SARE WANA Promotion

SARE WANA Promotion አዝናኝ አስቂኝና አስተማሪ የሀዲይሳና የአማረኛ ቀልዶች ይለቀቃሉ በተጨማሪ
ፖለቲካዊ ፣ማህበራዊ፣ኤኮኖሚያዊ መረጃዎችን እናደርሳለን/Amharic Drama � Also Every day we release photos of Ethiopian artists
(2)

03/10/2025

😭😭የሟች አቦዬ አንሽሶ አጭር የህይወት ታሪክ ..ስርዓተ ቀብራቸው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ዌራ ቀበሌ ሁለተኛ ቦንዴ ተፈፅሟል Kabeera Tube ከቤራ ቲዩብ

ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሲካሄድ የቆየው መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ የጸሎትና የምስጋና መርሃ ግብር ተጠናቀቀ
03/09/2025

ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሲካሄድ የቆየው መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ የጸሎትና የምስጋና መርሃ ግብር ተጠናቀቀ

የወንጌል አማኞችንም እምነት አክብሩ !!ከጥላቻ የፀዳ ትችት በየትኛውም መገድ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ከቀረበ ለመነጋገር ይቻላል። አለበለዚያ ልብኸና አዕምሮኸ በጥላቻ ታውሮ እንዴት በነፃነት ሰ...
03/08/2025

የወንጌል አማኞችንም እምነት አክብሩ !!

ከጥላቻ የፀዳ ትችት በየትኛውም መገድ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ከቀረበ ለመነጋገር ይቻላል። አለበለዚያ ልብኸና አዕምሮኸ በጥላቻ ታውሮ እንዴት በነፃነት ሰለ አገርም ሆነ ሰለ ሰላም መነጋገር ይቻላል?

በኢትዮጵያ ምድር ላይ አንዱ የአገሪቷ ባለቤት ። ሌላይኛው ደግሞ ባለቤት አልቦ የሆነበት ዘመን ላይመለሰ ተቀብሯል። ከማንም አይበልጡም። ከማንም አያንሱም። በአገራችን ላይ እኩል ድርሻ አላቸው። ምንም እንኳ አገራችን በሰማይ ነው ብለው ቢያምኑም።

i. ሀሳብን በሀሳብ መቃወም ይቻላል !!
ii. ፖለቲካን በፖለቲካ መቃወም ይቻላል !!!
iii. የመሪን ሀሳብ መቃወምም ሆነ መደገፍ ይቻላል!!!
iv. ፓርቲን መደገፍም ሆነ ፓርቲን አለመደገፍ ይቻላል !!!

ግን በሆነውም ባልሆነውም ዝም ብሎ የወንጌል አማኙን እንቅስቃሴ ና እምነት መቃወም ና ማንቋሸሽ የጤና አይመስልም።

ካውንስሉም ሆነ ማህበረ ምዕመኑ የራሱ የሆነ የቤት ስራ አለበት ። መስራት ያለበትን ያልሰራበት። ማስቀደም ያለበትን ያላስቀደመበት ። ያልተቀደሰ ጋብቻ ፣ የቅይጥነት ጣጣ፣ የአስተምህሮ ዝንፈት፣ የሞራል ስብራት፣ዘርኝነት (ብሔርተኝነት )፣ ጎጠኝነት፣አውራጃነት ወዘተ።
Article 11.State and religion are separate. There shall be no state religion. The state shall not interfere in religious matters and religion shall not interfere in state affairs.

ህገመንግስቱ ሀይማኖት የሌለው ሰው ነው ባለስልጣን መሆን ያለበት አይልም። ስልጣን ያለው ሀይማኖተኛ አይሁን አይልም። የሚለው መንግስትና ሀይማኖት የተለያየ ነው። የመንግስት ሀይማኖት የሚባል አይኖርም። እንደሚታወቀው የመንግስት ሀይማኖት የሚባል የለም አሁን ኢትዮጵያ ውሰጥ። ሀይማኖት በመንግስት ውስጥ ፣መንግስት በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ አይገባም ይላል። ግን ምን ማለት ነው? የህገመንግስት ትርጓሜ የሚፈልግ አንቀፅ ነው።

ከፍተኛ ጴንጤ ጠልነት አለ !!!

