

፩. ስቡሕ ወውዱስ እኩት ወቅዱስ እየተባለ በፍጹም ምስጋና የሚመሰገን፤ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን የሥላሴን ጥንተ ህልውና የሚናገር መጽሐፍ ለመጻፍ (ለመጸለይ) እንጀምራለን ።
፪. ነገር ግን እግዚአብሔር በሰጠን የችሎታ መጠን ለመናገር እንሞክራለን እንጂ ጽፈንስ ለመጨረስ፤ ችሎታ አይኖረንም።
፫. የምስጋናቸውንስ ነገር ሰማይና ምድር ወረቀት ወይም ብራና ቢሆኑ ከፍጥረተ ዓለም እስከ ኅልቀተ ዓለም ያለው ርደተ ዝናም ቀለም ቢሆን ይልቁንም ዓለም በጠቅላላው ለዚህ ተግባር ቢውል ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም ለዘለዓለሙ በእውነት።
፬. ሰማይና ምድር ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ሥላሴ በብቸኝነት ክብራቸው በአካል ሦስት በመለኮትና በፈቃድ በባሕርይ በትእዛዝ ግን አንዳችም ልዩነት ሣይኖርባቸው የነበሩ ናቸው ።
፭. አብ ያለወልድና ያለመንፈስ ቅዱስ ለአንዲት ሰዓት ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፮. ወልድም ያለ አብና ያለ መንፈስ ቅዱስ ለአንዲት ደቂቃ ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፯. መንፈስ ቅዱስም ያለ አብና ያለ ወልድ ለአንዲት ሰኮንድ ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፰. ለአብ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ልዩ ፈቃድና እዘዝ የለውም።
፱. ለወልድም ከአብና ከመንፈሰ ቅዱስ የተለየ ልዩ ሥልጣንና ክሂል የለውም።
፲. ለመንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ የተለየ ምንም ዓይነት ሥልጣን የለውም።
፲፩. በማደህየትና በማበልፀግ በማዋረድና በማክበር ፍጹም ልዩነት የለባቸውም።
፲፪. በአንድነት በሦስትነት ይሰገዳሉ ይመለካሉ፤ ሁሉንም በየነገዱ በመፍጠር ትክክል ናቸው እንጂ ጉድለት ወይም ሕፀፅ ያሣዩበት ጊዜ የለም።
፲፫. እንደዚሁም ለአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ቃል ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር አሉ።
፲፬. እነሆ በመጀመሪያዪቱ ቀን በዕለተ እሑድ ስምንት ፍጥረታትን ማለት ሰማይንና ምድርን ጨለማንና ብርሃንን ነፋስንና እሳትን ውሀን መላእክትን ፈጥረው መላእክትን ግን በመቶ ነገድ ከፈሏቸው የመላእክትም ሁሉ አለቃቸው ሳጥናኤል (ዲያብሎስ) ነበረ።
፲፭. ከዚህ በኋላ መላእክትን በሙሉ ጨለማ ጋረዳቸው ሸፈናቸው።
፲፮. በዚህን ጊዜ መላእክት እርስ በራሳቸው ማን ፈጠረን ጌታችን ማነው በማንስ እናመልካለን ተባባሉ።
፲፯. ትምክህተኛው ወይም ሰይጣኑ መልአክም ይህን ቃል ሰምቶ ግራ ቀኝ ቢመለከት ከሌሎቹ የእርሱ ማዕርግ በልጦ ስለአገኘው እነሆ አምላካችሁና ፈጣሪያችሁ ገዥአችሁም እኔ ነኝ ሲል በድፍረት ተናገረ።
፲፰. ከዚህ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከመከካላቸው ተነሥቶ ቆመና እናንት ማኅበረ መላእክት ሆይ፥ አምላካችንን እስክናውቅ ወይም እስክናገኘው ድረስ በእምነታችን ጸንተን መቆየት አለብን እንጂ በዚህ በሐሰተኛና በተንኮለኛ መልአክ አነጋገር ተወናብዳችሁ እንዳታምኑ ሲል በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ።
፲፱. በዚህም ጊዜ ኪሩቤልና ሱራፌል ዙፋኑን እንደ ተሸከሙ የሥላሴ ብርሃነ መለኮት ተገለጠ አንፀባረቀ በዓለሙ ሁሉ ላይም ብርሃን ይሁን አለ።
፳. ከዚህም በኋላ የዲያብሎስ የገዥነት ሥልጣኑ ተሽሮ እጅ እግሩን በእሳት ሠንሠለት ታሠረ።
፳፩. የተጐናጸፈውን ብርሃን ገፈው የጨለማ ጨርቅ አለበሱት የእሳት ነጐድጓድ አወረዱበት በልቡናው ፍርሃትን አሳደሩበት በዚህም ዘለዓለማዊው የሥላሴ መንግሥት በመላእክት ሁሉ ዘንድ ታወቀ ተረዳ።
፳፪. መላእክትንም ከነሱ ይለዩት ዘንድ አዘዝዋቸውና እነሱም ከመካከላቸው አውግዘው ለዩት።
፳፫. ሥሉስ ቅዱስም አንተ ርጉም ከኛ ራቅ መኖሪያህም በመንጸፈ ደይን ይሁን በማለት አስወገዱት።
፳፬. ይህ ርጉም መልአክም ጌቶቼ ከቶ ምሕረት የላችሁምን አላቸው።
፳፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በእርግጥ አንተን ለመሰለ ሁሉ ምሕረት የለንም አሉት።
፳፮. በዚህ ጊዜ ይህ ርጉም መልአክ ጌቶቼ ሆይ፥ ከነዚህ ሁሉ የተፈጥሮ ጓደኞቼ ነገደ መላእክት ተለይቼ ስሄድ አላሳዝናችሁምን ሲል በማሳዘን ጮኾ ተናገረ።
፳፯. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በማይቻልህ የአምላክነትን ባሕርይ ለመፈታተንና የማታልፈውን መንግሥታችንን ለመገልበጥ ያደረግኸው ሙከራና ድፍረት አያሳፍርህምን ይልቁንም በቃልህ አምነውበት አንተን የተከተሉ ሁሉ አብረውህ ከአንተ ጋር ይሂዱ አሉት።
፳፰. ቀጥሎም በልዩ አስተሳሰብህ አምላካዊ መንግሥትን ስትሻ ተገኝተሃልና መኖሪያህ ዕመቀ ዕመቃት ይሁን ቅዱስ ስማችን በተጠራበት ቦታ ሁሉ አትድረስ አሉት።
፳፱. ወገኖችህ መላእክት በጠላትነት ይነሱብህ በአለት ድንጋይ (ዕብነ ሩካም) በእሳት መንዶ እራስ እራስክን ይቀጥቅጡህ አሉት።
፴. ዳግመኛም ምግብህ የእሳት አሎሎ (ኮረት) መጠጥህ የእሳት ፍላት ይሁን መዘዋወሪያህ (መመላለሻህ) መንጸፈ ደይን ይሁን መቀመጫህ የእሳት መንኰራኵር ይሁን መኖሪያህም በጨለማ ውስጥ ይሁን ሲሉ ረገሙት።
፴፩. ይህንንም ካሉት በኋላ የቤቱ ዙሪያ በእሳት የታጠረ በውስጡም እሳት የሚነድበት ሆኖ ወደ ተዘጋጀለት ቤት በዚያ ይኖር ዘንድ ገባ ዕመቀ ዕመቃት መንጸፈ ደይን ወረደ።
፴፪. እሱ ግን በልቡ እግዚአብሔር እንደኔ ያለ ፍጡር አያገኝም ስለሆነም መልሶ እንደ ቀድሞው አገልጋዩ ያደርገኛል። ከቀድሞ የተፈጥሮ ጓደኞቼ ከሆኑ መላእክትም ሁሉ ጋራ ሥራዬን እቀጥላለሁ። ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እተካከላለሁ። ለአብ ምስጋና አቀርባለሁ ከእሱም ጋር ነግሼ እኖራለሁ። ስለዚህም እርሱ አብ ያከብረኛል ወልድም ከአእላፍ መላእክቶቹ ጋር መጥቶ ይቀበለኛል። ከእሱም ጋር እኖራለሁ። የአብን የዙፋን መጋረጃ ገልጬ እገባና በቀኙ ያስቀምጠኛል። ከዚያም በሱ ላይ እሠለጥናለሁ። ከወልድ ራስ ላይ ዘውድን እነጥቃለሁ። ከመንፈስ ቅዱስም ላይ የብርሃን አክሊል ወስጄ እቀዳጅና ለዚያች ከማዕርጌ ላይ ያዋረደችኝና እጅግ አስፈሪ ለሆነችው ዙፋን ባለቤት እሆናለሁ።
፴፫. ከዚያም የቀድሞ ሥልጣኔን በእጄ ከአደረግሁ በኋላ ከኔ አፈንግጠው መመሪያየን ሳይቀበሉ የቀሩትንና በእኔ ሥልጣን ላይ የተቀመጡትን ጠላቶቼን ሁሉ በቁጥጥሬ ሥር አውላቸዋለሁ በማለት ታበየ።
፴፬. ይህንንም በልቡ ሐሳብ በሚልበት ጊዜ ይህ ዲያብሎስ ትሉ ወደ ማያንቀላፋበት ጢሱ እሳቱ ወደ ማይጠፋበት በሲኦል የረግረግ ጨለማ በድንገት ተወርውሮ ሰጠመ (ሠረገ)።
፴፭. እንደዚሁም ሁሉ ጠላቶቼ በሲኦል መካከል ባለ ጨለማ ውስጥ ይጣሉ እኔ አገልጋያችሁ . . . በእናንተ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ተማፅኛለሁና እስከ ዘላለሙ አሜን።

ሰይፈ ሥላሴ ዘዘወትር

፩. አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምናለሁ እማጸናለሁ።
፪. የዓለም ገዥ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፥ በወዳጃችሁ በአብርሃም ቤት እንደገባችሁ ከናንተ ዘንድ የሚሰጠውን የሰማዕትነት አክሊል እቀዳጅ ዘንድ ተድላ ደስታ ካለበት ገነት አግቡኝ።
፫. ኃጢአቴን በይቅርታ ቃል ደምስሳችሁ ነፍሴን ከሚቃወሟት አጋንንት አድኗት።
፬. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በእውነት ስማችሁን እጠራ ዘንድ ከወደቅሁበት አንሡኝ በቸርነታችሁም ከሩቅ ጥቀሱኝ ከቀትር ጋኔን ከድንገተኛ መጋኛ ትጠብቁኝ ዘንድ እማፀናለሁ።
፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የምስጋና ፍሬ እንዳፈራና ከአንደበቴም የጸሎት እሸት አበረክትላችሁ ዘንድ በልቡናዬ እርሻ ላይ መልካሙን ፍሬ ትዘሩ ዘንድ እማፀናለሁ።
፮. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ኃያሉ ስማችሁ የሚጋፉኝን ይጋፋቸው ዘንድ የሚቃወሙኝንም እንዲቃወማቸውና ፈርኦንን በነቢዩ በሙሴ ምክንያት እንዳሰጠመው ያሰጥማቸው ዘንድ በእናንተ እማፀናለሁ።
፯. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በአርያም ባለው ጽርሐ መንግሥታችሁ እማፀናለሁ ስለ ዕዝራና ሄኖክም ሲባል ገነትን ስለጐበኛችሁ እኔን ባሪያችሁን በቸርነታችሁ ጐብኙኝ።
፰. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ኮከበ ክብር የተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፸ (ሰብዓ) ነገሥታትን ደምስሳችሁ እንዳጠፋችኋቸው የኔንም ጠላቶች ትደመስሱልኝ ዘንድ እማፀናለሁ።
፱. ጠላቶቾ የሆኑ ሁሉ በመለኮታዊ ሰይፍ ይ*ጨ*ፍ*ጨ*ፉ ነበልባላዊ በሚሆን ቃላችሁና ሥልጣናችሁ ይንደዱ ይቃጠሉ በሲኦል የጨለማ አዘቅት ውስጥ ይዝቀጡ ወይም ይስጠሙ ሐዘን ከላያቸው አይራቅ ትካዜም ከልባቸው አይጥፋ።
፲. ጠላቶቼ እኔ ከምድረ ገጽ ላይ እንድጠፋ በፈለጉ ጊዜ እነሱን ራሳቸውን እንደ ቃየልና ይሁዳ በዱርና በበረሃ በታትኗቸውና ሲቅበዘበዙ ይኑሩ።
፲፩. አዳምና ሔዋን ከገነት በመውጣታቸው እንዳለቀሱ ጠላቶቼንም የጨርቅ መቀነቻ አስታጥቋቸውና ሲያለቅሱ ይኑሩ።
፲፪. በኔም ላይ ጥፋትን እንዳያመጡብኝ ጥልቅ በሆነ በእሳት ባሕር አስጥሟቸው።
፲፫. አሁንም እነሆ ጠላቶቼ በእሾህና አሜካላ በተታታ ወጥመድ ውስጥ ይግቡ።
፲፬. ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ለእኔ ለባሪያችሁ ፍጹም ይቅርታን ታደርጉልኝ ዘንድ እማልዳለሁ።
፲፭. ጠላቶቼ ግን በፊታቸው ከፍርሃት በስተቀር በፍጹም ደስታን አያግኙ።
፲፮. ወንጀለኞች እንደሚታሠሩ እጅ እግራቸውን በእሳት ሠንሠለት እሠሯቸው እንጂ።
፲፯. ዳግመኛም ቀድሞ አዳም ከነ ልጆቹ በሲኦል ጨለማ እንደተከበበ እነሱንም የመከራ ጨለማ ይክበባቸው።
፲፰. ጠላቶቼን በውሾች ማደሪያ አሳድሯቸው የምታስፈራዋን ያችን የእሳት ባሕር አታሻግሯቸው።
፲፱. በእሳት ቀስት (ፍላፃ) ንደፏቸው ልዩ ልዩ ደዌና መቅሠፍት ይታዘዝባቸው የምሕረት ዝናም (ጠል) አይውረድላቸው የሕይወት ቃል አትመልሱላቸው።
፳. ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ጽንዕት በሆነች መለኮታዊት እጃችሁ ትባርኩኝና መላእክትም ሁሉ በክንፋቸው በእኔ ላይ ይረቡ ዘንድ እማፀናለሁ።
፳፩. ነፍሴ ወይም ሰውነቴ በእናንተ ዘንድ የተጠማች እንዳትሆን ከዐራቱ አፍላጋት በሚፈስ ውሀ አርኳት (አጠጧት)።
፳፪. ነፍሴ ወይም ሰውነቴ በፊታችሁ የተራበች ሆና እንዳትገኝ የሕይወት ኅብስት መግቧት።
፳፫. የነፍስና የሥጋ ገዥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የምስጋና ፍሬ አቀርብላችሁ ዘንድ ጾምና ጸሎት ወዳድ እንድታደርጉኝ እማጸናለሁ።
፳፬. ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር መኖሪያዬን በገነት አድርጉልኝ ከዕለት እኪት ከዘመን መንሱት ሠውሩኝ።
፳፭. እኔ በደለኛ የምሆን አገልጋያችሁ . . . ከድንገተኛ ሞት እድን ዘንድ ልዩ ሦስት በሚሆን ስማችሁ እማፀናለሁ ነፍሴንና ሥጋዬንም አደራ አስጠብቃለሁ። በዚያም ጊዜ ምሕረት ይደረግልኝ አሜን።
፳፮. ዳግመኛም በሁሉ ላይ ሥልጣን ባለው በእግዚአብሔር አብ ስም ዕውቀትን በሚገልጽ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እና ያዘኑትን በሚያረጋጋ እውነተኛ አዳኝ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ስም እማፀናለሁ።
፳፯. በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮት ግን አንድ አምላክ በሚሆን እማፀናለሁ።
፳፰. በየጊዜውና በየሰዓቱ እንግዳ ለሚሆንና ለማይጠገበው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ፍቅር እማፀናለሁ።
፳፱. በማይጠፋ በማያረጅና በማያልፍ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አነዋወር እማፀናለሁ።
፴. ተነግሮ በማያልቅ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የጌትነት ምስጋና እማፀናለሁ።
፴፩. ዓለሙን ሁሉ ለይኩን ብሎ በአንዲት ቃል በፈጠረ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ጥበብ እማፀናለሁ።
፴፪. በግልጽና በሥውር ያለውን ዓለም በሙሉ በአጸና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ኃይል እማፀናለሁ።
፴፫. ለመግደልና ለማዳን በሚችል በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ፍርድ እማፀናለሁ።
፴፬. ከምድረ ገጽ ጸብን ክርክርን በሚሽር በሚያጠፋና በሚደመስስ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ቃል እማፀናለሁ።
፴፭. በሚያደኸይና በሚያበለጽግ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ መንግሥት ወይም ሥልጣን እማፀናለሁ።
፴፮. እጅግ በሚያስፈራና ነፍስና ሥጋን በሚያስደነግጥ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ግርማ እማፀናለሁ።
፴፯. ከአፉ በሚወጣ የእሳት ሰይፍ የጠላትን ወጥመድ (አሽክላ) የሚቆራርጥ በመለኮት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እማፀናለሁ።
፴፰. አሌፍ፣ ቤት፣ ጋሜል፣ ዳሌጥ፣ ሄ፣ ዋው፣ ዛይ፣ ሔት፣ ጤት፣ ዮድ፣ ካፍ፣ ላሜድ፣ ሜም፣ ኖን፣ ሳምኬት፣ ዔ፣ ፌ፣ ጻዴ፣ ቆፍ፣ ሬስ፣ ሳን፣ ታው በሚባል (ሉ) በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያመንኩ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬ ወዳንተ ትቀርብ ዘንድ እማፀናለሁ።
፴፱. የመምጣቱ ዜና በነቢያት አንደበት በተነገረና ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም በተወለደ ጌታ እማፀናለሁ።
፵. ዳግመኛም በማየ ዮርዳኖስ በተጠመቀውና የጌትነቱ ክብር በደብረ ታቦር በተገለጸው አምላክ እማፀናለሁ።
፵፩. ሀገሩ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተብላ በምትጠራውና ማደሪያውን በአርያም መሠወሪያውንም የእሳት መጋረጃ ባደረገ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እማፀናለሁ።
፵፪. በለበሰው ሥጋ በተሰቀለበት በመካነ ስቅለቱ በቀራንዮ በመካነ መቃብሩ በጎልጎታ ከሙታን ተለይቶ በሦስተኛው ቀን በመነሣቱ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ በማረጉና ይህን ዓለም ለማሳለፍ ዳግመኛ በመምጣቱ እማፀናለሁ።
፵፫. ለአዳምና ለልጆቹ ለዘሩም ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ ከሰማይ በወረደ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ እማፀናለሁ።
፵፬. በዚህ ሁሉ በተጠሩትና ባልተጠሩት አምላካዊና የመማፀኛ ስሞች እናንት ርኵሳን አጋንንት እኵያንና መሠርያን ሰብዓዊ ፍጥረቶች ሁሉ በየጊዜውና በየሰዓቱ የእግዚአብሔር አገልጋዩ ከምሆን ከኔ ዘንድ እንዳትቀርቡ የተወገዛችሁ ሁኑ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን።
፵፭. የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር አብ ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፮. ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ አንድ ልጁ የሚሆን እግዚአብሔር ወልድም ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፯. የአብና የወልድ የባሕርይ ሕይወታቸው የሚሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፰. አብ የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱም ዙፋን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፵፱. ወልድ የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱም ዙፋን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፶. መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱ ዙፋንም ከአብ ከወልድ ጋር ትክክል ነው።
፶፩. እንግዲህ በአንድ የጌትነት ዙፋን ላይ የአካል ሦስትነትና የመለኮት አንድነት እንዳለ እናምናለን።
፶፪. ለማይጠቀለል ለሥላሴ አንድነት ምስጋና ይገባል።
፶፫. ለማይከፋፈል ለሥላሴ ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፶፬. የዝርውነት ባሕርይ ለሌለው ለሥላሴ ሐሳብ ምስጋና ይገባል።
፶፭. ለማይመረመር ለሥላሴ አነዋወር ምስጋና ይገባል።
፶፮. ሰማይና ምድር ለማይወስኑት ለአካለ ሥላሴ ምስጋና ይገባል።
፶፯. ተመራምሮ ለማይደረስበት ለሥላሴ ቅድምና ምስጋና ይገባል።
፶፰. ኅልፈት ውላጤ ለሌለበት ለሥላሴ መንግሥት ምስጋና ይገባል።
፶፱. ልዩ ተጨማሪ ስም ለማያስፈልገው (ለማይስማማው) ለሥላሴ ምስጋና ይገባል።
፷. ከፍጹም ሦስትነት ወደ ዐራተኛነት ከፍ ለማይል ፍጹም የስም ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፷፩. ከፍጹም የገጽ ሦስትነት ወደ ሁለተኝነት ገጽ ዝቅ ለማይል የገጽ ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፷፪. ለማይወሰን ለሥላሴ ቸርነት ምስጋና ይገባል።
፷፫. ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል።
፷፬. በልዩ የነደ እሳት ነፀብራቅ ለተከበበችና ሁሉ በሁሉ ሙሉ ለሆነች ሥላሴነት ምስጋና ይገባል። ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