እንደዚኸ አደባባዩን ሞልተን በማየቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። እግዚአብሔር ገና ከእዚህ በላይ ያበዛናል። ህዝብን አበዛ እየዘመርን ገና እንበዛለን ፡፡

ከጥላቻ የፀዳ ትችት በየትኛውም መገድ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ከቀረበ ለመነጋገር ይቻላል። አለበለዚያ ልብኸና አዕምሮኸ በጥላቻ ታውሮ እንዴት በነፃነት ሰለ አገርም ሆነ ሰለ ሰላም መነጋገር ይቻላል?

  በዚህ ሰዓት ያለው ስሜቱ ይህን ይመስለል😁
03/08/2025

በዚህ ሰዓት ያለው ስሜቱ ይህን ይመስለል😁

የጤና ሚኒስቴር ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት  ዘመናዊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር በሆኑት በዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ልዑካን ቡድን ባ...
03/06/2025

የጤና ሚኒስቴር ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ዘመናዊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር በሆኑት በዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ልዑካን ቡድን ባለፈው የካቲት 23/2017 ዓ.ም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት በሆስፒታሉ ተዟዙረው እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በመስክ ምልከታ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የነበረውን ምልከታ ተከትሎ እና ከዋቸሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ እና ከሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ይድነቃቸው ደዳቸው ሆስፒታሉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን መሠረታዊ የቴክኖሎጂ የህክምና መሳሪያዎችን ጥያቄ ተከትሎ ፈጣን ምላሽ በቀናት ውስጥ ከጤና ሚኒስቴር ድጋፍ ተደርጓል።

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ይድነቃቸው ደዳቸው ድጋፉን አስመልክቶ እንደገለፁት፥ በሆስፒታሉ የሚታዩ ችግሮችን በመለየትና ቅደም ተከተል በማስቀመጥ የሚታይ ለውጥ ለመምጣት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በዚህም በፋርማሲ መድኃኒት እንዲሟላና ዲጂታል እንዲሆን፣ የላቦራቶሪ አገልግሎት የምርመራ አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ ለባለሙያዎችና ለታካሚዎች ምቹና ማራኪ የሆነ የፅኑ ህሙማን አገልግሎት እንዲሰጥ መሰራቱን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን አውቶሜትድ በማድረግ የተሻለና የዘመነ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሠራ ሲሆን፤ በዛሬው እለት ከጤና ሚኒስቴር ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ የህክምና አሰጣጥን የሚያዘምንና ለአውቶሜሽን አገልግሎቱ የሚጠቅሙ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉ እንዳስደሰታቸው ጠቁመዋል።

በዚህም ደረጃ የህክምና አገልግሎትን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ያግዛል ብለዋል።

በመጀመሪያ ደረጃ የካርድ ክፍል አገልግሎት እና የተመላላሽ ህክምና፣ በሁለተኛ ደረጃ የድንገተኛ ህክምና፣ የራዲዮሎጂ እና የላቦራቶሪ እንዲሁም በሶስተኛ ደረጃ የተኝቶ ታካሚዎች ህክምና አውቶሜትድ ይሆናል ያሉ ሲሆን አጠቃላይ የአገልግሎት አውቶሜሽኑ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

በሆስፒታሉ የተጀመረው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያሳዩት ላለው ድጋፍ በተለይም የዩኒቨርሲቲውና የሆስፒታሉ ማኔጅመንት፣ የሆስፒታል ሠራተኞች፣ የሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ፣ የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል።

የሆስፒታሉ ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳለ ፍቅሬ ድጋፉን አስመልክቶ እንደገለፁት፦

ከጤና ሚኒስቴር ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ለረጅም ጊዜ ሆስፒታሉን የዘመነ ለማድረግ እና ለተጠቃሚዎች የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል፣ እንግልትን በመቀነስ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን የሚዘርጋ ልዩ አጋጣሚ የፈጠረ እንደሆነ ገልፀዋል።