09/08/2026
በጳጉሜን ንስሐን የሰበከ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ይታሰባል።👉"የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ ግን፥ ስለ ሄሮድያዳ ስለ ወንድሙ ስለ ፊልጶስ ሚስትና ሄሮድስ ስላደረገው ሌላ ክፋት ሁሉ ዮሐንስ ስለ...
09/08/2026

በጳጉሜን ንስሐን የሰበከ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ይታሰባል።

👉"የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ ግን፥ ስለ ሄሮድያዳ ስለ ወንድሙ ስለ ፊልጶስ ሚስትና ሄሮድስ ስላደረገው ሌላ ክፋት ሁሉ ዮሐንስ ስለ ገሠጸው፥ ይህን ደግሞ ከሁሉ በላይ ጨምሮ ዮሐንስን በወኅኒ አገባው።" ሉቃ. 3፥19-20

👉"ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም" ሉቃ. 7፥28

👉"But Herod the tetrarch, being reproved by him for Herodias his brother Philip's wife, and for all the evils which Herod had done, Added yet this above all, that he shut up John in prison." Luke 3:19-20

👉"Among those that are born of women there is not a greater prophet than John the Baptist" Luke 7:28

👉"ጌታ እግዚአብሔር አንተን አድንህ ዘንድ . . . ላከኝ" መጽሐፈ ጦቢት 12፥14👉"በበሽታ ሁሉ ላይና በሰው ልጆች ቍስል ላይ የተሾመ ቅዱስ ሩፋኤል ነው" መጽሐፈ ሄኖክ 10፥13👉"ሁሉ መዳ...
09/07/2026

👉"ጌታ እግዚአብሔር አንተን አድንህ ዘንድ . . . ላከኝ" መጽሐፈ ጦቢት 12፥14

👉"በበሽታ ሁሉ ላይና በሰው ልጆች ቍስል ላይ የተሾመ ቅዱስ ሩፋኤል ነው" መጽሐፈ ሄኖክ 10፥13

👉"ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?" ዕብ. 1፥14

👉"'የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ በገናናውና በቅዱሱ ጌትነት ፊት ከሚያቀርቡ ሰባቱ ቅዱሳን መላእክት አንዱ መልአክ እኔ ሩፋኤል ነኝ' አላቸው። ይህንም ሰምተው ሁለቱ ደነገጡ ፈርተዋልምና በግምባራቸው ወደቁ።" መጽሐፈ ጦቢት 12፥15-16

👉"ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ" ራእይ 22፥8/19፥10

👉"ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም፦ ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ። እነርሱም፦ በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም አሉት። እጅግም ዘበዘባቸው፤ ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ።" ዘፍ. 19፥1-3

👉"ለቅዱሳን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ሰላምታ አቅርቡ" ፊል. 4፥21

👉"ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ . . . መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ" ሮሜ. 13፥7

👉"And now God hath sent me to heal thee" Tobit 12:14

👉"It is the holy Raphael, who is appointed over all manner of sickness and over the afflictions of the children of men." Enoch 10:13

👉"Are they not all ministering spirits, sent forth to minister for them who shall be heirs of salvation?" Heb. 1:14

👉"I am Raphael, one of the seven holy angels, which present the prayers of the saints, and which go in and out before the glory of the Holy One. Then they were both troubled, and fell upon their faces: for they feared." Tobit 12:15-16

👉"I fell down to worship before the feet of the angel which shewed me these things" Rev. 22:8/19:10

👉"And there came two angels to S***m at even; and Lot sat in the gate of S***m: and Lot seeing them rose up to meet them; and he bowed himself with his face toward the ground; And he said, Behold now, my lords, turn in, I pray you, into your servant's house, and tarry all night, and wash your feet, and ye shall rise up early, and go on your ways. And they said, Nay; but we will abide in the street all night. And he pressed upon them greatly; and they turned in unto him, and entered into his house; and he made them a feast, and did bake unleavened bread, and they did eat." Gen. 19:1-3

👉"Salute every saint in Christ Jesus." Phil 4:21

👉"Render therefore to all their dues . . . fear to whom fear; honour to whom honour" Rom. 13:7

👉"ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ" ሉቃ. 1፥28👉"Hail, thou that art highly favoured, the Lord is with t...
09/07/2026

👉"ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ" ሉቃ. 1፥28

👉"Hail, thou that art highly favoured, the Lord is with thee: blessed art thou among women" Luke 1:28

👉"አንተ አምላኬ፥ ዝም አትበለኝ" መዝ. 27 (28)፥1 👉"be not silent to me" Ps. 28:1
09/07/2026

👉"አንተ አምላኬ፥ ዝም አትበለኝ" መዝ. 27 (28)፥1

👉"be not silent to me" Ps. 28:1

የማክሰኞ ሰይፈ ሥላሴ (መቅድሙና የዘወትሩ ከበታች ተካቷል)አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ። ፩. አቤቱ በረከትህን ስጠኝ በዚች በተባረከችው ዕለት ...
09/07/2026

የማክሰኞ ሰይፈ ሥላሴ (መቅድሙና የዘወትሩ ከበታች ተካቷል)