የሆስፒታሉ ቺፍ አስተዳደርና ልማት ዳይሬክተር አቶ ተክሌ እጃጆ በበኩላቸው፤ የአገልግሎት ማዘመን ሂደቱ ከካርድ ክፍል ጀምሮ ሲስተም ላይ በመመዝገብ ከካርድ ክፍል ጀምሮ ወደ ሚፈልግበት የአገልግሎት ቦታ የታካሚው መረጃ በቀጥታ በበይነ መረብ የሚላክበት ሁኔታን እንደሚፈጥር፤ ተገልጋዩ የሚያስፈልገውን አገልግሎት በቀላሉ የሚያገኝበትና በፍጥነት የሚከናውን በመሆኑ ወረቀት አልባ ስርዓትን እንደሚዘረጋና የህክምና ስህተት እንዳይፈጠር የማድረግ እድሉ የሰፋ እንደሆነ አብራርተዋል።

የካቲት 27/2017 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነት እና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

Let Your Light Shine

03/05/2025
02/27/2025

ለምንድን ነው የባል ዘመዶች እንደዚህ የሚያደርጋቸው💥

ማስታወቂያ!DMC Real Estate - Joy Starts Here!ዲኤምሲ ሪል ስቴት - ደስታ እዚህ ይጀምራል!For more info/ ለተጨማሪ መረጃTel: +251-974-878787Tel: +2...
02/26/2025

ማስታወቂያ!

DMC Real Estate - Joy Starts Here!

ዲኤምሲ ሪል ስቴት - ደስታ እዚህ ይጀምራል!

For more info/ ለተጨማሪ መረጃ
Tel: +251-974-878787
Tel: +251-905-888877/33
Email: [email protected]
Web: www.dmcrealestate.com

እግዚአብሔር መልካም ግዜ ሰጠን ክብር ለእሱ ይሁን 🥰እግዚአብሔር ትዳራችሁን የፍቅር የሰላም እና የበረከት ያድርግላችሁ 💥
02/22/2025

እግዚአብሔር መልካም ግዜ ሰጠን ክብር ለእሱ ይሁን 🥰
እግዚአብሔር ትዳራችሁን የፍቅር የሰላም እና የበረከት ያድርግላችሁ 💥

02/17/2025

የአፍሪካ ህብረት ተሳታፊዎች ስለ አዲስአበባ 💥

የሚቆጨኝ ጋዳፊ የዛሬዋን አዲስ አበባ ሳያይዋት መሞታቸው ነው።- የደሃ ቤት በባነር ሸሽጎ ስብሰባ ከማስተናገድ ከተማ ቀይሮ ወደ መጠበቅ፣(ተስፋዬ ዘ ሸገር)እርግጥ ነው፤ ድሆች መሆናችንን አል...
02/17/2025

የሚቆጨኝ ጋዳፊ የዛሬዋን አዲስ አበባ ሳያይዋት መሞታቸው ነው።

- የደሃ ቤት በባነር ሸሽጎ ስብሰባ ከማስተናገድ ከተማ ቀይሮ ወደ መጠበቅ፣

(ተስፋዬ ዘ ሸገር)

እርግጥ ነው፤ ድሆች መሆናችንን አልክድም። በዚያ ላይ ብዙ ችግር አለብን። ያም ሆኖ ግን የትናንትናዋ አዲስ አበባ ዛሬ የለችም። አንድ ወቅት የትሪፖሊው ቄንጠኛ የሊቢያው መሪ ኮሎኔል ጋዳፊ አዲስ አበባ ቆሻሻ ነች ብለው ስለ ግማቷ የሰበኩት አይረሳኝም። ዛሬ አዲስ አበባን ስመለከታት ጋዳፊ የዛሬዋን አዲስ አበባ ሳይመለከቱ መሞት ይቆጨኛል።

አዎ አዲስ አበባ ቆሻሻ ነበረች። ሌላው ቀርቶ በጽዳት ከሞቃዲሾም አትወዳደርም ነበር። ከብዙ የአፍሪካ ሀገር የመጣ ተሰብሳቢ ከሆቴሉ ውጪ ምንም የሚመለከተው ነገር እንደሌለ ለማስታወስ አዲስ አበባ ተወልዶ ማደግን ይጠይቃል።