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ።

፩. አቤቱ በረከትህን ስጠኝ በዚች በተባረከችው ዕለት የማቀርብልህን ጸሎት ስማኝ ልመናዬን ተቀበል ኃጢአቴንም ይቅር በለኝ።
፪. አቤቱ ለሚበረታቱብኝ እጅ አሳልፈህ አትስጠኝ የሰይጣንን ተንኮል እና የባለሥልጣኖችን ቁጣ አታድርስብኝ የጐረቤትን ጥል ከኔ አርቅልኝ ሐዘንና ችግርንም ከላዬ ላይ አስወግድልኝ።
፫. አቤቱ ትእዛዝህን እፈጽም ዘንድ ዓይነ ልቡናዬን አብራልኝ መፈራትህንም በዚች በዛሬይቱ ዕለት ፈጥነህ ላክልኝ።
፬. ደጋጎች ወገኖችህን በቀንና በሌሊት እንደጠበቅሃቸው ሁሉ በደሌንና ኃጢአቴን ይቅር ትል ዘንድ በእውነተኞች ወዳጆችህ አማላጅነት (ስም) እለምንሃለሁ።
፭. አቤቱ በፊተኛውም ሆነ በኋለኛው ኃጢአቴ ማረኝ ይቅር በለኝ ከምቀኛና ከተንኮለኛ እንዲሁም በእኔ ላይ ክፉ ለማድረግ ከሚፈልጉ ሁሉ ፈጽመህ አድነኝ በአንተ እታመናለሁ አቤቱ ከአንተ ሌላ አምላክ የለምና ።
፮. አምላኬ ሆይ ስማኝ ፈቃዴንም ፈጽምልኝ ወገኖችህ የጥምቀት ልጆችንም ጠብቃቸው።
፯. ጥንት የሌለብህ ቀዳማዊ ፍጻሜ የሌለብህ ደኃራዊ ሆይ አቤቱ በደሌን ታጠፋልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ እማልድሃለሁ በአባቴና በእናቴም ላይ ፍጹም ርኅራሄ አድርገህ ከወገኖችህ ጋር በመንግሥተ ሰማያት አንድ ታደርጋቸው ዘንድ ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው።
፰. ኃይል ምስጋና ጌትነትና መንግሥት ያንተ ናትና።
፱. በእውነት የሚጠሩህን የምትሰማቸው ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ ቸርነትህንም ከኔ አታርቅ አቤቱ በቸርነትህና በይቅርታህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
፲. ክብር ጌትነትና ምስጋና ለአንተ ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን።
፲፩. በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ ገጽታዬን አማትባለሁ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ በፊቴ አንፃር አማትባለሁ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ በስተኋላዬ አማትባለሁ።
፲፪. በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ ወደ ቀኝ አማትባለሁ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ ወደግራ አማትባለሁ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ በመላ ሰውነቴ አማትባለሁ።
፲፫. ይልቁንም ኃጥእና በደለኛ የምሆን በዚህ ዓለም በሕይወት በምኖርበትና ከሞትኩም በኋላ በሚመጣው ዓለም ርኵሳን መናፍስት እንዳይቀርቡኝና እንዳይፈታተኑኝ እግሮቼንና እጆቼን መቀመጫና መቆሚያዬን መውጫና መግቢያዬን ሁሉ በመለኮተ ሥሉስ ቅዱስ አማትባለሁ።
፲፬. አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ለሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ፤ በዚህም ሥላሴ በገጽ ሦስት በመለኮት አንድ መሆናቸው ይታወቃል።
፲፭. በገጽ ሦስት ስለመሆናቸው ሦስት በመለኮት ትክክል ስለመሆናቸው አንድ ይባላል።
፲፮. ልዩ ሦስት የሚሆኑ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአነዋወር ትክክል በመሆናቸው አንድ እግዚአብሔር እንላለን።
፲፯. በስም በአካል ሦስት ቢሆን በአገዛዝ በፍርድ አንድ ነው ጥበቡ ምክሩ የማይከፋፈል የማይነጣጠል ፍጹም አንድ ነው።
፲፰. አብ ያለወልድና ያለመንፈስ ቅዱስ ለብቻው አያስብም።
፲፱. ወልድም ያለአብና ያለ መንፈስ ቅዱስ ብቻውን አያስብም።
፳. መንፈስ ቅዱስም ያለአብና ያለወልድ ብቻውን አያስብም።
፳፩. እነሱስ ያለመለየት በአንድ ሐሳብ ጸንተው ይኖራሉ።
፳፪. ሥላሴ በአካል ሦስት በሥልጣን አንድ ናቸው።
፳፫. አብ በተለየ አካሉ ፍጹም ገጽ አለው በባሕርይ ግን ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ ነው።
፳፬. ወልድም በተለየ አካሉ ፍጹም ገጽ አለው በባሕርይ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ ነው።
፳፭. መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ ፍጹም ገጽ አለው በባሕርይ ግን ከአብ ከወልድ ጋራ አንድ ነው።
፳፮. አብ በተለየ ስሙ አብ ሲሆን መለኮቱ ግን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ አይለይም።
፳፯. ወልድም በተለየ ስሙ ወልድ ሲሆን መለኮቱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አይለይም።
፳፰. መንፈስ ቅዱስም በተለየ ስሙ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን መለኮቱ ግን ከአብ ከወልድ አይለይም።
፳፱. የአብ ስም ተለውጦ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም በመለኮቱ ግን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፴. የወልድ ስሙ ተለውጦ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም በመንግሥቱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ ነው።
፴፩. የመንፈስ ቅዱስ ስም ተለውጦ አብ ወይም ወልድ አይባልም የመለኮቱ ፈቃድ ግን ከአብ ከወልድ ጋራ አንድ ነው።
፴፪. አብ አባት በመሆኑ ከባሕርይ ልጁ ከወልድ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስም አይበልጥም።
፴፫. ወልድም ከአባቱ አያንስም ከባሕርይ አባቱና ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ አነዋወር ነው እንጂ።
፴፬. መንፈስ ቅዱስም ያለመጉደልና ያለመበላለጥ ከአብና ከወልድ ጋር በምክርና በአነዋወርም ትክክል ያለመለየት በጥበብ አንድ ናቸው።
፴፭. በመንግሥት ትክክል በአካል ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው።
፴፮. የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ሦስትነታቸውና አንድነታቸው እንደዚህ ነው። ሦስትነታቸው በትጉሃን መላእክት ምስጋና ይታወቃል።
፴፰. ኪሩቤልና ሱራፌል ሊቃናትም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር የአማልክቶች አምላክ እርሱ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ መመስገን ይገባዋል እያሉ በአንድ ቃል ያመሰግኑታል።
፴፱. በዚህም ምስጋና አርባዕቱ እንስሳ ለአምላክነቱ በመገዛት በአንድነት ሥላሴን ያመሰግናሉ።
፵. መንፈሳውያን የሆኑ ሱራፌልም ሦስትነቱንና አንድነቱን ለማጠየቅ አሸናፊ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሰገናለህ የጌትነትህም ምስጋና በሰማይና በምድር የመላ ነው እያሉ ኃይል ገንዘቡ ለሚሆን አምላክ ምስጋና ያቀርባሉ።
፵፩. በዚህ የምስጋና ቃል የሥላሴ አነዋወር ይታወቃል እነሆ ለሦስትነቱ ምስጋና በሚያቀርቡበት ጊዜ ቅዱስ ብሎ ማመስገን ከሦስትነት አይወርድም አይወጣምና።
፵፪. አኛም እንደዚሁ መለኮተ ሥላሴን እናመሰግናለን የተመሰገነ አብ ልዑል ነው የተመሰገነ ወልድም ክቡር ነው የተመሰገነ መንፈስ ቅዱስም ታላቅ ነው እያልን ልዩ ሦስት ለሚሆን እንሰግዳለን።
፵፫. በሦስትነቱ ፈጽመን እናመልክበታለን እሱንም እናመሰግነዋለን ለዘለዓለሙ በእውነት።
፵፬. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በገጽ ሦስት በባሕርይ አንድ ናቸው በስም ሦስት በመንግሥት ትክክል በአካል ሦስት በመለኮት በችሎታ ሁሉ አንድ ናቸው።
፵፭. ሦስት ፀሐይ አንድ ብርሃን ሦስት ገጽ አንድ አምላክ ከፍጹም ሦስትነት ባለመለየት አንድ ቃል አንድ መለኮት ነው።
፵፮. አብ በሚናገርበት ገንዘብ እሱ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በአንድነት ይናገራሉ።
፵፯. አብ በባሕርይ ልጁ በወልድ በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ አንድነት ይናገራል።
፵፰. ወልድም በባሕርይ አባቱ በአብ በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ አንድነት ይናገራል።
፵፱. መንፈስ ቅዱስም በአብ በወልድ አንድነት ይናገራል።
፶. የአብ ቃል ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፶፩. የወልድም ነገር ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፶፪. የመንፈስ ቅዱስም ነገር ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
፶፫. አብ በሚናገርበት ገንዘብ እርሱ ወልድ በአብ ይናገራል።
፶፬. ወልድም በሚናገርበት ገንዘብ እርሱ አብ በወልድ ይናገራል።
፶፭. የመንፈስ ቅዱስም ነገር ከአብ ከወልድ ነገር ጋር አንድ ነው፤ እሱ በፍጹም አካሉ አምላክ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ የአብ የወልድ የባሕርይ ሕይወት ወይም እስትንፋስ ነው ተብሎ እንደተነገረ መንግሥቱ ከአብ ከወልድ አይለይምና።
፶፮. ወልድም እንደዚሁ እንደ አብና እንደ መንፈስ ቅዱስ ፍጹም ገጽ ሲኖረው በመለኮቱ ግን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነውና።
፶፯. እርሱ ቃል (ወልድ) እኔ በአብ አብም በእኔ ህልዋን ሆነን እንኖራለን ብሎ እንደተናገረ እርሱ የአብ ቃል ይባላል።
፶፰. እንደዚሁ በአንድ ቃል ሦስት ነገር (አካል) እንዳለ እናምናለን አስቀድሞ ወንጌላዊው ዮሐንስ እንደ መሰከረ እንዲህ ሲል።
፶፱· ቃል አስቀድም ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
፷· ይህም አስቀድሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
፷፩. ሁሉም በእርሱ ሆነ ከሆነውም ሁሉ ያለእርሱ ምንም ምን የሆነ የለም።
፷፪. ሕይወት በእርሱ ነበረች ያችም ሕይወት የሰው ልጅ ብርሃን ነበረች።
፷፫. ብርሃኑም በጨለማ ያበራል ጨለማም አላገኘውም አይቀርበውምም።
፷፬. ይህ ብሩክ ቃል ቡርክት ለሆነች ለማርያም በመልአኩ በገብርኤል አምሣል እንደተገለጸላት ለኔም እንዲሁ ተገልጻችሁልኝ የሕይወት ቃል አሰሙኝ።
፷፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው ከዚህ አይወጡም ወይም አይወርዱም።
፷፮. ከዚህ አይበልጡም ወይም አይጐድሉም ጉድለት ወይም ተጨማሪ አይስማማቸውምና።
፷፯. በአንድ ይሰገዳሉ በገጽ ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው ቅድመ ዓለም ያለመጉደል በአንድነታቸውና በሦስትነታቸው ጸንተው የነበሩ ናቸው።
፷፰. አብ አባት በመሆን ከወልድ አይቀድምም ወልድም ልጅ በመሆን ተድኅሮ የለበትም መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ቅድምና ወይም ተድኅሮ የለበትም።
፷፱. ከዓለሙ ሁሉ በፊት በአንድ አገዛዝ በአንድ ሥልጣን በሦስትነታቸው የነበሩ ናቸው።
፸. መለኮትነታቸውን አስቦ ለመናገር የህልውናቸውንም ጥልቀት ለመመርመር ፈጽሞ አይቻልም ጥንት የሌለበት የመኖር ቅድምና ባለቤት ናቸው እንጂ።
፸፩. ያለምንም መለየት ወይም ልዩነት በሦስትነታቸው ያሉ ናቸው። ያለምንም መጉደል በትክክል ለዘለዓለሙ የሚኖሩ ናቸው።
፸፪. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ዙፋን ይቀመጣሉ (ህልዋን ናቸው) የአብ ህልውና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ህልውና አይለይም የወልድም ህልውና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ህልውና አይለይም የመንፈስ ቅዱስም ህልውና ከአብ ከወልድ ህልውና አይለይም።
፸፫. አብ በፍጹም አካሉ ህልው ነው ነገር ግን አርአያ መለኮቱ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ አርአያ መለኮት የተለየ አይደለም።
፸፬. ወልድም በፍጹም አካሉ በአብ ቀኝ ህልው ነው ነገር ግን ሥነ መለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሥነ መለኮት አይለወጥም።
፸፭. መንፈስ ቅዱስም በፍጹም አካሉ በአብና በወልድ ቀኝ ህልው ነው ነገር ግን ሕብረ መለኮቱ ከአብና ከወልድ ሕብረ መለኮት አይለይም።
፸፮. እንግዲህ የሥላሴ በአንድ የጌትነት ዙፋን አነዋወራቸው ይህ ነው ነቢዩ እንደተናገረ እንዲህ ሲል።
፸፯. እንደመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ ጌታ ጌታዬን በቀኜ ተቀመጥ አለው።
፸፰. እነሆ ልዩ ሦስት የሚሆን የሥላሴን የአንድነት አነዋወር በየክፍሉ ተረዳን።
፸፱. በዚህ በቅድስት ሥላሴ አነዋወር እኔ አገልጋያችሁ . . . እማፀናለሁ ነፍሴና ሥጋዬንም አማፅናለሁ ልዩ ሦስት የሚሆን እሱ በማይደርቅ የቸርነቱ ባሕርይ በየጊዜውና በየሰዓቱ ያጠምቀኝ ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።