አንዳንዱ የዛሬዋን አዲስ አበባ እንጂ የትናንቷን አያውቃትም፤ ለውጧን ማብለጭለጭ ብቻ አድርጎ ያየዋል። እርግጥ ነው፤ የነዋሪውን ህይወት ለማሻሻል ምንም አልተሰራም። ያ ማለት ግን ከተማዋ አልተሰራችም ማለት አይደለም።

ቀደም ሲል ባማኮም በሉት ካርቱም ብቻ የሆነውን የአፍሪካ ሀገር ጎዳና ስንመለከት ይቆጨን ነበር። የማይቻል መስሎን እነሱ እኮ ቅኝ ግዛት ስለተገዙ ነው ብለን ቅኝ ስለመገዛት ጥቅም ወግ ጠርቀናል እውነቱ ግን መስራት ነው።

ከአስር ዓመት በፊት ኪጋሊ ለአዲስ አበባ አውሮፖ ናት። ሩዋንዳን በዋና ከተማዋ ፅዳትና ውበት ያላደነቀ አልነበረም። ያንን ቀልብ አሁን አሁን አዲስ አበባ እየወሰደች ነው። መሪዎች ከህብረቱ አዳራሽ መሰብሰቢያ ውጪ ቀደም ሲል ሂልተን እና ግዮን ኋላ ደግሞ ሸራተን ካልሆነ ምን መሄጃ ነበራቸው?

ዛሬ የዓለም መሪ አዲስ አበባ ውስጥ ብዙ ቦታ ቀጠሮ ሊያዝለት ይችላል። እንጦጦ ብናወጣው አይመጥነኝም አይልም። ወዲህ ደግሞ ወዳጅነት የየሀገሩ መሪ እራት ሲጋበዝ የተሰማውን ደስታ አይተናል። ያ ወዳጅነት የሚባለው ቦታ እኮ ቀደም ሲል እንኳን የሀገር መሪ የቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሽታውን የማይቋቋሙት የድህነት ዓለም ምሳሌ ነበር።

በየጊዜው ለህብረቱ መሪዎች ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አዲስ ነገር ማየት ልምድ አድርገንባቸው እየተገረሙ ነው። የአዲስ አበባ እድገት መብለጭለጭ ብቻ አይደለ፤ ይልቁንም መዘመን ጭምር ነው።

ከዚህ ቀደም ሞገስ ያለው እንግዳ አቀባበል እንደ ዘመኑ አቅም በግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመን የቀረ ነበር። አሁን የቤተ መንግሥቱ ቤተ መንግሥታዊ ሥርዓት ሦስት ሺህ ዓመት ታሪክ አለኝ ለምትለው ኢትዮጵያ ኩራት በሚሆን መልኩ መተግበር ጀምሯል።

አድዋ መካነ ቅርስን ጨምሮ በርካታ መዳረሻዎች የአዲስ አበባ ለውጥ መንገድ ብቻ ነው ለሚሉት ምላሽ ይሆናል። አዲስ አበባ ዛሬ ያኔ ጋዳፊ እንደገለጿት ቆሻሻ ከተማ አይደለችም። ከየትም ዓለም የመጣ እንግዳ በሚመለከተው ነገር ለውጡን ይመሰክራል።

ያም ሆኖ የኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እጦት፣ ኑሮ ውድነት፣ ጦርነት፣ ድህነት፣ መፈናቀልና መሰል ችግሮች እንዳሉ አንክደውም። ያንን የምናምነውን ያህል ግን የመዲናዋ አስደንጋጭ እድገት የደሃ ቤት በባነር ሸሽጎ ስብሰባ ከማስተናገድ ከተማ ቀይሮ ወደ መጠበቅ ተሸጋግሯል። የአፍሪካ መሪዎች ለስብሰባ በመጡ ቁጥር የሚፈዙበት እንዳያጡ አድርገናል።

Address

America
Las Vegas, NV

Telephone

+251954743191

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SARE WANA Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share