ተአምር፦

፩. ይቅርታቸው ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው በ . . . ላይ ይደርና የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተአምራቸው ይህ ነው።
፪. የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን መታሰቢያ የምታደርግ ልጅ የሆነ አንድ ሕፃን ነበር።
፫. ከዕለታት በአንደኛው ቀን ይህቺ ሴት ለሥላሴ መታሰቢያ እንጀራ የምትጋግርበት ደረቅ እንጨት ፈልጋ ባጣች ጊዜ ያን ሕፃን ልጅዋን ውድ ልጄ ሆይ ባደግህ ጊዜ የምትከፍለው ደረቅ እንጨት የሚሰጥህ ሰው ፈልግ እኔ እንጨት በመፈለግ ብዙ ደክሜ አጥቻለሁና አለችው።
፬. ሕፃኑም መልሶ መልካሟ እናቴ ሆይ ሁሉንም ነገር ተይው ይቅር ብዙውን አትድከሚ ነገር ግን ጌቶቻችን ሥላሴ ያውቁልናል አላት።
፭. ይህን ከተባባሉ በኋላ ዳግመኛ እናቱን ጠራትና አስኪ ተነሽና የመጣልሽን ደስታ ተመልከች አላት።
፮. ልቡሳነ መብረቅ በሆኑ መላእክት እጅ የተዘጋጀ እንጂ በሰው እጅ የተጋገረ ያይደለ የትኩስ እንጀራ መዓዛ ሽታ በዚህ አዳራሽ ውስጥ ይሸታልና አላት።
፯. ይህንንም በሰማች ጊዜ ፈጥና ወደ ቤት ገባችና መዓዛው ሽታው ወይም የሰውን ልብ እጅግ አድርጎ የሚመስጥና የሚያስደስት እንጀራ በመሶብና በገበታ ተሠርቶ አገኘች። ሰዎችም ከመዓዛው ጣፋጭነት የተነሣ በሽታው ብቻ እንደበሉ ሆነው ጠገቡ።
፰. በዚህም ጊዜ ዘመዶችዋንና ጐረቤቶችዋን ጠርታ ወዳጆቼ ሆይ በቤቴ ውስጥ የሆነውን ማለት ሥላሴ ያደረጉትን ድንቅ ድንቅ ሥራ ኑና ተመልከቱ አለቻቸው።
፱. የሀገሩም ሰዎች ለደጋጐች ወዳጆች የሆኑ እሊህ ሥሉስ ቅዱስ ያደረጉትን ድንቅ ሥራ ተመልክተው አደነቁ በታላቅ ደስታም እየተደሰቱ በአንድነት ወደ አዳራሹ ገቡ።
፲. ከዚህ በኋላ የሀገሩ ሰዎች ሁሉ ሥሉስ ቅዱስ ሰዶምና ገሞራን ያጠፉበትን ጥር ፯ (7) ቀን ምክንያት በማድረግ እንደዚች ሴት ሁሉም በየራሳቸው የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን መታሰቢያ ማድረግ ጀመሩ።
፲፩. እነሆ ነዳያንና ችግረኞችን እየጠሩ ከተዘጋጀው ምግብ አብልተው አጠገቧቸው ወይንና ብርዝም አጠጥተው አረኳቸው ወደ እነሱ የመጡትን ሁሉ በእርጋታ እየጋበዙ አስደሰቷቸው።
፲፪. በየወሩ ሁሉ በየራሳቸውና በየግል ቤታቸው የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን የበዓላቸውን መታሰቢያ የሚያደርጉ ሆኑ ይልቁንም በጥርና በሐምሌ ፯ ቀን ያለማጓደል በፍጹም ትጋት ይዘክሩ ጀመር።
፲፫. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው . . . ጋር ለዘላለም ይኑር አሜን።

***************

የሰይፈ ሥላሴ መቅድም

፩. ስቡሕ ወውዱስ እኩት ወቅዱስ እየተባለ በፍጹም ምስጋና የሚመሰገን፤ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን የሥላሴን ጥንተ ህልውና የሚናገር መጽሐፍ ለመጻፍ (ለመጸለይ) እንጀምራለን ።
፪. ነገር ግን እግዚአብሔር በሰጠን የችሎታ መጠን ለመናገር እንሞክራለን እንጂ ጽፈንስ ለመጨረስ፤ ችሎታ አይኖረንም።
፫. የምስጋናቸውንስ ነገር ሰማይና ምድር ወረቀት ወይም ብራና ቢሆኑ ከፍጥረተ ዓለም እስከ ኅልቀተ ዓለም ያለው ርደተ ዝናም ቀለም ቢሆን ይልቁንም ዓለም በጠቅላላው ለዚህ ተግባር ቢውል ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም ለዘለዓለሙ በእውነት።
፬. ሰማይና ምድር ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ሥላሴ በብቸኝነት ክብራቸው በአካል ሦስት በመለኮትና በፈቃድ በባሕርይ በትእዛዝ ግን አንዳችም ልዩነት ሣይኖርባቸው የነበሩ ናቸው ።
፭. አብ ያለወልድና ያለመንፈስ ቅዱስ ለአንዲት ሰዓት ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፮. ወልድም ያለ አብና ያለ መንፈስ ቅዱስ ለአንዲት ደቂቃ ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፯. መንፈስ ቅዱስም ያለ አብና ያለ ወልድ ለአንዲት ሰኮንድ ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፰. ለአብ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ልዩ ፈቃድና እዘዝ የለውም።
፱. ለወልድም ከአብና ከመንፈሰ ቅዱስ የተለየ ልዩ ሥልጣንና ክሂል የለውም።
፲. ለመንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ የተለየ ምንም ዓይነት ሥልጣን የለውም።
፲፩. በማደህየትና በማበልፀግ በማዋረድና በማክበር ፍጹም ልዩነት የለባቸውም።
፲፪. በአንድነት በሦስትነት ይሰገዳሉ ይመለካሉ፤ ሁሉንም በየነገዱ በመፍጠር ትክክል ናቸው እንጂ ጉድለት ወይም ሕፀፅ ያሣዩበት ጊዜ የለም።
፲፫. እንደዚሁም ለአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ቃል ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር አሉ።
፲፬. እነሆ በመጀመሪያዪቱ ቀን በዕለተ እሑድ ስምንት ፍጥረታትን ማለት ሰማይንና ምድርን ጨለማንና ብርሃንን ነፋስንና እሳትን ውሀን መላእክትን ፈጥረው መላእክትን ግን በመቶ ነገድ ከፈሏቸው የመላእክትም ሁሉ አለቃቸው ሳጥናኤል (ዲያብሎስ) ነበረ።
፲፭. ከዚህ በኋላ መላእክትን በሙሉ ጨለማ ጋረዳቸው ሸፈናቸው።
፲፮. በዚህን ጊዜ መላእክት እርስ በራሳቸው ማን ፈጠረን ጌታችን ማነው በማንስ እናመልካለን ተባባሉ።
፲፯. ትምክህተኛው ወይም ሰይጣኑ መልአክም ይህን ቃል ሰምቶ ግራ ቀኝ ቢመለከት ከሌሎቹ የእርሱ ማዕርግ በልጦ ስለአገኘው እነሆ አምላካችሁና ፈጣሪያችሁ ገዥአችሁም እኔ ነኝ ሲል በድፍረት ተናገረ።
፲፰. ከዚህ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከመከካላቸው ተነሥቶ ቆመና እናንት ማኅበረ መላእክት ሆይ፥ አምላካችንን እስክናውቅ ወይም እስክናገኘው ድረስ በእምነታችን ጸንተን መቆየት አለብን እንጂ በዚህ በሐሰተኛና በተንኮለኛ መልአክ አነጋገር ተወናብዳችሁ እንዳታምኑ ሲል በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ።
፲፱. በዚህም ጊዜ ኪሩቤልና ሱራፌል ዙፋኑን እንደ ተሸከሙ የሥላሴ ብርሃነ መለኮት ተገለጠ አንፀባረቀ በዓለሙ ሁሉ ላይም ብርሃን ይሁን አለ።
፳. ከዚህም በኋላ የዲያብሎስ የገዥነት ሥልጣኑ ተሽሮ እጅ እግሩን በእሳት ሠንሠለት ታሠረ።
፳፩. የተጐናጸፈውን ብርሃን ገፈው የጨለማ ጨርቅ አለበሱት የእሳት ነጐድጓድ አወረዱበት በልቡናው ፍርሃትን አሳደሩበት በዚህም ዘለዓለማዊው የሥላሴ መንግሥት በመላእክት ሁሉ ዘንድ ታወቀ ተረዳ።
፳፪. መላእክትንም ከነሱ ይለዩት ዘንድ አዘዝዋቸውና እነሱም ከመካከላቸው አውግዘው ለዩት።
፳፫. ሥሉስ ቅዱስም አንተ ርጉም ከኛ ራቅ መኖሪያህም በመንጸፈ ደይን ይሁን በማለት አስወገዱት።
፳፬. ይህ ርጉም መልአክም ጌቶቼ ከቶ ምሕረት የላችሁምን አላቸው።
፳፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በእርግጥ አንተን ለመሰለ ሁሉ ምሕረት የለንም አሉት።
፳፮. በዚህ ጊዜ ይህ ርጉም መልአክ ጌቶቼ ሆይ፥ ከነዚህ ሁሉ የተፈጥሮ ጓደኞቼ ነገደ መላእክት ተለይቼ ስሄድ አላሳዝናችሁምን ሲል በማሳዘን ጮኾ ተናገረ።
፳፯. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በማይቻልህ የአምላክነትን ባሕርይ ለመፈታተንና የማታልፈውን መንግሥታችንን ለመገልበጥ ያደረግኸው ሙከራና ድፍረት አያሳፍርህምን ይልቁንም በቃልህ አምነውበት አንተን የተከተሉ ሁሉ አብረውህ ከአንተ ጋር ይሂዱ አሉት።
፳፰. ቀጥሎም በልዩ አስተሳሰብህ አምላካዊ መንግሥትን ስትሻ ተገኝተሃልና መኖሪያህ ዕመቀ ዕመቃት ይሁን ቅዱስ ስማችን በተጠራበት ቦታ ሁሉ አትድረስ አሉት።
፳፱. ወገኖችህ መላእክት በጠላትነት ይነሱብህ በአለት ድንጋይ (ዕብነ ሩካም) በእሳት መንዶ እራስ እራስክን ይቀጥቅጡህ አሉት።
፴. ዳግመኛም ምግብህ የእሳት አሎሎ (ኮረት) መጠጥህ የእሳት ፍላት ይሁን መዘዋወሪያህ (መመላለሻህ) መንጸፈ ደይን ይሁን መቀመጫህ የእሳት መንኰራኵር ይሁን መኖሪያህም በጨለማ ውስጥ ይሁን ሲሉ ረገሙት።
፴፩. ይህንንም ካሉት በኋላ የቤቱ ዙሪያ በእሳት የታጠረ በውስጡም እሳት የሚነድበት ሆኖ ወደ ተዘጋጀለት ቤት በዚያ ይኖር ዘንድ ገባ ዕመቀ ዕመቃት መንጸፈ ደይን ወረደ።
፴፪. እሱ ግን በልቡ እግዚአብሔር እንደኔ ያለ ፍጡር አያገኝም ስለሆነም መልሶ እንደ ቀድሞው አገልጋዩ ያደርገኛል። ከቀድሞ የተፈጥሮ ጓደኞቼ ከሆኑ መላእክትም ሁሉ ጋራ ሥራዬን እቀጥላለሁ። ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እተካከላለሁ። ለአብ ምስጋና አቀርባለሁ ከእሱም ጋር ነግሼ እኖራለሁ። ስለዚህም እርሱ አብ ያከብረኛል ወልድም ከአእላፍ መላእክቶቹ ጋር መጥቶ ይቀበለኛል። ከእሱም ጋር እኖራለሁ። የአብን የዙፋን መጋረጃ ገልጬ እገባና በቀኙ ያስቀምጠኛል። ከዚያም በሱ ላይ እሠለጥናለሁ። ከወልድ ራስ ላይ ዘውድን እነጥቃለሁ። ከመንፈስ ቅዱስም ላይ የብርሃን አክሊል ወስጄ እቀዳጅና ለዚያች ከማዕርጌ ላይ ያዋረደችኝና እጅግ አስፈሪ ለሆነችው ዙፋን ባለቤት እሆናለሁ።
፴፫. ከዚያም የቀድሞ ሥልጣኔን በእጄ ከአደረግሁ በኋላ ከኔ አፈንግጠው መመሪያየን ሳይቀበሉ የቀሩትንና በእኔ ሥልጣን ላይ የተቀመጡትን ጠላቶቼን ሁሉ በቁጥጥሬ ሥር አውላቸዋለሁ በማለት ታበየ።
፴፬. ይህንንም በልቡ ሐሳብ በሚልበት ጊዜ ይህ ዲያብሎስ ትሉ ወደ ማያንቀላፋበት ጢሱ እሳቱ ወደ ማይጠፋበት በሲኦል የረግረግ ጨለማ በድንገት ተወርውሮ ሰጠመ (ሠረገ)።
፴፭. እንደዚሁም ሁሉ ጠላቶቼ በሲኦል መካከል ባለ ጨለማ ውስጥ ይጣሉ እኔ አገልጋያችሁ . . . በእናንተ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ተማፅኛለሁና እስከ ዘላለሙ አሜን።

ሰይፈ ሥላሴ ዘዘወትር

፩. አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምናለሁ እማጸናለሁ።
፪. የዓለም ገዥ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፥ በወዳጃችሁ በአብርሃም ቤት እንደገባችሁ ከናንተ ዘንድ የሚሰጠውን የሰማዕትነት አክሊል እቀዳጅ ዘንድ ተድላ ደስታ ካለበት ገነት አግቡኝ።
፫. ኃጢአቴን በይቅርታ ቃል ደምስሳችሁ ነፍሴን ከሚቃወሟት አጋንንት አድኗት።
፬. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በእውነት ስማችሁን እጠራ ዘንድ ከወደቅሁበት አንሡኝ በቸርነታችሁም ከሩቅ ጥቀሱኝ ከቀትር ጋኔን ከድንገተኛ መጋኛ ትጠብቁኝ ዘንድ እማፀናለሁ።
፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የምስጋና ፍሬ እንዳፈራና ከአንደበቴም የጸሎት እሸት አበረክትላችሁ ዘንድ በልቡናዬ እርሻ ላይ መልካሙን ፍሬ ትዘሩ ዘንድ እማፀናለሁ።
፮. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ኃያሉ ስማችሁ የሚጋፉኝን ይጋፋቸው ዘንድ የሚቃወሙኝንም እንዲቃወማቸውና ፈርኦንን በነቢዩ በሙሴ ምክንያት እንዳሰጠመው ያሰጥማቸው ዘንድ በእናንተ እማፀናለሁ።
፯. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በአርያም ባለው ጽርሐ መንግሥታችሁ እማፀናለሁ ስለ ዕዝራና ሄኖክም ሲባል ገነትን ስለጐበኛችሁ እኔን ባሪያችሁን በቸርነታችሁ ጐብኙኝ።
፰. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ኮከበ ክብር የተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፸ (ሰብዓ) ነገሥታትን ደምስሳችሁ እንዳጠፋችኋቸው የኔንም ጠላቶች ትደመስሱልኝ ዘንድ እማፀናለሁ።
፱. ጠላቶቾ የሆኑ ሁሉ በመለኮታዊ ሰይፍ ይ*ጨ*ፍ*ጨ*ፉ ነበልባላዊ በሚሆን ቃላችሁና ሥልጣናችሁ ይንደዱ ይቃጠሉ በሲኦል የጨለማ አዘቅት ውስጥ ይዝቀጡ ወይም ይስጠሙ ሐዘን ከላያቸው አይራቅ ትካዜም ከልባቸው አይጥፋ።
፲. ጠላቶቼ እኔ ከምድረ ገጽ ላይ እንድጠፋ በፈለጉ ጊዜ እነሱን ራሳቸውን እንደ ቃየልና ይሁዳ በዱርና በበረሃ በታትኗቸውና ሲቅበዘበዙ ይኑሩ።
፲፩. አዳምና ሔዋን ከገነት በመውጣታቸው እንዳለቀሱ ጠላቶቼንም የጨርቅ መቀነቻ አስታጥቋቸውና ሲያለቅሱ ይኑሩ።
፲፪. በኔም ላይ ጥፋትን እንዳያመጡብኝ ጥልቅ በሆነ በእሳት ባሕር አስጥሟቸው።
፲፫. አሁንም እነሆ ጠላቶቼ በእሾህና አሜካላ በተታታ ወጥመድ ውስጥ ይግቡ።
፲፬. ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ለእኔ ለባሪያችሁ ፍጹም ይቅርታን ታደርጉልኝ ዘንድ እማልዳለሁ።
፲፭. ጠላቶቼ ግን በፊታቸው ከፍርሃት በስተቀር በፍጹም ደስታን አያግኙ።
፲፮. ወንጀለኞች እንደሚታሠሩ እጅ እግራቸውን በእሳት ሠንሠለት እሠሯቸው እንጂ።
፲፯. ዳግመኛም ቀድሞ አዳም ከነ ልጆቹ በሲኦል ጨለማ እንደተከበበ እነሱንም የመከራ ጨለማ ይክበባቸው።
፲፰. ጠላቶቼን በውሾች ማደሪያ አሳድሯቸው የምታስፈራዋን ያችን የእሳት ባሕር አታሻግሯቸው።
፲፱. በእሳት ቀስት (ፍላፃ) ንደፏቸው ልዩ ልዩ ደዌና መቅሠፍት ይታዘዝባቸው የምሕረት ዝናም (ጠል) አይውረድላቸው የሕይወት ቃል አትመልሱላቸው።
፳. ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ጽንዕት በሆነች መለኮታዊት እጃችሁ ትባርኩኝና መላእክትም ሁሉ በክንፋቸው በእኔ ላይ ይረቡ ዘንድ እማፀናለሁ።
፳፩. ነፍሴ ወይም ሰውነቴ በእናንተ ዘንድ የተጠማች እንዳትሆን ከዐራቱ አፍላጋት በሚፈስ ውሀ አርኳት (አጠጧት)።
፳፪. ነፍሴ ወይም ሰውነቴ በፊታችሁ የተራበች ሆና እንዳትገኝ የሕይወት ኅብስት መግቧት።
፳፫. የነፍስና የሥጋ ገዥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የምስጋና ፍሬ አቀርብላችሁ ዘንድ ጾምና ጸሎት ወዳድ እንድታደርጉኝ እማጸናለሁ።
፳፬. ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር መኖሪያዬን በገነት አድርጉልኝ ከዕለት እኪት ከዘመን መንሱት ሠውሩኝ።
፳፭. እኔ በደለኛ የምሆን አገልጋያችሁ . . . ከድንገተኛ ሞት እድን ዘንድ ልዩ ሦስት በሚሆን ስማችሁ እማፀናለሁ ነፍሴንና ሥጋዬንም አደራ አስጠብቃለሁ። በዚያም ጊዜ ምሕረት ይደረግልኝ አሜን።
፳፮. ዳግመኛም በሁሉ ላይ ሥልጣን ባለው በእግዚአብሔር አብ ስም ዕውቀትን በሚገልጽ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እና ያዘኑትን በሚያረጋጋ እውነተኛ አዳኝ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ስም እማፀናለሁ።
፳፯. በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮት ግን አንድ አምላክ በሚሆን እማፀናለሁ።
፳፰. በየጊዜውና በየሰዓቱ እንግዳ ለሚሆንና ለማይጠገበው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ፍቅር እማፀናለሁ።
፳፱. በማይጠፋ በማያረጅና በማያልፍ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አነዋወር እማፀናለሁ።
፴. ተነግሮ በማያልቅ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የጌትነት ምስጋና እማፀናለሁ።
፴፩. ዓለሙን ሁሉ ለይኩን ብሎ በአንዲት ቃል በፈጠረ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ጥበብ እማፀናለሁ።
፴፪. በግልጽና በሥውር ያለውን ዓለም በሙሉ በአጸና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ኃይል እማፀናለሁ።
፴፫. ለመግደልና ለማዳን በሚችል በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ፍርድ እማፀናለሁ።
፴፬. ከምድረ ገጽ ጸብን ክርክርን በሚሽር በሚያጠፋና በሚደመስስ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ቃል እማፀናለሁ።
፴፭. በሚያደኸይና በሚያበለጽግ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ መንግሥት ወይም ሥልጣን እማፀናለሁ።
፴፮. እጅግ በሚያስፈራና ነፍስና ሥጋን በሚያስደነግጥ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ግርማ እማፀናለሁ።
፴፯. ከአፉ በሚወጣ የእሳት ሰይፍ የጠላትን ወጥመድ (አሽክላ) የሚቆራርጥ በመለኮት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እማፀናለሁ።
፴፰. አሌፍ፣ ቤት፣ ጋሜል፣ ዳሌጥ፣ ሄ፣ ዋው፣ ዛይ፣ ሔት፣ ጤት፣ ዮድ፣ ካፍ፣ ላሜድ፣ ሜም፣ ኖን፣ ሳምኬት፣ ዔ፣ ፌ፣ ጻዴ፣ ቆፍ፣ ሬስ፣ ሳን፣ ታው በሚባል (ሉ) በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያመንኩ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬ ወዳንተ ትቀርብ ዘንድ እማፀናለሁ።
፴፱. የመምጣቱ ዜና በነቢያት አንደበት በተነገረና ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም በተወለደ ጌታ እማፀናለሁ።
፵. ዳግመኛም በማየ ዮርዳኖስ በተጠመቀውና የጌትነቱ ክብር በደብረ ታቦር በተገለጸው አምላክ እማፀናለሁ።
፵፩. ሀገሩ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተብላ በምትጠራውና ማደሪያውን በአርያም መሠወሪያውንም የእሳት መጋረጃ ባደረገ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እማፀናለሁ።
፵፪. በለበሰው ሥጋ በተሰቀለበት በመካነ ስቅለቱ በቀራንዮ በመካነ መቃብሩ በጎልጎታ ከሙታን ተለይቶ በሦስተኛው ቀን በመነሣቱ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ በማረጉና ይህን ዓለም ለማሳለፍ ዳግመኛ በመምጣቱ እማፀናለሁ።
፵፫. ለአዳምና ለልጆቹ ለዘሩም ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ ከሰማይ በወረደ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ እማፀናለሁ።
፵፬. በዚህ ሁሉ በተጠሩትና ባልተጠሩት አምላካዊና የመማፀኛ ስሞች እናንት ርኵሳን አጋንንት እኵያንና መሠርያን ሰብዓዊ ፍጥረቶች ሁሉ በየጊዜውና በየሰዓቱ የእግዚአብሔር አገልጋዩ ከምሆን ከኔ ዘንድ እንዳትቀርቡ የተወገዛችሁ ሁኑ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን።
፵፭. የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር አብ ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፮. ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ አንድ ልጁ የሚሆን እግዚአብሔር ወልድም ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፯. የአብና የወልድ የባሕርይ ሕይወታቸው የሚሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፰. አብ የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱም ዙፋን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፵፱. ወልድ የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱም ዙፋን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፶. መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱ ዙፋንም ከአብ ከወልድ ጋር ትክክል ነው።
፶፩. እንግዲህ በአንድ የጌትነት ዙፋን ላይ የአካል ሦስትነትና የመለኮት አንድነት እንዳለ እናምናለን።
፶፪. ለማይጠቀለል ለሥላሴ አንድነት ምስጋና ይገባል።
፶፫. ለማይከፋፈል ለሥላሴ ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፶፬. የዝርውነት ባሕርይ ለሌለው ለሥላሴ ሐሳብ ምስጋና ይገባል።
፶፭. ለማይመረመር ለሥላሴ አነዋወር ምስጋና ይገባል።
፶፮. ሰማይና ምድር ለማይወስኑት ለአካለ ሥላሴ ምስጋና ይገባል።
፶፯. ተመራምሮ ለማይደረስበት ለሥላሴ ቅድምና ምስጋና ይገባል።
፶፰. ኅልፈት ውላጤ ለሌለበት ለሥላሴ መንግሥት ምስጋና ይገባል።
፶፱. ልዩ ተጨማሪ ስም ለማያስፈልገው (ለማይስማማው) ለሥላሴ ምስጋና ይገባል።
፷. ከፍጹም ሦስትነት ወደ ዐራተኛነት ከፍ ለማይል ፍጹም የስም ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፷፩. ከፍጹም የገጽ ሦስትነት ወደ ሁለተኝነት ገጽ ዝቅ ለማይል የገጽ ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፷፪. ለማይወሰን ለሥላሴ ቸርነት ምስጋና ይገባል።
፷፫. ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል።
፷፬. በልዩ የነደ እሳት ነፀብራቅ ለተከበበችና ሁሉ በሁሉ ሙሉ ለሆነች ሥላሴነት ምስጋና ይገባል። ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

Address

Lancaster, PA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ermiyas Girma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ermiyas Girma:

Shortcuts

Share